Аналитика Telegram-канала
Подписчики
1 800
Охват за 24 ч
81
ER за 24 ч
4,50%
Публикаций
1 433
Динамика подписчиков
7 дней
30 дней
6 месяцев
Больше
22 ноя25 ноя28 ноя
Показаны последние 7 дней
Больше истории →
Охваты публикаций
25.1125.1125.1125.1125.1127.11
14
Средний охват
62
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале
Больше статистики →
Упоминания
557
Упоминаний
61
Из них репостов
17
Каналов
10
Упоминаний за 90 дней
2
Из них репостов
7
Каналов за 90 дней
Последние посты
3 из 1 433 2 из 1 433
ጥቆማ‼
የሶፍትዌር ካምፓኒዎች ይህን የ10 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ተሳተፉ።
10 ሚሊዮን ዶላር የተበጀተለት "ካማ" (KAMA) ፕሮጀክት እንዴት ይሰራል ?
(ቲክቫህ ኢትዮጵያ)
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) በስምንት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ለተለዩ 21 ችግሮች መፍትሔ የሚያመጡ ሥራ ፈጣሪዎችን የሚያሳትፍና 10 ሚሊዮን ዶላር የተበጀተለት "ካማ" (KAMA) ፕሮጀክት ይፋ አደረገ።
የሆልዲንጉ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ታዬ በሰጡት መግለጫ፣ ፕሮግራሙ የተነደፈው የልማት ድርጅቶቹ "ይህ ተግዳሮት አለኝ፤ በስታርታፖች፣ በሥራ ፈጣሪዎችና በወጣቶች እንዲፈታልኝ እፈልጋለሁ" በሚል ባቀረቡት የችግር ማብራሪያ ላይ ተመሥርቶ መሆኑን አስረድተዋል።
እነማን መሳተፍ ይችላሉ ? ጥሪው በየትኛው ደረጃ ላሉ ሥራ ፈጣሪዎች ነው ?
ዶ/ር ብሩክ ፕሮጀክቱ ስታርታፖችን በመጠን እንደማይከፋፍል ገልጸው፣ "ትንሽ እና ትልቅ ብለን አይደለም ስታርታፖቹን ዲፋይን ያደረግናቸው። ለኛ ማንኛውም አይዲያ ትልቅ ነው" ብለዋል።
አክለውም፥ "ማንኛውም ሰው ብሪፉን (የተለዩትን ችግሮች) ሲመለከት የሚጠይቀው 'ይህንን መፍታት እችላለሁ ወይስ አልችልም፤ ከቻልኩስ በምን መንገድ?' የሚለውን ነው። የስታርታፑ ትልቅ መሆን ወይም ትንሽ መሆን አይደለም ዲተርሚን የሚያደርገው። ስለዚህ ለሁሉም እኩል ክፍት ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ሂደቱ ምን ይመስላል ?
ለመጀመሪያው ዙር ለተለዩት 21 ችግሮች የመፍትሔ ሐሳብ ያላቸው ሥራ ፈጣሪዎች፣ የተሟላ ፕሮቶታይፕ ወይም የተጠናቀቀ መፍትሔ ማቅረብ አይጠበቅባቸውም።
ማመልከቻቸውን አሟልተው የተመረጡት በድርጅቶቹ ውስጥ ሦስት ደረጃዎችን የሚያልፉ ሲሆን እነዚህም፥ የ4 ሳምንት የልምድ ልውውጥና ትውውቅ፣ የ12 ሳምንት የጋራ ልማት (Co-development) እና የ3 ወር ወደ ንግድ ሥራ የማሸጋገር (Commercialisation) ሂደት ያካትታል።
ዶ/ር ብሩክ እንዳሉት፥ የፕሮጀክቱ ግብ፣ በአንድ ዓመት ውስጥ ሐሳቡን ኢንኪዩቤት አድርጎ፣ አነስተኛ አዋጭ ምርት (MVP) ፈትሾ፣ ለኢንቨስትመንት ዝግጁ ምርት ማውጣት ነው።
ኤ.ኤል.ኤክስ (ALX) በፋይናንስ፣ በስትራቴጂና በገበያ ክፍተት ያለባቸውን ስታርታፖች በቅርበት ለመደገፍ የፕሮጀክቱ አጋር ሆኖ ተመርጧል።
ለሥራ ፈጣሪዎቹ የሚሰጠው ገንዘብ ብድር ነው ?
ዶ/ር ብሩክ ገንዘቡ እርዳታም ሆነ ብድር እንዳልሆነ በመግለጫቸው አስምረውበታል። "ድጋፍ አይደለም፣ እርዳታ አይደለም፣ ብድር አይደለም። እኛ ያዋጣል ብለን ካመንንበት ኢንቨስት የምናደርገው ነው፤ ለዚያም ሪተርን እንጠብቃለን" ብለዋል።
"ይህን ያህል ፐርሰንት ኢኩቲ እንፈልጋለን" የሚለው በየሐሳቡ እንደሚወሰን በመጥቀስም፣ ሆልዲንጉ በመፍትሔዎቹ ውስጥ ድርሻ እንደሚኖረው አመልክተዋል።
10 ሚሊዮን ዶላሩ እስከመቼ ነው ?
10 ሚሊዮን ዶላሩ ለዚህ ዓመት ብቻ የተመደበና የEIH መዋጮ ብቻ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ብሩክ፤ ለቀጣይ ዓመት እንደ ሁኔታው እንደሚጨምርና ሌሎች ኢንቨስተሮችም ፍላጎት ማሳየታቸውን ነው የጠቆሙት።
ፈንዱ በስታርታፕ አዋጁ ከተቀመጠው የስታርታፕ ፈንድ ጋር እንደማይገናኝ፣ እሱ ራሱን የቻለ ማዕቀፍ መሆኑንና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚተገብርበትን መንገድ እየሠራ እንደሆነ አስረድተዋል።
እንዴት ማመልከት ይቻላል ?
ከዛሬ ጀምሮ አመልካቾች እስከ ታኅሣሥ 29 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ በፕሮጀክቱ ድረ-ገጽ kama.et በኩል ማመልከት ይቻላል ተብሏል።
የምርጫ መስፈርቶቹ፣ ማለትም ምን ዓይነት ሰነዶች፣ ልምድና ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ በማመልከቻው ላይ በግልጽ መቀመጡን በመግለጬቸው ተጠቅሷል።
አመልካቾችን የሚመዘኑት ለዚሁ ፕሮጀክት በተቋቋመው የEIH ፓናል ሲሆን፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችም በሂደቱ ይሳተፋሉ ተብሏል።
ሥራ ፈጣሪዎች በዋናነት ምን ያስፈልጋቸዋል ?
ለዚህ ጥያቄ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ የሰጡት ዶ/ር ብሩክ "ትልቅ ድራይቨር የሚሆነው ችግሩን የመፍታት አቅም ነው። እኔ ይህ ችግር ኤክስ ነው ብዬህ አንተ ዋይ የሚሆን ሶሉሽን ብትሰጠኝ አይሆንልኝም። ኤክስን የምትፈታ ከሆነ ሳልወድ በግድ ካንተ ጋር መሥራት እገደዳለሁ" ብለዋል።
ስለዚህ አመልካቾች ድርጅቶቹ "የተቸገርነው በዚህ ነው" ብለው ባስቀመጡት ችግር ላይ በማተኮር፣ በፈጠራ መንገድ እንዴት እንደሚፈቱት ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።
ቲክቫህ
ещё
6
0
27 ноя, 14:19
ещё
12
0
25 ноя, 15:02
🥇 Top 10 Powerful ChatGPT Prompts for Students
ещё
62
0
25 ноя, 15:01
Продолжить анализ этого канала
- История роста подписчиков
- Просмотры и охваты публикаций
- Кто упоминает канал и кого упоминает он
- Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней