Аналитика Telegram-канала
Подписчики
37
Охват за 24 ч
5
ER за 24 ч
13,51%
Публикаций
246
Динамика подписчиков
7 дней
30 дней
6 месяцев
Больше
12 ноя15 ноя18 ноя
Показаны последние 7 дней
Больше истории →
Охваты публикаций
13.1113.1113.1113.1116.1118.11
1
Средний охват
1
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале
Больше статистики →
Упоминания
23
Упоминаний
10
Из них репостов
3
Каналов
85
Упоминаний за 90 дней
49
Из них репостов
30
Каналов за 90 дней
Последние посты
3 из 246 2 из 246ещё
1
0
18 ноя, 11:51
https://t.me/arabegnatagwide/7059
ещё
1
0
16 ноя, 08:50
🔳 [ 2 ] በዝምታና በትኩረት ሰዎችን ማሸበር
አንድ ሰው ሊንቅህ ወይም ወሰንህን ሊጥስ ሲሞክር አትጮኽ፣ አትከራከር። ዝም ብለህ ወደ ዓይኖቹ በትኩረት ተመልከተው፤ ዝምታህ አቅምህን፣ በእሱ ውስጥ ደግሞ ጭንቀትን ይፈጥራል።
🔳 [ 3 ] ስለራስህ መረጃዎችን በድብቅ መያዝ
ሁሉንም እቅድህን፣ ምስጢርህንና ደካማ ጎንህን ለሰው አታውራ። ሰዎች አንተን ማንበብ ሲያቅታቸው በቀላሉ ሊገምቱህና ሊቆጣጠሩህ አይችሉም።
🔳 [ 4 ] ከማማረርና ሰበብ ከመደርደር መውጣት
ድህነትህን፣ ውድቀትህን ወይም መጥፎ አጋጣሚህን በሌላ ሰው ላይ አታሳብብ። ሕይወትህ ያንተ ኃላፊነት ናት፤ ሰበብን አቁምና መፍትሔ ላይ አተኩር።
🔳 [ 5 ] ቃላትን መቀነስና በተግባር መናገር
ብዙ የምታወራ፣ የምትፎክርና የምትምል አትሁን። ድምፅህን አጥፋና በዝምታ ሥራ፤ ውጤትህና ስኬትህ ራሱ ጮክ ብሎ ይናገርልሃል።
🔳 [ 6 ] ራስህን መውቀስ ማቆም
ባለፈው ስህተትህ ላይ ቁጭ ብለህ አታልቅስ። ማዘን ምንም አይቀይርም፤ ካለፈው ተማርና አሁኑኑ ተነስተህ ፊትህን ወደ ሥራ አዙር።
🔳 [ 7 ] የአእምሮህን ቁልፍ ለሰው አታስረክብ
አንድ ሰው በተናገረው ቃል አንተን ማናደድና ማበሳጨት ከቻለ፣ እሱ ያንተ የበላይ ሆኗል ማለት ነው። በማንም ንግግር አትናወጥ።
🔳 [ 8 ] በብቸኝነት ውስጥ ጥንካሬን መፈለግ
ሰው በሌለበት፣ ማንም በማያይህ ሰዓት የምታደርገው ነገር እውነተኛ ማንነትህን ይገልጻል። በብቸኝነትህ ጊዜ ራስህን በዕውቀትና በሥራ ገንባ።
📌 ክፍል 2፦ የኃላፊነት፣ የሥራና የገንዘብ ሕጎች
🔳 [ 9 ] ቤተሰብህ እየተራበ አንተ በቁም ሬሳ አትሁን
አቅምና ጉልበትህ እያለ ቤትህ ውስጥ ችግርና ረሃብ ገብቶ ቤተሰብህ ሲበተን ዝም ካልክ አንተ በቁም የሞትክ ሬሳ ነህ። ተነስና ኃላፊነትህን ተረከብ።
🔳 [ 10 ] ሥራን ፈጽሞ አለመንቅ
“ይህ ሥራ አይመጥነኝም” እያልክ የምትመርጥ ከሆነ ቤተሰብህን እየበደልክ ነው። ወንድ ልጅ የቤቱን እቶን ለማንደድ ማንኛውንም ታማኝ ሥራ ዝቅ ብሎ ይሠራል።
🔳 [ 11 ] ከቁማርና ከጥፋት ሱሶች በአስቸኳይ መራቅ
ኪስህ ያለውን ሳንቲም ለቤት እህል መግዣ ከማድረግ ይልቅ ቁማር ቤትና አላስፈላጊ ቦታ የምታጠፋው ከሆነ የቤተሰብህን ተስፋ እየቀበርክ ነው።
🔳 [ 12 ] ጊዜህንና ጉልበትህን በከንቱ አታባክን
በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ያለ ዓላማ የምታጠፋውንና የምትንከራተተውን ሰዓት ቀንስ። ጊዜህ የወደፊት ስኬትህ መገበያያ ገንዘብህ ነው።
🔳 [ 13 ] “ገንዘብ የለኝም” ብለህ ፊትህን አታስደፋ
ዛሬ ባዶ መሆንህ የነገ ማንነትህን አይወስነውም። ባንተነትህ አትፈር፤ ጉልበትህ ላይ ተነስና ኑሮህን ለመቀየር ቆርጠህ ሥራ።
🔳 [ 14 ] ሁልጊዜ አዳዲስ ክህሎቶችን ማሳደግ
ባለህበት ቦታ አትቆም፤ መጽሐፍትን አንብብ፣ አዳዲስ የሥራ ጥበቦችን አምጣ፣ ራስህን በየቀኑ አሻሽል። ዕውቀት ያለው ወንድ በማንኛውም ቦታ መውጫ አያጣም።
🔳 [ 15 ] የራስህ ውድ ዋጋና ወሰን ይኑርህ
በጠሩህ ቁጥር የምትገኝ፣ ሁልጊዜ ለእነሱ ዝግጁ የሆንክና የምትለማመጥ አትሁን። የራስህ ትልቅ ቁም ነገርና ማንም የማይጥሰው ወሰን (Boundary) ይኑርህ።
🔳 [ 16 ] ዕዳን መጥላትና ራስን መቻል
ሰነፍ ወንድ በየቦታው ተበዳሪና እጁን ዘርጊ ይሆናል። የራስህን ኑሮ በራስህ ጥረት ለመምራት ቁጠባንና ጠንክሮ መሥራትን ልመድ።
📌 ክፍል 3፦ የግንኙነት፣ የሴቶችና የማኅበራዊ ሕይወት ሕጎች
🔳 [ 17 ] በሴሰኝነትና በጊዜያዊ ስሜት አለመታወር
ከቤት ውጭ ላለች ሴትና ለጊዜያዊ አምሮት ገንዘብህንና ጊዜህን ስትገብር፣ እዚያ ቤት ውስጥ ግን እናትህ በችግር እንባዋን እንዳታብስ ተጠንቀቅ።
🔳 [ 18 ] ክብሯንና እምነቷን የጠበቀች ሴትን ብቻ ማቅረብ
ለውጫዊ ውበት ብቻ ብለህ የውስጥ ሰላምህን የሚነጥቅህን ግንኙነት አታሳድድ። በችግርህ የምትቆምና ለክብርህ የምትጨነቅ ሴት ምርጥ ስጦታህ ናት።
🔳 [ 19 ] የእናትህን ተስፋ መቁረጥ አትፍቀድ
አንተን አሳድጋ “ነገ ይደርስልኛል” የምትል እናት ባንተ ሰነፍ ማንነትና ሱስ ምክንያት ተስፋ እንድትቆርጥ ካደረግክ፣ የሕይወትህ በረከት አብሮ ይቆማል።
🔳 [ 20 ] አጥፊና የማይጠቅሙ ጓደኞችን መቁረጥ
አንተን ለቁማር፣ ለሴትና ለወሬ የሚያበረታቱህን፣ ጊዜህንና ኪስህን የሚያባክኑ ሰዎችን በአስቸኳይ ከሕይወትህ አስወጣ።
🔳 [ 21 ] ለሰዎች ስትል ራስህን አታሳንስ
ሰዎችን ለማስደሰት ወይም ተቀባይነት ለማግኘት ብለህ ማንነትህንና ክብርህን አ አትቀንስ። ለራስህ ያለህ አክብሮት ይቀድማል።
🔳 [ 22 ] ፍቅርን አትለምን
ከአንተ መራቅና አንተን መተው የሚፈልግን ሰው በጭራሽ አትለምን። በሩን ክፈትለትና በክብር እንዲወጣ አድርግ፤ የራስህ ክብር ትልቅ ነው።
🔳 [ 23 ] በሰዎች ስኬትና ሀብት አትቅና
የሌላውን ሰው ሕይወት እያየህ አትቅና፣ አታትማትር። በራስህ መስመር ላይ አተኩርና ያንተን ታሪክ ለመጻፍ ሌት ተቀን ልፋ።
🔳 [ 24 ] ቃልህን የከበረ አድርገው
ለአንድ ሰው “አደርገዋለሁ” ካልክ ምንም ዓይነት ከባድ መስዋዕትነት ቢጠይቅህ እንኳ ቃልህን ጠብቅ። የማይታመን ወንድ ዋጋ የለውም።
📌 ክፍል 4፦ የስብዕና፣ የጥንካሬና የመንፈስ ሕጎች
🔳 [ 25 ] የአካል ብቃትና ጤናን መጠበቅ
አካልህ ያንተ መንፈስ መኖሪያና መዋጊያ ጋሻህ ነው። በስፖርትና በጥሩ አመጋገብ ራስህን ጠንካራና ዝግጁ አድርገህ ጠብቅ።
🔳 [ 26 ] ፍርሃትን መጋፈጥ
ወንድ ልጅ አይፈራም ማለት አይደለም፤ ነገር ግን ፍርሃቱ እያለም እንኳ ወደፊት መራመድና ያንን ነገር መስበር ይችላል። ፈተናዎችን ፊት ለፊት ግጠማቸው።
🔳 [ 27 ] ክብርንና ትሕትናን ማጣመር
ለታናናሾችና ለደካሞች ትሑትና አጋዥ ሁን፤ ነገር ግን ለአንተ ክብር ለሌላቸውና ለትዕቢተኞች እጥፍ የሚበልጥ ኩራትና አቋም ይኑርህ።
🔳 [ 28 ] ከማንም በላይ መሪ መሆን
በየትኛውም ቦታ ስትገኝ ተመሪና ተላላኪ አትሁን። አቋም ይኑርህ፣ ሃሳብህን በድፍረት ግለጽ፣ በችግር ጊዜ ደግሞ መፍትሔ አመጪ ሁን።
🔳 [ 29 ] ለነገው ትውልድ አርአያ መሆን
ዛሬ የምትኖረው ሕይወት ለኋላህ ላሉት እህትና ወንድሞችህ፣ ነገ ለሚመጡት ልጆችህ ኩራትና አርአያ ሊሆን የሚችል መሆኑን አትዘንጋ።
🔳 [ 30 ] አላህን ፍራ፣ ከእምነትህ አትራቅ
የሰው ልጅ ጥንካሬው፣ መረጋጋቱና መሠረቱ መንፈሳዊነቱ ነው። ከፈጣሪህ ጋር ያለህን ግንኙነት አጥብቅ፤ እሱ በሥራህ ላይ በረከትን፣ በውስጥህ ደግሞ ሰላምን ይሰጥሃልና.
ተጠናቀቀ።
✍️Ja M
ещё
1
0
13 ноя, 14:58
Продолжить анализ этого канала
- История роста подписчиков
- Просмотры и охваты публикаций
- Кто упоминает канал и кого упоминает он
- Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней