Тарифы до −50% до 30.11
Аналитика Telegram-канала
Подписчики
2 089
Охват за 24 ч
152
ER за 24 ч
7,28%
Публикаций
143

Динамика подписчиков

7 дней 30 дней 6 месяцев Больше
22 ноя25 ноя28 ноя
Показаны последние 7 дней Больше истории →

Охваты публикаций

27.1127.1128.1128.1128.1128.11
19
Средний охват
56
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале Больше статистики →

Упоминания

5
Упоминаний
2
Из них репостов
4
Каналов
Все упоминания

Последние посты

3 из 143 2 из 143
+ ሰውማ እናታችን ጽዮን ይላል + ሰው በምድር ላይ ያቃተው ነገር ቢኖር ሰው መሆን ብቻ ነው:: ብዙ ነገር መሆን ችሎአል:: እንደ አሣ በባሕር እንደ ወፍ በሰማይ በርሮአል:: እንደ እንስሳ መኖር ችሎአል እንደ አውሬም መጨከን ተሳክቶለታል:: እንደ ንስር ከሩቅ አይቶአል:: እንደ ውኃ ሰርጎ ብዙ ተመራምሮአል:: ለብዙ ሰው የከበደው ነገር ቢኖር ሰው መሆን ነው:: አንዱ ወደ አንድ አባት ቀረብ ብሎ "ድንግል ማርያም እኮ እንደ እኛ ሰው ናት" አላቸው። እርሳቸውም "ልክ ነህ እርስዋ በተፈጥሮዋ ሰው ናት ፣ አንተ ግን ሰው ነህ?" አሉት። ነገሩ ስድብ ይመስላል ፣ አስተውሎ ላየው ግን ሰው ነኝ ለማለትም መሥፈርት እንዳለው ያስታውሳል። "ኤልያስ እንደ እኛ ሰው ነበረ" ነገር ግን ዝናምን በጸሎቱ ያቆመ መሆኑን ስንሰማ ግን እኛም እንደርሱ ሰው ነን ለማለት እንፈራለን። ንጉሥ ዳዊት ለልጁ ሰሎሞን "ሰው ሁን" ያለው ሰው መሆን ማለት እንደ ሰው ክብርን አውቆ መኖር ስለሆነ ነው። ክቡር ሆኖ ሳለ ካላወቀና በኃጢአቱ ከጸና እንደሚጠፉ እንስሳት ይመስላል። ሰው በምድር ላይ ያቃተው ነገር ቢኖር "ሰው መሆን ነው"! አዋቂ መሆን ቀላል ነው! ኃያል መሆንም ይቻላል:: ባለ ጥበብ መሆንና መራቀቅም ይቻላል:: ጀግና መሆንም እንዲሁ:: ሰው ያቃተው ሰው መሆን ብቻ ነው:: ሰው መሆን ትልቅ ዋጋ አለው:: ይህንን ዋጋ ስንዘነጋ በአርኣያ ሥላሴ ለተፈጠረው ሰው ሌላ ሚዛን እንፈልግለታለን:: ሰውነቱን ትተህ በሀብቱ በእውቀቱ በዘሩ በቋንቋው ከመዘንከው አንተም ሰውነትህን ታጣለህ:: ሰው ለመሆን ብዙ መሥፈርቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ተቀምጠዋል ፣ የድንግል ማርያምን እናትነት መቀበልም ሰው የመሆን ምልክት ነው። "ሰው እናታችን ጽዮን ይላል" ተብሎ እንደተጻፈ "ጽዮን እናታችን" ማለት ያልቻለ ምኑ ሰው ይባላል? በውስጥዋም ሰው ተወለደ የተባለው ስለ ጌታ ነው:: እሱን የሚመስሉ እውነተኛ ክርስቲያኖችም ሰዎች ናቸው:: ሰው ከሆንክ "እናታችን ጽዮን" ትላለህ:: ጽዮንን "እናታችን" ብሎ ለመጥራት ግን "ወንድሜ ወንድሜ" መባባል ይቀድማል:: ይህን ማለት ያልቻለ ግን ሰው አይደለም:: ጽዮንም እናቱ አይደለችም:: ነቢዩ በባቢሎን ሆኖ ስለ ጽዮን ሲያስብ መዝሙር ለመዘመር ተቸግሮ ነበር:: "በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን" ብሎ ነበር:: እኛም የአንዲትዋ የጽዮን ልጆች ሆነን በተለያየንበት ዘመናችን እንዲህ እንላለን :- በዘረኝነት ወንዝ ውስጥ ሆነን አክሱም ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን የማረኩን ኃጢአቶቻችን ሳንላቀቃቸው የዝማሬ ቃል ፈለጉብን የእግዚአብሔርን ዝማሬ እንዴት በጥላቻ ልብ እንዘምራለን? የጽዮንንስ ዝማሬን ቂምና በቀል አርግዘን እንዴት እንዘምራለን? ታቦተ ጽዮን ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ባላስብሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ ከዘር ከነገዴ በላይ ቤተ ክርስቲያንን ባልወድድ! እናታችን ጽዮን ሆይ እባክሽን አንቺን እናታችን ብለን ሰው ለመሆን አብቂን:: ከራሳችን ጠብቂን የጥላቻን ዳጎን ሰባብሪልን:: ፍልስጥኤማውያን በአንቺ ግርማ የተነሣ ፈርተው የዳጎን መድረክን እንዳልረገጡት እልቂትና ደም መፋሰስ በአማላጅነትሽ የኢትዮጵያን ምድር አይርገጥ:: እንደ ጣዖት በልባችን የነገሠውን ክፋት ሰባብረሽ ከእግርሽ በታች አድርጊልን:: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ኅዳር 20 2013 ቦረና ኢትዮጵያ ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :- ዩቱብ https://www.youtube.com/@12Samual ቴሌግራም https://t.me/tsidq
ещё
14 0 1 28 ноя, 09:50
+ ቅዱሳን አበው እንዲህ አሉ+ ‘’ መጽሐፍ ቅዱስ የተለወጡ ሰዎች ታሪክ መጽሐፍ ነው፡፡ አታላዩ ያዕቆብ እስራኤል ተብሎ አባት ሆነ ፣ ነፍስ የገደለው ሙሴ ትሑትና ነጻ አውጪ ሆነ ፣ ስምኦን ጴጥሮስ ሆነ ፣ ሳውልም ጳውሎስ ሆነ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የተለወጡ ሰዎች የታሪክ መጽሐፍ ነው’’                     ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "በጽድቁ ከሚመካ ጻድቅ ሰው ይልቅ ስለ ኃጢአቱ የሚያለቅስ ዘማዊን እግዚአብሔር ይወድደዋል"                           ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ "የትናንት ታሪክ የሌለው ጻድቅ የነገ ተስፋ የሌለው ኃጢአተኛ የለም"  ቅዱስ አውግስጢኖስ ‘የኖኅ መርከብ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ናት፡፡ ሆኖም ቤተ ክርስቲያን ከኖኅ መርከብ እጅግ ትለያለች፡፡ ወደ መርከቡ የገባ ዶሮ ሲወጣም ዶሮ ነው፡፡ ተኩላውም ከመርከቡ ሲወጣ ተኩላ ነው፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ግን ዶሮ ገብቶ ርግብ ሆኖ ይወጣል፡፡ ተኩላውም በግ ሆኖ ይወጣል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ኃጢአተኞችን ተቀብላ ጻድቃን አድርጋ የምታወጣ መርከብ ናት’’ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‘’አልጋ መግዛት ለምትፈልጉ ኑ አልጋ ላሳያችሁ! ይህ አልጋ የተራ ሰው ወይም የወታደር አልጋ አይደለም፡፡ የንጉሥ አልጋ ነው፡፡ ንጉሥም ቢባል ተራ ንጉሥ ሳይሆን በዓለም ሁሉ የሚዘመርለት ታላቅ ንጉሥ አልጋ ነው፡፡ የንጉሥ ዳዊትን አልጋ ላሳያችሁ፡፡ ይህ አልጋ ከወርቅ ወይም ከአልማዝ ወይም ከከበሩ ድንጋዮች የተሠራ አይደለም፡፡ ይህ አልጋ ከዕንባ የተሠራ አልጋ ነው፡፡ እርሱ ‘ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን አጥባለሁ ፤ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ’ ብሏልና’’ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ሌላውን በማቁሰል የራስን ቁስል መፈወስ አይቻልም"                   ቅዱስ አምብሮስ "መላእክትን ወደ አጋንንት የቀየረው ትዕቢት ነው:: ሰዎችን ወደ መላእክትነት የሚቀይረውም ትሕትና ነው"                             ቅዱስ አውግስጢኖስ ‘’ኃጢአት ከጣለችው ይልቅ ውዳሴ ከንቱ የጣለችው ሰው ይበዛል’ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “ሣራ እስማኤልን ከቤትዋ ያባረረችው በይስሐቅ በኩል የአንተ አያት የመሆን ክብርን እንዳታጣ ነበር:: ሩት ከቦዔዝ እግር ሥር ተኝታ እንዲያገባት ጠየቀች:: ጨዋይቱ ትዕማርም እንደ ጋለሞታ ለብሳ ከይሁዳ ጋር ተኛች:: ጌታ ሆይ የአንተ አያቶች ሊሆኑ ሴቶች ወንዶችን ለመኑ ጨዋዎቹም እንደ ጋለሞታ ለበሱ"              ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ‘‘ደሃው ወደ አንተ ሊለምን ሲመጣ ‘ራቁቱን ሆኖ የሚለምነው ሲያስመስል ነው‘ ትላለህ፡፡ እርሱን አታላይ ያደረገው ግን የአንተ ጭካኔ ነው፡፡ ርኅሩኅ ብትሆንለት ኖሮ አንተን ለማራራት ሲል እንዲህ ባልደከመ ነበር፡፡ እሱ እኮ በየቀኑ እየመጣ ይለምነኛል ብለህ አትበሳጭ በየቀኑ የሚለምንህ እርሱም እንደ አንተ በየቀኑ ስለሚበላ ነው’’   ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‘’ንግግርህ ምንም ያህል እውነተኛ ቢሆን በቁጣ ከተናገርክ ሁሉንም ነገር ታጠፋዋለህ’ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከየስብከቶቹ  የተሰበሰቡ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ታኅሣሥ 9 2012 ዓ ም አዲስ አበባ ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :- ዩቱብ https://www.youtube.com/@12Samual ቴሌግራም https://t.me/tsidq የቲክቶክ ቻናሌ https://vm.tiktok.com/ZMFESAMtP
ещё
56 0 28 ноя, 07:27
ещё
3 0 28 ноя, 07:27
Больше постов

Продолжить анализ этого канала

  • История роста подписчиков
  • Просмотры и охваты публикаций
  • Кто упоминает канал и кого упоминает он
  • Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней