Аналитика Telegram-канала
Подписчики
15 355
Охват за 24 ч
75
ER за 24 ч
0,49%
Публикаций
4 471

Динамика подписчиков

7 дней 30 дней 6 месяцев Больше
8 ноя11 ноя14 ноя
Показаны последние 7 дней Больше истории →

Охваты публикаций

12.1112.1113.1113.1114.1114.11
7
Средний охват
17
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале Больше статистики →

Упоминания

127
Упоминаний
8
Из них репостов
31
Каналов
Нет примеров за последние 90 дней
Все упоминания

Последние посты

3 из 4 471 2 из 4 471
#መጨረሻችን_ያማረ_ይሁን ይሄ መልዕክት የብዙዎች ጸሎት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ ጌታ በልቤ ላይ ያከበደው መልዕክት ነው አታሰልፉ የምድር ሕዝቦች ሁሉ የሚደነቁበትንና ማንም ያላየውን ጥበብና ዕውቀት እግዚአብሔር ለሰለሞን ሰጥቶ ነበር በምድር ላይ ከነበሩት ነገስታት ሁሉ በጥበብ፣ በዝና ሆነ በሀብት የሚደርስ ሰው አልነበረም። ከአንደበቱ የሚወጣውን ቃል ብቻ ለመስማት ሰዎች ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ይመጡ ነበር። #1ነገ4:34 ሰለሞን አጀማመሩ መልካም ነበር እግዚአብሔርንም እየሰማ በትክክለኛ ጎዳና የሚሄድ ንጉሥም ነበር። ነገር ግን መጨረሻው እንደ መጀመሪያው አልሆንም መጥፎ አወዳደቅ ወደቀ። እግዚአብሔር ከዚህ ይጠብቀን🙏 በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እግዚአብሔር እስራኤላውያን የጋብቻ ሕይወት እንዳይመሰርቱ የነገራቸው ነበሩ እነሱም #ሞዓባውያን፤ #አሞናውያን፤ #ኤዶማውያን፤ #ሲዶናውያን፤ #ኬጢያዊውን ነበሩ። እግዚአብሔር ልባችሁን ወደ አምልክታቸው ይመልሱታልና ከእነርሱ ጋር መጋባት የለባችሁም ብሎ ነበር። ግን አንድ ቀን ንጉሥ ሰለሞን ከእነዚህ ጋር የፍቅር ግንኘነት ጀመረ። ከዚያም እነዚህ አሕዛብ ሴቶች ንጉሥ ሰለሞንን ወደ ጣኦት አምልኳቸው መለሱት። 1ኛ ነገሥት 11 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ² እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች፦ አምላኮቻቸውን ትከተሉ ዘንድ ልባችሁን በእውነት ያዘነብላሉና ወደ እነርሱ አትግቡ፥ እነርሱም ወደ እናንተ አይግቡ ካላቸው ከአሕዛብ፥ ከእነዚህ ጋር ሰሎሞን በፍቅር ተጣበቀ። ³ ለእርሱም ወይዛዝር የሆኑ ሰባት መቶ ሚስቶች ሦስት መቶም ቁባቶች ነበሩት፤ ሚስቶቹም ልቡን አዘነበሉት። ⁴ ሰሎሞንም ሲሸመግል ሚስቶቹ ሌሎችን አማልክት ይከተል ዘንድ ልቡን አዘነበሉት፤ የአባቱ የዳዊት ልብ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም እንደ ነበረ የሰሎሞን ልቡ እንዲሁ አልነበረም። ⁵ ሰሎሞንም የሲዶናውያንን አምላክ አስታሮትን፥ የአሞናውያንንም ርኵሰት ሚልኮምን፥ ተከተለ። ⁶ ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገርን አደረገ፥ እንደ አባቱም እንደ ዳዊት እግዚአብሔርን በመከተል ፍጹም አልሆነም። የሰለሞን ፍጻሜ የክብር አልነበረም የውርደት እንጂ ወዳጆቼ የብዙ ሰዎች መጀመሪያቸው መልካም ሆኖ መጨረሻቸው ግን መጥፎና ልብ የሚሰብር ሆኖአል እግዚአብሔር የእኛንም ፍጻሜ መልካም ያደርግልን። የሁልጊዜ ጸሎታችሁ ፍጻሜዬን አሳምርልኝ የምለው ይሁን🙏 የሰው መጨረሻው ስያምር ነውና ደስ የምለው አምላክ መጨረሻችሁን ያሰምር🙏 በመንፈስ ጀምራችሁ በስጋ አትጨርሱ🙏 ወንድማችሁ ፍሬ ነኝ .          #እወዳችኋለሁ❤ 👉እኔን ማገኘት ለምትፈልጉ 👉  @abit9 🔹🔸🔹Join Us🔹🔸🔹 @superchristiantube7 @superchristiantube7 @superchristiantube7 sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
ещё
5 0 14 ноя, 13:27
🤩ምን አይነት ትምህርት ይፈልጋሉ አሁን በዳምጣው የምትሉትን መርጣው "Join" ያድርጉ 🙏🙏
ещё
4 0 14 ноя, 08:03
🤦‍♀ከራስ ጋር ትግል🤦‍♀ 📖ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ📖         ምዕራፍ=አንድ          ክፍል=24 ድንገት ሳላስበው ጀርባዬን ያዘኝ በጣም ደንግጬ "በእየሱስም!!!" አልኩ ከድንጋጤዬ ብዛት እጄ ይንቀጠቀጣል ሊዱም እጄን ጥብቅ አድርጋ ያዘችኝ ሁለታችንም ዞር ስንል ዮናስ ነው "ሜሪ ይቅርታ አስደነገጥኳችሁ እንዴ? አለን በውስጤ ኡፍፍፍ እሱ ነው እንዴ ስንቱን አሰብኩት አልኩኝና ለመረጋጋት ሞከርኩ ሊዱዬ መደንገጧ አልተዋትም በጣም ኮስተር ብላ "እንዴ ዮናስ እዚህ ምን ታደርጋለህ?" አለችው "እ ሜሪዬ  ሊዱ አንድ የማናግራችሁ ነገር ነበር" አለን እውነት ለመናገር ዮናስ ምኑም አይመቸንም ገና ያየሁት ቀን ነው የሆነ የጨነቀኝ "ስለ ምን ጉዳይ" አልኩት ግራ በመጋባት ስሜት ውስጥ ሆኜ "እሱን እንኳን እየሄድን ነግራችኋለሁ"  አለን ምንም አልተዋጠልንም ግን እሺ ብለነው አብረን መሄድ ጀመርን "እና ምን ነበር? አልነው "እየውላችሁ እኔ ስለማስብላችሁ እና እንድትጎዱ ስለማልፈልግ ይህን ነገር ነግራችኋለሁ ከእነ ሊያ ጋር ግንኙነታችሁን አቁሙ እነሱ ቆርጠው ሊያጠፏችሁ ነው የቀረቧችሁ" አለን ይህ ቀን ዮናስ እንዲህ ሲለኝ ህይወቴ ላይ ከማልረሳቸው ቀናቶች መሀል አንድ ነው ልቤን የሆነ ስሜት ተሰማኝ ሊዱም በጣም ደነገጠች ሁለታችንም የምንመልሰው ነገር አጣን ያለን አማራጭ ዝምታ ነበር ዝም አልነው። ሊዱ ቤት ደረሰች "በቃ ሰላም እደሩ" አለችን የሆነ ግራ እንደተጋባች ያስታውቅባታል ሁለታችንም ተወዛግበናል ዮናስ ዞር ሲልልን ሊዱዬ ድምፅ ሳታወጣ "ማታ እናወራለን" አለችኝ እኔም ከዮናስ ጋር ተመለስኩ "እና ሜሪዬ" አለኝ እየተቅለሰለሰ በሚደብር ሁኔታ ምንም ቀልቤ አልገባም ያወራውንም ጭራሽ አላመንኩት ብቻ እያንገራገርኩም በሀሳብ ተዋጥኩ "ሜሪ!" አለኝ " እ እ ምን አልከኝ?" አልኩት "የት ሄድሽ የኔ ቆንጆ?" አለኝና በሚደብር አስተያየት አይቶ አቀፈኝ ከመጀመሪያውም ያላማረኝ አሁንማ ጭራሽ አስጠላኝ ፊቴን ሳልፈታ እንደዛው እንደተኮሳተርኩ "በቃ ደረስኩ ቻው" ብዬው ሊያቅፈኝ የነበረውን ልጅ አገርጥቼ እጄን ዘርግቼለት ጨበጥኩብ ብቻ እንደደበረኝ ገብቶታል "እሺ ቻው" ብሎኝ ሄደ እኔም ወደቤት ገባሁ ስገባ አባዬ እና ሶሲ መጥተዋል ቤት ሆነው ድምፃቸው የውጭ በር ድረስ ይሰማል ስገባ አለማቸውን ረስተው ያሽካካሉ "ሰላም ለዚህ ቤት" አልኩና ገባሁ "ሰላማችሁን ተቀብለናል" አለኝ አባ ወደ እነሱ ሄጄ አባቴንም ሶሲንም ሰላም አልኳቸው ትንሽ ቁጭ ብዬ አወራኋቸው እና ወደ ክፍሌ ገባሁና ስልኬን ከፍቼ ለሊዱ ደወልኩላት "ሄሎ ሊዱ" አልኳት "ውይ ልደውልልሽ ስል ገባሽ?" አለችኝ "አዎ ገባሁ" አልኳት "እና ሜሪዬ ዮናስን አመንሽው??" አለችኝ "በፍፁም ሲጀምር ከመች ጀምሮ ነው እሱ እኛን የሚመክረው መንገድ ላይ ራሱ እየተጃጃለ ነበር የሆነ አብረነው እንድንለወ ይፈልጋል" አልኳት በንዴት መልክ ጮክ ብዬ "ሜሪዬ ግን እንጃ ውስጤን ምንም ደስ እያለው አይደለም በቃ ግን ዮናስ ልክ ይሁን አይሁን አላውቅም ግን ብቻ ውስጤ ህመም እየተሰማኝ ነው" አለችኝ ሊዱ እንዲህ ስትለኝ የወሰድኩት አማራጭ እሷን ማሳመን እንጂ ነገሮችን ማስተዋልን አልነበረም "ሊዱዬ ዮናስ አጉል ለመወደድ ብሎ ያወራን ይመስለኛል ደሞ ለምን እኛን ብቻ አወራን ለምን ከነቢኒ ጋር ሆነን አልነገረንም እ ብቻ ግን እንጃ" አልኳት ውስጤን እየታወቀው አዕምሮዬ ግን አያታለለኝ ራሴን ከራሴ እየሸወድኩ "እሱማ አዎ ብቻ ግን ለእነቢኒ ተሳስተሽም ቢሆን እንዳትነግሪያቸው በባዶ ሜዳ ማጨናነቅ ነው የሚሆንብን" አለችኝ "እሺ በቃ አልነግራቸውም" አልኳት እና ቻው ብያት ስልኩን ዘጋሁት እውነት ለእነ ቢኒ እንዳትነግሪያቸው ስላለችኝ ትንሽ ደብሮኛል ምንም ነገር ደብቀናቸው አናውቅም ነበር ግን ደግሞ እውነቷን ነው ማስጨነቅ ብቻ ነው ትርፉ እኔም ነገሩን ትቼ ማጥናት ጀመርኩ "ሜሪ ራት ቀርቧል" አለችኝ ሶሲ ጮክ ብላ "እሺ መጣሁ" ብዬ መፅሀፎቼን አስተካክዬ ወደ ሻወር ቤት ሄድኩና ታጥቤ ወደ ማዕዱ ቀረብኩ በጥሩ ሁኔታ ራት በላን ሰላም ነኝ ብዬ ድንገት ዮናስ ያለን ነገር በማሰብ ውስጤ ይረበሻል እውነቱን ይሆን እንዴ?? አይ አይ ሊሆንማ አይችልም እያልኩ ከራሴ ጋር ክርክር ጀመርኩ ነገሩን ሳብሰለስለው ምግቡም አልበላ አለኝ እና ለሶሲ እንደደከመኝ ነግሬያት ክፍሌ ገብቼ ተኛሁ። ነገ ቅዳሜ ነው ክላስ የለም ጭው ያለ እንቅልፍ ወስዶኝ ለካ ነግቷል አባ ወደ ክፍሌ መጥቶ "እረ ሜሪ! ወይ ታሪክ እኔ አጥኚ እላለሁ እሷ ቢወስዷትም አትሰማ" እያለ የወደቁብኝን ወረቀቶች ያነሳሳል በዛ መሀል ተነስቼ "ውይ አባ!!"  አልኩት "ወዬ አስደነገጥኩሽ እንዴ?" አለኝ "ኸረ አላስደነገጥከኝም" አልኩት ከአልጋዬ እየወረድኩ "እነ እማስ?" አልኩት "አለች ሳሎን ቡና እያቀራረበች ነው ሶሲም እዛ ነች" አለኝ "እንዴ! ሶሲ ምን አስባ ነው?" አልኩት አልጋዬን ለማንጠፍ እያዘጋጀሁ እሱም ነገሩ ገብቶት ፈገግ እያለ "ግድ ሆኖባት ነው ትምህርት አላት" አለኝ "እ እንደሱ በለኛ" አልኩት እኔም እየሳኩ "በቃ ነይ" ብሎኝ ወጣ ክፍሌን አፀዳድቼ ተጣጥቤ ወደ ሳሎን ሄድኩ እማዬ  "ሜሪዬ" አለችኝ ቁርስ ቀርቦ ሶሲ ድፍት ብላበታለቻ ላያት ምግብ ከበላች ብዙ አመታት ያለፉ ትመስላለለች "ቀን ወጣልኝ አየሽ ቀደምኩሽ" አለችኝ የጎረሰችው የፍጥኝ ይዞ አላስወራ እያላት🤭 "እረ እሱን ትተሽ ቶሎ ብዪና ሂጂ አለቻት እማ እኔም ተቀላቀልኳቸውና በልተን ተነሳን የበላላሁበትን እያነሳሳሁ  እያለ የሶሲ ስልክ ጠራ "ሶሲ! ሶሲ! ስልክሽ እየጠራ ነው" አልኳት "ውይ እሺ ብላኝ" እየሮጠች ሄደች ጓደኛዋ ነበረች "በቃ እንውጣ ልትለኝ ነው ቻው ሰላም ዋሉ" ብላን ወጣች ትንሽ ቆይቶ አባቴም ወጣ እኔና እማ ቀረን "ውሹዬ ክላስ አለሽ እንዴ?" አለችኝ "እረ የለኝም" አልኳት "በቃ እኔ ቸርች የእናቶች ፀሎት አለን ልሂድ" አለችኝ "እሺ እማ በቃ ሂጂ" አልኳትና ወጣች እኔም ቤት አፀዳድቼ የቤት ውስጥ ስራዎችን ሰራራሁና ቲቪ ከፍቼ ሶፋ ላይ አረፍ አልኩ ወዲያው ስልኬ ጠራ ሳየው ልቤ በሀይል መታ ንዴት ይሁን መሰልቸት ግራ መጋባት ልቤን ተሰማኝ እየተርበተበትኩ አነሳሁት . . .   . . . .ይቀጥላል. . . . . 🔹🔸🔹Join Us🔹🔸🔹 @ReformationNeeded @ReformationNeeded @ReformationNeeded     ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ   sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ
ещё
5 0 1 13 ноя, 21:37
Больше постов

Продолжить анализ этого канала

  • История роста подписчиков
  • Просмотры и охваты публикаций
  • Кто упоминает канал и кого упоминает он
  • Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней