Аналитика Telegram-канала
Подписчики
9 727
Охват за 24 ч
841
ER за 24 ч
8,65%
Публикаций
1 322

Динамика подписчиков

7 дней 30 дней 6 месяцев Больше
18 ноя21 ноя24 ноя
Показаны последние 7 дней Больше истории →

Охваты публикаций

22.1122.1122.1122.1123.1124.11
158
Средний охват
654
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале Больше статистики →

Упоминания

9
Упоминаний
0
Из них репостов
4
Каналов
Все упоминания

Последние посты

3 из 1 322 2 из 1 322
ማክሰኞ ህዳር 15 Nov 24 የክርስቶስ ስጋ መልበስ 1ኛ ዮሐንስ 4፥1-3 የሚነግረን ክርስቶስ ስጋ ለብሶ መምጣቱን የማመን ፈተና ከሌሎች ታላላቅ ሃይማኖቶች የመጡ ነቢያት እንደሆኑ የሚናገሩትን ወይም ከማንኛውም ሃይማኖት ጋር ግንኙነት ሳይኖራቸው ከመንፈሳዊው ዓለም ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የሚናገሩ ሰዎች ክርስቶስ ሥጋ ለብሶ መምጣቱን ሳያምኑ ነቢያት ነን ቢሉ ተቀባይነት እንደሌላቸው እናውቃለን። “ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም” (1ኛ ዮሐ 4፥3)። ዮሐንስ ይህን ጥቅስ ሲጽፍ ክርስቶስ ሰው ነኝ ይላል እንጂ ሰው አይደለም እያሉ ስለሚያስተምሩ ሀሰተኛ መምህራን እያሰበ ነበር። ይህ ፈተና ከዚህም ያልፋል። መፈተኛው ነቢይ ነኝ የሚለው ሰው ክርስቶስ ስጋ ለብሶ በምድር ላይ የኖረ ትክክለኛ ሰው ነው ብሎ ማመኑ ብቻ እውነተኛ ነቢይ አያደርገውም። አብዛኞች ክርስቲያኖች ስለ ኢየሱስ ይህን ያምናሉ። የዮሐንስ ትንቢታዊ ማስጠንቀቂያ፣ ለአንድ የተወሰነ ሁኔታ የተፈለገ ቢሆንም፣ ለኋለኞቹ ትውልዶች የሚያስፈልጉ አስፈላጊ (ወሳኝ) እውነቶችን የያዘ ነው። የሚከተሉት ጥቅሶች ስለ ኢየሱስ ምን ይነግሩናል? ዮሐ. 3:16፤ 2ኛ ቆሮ. 5:21፤ ዮሐ. 11:25፤ ዕብ. 4:14፣ 15፤ ዮሐ. 14:1-3። Save Notes እውነተኛ ነቢያት ክርስቶስ ስጋ የለበሰ መለኮትና በርግጥም ሰው መሆኑን ማመንና ማስተማር አለባቸው። ስለ ክርስቶስ ሙሉ እውነት--ስለ ተልዕኮው፣ ስለ ኃጢአት የለሽ ሕይወቱ፣ ስለ የስርየት ሞቱ፣ ስለ ትንሳኤው፣ በሰማይ ስለሚያከናውነው የሊቀ ክህነት አገልግሎቱና ስለ ዳግም ምጻአቱ የተሟላ እውነት ማቅፍ አለባቸው። ይህ ክርስቶስ በምድር ላይ ስለ መኖሩ በሀሳብ ተስማምቶ ብቻ የሚታለፍ ነገር አይደለም። የነቢይ መልእክት ዋናው ትኩረቱ ኢየሱስ ላይ ነው እንጂ እንዲሁ እግረ መንገዱን ነካ አድርጎ የሚያልፈው ርዕሰ አይደለም። መልእክቱ ወይም መልዕክቷ ሰዎችን ከክርስቶስ ጋር የሚያድን ግንኙነት ወደ መፍጠር መምራት አለበት። በመንፈስ ቅዱስ የተመራ ትንቢታዊ የእግዚአብሔር ቃል የንጋት ኮክብ የሆነው ኢየሱስ በውስጣችን ያለውን ጨለማ እስኪያስወግድ ድረስ በልባችን ውስጥ እንዲነጋና ትንቢታዊው ስጦታው ከእርሱ ጋር አቆራኝቶን በቀጣይነት ወደ እርሱ እንዲያመለክተን ማድረግ ነው። ክርስቶስን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ነቢያት የራሳቸውን ተከታዮች አይሰበስቡም፣ ወይም ራሳቸውን ከፍ ከፍ አያደርጉም (የሐዋ 4፥12)። መልእክቱን እንዲያደርሱ የተላኩባቸውን ሰዎች ያገለግላሉ እንጂ ሰዎቹ እንዲያገለግሏቸው አያደርጉም። ይህ እንዳለ ሆኖ በነገው ክፍል እንደምናየው፣ የእግዚአብሔር ነቢያት እንደ እኛ ሰዎች ነበሩ። እንደ ሁላችንም ወንጌሉ የሚያስፈልጋቸው ኃጢአተኞች ነበሩ። ክርስቶስ፣ ሙሉ በሙሉ አምላክ፣ በእኛ ምትክ የሀጥያታችንን ሸክም ተሸክሞ መሞቱን ማስተዋል የእምነታችን ማዕከል የሆነው ለምንድን ነው? ይህን አስተምሮ ካላስተዋልነው ምን ይቀርብናል? @SabbathSchool @TekalignSorato
ещё
14 0 24 ноя, 06:01
ሰኞ ህዳር 14 Nov 23 ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር መጣጣም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር መጣጣም/መስማማት መስማማት እኛ ሰዎች በቃላችን ባንቆምም እግዚአብሔር ግን አይዋሽም (ዘሁ 23፥19ን ይመልከቱ)። በነቢያት በኩል የሚሰጣቸው ትንቢታዊ መልዕክቶች ይህኑ የማይዛነፍ እውነተኛነቱን ያሳያሉ። ኢሳያስ 8፥20ን ያንብቡ። ምን ወሳኝ ነጥብ ይጠቁማል? Save Notes የትንቢታዊ ስጦታ መመዘኛ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው። ነቢያት የሚናገሩት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር መስማማት አለመስማማቱ መፈተን አለበት። እውነተኛ ነቢይ መጽሐፍ ቅዱስን አይቃረንም፣ አያጣጥልም ወይም ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ሰዎችን አያወናብድም። በሀሰተኛ ነቢያት እንዳይታለሉ ወይም እነርሱን እንዳይከተሉ ነገር ግን እግዚአብሔርን እንዲከተሉ እንዲረዳቸው ሰዎች ቃሉን ጠንቅቀው ማወቅ አለባቸው። በብሉይ ኪዳንም ሆነ በአዲስ ኪዳን ነቢያት ትንቢታዊ መልእክታቸውን ለማጠናከር ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ነቢያት ይጠቅሳሉ። እነዚህ ነቢያት ካለፉት ትንቢቶች አዲስ ማብራሪያዎችን ያክላሉ እንጂ በፍጹም ተቃራኒ መልዕክት አያስተላልፉም። ባለፉት ምዕተ-አመታት እግዚአብሔር ስለሰጠን ትንቢታዊ መልዕክቶች እነዚህ ጥቅሶች ምን ያስተምሩናል? 2ኛ ጴጥ 1፥19-21፣ ሮሜ 15፥4፣ ያዕ 1፥17። Save Notes የድነት ዕቅድን ለመረዳት የብሉይ ኪዳን መሠረት ያለው እገዚአብሔር ራሱ በዘፍጥረት 3፥15 ላይ በሰጠው የመጀመሪያው ተስፋ ውስጥ ነው። የመስዋዕቱ ስነ- ስርአት የዚያ የማዳን ዕቅድ ምሳሌያዊ መግለጫ ነበር። ነገር ግን የእግዚአብሔር በግ ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቶ ከሰዎች መካከል በመኖሩ፣ በመሞቱና በመነሳቱ ተስፋ እንዴት እንደሚፈጽም በተከታታይ ለነቢያት ተብራርቷል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዘገባ የሚያሳየው ደግሞ እግዚአብሔር እውነቱን የሚገልጠው ሰዎች ሊያስተውሉት በሚችሉት መንገድ መሆኑን ነው። በተከታታይ ትውልዶች ሰዎች ቃሉን የማስተዋል ችሎታቸው ጠለቅ እያለ ይሄዳል። “የእውነቱ መገለጥ” ወይም “የእውነት እድገት” የሚባለው ለዚህ ነው። ይህ ማለት አዲስ ትውልድ ካለፈው ትውልድ ይልቅ እውነቱን በበለጠ ለመረዳት ይችላል ማለት ነው። ነገር ግን አንድ መገንዘብ የሚገባን ወሳኝ ነገር አለ። አዲሱ እውቀት የቀድመውን እውቀት የሚቃረን መሆን የለበትም። @SabbathSchool @TekalignSorato
ещё
133 0 23 ноя, 06:01
Фото
https://t.me/sabbathschool?livestream=08d59c9285fb7906f0
ещё
116 0 22 ноя, 20:14
Больше постов

Продолжить анализ этого канала

  • История роста подписчиков
  • Просмотры и охваты публикаций
  • Кто упоминает канал и кого упоминает он
  • Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней