Аналитика Telegram-канала
Подписчики
573
Охват за 24 ч
20
ER за 24 ч
3,49%
Публикаций
467
Динамика подписчиков
7 дней
30 дней
6 месяцев
Больше
23 окт26 окт29 окт
Показаны последние 7 дней
Больше истории →
Охваты публикаций
20.1022.1022.1023.1028.1029.10
7
Средний охват
10
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале
Больше статистики →
Упоминания
5
Упоминаний
4
Из них репостов
4
Каналов
70
Упоминаний
28
Из них репостов
36
Каналов
Последние посты
3 из 467 2 из 467Psalms 92 አማ62 - መዝሙር
12: ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል፥
እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል።
13: በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተተክለዋል፥
በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ።
14: ያን ጊዜ በለመለመ ሽምግልና ያፈራሉ፡
ደስተኞችም ሆነው ይኖራሉ።
ещё
3
0
29 окт, 13:12
ещё
10
0
28 окт, 20:46
እንደ ወንጌላውያን አማኞች ሕብረት ቅጠላ ቅጠልን 🌿 የህይወት እና የክርስትና መመዘኛ ካደረግን 10ት አመታት አስቆጥረናል። በ ...ጣ... ም ሰነባብተናል። ስለሆነም የትየለሌ መዘዝ አግኝቶናል ።
ወሬዬ እንዳይረዝም ወደገደለው ልግባ ✍️
ያቺ ምስኪን ለብቻዋ ፋሽን ሾው የወጣች የምትመስለዋ ዛፍ እንዴት ታሳዝነኛለች መሰላችሁ? አንዳንዴ ምነው ኢየሱስ ባልሆነና ደቀ መዝሙርቱ በሆኑ ኖሮ ቀርበው ያዩአት ብዬ አንጀቴን ትበላኛለች።
ለምን አትሉኝም? ቁንጅናዋ ከእርግማን አላተረፋትም 😢 ተጠግቶ ያያት አምላክ ስለሆነ : ከሩቅ ያሳየችውን ውበት ሲጠጋት ሆና መገኘት አልቻለችም !
📖 (የማቴዎስ ወንጌል 21:19 )
በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና። ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች።
🌿 በብዙ ቅጠል ራሷን ሸፍና ልታመልጥ ሞከረች ። ነገር ግን ልትሸፍነው ያልቻለችዉ ባዶነት ነበረባት።
👇 👇 👇 👇
🥭 እናማ እያነበባችሁ እዚህ ከደረሳችሁ አይቀር ቅጠል ምን እንደሆነ ልንገራችሁ፡
🌿 ቅጠል 1 - #መምራት
ቤተክርስቲያን መምራት፣ (ፓስተር፣ ወንጌላዊ፣ ነብይ፣ አፖስትል፣ ዘማሪ፣ አስተማሪ፣ ሬቨረንድ፣ ቄስ) ሆኖ መሾም ፣ የተለያዩ የአገልግሎት ክፍሎችን ማስተባበር እና መምራት ፣ የአብያተክርስቲያናት ህብረትን መምራት ፣ ካውንስሉን መምራት
🌿 ቅጠል 2 - #የመድረክ_አገልግሎት
በመድረክ ላይ ወጥቶ መስበክ ፣ መዘመር፣ መዝሙር ማውጣት ፣ ፕሮግራም መምራት ፣ ማፀለይ፣ አጋንንት ማውጣት ፣ ትንቢት ማምጣት ፣ የጀማ ስብከት፣ የታመመ መፈወስ ፣ ተከታታይ ትምህርት ማስተማር፣ ቲዮሎጂ መማርና መመረቅ
🌿 ቅጠል 3 - #ማውራትና_መፃፍ
መፅሐፍ መፃፍ ፣ የመፅሃፍ ቅዱስ ማብራሪያ ማሳተም፣ ወይም እንደ እኔ ቲክቶክ ላይ መፃፍ ✍️ ፣ ቲክቶክ ላይ ለሊቱን "ሲያገለግሉ" ማደር ፣ ወይም መፅሃፍ ቅዱሳዊ ሃሳቦችን በቪዲዮ ማጋራት ።
ይሄ ሁሉ ቅጠል ከሆነ እና ፍሬው የቱ ነው ? 🤔 🤔 👇 👇 👇
🥭 ፍሬ 1 - #ተግባራዊ_መውደድ
ሰውን በኑሮ ደረጃ ሳይከፋፍሉ መውደድ፣ የጠሉንንም መውደድ ፣ እርስ በርስ መከባበር፣ የሚያሳድዱንን መመረቅ እንጂ አለመርገም ፣ ይቅር ማለት ። ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ መሰኘት፤ ከሚያዝኑም ጋር ማዘን ። ችግረኛ ለሆኑ ማካፈል ፣ እንግዶችን መቀበል ።
🥭 ፍሬ 2 - #ራስን_መግዛት
ከንዴት፣ ከስድብ፣ ከሐሜትና አሳፋሪ ንግግርን ፣ ለስራ ከመለገም ፣ ከመጠጥ ፣ ከውሸት ፣ ከሌብነት ፣ ከሴሰኝነት ፣ ከዝሙት፣ ከመኩራራት ፣ ለሰው ፊት ከማድላት ፣ ከአድመኝነት ፣ ከስግብግብነት ፣ ከማጭበርበር ........ (ሮሜ 12:9-11, 13-18 ) (ቆላስይስ 3:8) (ገላትያ 5:22)
🥭 🌿 ቅጠል በራሱ ክፋት ባይኖረውም ፍሬ ከሌለው ግን አስመሳይነት ነው። ፍፁም ባዶነት ነው። የአንድ ክርስቲያንም ህይወት መመዘን ያለበት በቅጠል ሳይሆን በፍሬ ነው።
2019 እና የቀረው ዘመናችን ከቅጠላ ቅጠልነት 🌿 ወደ ፍራፍሬነት 🥭 የምንሸጋገርበት ዘመን ይሁንልን!
ещё
9
0
23 окт, 08:07
Продолжить анализ этого канала
- История роста подписчиков
- Просмотры и охваты публикаций
- Кто упоминает канал и кого упоминает он
- Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней