Аналитика Telegram-канала
Подписчики
40
Охват за 24 ч
3
ER за 24 ч
7,50%
Публикаций
261
Динамика подписчиков
7 дней
30 дней
6 месяцев
Больше
21 ноя24 ноя27 ноя
Показаны последние 7 дней
Больше истории →
Охваты публикаций
24.1124.1125.1126.1126.1126.11
1
Средний охват
1
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале
Больше статистики →
Упоминания
13
Упоминаний
8
Из них репостов
7
Каналов
5
Упоминаний за 90 дней
3
Из них репостов
3
Каналов за 90 дней
Последние посты
3 из 261 2 из 261
ещё
1
0
26 ноя, 10:21
የሕይወት መንኮራኩር ተሽከርክሮ እና የጊዜ መጽሐፍ ተዘግቶ፣ አሜሪካ ሰውን ከቁስ፣ በእርግጥም የሰው ልጅን ከእንስሳት የሚለየውን የሥነ ምግባር ሂሳብ ምንም ወይም ምንም ማለት በሚቻል ደረጃ ሳትጨምር እንዳታልፍ እሠጋለሁ” ሲሉም ጽፏል።
❸ የሰይድ ስቅላት እና የጂሃዲስት ሕዋስ
ጥቅምት 1954 ፕሬዚዳንት ናስርን ለመግደል ሞክረሃል ተብሎ የተከሰሰው ኩታብ፣ ወደ እስር ቤት ተወርውሮ መሰቃየቱ ይበልጥ ወደ ወታደራዊ ታጣቂነት እንዲገፋ እንዳደረገው ነበር። “እንዴት የናስር ሙስሊሞች እንደ እነርሱ ያሉ አማኞች ላይ ስቃይ ሊያደርሱ ቻሉ?” ሲልም ተከታዮቹን ጠይቆ ነበር።
እ.ኤ.አ. በ1966 ከመሰቀሉ በፊት፣ ኩታብ የመጨረሻ መጽሐፉን የእጅ ጽሑፍ ምዕራፍ በምዕራፍ አሾልኮ ማውጣት ችሎ ነበር። በመግቢያው ላይ በጠቀስነው ይኸው መጽሐፉም፣ “መለኮታዊ ማኅበረሰብ” እንዲፈጠር ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፣ የሚነሣውን የአማኞች ትውልድ ለተግባር ጠርቷል።
ለትጥቅ የተላለፈውን ጥሪም እንደ አል-ቃይዳው አል ዘዋሂሪ (Ayman al-Zawahiri) ያሉ ሰዎች ተቀብለውት፣ እ.ኤ.አ. በ1967 በአረቡ ዓለም የመጀመሪያውን የጂሃዲስት ሕዋስ አቋቋሙ።
ኩታብ እነርሱን ያየው የሙስሊሙን ማኅበረሰብና ፖለቲካ ከ”ጃሂሊያ” በማጽዳት እና “ሐኪሚያን” በምድር ላይ በመመለስ ወደ ዋነኛው ዓላማ የሚያመላክቱ አድርጎ ነበር።
ኩታብም በዚኹ መጽሐፍ መግቢያ ላይ፣ “ይህንን ማይልስቶንስ የጻፍኩት ሊጨበጥ በተቃረበ እውነታ ላይ እንደሆነ ለምቆጥረው ለዚህ ግንባር ቀደም ክፍል ነው” ብሎ ነበር።
ይህ አስተሳሰብ የጂሃዲስት ሕዋስ አዋልዶ፣ በቀጣዩች ጊዜያት ለተፈጠረው እስላማዊ ጽንፈኝነት መሰረቱን የጣለ እንደሆነ በርካታ ማስረጃዎች ይቀርባሉ፡፡
❹ እሳቱ በእኛ እና በጎረቤቶቻችን
እሳቱ መጠኑ ቢለያይም የኛንም አገር እያዳረሰ ነው፡፡ በይበልጥ ደግሞ ጎረቤቶቻችን አዳርሷል፡፡
የሱዳኑ ሙስሊም ወንድማማቾች ንቅናቄ (የሱዳን እስላማዊ ንቅናቄ) እና ታጣቂ ክንፉ የሆነው አል-ባራ ቢን ማሊክ ብርጌድ (Al-Baraa Bin Malik Brigade) የዚህ ውርስ ውጤት ነው፡፡ ሐሰን አልቱራቢ የዚህ ግርፍ ከሆኑት አንዱ ነው፡፡
አል-ባራ ቢን ማሊክ ብርጌድ በጥር 2020 የተመሠረተ ሲሆን፣ የሱዳኑ ሙስሊም ወንድማማቾች ንቅናቄ እና የሐሰን አልቱራቢ እና የአልበሽር አገዛዝ ርዝራዦች ዋነኛ ወታደራዊ ክንፍ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል፡፡
እንደ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ሪፖርቶች፣ የዚህ ንቅናቄ ተዋጊዎች ከኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ (IRGC) ወታደራዊ ስልጠናና ድጋፍ ያገኛሉ፡፡ አሜሪካ በያዝነው ዓመት በሽብርተኝነት ፈርጃዋለች፡፡ የግብፅ መንግሥትም የሰይድ ኩታብ ዓላማ ወራሾችን (ሙስሊም ወንድማማቾች) በሽብርተኝነት የፈረጀችው እ.አ.አ 2013 ሲሆን፤ በሕዳር 2026 ደግሞ በቋሚ የሽብርተኝነት መዝገብ ውስጥ አስገብታዋለች፡፡
በኢትዮጵያ ይህ ንቅናቄ ተቋማዊ መሰረት እየያዘ ይገኛል፡፡ በበርካታ የኢትዮጵያ ክፍሎች በካውንስል ስም አደረጃጀቱን በመዘርጋት ላይ ነው፡፡ እጅግ የሚደንቀው ነገር ወጣት ካውንስል በሚል የሚያደራጁት ቡድን፣ የወሀቢያ መዝሃብ ተከታይ የሆኑ ወጣቶችን እንጅ ሰፊውን የሙስሊሙን ወጣት ያቀፈ አለመሆኑ እየታወቀ፤ የአገዛዙ ዝምታ ነው፡፡
የዛሬ አራት ዓመት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማቸውን ሲነጠቁ “የጌታ ሰው” ዐቢይ አሕመድ ይሁንታ የሰጠበት ጉዳይ ነው፡፡
እንቀጥላለን!
ещё
1
0
26 ноя, 10:20
#የሙስሊም ወንድማማቾች ንቅናቄ እና ሠይድ ኩታብ
------
#የጂሃድ ጽንሰ-ሐሳብ ዘላለማዊ አብዮት በኩታብ መነጽር
ሽብርተኝነትን በጋራ እንከላከል!
(በቅድሚያ፤ አክ*ራሪው ኃይል ይህን ጽሑፍ ሪፖርት አድርገው ስለሚስነሱት ጽሑፉን ኮፒ አድርጋችሁ ውሰዱት)
❶ . ሠይድ ኩታብ ማንነው ?
ሠይድ ኩታብ በግብፅ የሙስሊም ወንድማማቾች ንቅናቄ አባል የነበረ ሰው ነው፡፡ ይህ ሰው በመጀመሪያ የታሪክ ምዕራፉ ገጣሚና ጸሐፊ ነበር፡፡ በግብፅ ሙስሊም ወንድማማቾች ንቅናቄ ውስጥ በነበረው ተሳትፎ፣ እስራት የደረሰበት ሲሆን፤ ከእስር በኋላ ወደ ጽንፈኛና አብዮታዊ የፖለቲካ እስልምና አስተሳሰብ ተሸጋገረ፡፡
በ1950ዎቹ ዓመታት የጂሃድን ጽንሰ-ሐሳብ ዘላለማዊ አብዮት በሚል በመተርጎም እና በ1964 በታተመው “Milestones on the Road” በተባለ መጽሐፉ አማካኝነት ዘመናዊውን አክራሪ እስላማዊ አስተሳሰብ በማቅረጽ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደረ ቢሆንም፣ በ1966 በናስር መንግሥት በስቅላት ሕይወቱ እንዳለፈ በታሪክ ተመዝግቧል።
ሠይድ ኩታብ፣ በግብፅ አብዮታዊ ናስር መንግሥት ተይዞ በእስር ቤት ታስሮ በነበረበት ጊዜ በአል-መውዱዲ አስተሳሰብ ተጽዕኖ ሥር ወደቀ። የወሃቢ ድጋፍም አልነበረውም።
ሰይድ አቋሙን ቀይሮ ሙሉ በሙሉ አክራሪ የሆነው በእስር ከተገረፈና ከተሰቃየ በኋላ ነበር። ኃይለኛ አክራሪ ከሆነ በኋላ ደግሞ፣ ከላይ የተጠቀሰውን ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆነውን መጽሐፉን ጻፈ። ሠይድ በዚኹ መጽሐፉ እርሱ እውነተኛ እስላማዊ ማህበረሰብ እና እውነተኛ እስልምና ምን መምሰል እንዳለበት የሚያምንበትን አብራርቷል።
የኩታብ መጽሐፍ በተግባር ሲታይ ግን ሙሉ በሙሉ የፋሽስት ርዕዮተ ዓለም በሆነ መንገድ ላይ የተመሠረተ እስላማዊ መንግሥትን ለመመስረት የሚጥር ነበር።
በሠይድ ኩታብ አመለካከት ሁሉም ሙስሊሞች እውነተኛ እስልምና ወዳለበት ምድር መሰደድ (ሂጅራ ማድረግ) ግዴታቸው ነው። ይህን የማያደርጉ ሙስሊሞች ሃይማኖታቸውን የተው እና የካዱ (Kuffar) ናቸው።
ሠይድ ኩታብ በአንጽኖት እንደሚያቀነቅነው የሁሉም እውነተኛ ሙስሊሞች ህገመንግስት ቁርአን ብቻ ነው። ስልጣንም ያለው አላህ ብቻ ነው። የተሟላና ትክክለኛ ፍትህ የሰፈነበት የአላህ መሪ የፈጣሪን ትዕዛዝ በታማኝነት ተግባራዊ ሲያደርግ ብቻ ነው።
የእውነተኛ እስልምና ምድር በአላህ መመሪያዎች፣ በሁሉም ጉዳዮች ላይ በእስላማዊ ህግ መገዛት አለበት። ከእስላማዊ ህግ ውጭ ሌላ ህግ መኖር የለበትም። ህግ ከፈጣሪ ብቻ ነው ባይ ነው። በርግጥም ሠይድ ኩታብም በህግ ፍልስፍና አሠራር ትምህርት የሰለጠነ የህግ አዋቂ አልነበረም። ስለእስላማዊ የህግ ፍልስፍና እና ታሪክ ያለው እውቀትም በጣም ውሱን እንደነበር ይነገራል።
የሆነው ሆኖ ሠይድ፣ እስላማዊ ህግ ግልጽና ወዲህ- ወዲያ የማይል ደረቅ አሉታዊ ትዕዛዛት ያሉትና በሙስሊሙ ህይወት ውስጥ የሚኖሩና የሚከሰቱ ጉዳዮችን በሙሉ የሚቆጣጠር ህግ መሆን እንዳለበት ያምናል። እስላማዊ ህግ የሁሉም የህይወት ጉዳዮች መድኃኒት ቤዛ ለሁሉ ስለሆነ እሱን መተግበር ማለት የአላህን ህግ መተግበር ማለት ነው። የፈጣሪ ህግ ደግሞ ሁልጊዜም ትክክልና የተሟላ ነው የሚል ጽኑ አቋም አለው።እንደ ሠይድ እምነት፣ እንዲህ አይነቱ የእስላም አገር ሲመሠረት ሙስሊሞች በሙሉ ወደዚያ ሂጅራ አድርገው (ሄደው) መኖር አለባቸው።
እንዲህ አይነት አገር ካልተመሠረተ ግን እውነተኛዎቹ ሙስሊሞች (ሰለፊዎች) ከተቀረው ህብረተሰብ ራሳቸውን ነጥለው መኖር (ኢቲዛል) አለባቸው ብሎ ይመከራል።
የግለሰቡ አቋም፣ በስም ብቻ ሙስሊም ከሆኑ ነገር ግን በተግባራቸው መናፍቅ (ሙናፊቅ) ከሆኑ ህዝቦች ራሳቸውን መነጠል አለባቸው የሚል ነው። እውነተኛ ሙስሊሞች (ወሀቢያ-ሰለፊዎች ማለት ነው) ከተቀረው ሙስሊም ነኝ ባይ ተነጥለው የእነሱ በሽታ ሳይጋባባቸው እምነታቸውን በንፅህና ጠብቀው መኖር መቻል አለባቸው።
ራሳቸውን ከሌላው ለይተውና የራሳቸውን ማህበረሰብ ፈጥረው ከኖሩ በኋላ እውነተኛውን እስላማዊ መንግስት ለመመስረት ባላቸው አቅምና ብቃት አጋጣሚ ሁሉ ያልተቆጠበ ጥረት የማድረግ ግዴታ አለባቸው።
በግልጽ እንደሚታየው ሙስሊሞችን ሃይማኖቱን እንደካደ አድርጐ ለመፈረጅ ያለው አመለካከት ደረቅና ከሌላው አለም ጋር አብሮ የመኖርን አስፈላጊነት አደጋ ላይ የሚጥል ነቀርሳ ነው ሲል ተከራክሯል፡፡
በዚህ ረገድ እንደ አብደል ወሃብ ሳይሆን ሰይድ የምዕራባውያን ፈላስፎች በተለይም የጀርመን ፋሽስት ፈላስፋ ካርል ሽሚት (carl schmidt) ተፅዕኖ ነበረበት፡፡ ምንም እንኳን ሠይድ ኩታብ የዚህን የፋሽስት ስም እንዲሁ እንኳን በመጽሐፉ ውስጥ ያልጠቀሰ ቢሆንም ይህን የሰይድ መጽሐፍ በጥልቀት በጥንቃቄ ያነበበ ሰው በርካታ የሰይድ ሃሳቦች የታቀፉት አጠቃቀም የቀደሙ ትክክለኛ አስተዳደርና የሃሳብ አገባብ በአብዛኛው ከጀርመኑ ፋሽስት ፈላስፋ ጽሁፎች ውስጥ የተወሰዱ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
የፋሽስቱ ፈላስፋ ንድፈ ሐሳብ፣ በሠይድ ኩታብ አስተሳሰብ ላይ ያሳደረውን ተፅዕኖ የሚመለከት በበርካታ ምሁራን የተጻፉ የሰነድ ማስረጃዎች አሉ፡፡ (ጥቂቶቹ እነሆ፦ Roxane I. Euben: Enemity in the mirror: Islamic Fundamentalism and the limits of modern rotionalism princeton 1999.Aziz al-Azimeh Islam and Modernities. London 1996Ahmed S.mdisalli radical Islamic Fundamentalism The Ideological and political discourse of sayyid qutb lebanon 1992.)።
❷ ሰይድ እና የምዕራቡ ዓለም ግንዛቤው….
ኩታብ በወጣትነቱ ድርሰቶችንና ግጥሞችን የሚጽፍ ተስፋ ሰጪ ደራሲ ነበር። እ.ኤ.አ. በ1948 የግብፅ የትምህርት ሚኒስቴር ወደ አሜሪካ ላከውና፣ በዚያም በዋሽንግተን ዲ.ሲ. በዊልሰን ቲቸርስ ኮሌጅ ትምህርት ተከታትሎ ነበር።
በኮሎራዶ ስቴት ኮሌጅ ኦፍ ኢዱኬሽን (አሁን የሰሜን ኮሎራዶ ዩኒቨርሲቲ) በትምህርት የማስተርስ ዲግሪ እንዳገኘና ከዚያም በስታንፎርድ የትምህርት ኮርሶችን መውሰድ ጀምሮ ነበር። ከጦርነቱ በኋላ የነበሩ የግብፅ ሀገር ገንቢዎች ምርጥና ብሩህ ወጣት አእምሮዎችን በብሪታንያና በአሜሪካ እንዲማሩ መላክ፣ ወደ ሀገር ሲመለሱ ዘመናዊነትን ለመመሥረት የሚያስችል መሣሪያ ይሰጣቸዋል ብለው ያምኑ ነበር። ኩታብ ባሕላዊ ብርሃን ከማግኘት ይልቅ፣ ሱስ በሆነ ቁሳዊነት እና በአሜሪካዊው ሰው መንፈሳዊ ጭካኔ (ባርባራዊነት) አድርጎ በተመለከተው ነገር መጸየፍ እንደተሰማ ተጽፏል።
ወደ ግብፅ ከተመለሰ በኋላ፣ በአል-ሪሳላ መጽሔት ላይ «ያየኋት አሜሪካ» በሚል ርዕስ በአሜሪካ የአኗኗር ዘይቤ ላይ ኃይለኛ ነቀፌታ ያዘለ ጽሑፍ አሳተመ። ይህ ጽሑፍ በኋላ በመጽሐፍ መልክ የታተመ ሲሆን፣ ለትውልዶች በተቀጠሉ እስላማውያን ዘንድ ስለ አሜሪካ የነበራቸውን ግንዛቤ የቀረጸ ነበር።
ኩታብ እንደጻፈው፣ አሜሪካውያን ዓለም አቀፍ እውነቶችንና ሰብዓዊ እሴቶችን እያገለሉ፣ በተግባራዊ ሳይንስና በምርታማነት መሠዊያ ላይ ይሰግዱ ነበር። “ይህች ታላቋ አሜሪካ፣ በሰብዓዊ እሴቶች ሚዛን ዋጋዋ ምንድን ነው? ለሰብዓዊነት ሥነ ምግባርስ ምን ትጨምራለች? በጉዞው መጨረሻስ ፍጻሜዋ ምን ይሆናል?” ሲልም ያስተማረችውን አሜሪካ ሥልጣኔ ሊያጠይቅ ታትሯል። “በአሜሪካ ቁሳዊ ታላቅነት እና በሕዝቦቿ መንፈሳዊ ጥራት መካከል ሚዛን ላይኖር እንደሚችል እሠጋለሁ።
ещё
1
0
26 ноя, 10:20
Продолжить анализ этого канала
- История роста подписчиков
- Просмотры и охваты публикаций
- Кто упоминает канал и кого упоминает он
- Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней