Не попадитесь на накрученные каналы! Узнайте, не накручивает ли канал просмотры или подписчиков Проверить канал на накрутку
Прикрепить Телеграм-аккаунт Прикрепить Телеграм-аккаунт

Телеграм канал «QUOTEOPIA 📚»

QUOTEOPIA 📚
3.3K
55
213
1
1.1K
your daily source of inspiration and wisdom! From ancient teachings to modern insights, we bring you powerful quotes that motivate, uplift, and ignite creativity.Join us on a journey through words that shape minds and inspire greatness.
Contact:-@fammetz
Подписчики
Всего
1 208
Сегодня
0
Просмотров на пост
Всего
83
ER
Общий
6.86%
Суточный
5.22%
Динамика публикаций
Telemetr - сервис глубокой аналитики
телеграм-каналов
Получите подробную информацию о каждом канале
Отберите самые эффективные каналы для
рекламных размещений, по приросту подписчиков,
ER, количеству просмотров на пост и другим метрикам
Анализируйте рекламные посты
и креативы
Узнайте какие посты лучше сработали,
а какие хуже, даже если их давно удалили
Оценивайте эффективность тематики и контента
Узнайте, какую тематику лучше не рекламировать
на канале, а какая зайдет на ура
Попробовать бесплатно
Показано 7 из 3 283 постов
Смотреть все посты
Пост от 26.10.2026 20:30
35
0
0
𝓦                   ❀༉‧₊˚. ኤሴቅ .˚₊‧༉❀
                         𖤣𖥧 #ክፍል_228 𖥧𖤣

..... ሙሉቀን ዳሳሽን ወደ ውጪ አስወጥቶ "ዘይት ምናምን በደንብ አለሽ?"አለ " አይ አይቨቃም ትንሽ ነው የቀረው" "ስለዚህ ወደ ገበያ ቶሎ ሄደሽ ወይም ልጅ ልከሽ አምስት ሊትር ዘይት ግዥ። እንዲሁም ሽንኩርት በርበሬ ብቻ የቀረውን አሟይ ወይም ከእናቴ ሄደሽ ይዘሽ ነይ ያው ማታ ሙክቱን መጣላችን ስለማይቀር " "እሺ ይሁን እኔ ሰንዳ ሰንዳ ልበል እንግዲያውስ ቀዳማዊን አንተ አጫውተው። "ብላው ወደ ውስጥ ገባች። ቀዳማዊና ሙሉቀን ስላለፏቸው ጊዚያቶች እያነሱ በሚያስቀው እየሳቁ በሚያሳዝነው እየተከዙ በሚያኮሩት እየኮሩ ለረጅም ስዐት ተራራው ላይ ተቀምጠው ይጫወታሉ።
○●○●
የራስ አምባ ነዋሪ አበይት ዜናው የቀዳማዊ መምጣት ሆነ። ከልጅ እስከ አዋቂ ሁሉም መምጣቱን ሰማ። በትንሽ ስዐታት ነበር ለሁሉም የተዳረሰው። አጠያያቂውና አስገራሚው ነገር ግን ከመምጣቱ በላይ የሚያርፍበት ቦታ ግራ ማጋባቱ ነው። አንዳንድ የቀበሌው ነዋሪዎች <በጭራሽ የወይዘሮ አትጠገብ ቤት እንደማያርፍ ምለው ሲናገሩ> አንዳንዶቹ ደግሞ እርግጠኛ ባይሆኑም ግን ምንም ቢሆን እናቱ ስለሆነች እናቱ ጋር ነው የሚያርፈው ብለው በሌላ ጎራ ሆነው ይሟገታሉ። የተወሰኑት ደግሞ እናቱ ጋር በጭራሽ አያርፍም። ከባልንጀራው ጋር ነው የሚቆይ ይላሉ ቆፍጠን ብለው። ወሬው ገበያ የነበረው ሰው ተሳምቶ ገበያ ያልሄዱት ሁሉ ሰሙ የወይዘሮ አትጠገብ ሴት ልጆች የሰሙትን ለማመን የከበዳቸው ይመስላል። ርብቃ ከባለቤቷ ጋር ሆነው ዜናውን ሲሰሙ "ይሄው በስተመጨረሻ መጣ። ወትሮስ ሰይጣን አይሞት"አለች። ባለቤቷ እርገጤ መኮነን "እየውልሽ ልብ ግዢ ልጁ እንደሁ ከተሜ ነው። በዛ ላይ የተማረ ነው። ስለዚህ ሰከን ማለት ነው የሚበጅ። ታልሆነ ነገሩን ታበላሹታላችሁ። ህጉንም ምኑንም ያውቀዋል። እና በኋላ ዋይዋይታ አይሰራም። እሱ ገፍቶ እስካልመጣ ድረስ አርፈሽ ተቀመጭ"አለ ኮስተር ብሎ "አንተ ደግሞ ምን አይነት ምክር ይሉት ነው የምትናገረው? እስኪመጣብሽ ድረስ አርፈሽ ተቀመጭ ማለት ምን ማለት ነው? ስታስበው የመጣው ለምን ይመስልሀል? ነው አትዘጋጅ እያልከኝ ነው?"አለች እሷም ኮስተር ብላ። "ተይ እንጅ ርብቃ አሁን እንደዛ አልኩ ወጣኝ? እሺ እኔ የታየኝን ነው የነገርኩሽ። ከዚህ በላይ ምንም አልልሽም ልብሽ የፈቀደውን አድርጊ"ብሎ ጋቢውን አጣፍቶ ተቀመጠ። ማለፊያም አድናም ሌሎቹም እህታማቾች የቀዳማዊን መምጣት ሰምተው መረበሽ ጀመሩ። ጉዳዩን ሰምተውም ዝም አላሉም ለእናታቸው ለወይዘሮ አትጠገብ ለመናገር ተስማምተዋል። ከነ ማለፊያ በፊት የቀዳማዊ መምጣትን ግን ወይዘሮ አትጠገብ ቀድመው ሰምተው በሀሳብና በጭንቀት የሳር ጎጇቸው በር ላይ የያዟትን እንጨት እየቆረቆሩ ተቀምጠዋል።
○●○●
ጀንበር የተከዜን ውሃ ለሁለት እየሰነጠቀች። በተራሮቹ መሀል ሆና ግራ ና ቀኝ ሞገስ የሆኗትን ተራሮች ውበትና ጥላ አግዝፋ እያሳየች የዛፎቹ ጥላም ተሸቀንጥሮ ማዶ ደርሷል። ቀዳማዊና ሙሉቀን ጎን ለጎን ተቀምጠው ይመለከቷት ነበር። " መቼም ለእሱ ሁሉም ነገር ቀላል ነው። ለብዙ አመታት ሁለታችንም ይችን ጀንበር ለየብቻችን ስንቀበልና ስንሸኛት ብንቆይም በስተመጨረሻ ግን በፈጣሪ ፈቃድ ተገናኝተን አብረን ልናስገባት ቻልንን"አለ ቀዳማዊ። "በጣም እንጅ። እኔማ በዛው ሰምጠህ ትቀራለህ ብዬ እፈራ ነበር የማትመጣ እየመሰለኝ..... ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ዳሳሽ ጠራቺው። "አቤት ዳሳሽ"አለ ከተቀመጠበት እየተነሳ "እረኛው ስለመጣ ና ና በጊዜ አፍስሰው"አለች። "እሺ መጣሁ "አለና "ወንድሜ ትንሽ መቆየት ከፈለክ ተቀመጥ። እኔ የሆነች የማደርጋት ነገር አለች"አለና ትቶት ሄደ። ቀዳማዊም "እሺ ሂድ እኔም ትንሽ ብቻ ነው የምትቆየው ከዛ እመጣለሁ"ብሎት እርሻውን እና አካባቢውን እያፈራረቀ ይመለከታል። ወቅቱ እየመሸ በመሆኑ እረኞች ከከተቱበት ውሎ ቆይተው እንጨት በትከሻቸው ይዘው ግልገሎቻቸውን እየቀረቡ ወደየ ቤታቸው ይገባሉ። ትልልቆቹም ከየዋሉበት ቆይተው ሲመጡ ቀዳማዊን እየተመለከቱ ግራ እየተጋቡ ይሄዳሉ። ይህን ሁሉ የሕይወት መስተጋብር ከተፈጥሮ ጋር በቀዝቃዛ ነፋስ ሽውሽውታ ከኮመኮመ በኋላ ነበር ምሽቱ መሄዱን ያስተዋለው። ሙሉቀን ለአምስት አመት ያህል ያሰባውን ሙክት የቀዳማዊን መምጣት ተከትሎ በደስታ ሸክ አደረገው። ብረትምጣዱና የተለያዩ ቅመሞች ተዘጋጅተው ተቀመጡ። ጥሪ የተደረገላቸው መልካሙና ቤተሰቡ እንዲሁም የሙሉቀን ሚዜዎች በጊዜ መጥተው ሙክቱን እያስተራረዱት ይገኛሉ። ቀየው ላይ ልክ እንደ ካንፋየር እሳቱ እየነደደ። ዙሪያውን ሆነው እንደ እሳት ዳር ጨዋታ እየተጫወቱ ጥብሱን እየጠበሱ ነው። በየተራ እያማሰሉ የባጥ የቆጡን እያሉ ይጫወታሉ። ሙሉቀን ቀደም ብሎ የቀዳማዊን መምጣት ለእናቱ ስለነገራት በእልልታ ገባች። ጎረቤቱ ሁሉ ምን ሆና ነው ብሎ እስኪታዘበታ በእልልታ ጮኸች። ቀዳማዊንም ለረጅም ደቂቃ እያዟዟረች ስትስመው ቆየች። ቀዳማዊም አቀፋት በቅቤ የታጠነው ነጠላዋና አድሩስ አድሩስ የሚሸተው ማዕዛዋ አንዳች የደስታ ስሜትና የእናትነት ቀና ሰጥቶት በደስታ አይኖቹን ጨፈን አድርጎ ይስብ ጀመር። ከዚህም ከዚያም የቀዳማዊን መምጣት የሰሙ ጎረቤቶችና የሙሉቀን ዘመዶች ምንም እንኳ ቀዳማዊ ምናቸውም ባይሆን ሙሉቀንን እንኳን ደስ አለህ ለማለት ወደ ቤት ይጎርፉ ጀመር። ቤቱ በሰው ተጥለቀለቀ። ቤት ውስጥ መቀመጫ ስላልነበር አግዳሚ ጣውላ ላይ ከደጅ ተደርድሮ ሰው እዛ መሆን ጀመረ። ሙሉቀን ለመጣው ሁሉ ጥብስ እና ዱለት እያቃመሰ ሸኘ። ምሽቱ እየገፋ በመሄዱ ሰዎቹ ቀዳማዊን "እንኳን ለአገርህ አበቃህ!"እያሉ ተሰነብተውት እየወጡ ሄዱ።
○●○●
ወይዘሮ አትጠገብ በሀዘን ቀዬ ቀዬውን እያየች ሳለ ማለፊያና አድና መጡ። "ምነው እታተዬ እዚህ ኩርምት ብለሻል?"አለች አድና። "እንዲሁ ነው ልጄ ግቡ"አለች እሷም ከተቀመጠችበት እየተነሳች። ማለፊያና አድናም ተከታትለው ገብተው ተቀመጡና ሁለቱም በዝምታ ተውጠው ወይዘሮ አትጠገብን ይመለከታሉ "ምን ሆናችሁ ነው?"አለች ሁለቱንም እየተመለከተች። "የቀዳማዊን መምጣት አልሰማሽም ማለት ነው?"አለች አድና "እሱንማ ሰምቻለሁ"አለች አትጠገብ "እና ከዚህ በላይ ችግር ኖሮ ነው። ምን ሆናችኋል የምትይን "አለች ማለፊያ "አይ ልጆቼ እና እኔ ምን ማድረግ እችላለሁ። እኔ ጋር እኮ አይደለም የመጣው። እኔ ጋር ቢመጣስ የምትሉትን አደርግላችሁ ነበር። እና አሁን የሰው ቤት ሄጄ ምን እንዳደርግ ነው የምትፈልጉት? ይሄ ድንበር መሻገር ነው። የሌላን ሰው እንግዳ ምን እንዳደርግ እየጠየቃችሁኝ ነው?"አለች በስጨት ብላ። ማለፊያና አድና ደነገጡ። ወይዘሮ አትጠገብ እንደዚህ ሆና አታውቅም። እንኳን ልትበሳጭባቸው ይቅርና ቁጣ የቀላቀለበት አነጋገር ልትናገራቸው በውል እንኳ ለሚጠይቋት ነገር አቅማምታም ሆነ እሺ ከማለት ውጪ መልስ መልሳላቸው አታውቅም። እርስ በእርስ ተያዩና "እታተዬ ምንድን ነው የሆንሺው?" አለች ማለፊያ ወደ ወይዘሮ አትጠገብ እየተጠጋች። ወይዘሮ አትጠገብ ቀዬ ቀዬውን እያየች ከመጨሞጩ አይኖቿ እምባወቿ ይፈሳሉ።.....
                  🖎​✐✎ ይቀጥላል...​ ✎​✐✍︎
            ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ like...
@quoteopia
@quoteopia
❤ 8
Пост от 26.10.2026 19:30
14
0
0
𝓦                   ❀༉‧₊˚. ኤሴቅ .˚₊‧༉❀
                         𖤣𖥧 #ክፍል_227 𖥧𖤣

..... ዳጊዬ ና አጎትህን አስታጥበው"አለች ህፃኑ ዳግም እንደ ቅንቡርስ እየተንከባለለ መጣና ከእሱ ክንድ ክብደት በላይ የሚመዝነውን ማስታጠቢያ አንስቶ ከእንደገና ወደቀበት ውሃው ወለሉ ላይ ፈሰሰ። ቀዳማዊ የህፃን ዳግምን መደንገጥ ተመለከና በፍፁም ፈገግታ "ተወው ይደፋ ና እኔ ልርዳህ"አለና ራሱ ጆጉን እየመጠነ ከታጠበ በኋላ አቅፎ ሳመና አቀፈው። "ኧረ ያቆሽሽሀል። አቧራው ላይ ነው ሲጫወት የነበረው"አለች ዳሳሽ ፊቷን እያጨፈገገች። "እና ቢቆሽሽስ የሚቆሽሸው እኮ ልብስ ነው። ልቤ አይቆሽሽ ደግሞ ልብስ ቢቆሽሽ ይታጠባል። ልጆች ደግሞ ጣፋጮች ናቸው። በዛ ላይ አሁንም አሁንም ነው ከአቧራውም ከጭቃውም የሚሉት። እና አቧራ ሆነዋል ብለን ከማቀፍ ወደ ኋላ አንል"አለና ይበልጡን አቅፎ ሳመው። ዳሳሽ "ጥሩ እንግዲያውስ በፈቃድህ ከሆነ ጥሩ" አለቺና ወደ ጓዳ በመግባት አዲስ በተቋጨች ሞሰብ በአለላና ጎንጋ ባጌጠች ሞሰብ እንጀራው ታጥፎ ታጥፎ በዳር በዳር በአራት አቅጣጫ ምሳሌ አራት እንጀራና ከውስጥ ደግሞ ሁለት እንጀራ ደራርባ አቀረበች። ገንቦውን ቀረብ አደረገችና ሞሰቡ ላይ እርጎውን ዘረገፈችው። ቀዩን ወጥ በጎን አድርጋ እንቁላሉን ደግሞ በአንደኛው ገፅ በማድረግ መሀሉን በእርጎ ሞላችው። ቃሪያውን በዳር በዳር ጣል ጣል አድርጋ ከእርጎው ጎን ትንሽ ድቁስ በእንጨት ማኔኪያ ቀንሳ ካስቀመጠች በኋላ በወተት ማለቢያ ቅሉ እርጎውን ሞልታ እንዲሁም በጠላ መጠጫ ሽክናውም እርጎውን ቀድታ ለቀዳማዊና ለመልካሙ በእጃቸው አስይዛ ማዕዱን አቀረበች። "ዳግሜ ና ወደ እኔ አጎትህ በደንብ እንዲበላ ከእቅፉ ውጣ" ብላ ኮስተር አለች። ቀዳማዊ ላለመልቀቅ ቢያንገራግርም ዳሳሽ ግን ኮስተር አለች። ህፃኑም የቀዳማዊ ፍቅር ና እቅፍ ሳያሸንፈው የእናቱን ቁጣ በመፍራት ለእናቱ ድልን አቀዳጅቶ እያኮረፈም ቢሆን ወደ እሷ ሄደ።

ሙሉቀን ዳሳሽ በአስቸኳይ ስላስጠራችበት ምክንያትና እንግዳ ማንነት እያብሰለሰለና ብዙ እያሰበ መንገዱ ሳይታወቀው ቤት ደረሰ። መጥረቢያውን የቤቱ የውጭ ግድግዳ ላይ አስቀምጦ ወደ ቤት ግብት ብሎ መደቡን ሲመለከት ቀዳማዊን ተመለከተው። በቆመበት እንደ ሀውልት ድርቅ ብሎ ቆመ። አይኖቹ ይርገበገባሉ አሁንም አሁንም እይታውን ሳይሰብር ይመለከተዋል ነገር ግን አፉ ተያያዞ አንደበቱ ምንም ቃል ሊያወጣ አልቻለም። አመታት የፈጀ የወንድምነት ናፍቆት በፊቱ ተመልሶለት ሲመለሰት መልሱ ከአቅሙ በላይ ሆነበት። ሰውነቱ ሊቋቋመው ያልቻለ የልቡ የብስ ሊቆጣጠረው ያልቻለ የናፍቆት ማዕበል መልስ። ከጓደኝነት የሚያልፈው እና ከስጋ ዝምድና በላይ የሚርቀው የመዋደዳቸውን መልስ ሙሉቀን መቀበል ተሳነው። ሰውነቱ እየተርበተበተ እንደ ሴት ልጅ መልፈስፈስ ያዘ። የቀዳማዊ የወጣት እድሜ ላይ የእራሱን ልጅነትና የቀዳማዊን የመከራ ጊዜያት በትዝታ የኋሊት ተመልሶ ቃኛቸው። ፊቱ ላይ ያለውን ጓደኛውን በስስት በህይወት እንዳየው ሲያይ በደስታ የሚያደርገው ጠፋው። ቀዳማዊ በሙሉቀን ሁኔታ ሆድ ባሰው። እሱ ጋር የነበረው ናፍቆትና ሆድ መባስን ተመለከተ። ሙሉቀንም እንደ እሱ ለአመታት በናፍቆት እንደተጎዳ በራሱ ህመም ስም ተሰማው። አለቀሰና ከማዕዱ ተነስቶ ተጠመጠመበት ሙሉቀን በእንባ ታጥቦ አቀፈው ተቃቀፉ የእነሱን ሁኔታ እያየች ዳሳሽ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። መልካሙም ከእንደገና ተንሰፈሰፈ። ለብዙ ደቂቃዎች ትከሻቸውን እየተቀያየሩ ተላቅሰው ተሳሳሙና ሙሉቀን አይኖቹን ጠረግ ጠረግ አደረገና "በቃ አታልቅስ ወንድሜ "ብሎ የቀዳማዊን ጉንጮች በሻከረ መዳፉ ጠረጋቸው። ቀዳማዊም ቀና ብሎ ተመለከተውና ከእንደገና አቀፈው። ሙሉቀንም በድጋሚ አቀፈው። " ሙሌዋ ጊዜ እኮ ለሁሉም ነገር መላ አለው። ይሄው አመታት ቢሄዱም ፈጣሪ የውስጣችሁን ንፁህነት ስላዬ አገናኛችሁ። እና አሁን ማልቀስ የለባችሁም። እሱ የሰው አገር ሰው ስለሆነ እንባውን የምታብስለት አንተ ነህ። ከአንተ ውጪ በማያቀው ሀገር ነው ሲኖር የነበረው ስለዚህ አሁን መላቀሱን ተውና በፍቅር ማዕዱን እንጨርስ" አለ መልካሙ "እሱስ እውነትህን ነበር ምን ላርግ ብለህ ነው መልኬ ላመታት እኮ ስብሰለሰል ነበር። ግን ክብሩ ይስፋ በስተመጨረሻ ለአይነ ስጋ አበቃን"አለና እጆቹን ወደ ላይ ከፍ አደርገ። የቀዳማዊ ጎን ላይ ሆኖ ሙሉቀን ምግቡን ትቶ ዝም ብሎ ቀዳማዊን ይመለከታል። ቀዳማዊም አልፎ አልፎ እየተመለከተው ይጎርሳል። "እንግዲህ በደንብ ብላ እህል ተቀረበ ወዲያ ብሉ ማለት አትብሉ ነው"አለች ዳሳሽ። ቀዳማዊ ሳቅ አለና "ኧረ በደንብ እየበላን ነው"አለ። "ዳሳሼ እስኪ ሌላ ነገር አቅርቢለት። ምን ይሰናዳል?"አለ ሙሉቀን። "ኧረ በጭራሽ ያለው በቂ ነው ወንድሜ። በጣም ጣፍጦኝ ነው እየበላሁ ያለሁት"አለ ቀዳማዊ "እሺ የሚጠጣ እርጎ ጨምሪለት!"አለ "እሺ ብላ ተነሳችና ይዛ መጥታ ጨመረችለት። ቀዳማዊ ምንም ቢል እንደማይሰሙት ሲረዳ ዝም አለ። ሙሉቀን አይቶ አልጠግበው አለ። "እኔ እኮ ዛሬ ካለወትሮዬ ልቤ ይደነግጣል። ሆዴን ፍርሀት ፍርሃት አለው። ዛሬ ምን ሊገጥመኝ ነው እያልኩ ለካ ደስታየን ሊያሳየኝ ኖሯል በፍርሃቴ የሚነግረኝ "አለና እጁን ወደ ማዕዱ በመላክ ደህና ጉርሻ በመያዝ ቀዳማዊን አጎረሰው። " እስካሁን እኮ ለራስህ አልበላህም። አንተም እየበላህ እንጅ "ብሎ ቀዳማዊ እንደ ሙሉቀን በዛ ያለ ጉርሻ ባይሆንም ይበቃል ብሎ ያሰበውን ያህል ጠቅልሎ አገረሰው። ሙሉቀን በደስታ ተቀብሎ ጎረሰ። "እስኪ ዳሳሼ እንጀራም ወጥም ጨመር ጨመር አድርጊ"አለ ሙሉቀን የሚለው ነገርና የሚያደርገው ነገር ቢጨንቀው። ቤቱ ውስጥ ያለውን በሙሉ ቢያደርግ የሚረካ አይመስልም። ዳሳሽም የሚለውን ሁሉ በደስታና በፍቅር ብታቀርብም እሷም ምንም አትጠግብም። ብቻ ደስታቸው ከጣራ በላይም ከሰማይም በላይ ሆኖባቸዋል። ባላሰቡበት ባልጠበቁበት ጊዜና ወቅት ስለመጣ ደስታቸው እጥፍ ሆኗል። ቀዳማዊ መልካሙን ረጅም ስዐት አብሯቸው እንደቆየ ሲረዳ "ስራ አስፈታውህ እኮ ወንድም መልካሙ"አለ "ኧረ ችግር የለም። ደግሞም ያን ያህል ስራ አይኖርም። እንዳየኸው ብዙ ታክሲ ስለሆነ ያለው ብዙም አይገኝም"አለ መልካሙ ፀጉሩን እያሻሸ "ቢሆንም ወንድሜ ከእኔ ጋር ነገ ነገወዲያም ቢሆን እንጫወታለን። እኔንም ደስ እንዲለኝ ወደ ስራህ ተመለስ። መኪናዋንም ማንቀሳቀስ ይኖርብሀል"አለና አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር አውጥቶ ሊሰጠው ሲል መልካሙ "በጭራሽ አልቀበልም"አለ። ቀዳማዊ "እኔም ልሰጥህ እኮ አልፈለኩም ነበር። ነገር ግን መኪናው የአንተ ስላልሆነ ነው። በዛ ላይ የመጣነው መንገድ ምቹ አይደለም። በዛ ላይ የመኪና ነዳጅ አለ ብቻ ብዙ ነገር እና እምቢ ካልከኝ ነው የምቀየምህ ባይሆን ስመለስ በነፃ ትወስደኛለህ"ብሎ ካግባባው በኋላ ብሩን ኪሱ ላይ አስገብቶለት ሰላምታውን ሰጥቶት ሸኘው። "መልክዬ ማታ ላይ ብቅ እንድትል ስንጫወት አምሽተህ ትሄዳለህ። እነ አባባንም ንገራቸው ለነ ወንድም ቢሆነኝና ለነ ማስሬ እንዲሁም ሞላንም ነግረሀቸው ሰብሰብ ብላችሁ ኑ እንግዳችንን በደንብ እንድናጫውተው"አለ ሙሉቀን። መልካሙ በጥሞና ሲያዳምጠው ከቆየ በኋላ በእሽታ አንገቱን አወዛውዞለት መንገዱን ቀጠለ። ሙሉቀን ዳሳሽን ወደ ውጪ አስወጥቶ "ዘይት ምናምን በደንብ አለሽ?"..
                  🖎​✐✎ ይቀጥላል...​ ✎​✐✍︎
            ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ like...
@quoteopia
@quoteopia
❤ 3
Пост от 25.10.2026 20:24
5
0
0
𝓦                   ❀༉‧₊˚. ኤሴቅ .˚₊‧༉❀
                         𖤣𖥧 #ክፍል_226 𖥧𖤣

..... መልካሙ የቀዳማዊን ዕቃ ተቀብሎ የእሱንም አስገብቶ ካስቀመጠ በኋላ አህያዋ ላይ የተጫነውን ዕቃም አውርዶ ውስጥ አስገባው። "እስኪ ራስህን ችለህ ቁጭ በል"አለችና አጠገቧ የነበረውን ህፃን ገፋ አደረገችው። ቀዳማዊንና መልካሙን አይቶ አፈረና እየሮጠ ወደ ደጅ ወጣ። "መንደር እንዳትሄድ ዳግሜ ዋ ኋላ ነግሬሀለሁ" አለችና ወደ እንግዶቹ ዞረች። ምድጃው አጠገብ ከእንጨት ፍልጥ ከተሰራች ኩርሲ ተቀምጣ "መልካሙ ይሄን እንግዳ አትነግረኝም? አታስተዋውቀኝም?" "እንዴ እኔ እኮ ግቡ ስትይ ያወቅሽው መስሎኝ ነበር"አለ መልካሙ እንደመሳቅ እያለ " ኧረ በፍፁም ባየው ባየው በጭራሽ ሊመጣልኝ አልቻለም" ብላ ከእንደገና ቀዳማዊን ተመለከተችው። ቀዳማዊ ግን አይኖቹ ደጁ ላይ ቁጭ ብሎ ከሚጫወተው ሕፃን ዳግማዊ ሙሉቀን ላይ ነበር። " ለማንኛውም ቀዳማዊ ታረቀኝ ይባላል"አለ መልካሙ። " እ ማ ማ ማን አልከኝ" አለች አፏን ከፍታ አይኖቿ እየተበለጠጡ" አዎ ቀዳማዊ ነው። "አለ መልካሙ ራሱን እየነቀነቀ። ቀዳማዊና ዳሳሽ ተሳሳሙ። ጉንጩን እያገላበጠች ለረጅም ደቂቃ ሳመችው። እሱም ጉንጯን በመሳም አፀፋውን መለሰ። "እግዚኦ እግዚኦ አይ ሰማዕቱ ለአንተ ምን ይሳንሀል"አለች የግድግዳው ደመደም ላይ የተቀመጠውን ትንሽዬ የጊዮርጊስን ምስል እየተመለከተች " መቼም ያልሞተ ሰው ይገናኛል "አለችና እጇን አገጩ ላይ አስደግፋ ትመለከተው ጀመር። " በጣም እንጅ እኔ ራሱ እኮ ቀዳማዊ ነኝ ሲለኝ ደንግጬ ተጋጭቼ ነበር።" "እንጀው ከየት ተገናኛችሁ?" ዳሳሽ መልካሙን ጠየቀች "ከአውሮፕላን ማረፊያ ነው። በአየር ስለነበር የመጣው" "ጉድ ነው እኮ አይ አምላክ እንደው ለእሱ ምን ይሳነዋል"አለችና ተነስታ ጉድ ጉድ ማለት ጀመረች። "እኔምልሽ ዳሳሽ ልጅ ይኖራል እንዴ አህያዋን ገበያ ለአቶ አያሌው የሚያደርስልኝ?" አለ መልካሙ " ቆይ እስቲ አንዱን እረኛ ልጥራው "አለችና ወጥታ ተራራው ላይ ሆና አንዱን እረኛ ጠርታው መጣች። አህያዋን ለሚወስደው እረኛ ቀዳማዊ መቶ ብር አውጥቶ ሊሰጠው ሲል "ለልጅ እኮ ይሄን ያህል ብር አይሰጥም ቀዳማዊ" አለና እጁን ወደ ኪሱ እንዲመልስ አይኖቹን ጣል አድርጎ ከነገረው በኋላ አስር ብር አውጥቶ "በል በዚች ሻይ ጠጣ እዛ ደግሞ አንዱን ሸንኮራ አገዳ እየበላህ ሂድ"አለው መልካሙ። "እሺ ግን ለአባባ የተወሰነ ብር መስጠት እፈልጋለሁ። ይቺን ብር ለእሳቸው ስጥልኝ "አለና ስድስት መቶ ብር አውጥቶ ለእረኛው ሰጠው። እረኛው በደስታ ብሩን ከተቀበለ በኋላ አገዳውን ይዞ አህያዋን እየነዳ ወጣ። ከቀዳማዊ አይኖች ስር ርህራሄና ሀዘን ይነበባል። ለተወሰነ ደቂቃ ወደ መልካሙና ዳሳሽ ፊቱን አዙሮ ቆይቶ ከእንደገና እይታውን ወደ ዳግማዊ ሙሉቀን ያደርጋል። "ሙሉቀን የት ሄዶ ነው?" አለ መልካሙ። የሙሉቀን ስም ሲነሳ የቀዳማዊ ጆሮ እንደ አንቴና ቆመ "አሁን ከመምጣታችሁ ትንሽ ቀደም ብሎ ነው ወደ ተከዜ የሄደው " "እና ውሎ ነዋ የሚመጣው አይይ"አለ መልካሙ "አዎ። ያው ታውቀውየለ መቼም ውሃ ሲወድ ልክ እንደ ዓሳ ነው። ግን የአስማረን እረኛ እንዲጠራው እሱን እልከዋለሁ"አለችና ብረት ድስቷን ይዛ ወደ ሌላኛው ቤት ሄደች። ቀዳማዊ የቤቱን ግድግዳና የቤቱን ጣራ ይመለከት ጀመር። "መቼም የገጠርን ኑሮ ታውቀዋለህ"አለ መልካሙ "በደንብ እንጅ ያደኩበት አይደል!"አለ "አደኩበት እንኳ ማለት አትችልም። ገና ልጅ እያለህ አይደል የወጣኸው!" አለ።
○●○●
"አባ አያሌው ያ መልካሙ የማንን ሰው ይዞ ነው"አለ አንድ ጎረቤቱ " የደጃዝማች ታረቀኝን ልጅ ነዋ" አለ " ኧረ ባክህ የአባ ታረቀኝ ልጅ እኮ ቀዳማዊ?"አለ በድጋሚ ባለማመን "አዎ ያ መከረኛ ልጅ ይሄው በስንት ዘበኑ መጣ። መቼም ትውልድ ቦታ ሁሌም ከነ መጥፎ እንከኑ አይረሳም እሱም የደም ሀረጉን ተከትሎ መጣ።"አሉ አባ አያሌው የሸበተ ፂማቸውን እየነካኩ " ኧረ በለው ወይዘሮ አትጠገብ ምን ትል?"አለ እጁን አፉ ላይ ጭኖ። "አይ እሷ ምን ትላለች? "አሉና አባ አያሌው ነገሩን ጎተት አደረጉት። "ማለቴ እንዴት እናቴ ሞታለይ ብሏት ቤቷ ታስገባዋለች ብይ ነው" " እሱ እሷ ቤት ለመሄዱ ምን ማስተማመኛ ኖሮህ ነው እንዴት ታስገባዋለች ማለትህ የአያ ጥጋቡ ብኸር አሉና አባ አያሌው በፌዝ አነጋገር አንድ ወቅት ጠላ ቤት ውስጥ ሙሉቀን ለአዝማሪው የሰጠውን ግጥም አስታወሱ ጨመር ጨመር አርጊው ጠጁን
ጠጣ ጠጣ የባልንጀር ናፍቆት
በህልም እንዲመጣ
ሊቀ መኳስ ገብሬ እስኪ በል አጫውተኝ
የወንድሜ ናፍቆት ምን አልባት ቢለቀኝ" ብሎ የሰጠው ግጥም። አባ አያሌውም ከተል አደረገና "አንዳንድ ጊዜማ ከወገን ይልቅ ጥሩ ባልንጀር ዝምድናው ሳያይል አይቀርም" በማለት ጎንበስ አለና የእህሉን አይነት መዳፉ ላይ በማድረግ ያገላብጥ ያዘ። "አባ አያሌው አባ አያሌው" "አቤት ልጄ" አሉ አባ አያሌው ወደ ሚያለከልከው ልጅ እየዞረ። "አብዬ አህያዋን ይዤለዎት መጥቻለሁ። እ ደግም መልካሙ እንዳለዎት እግዚሀር ይስጥልኝ። በጣም እናመሰግናለን። "ብለው ይችን ብር ደግሞ እንግዳው ልጅ ለእርሰዎ እንድሰጠዎት ሰጥቶኛል" አለና የተጠቀቀለውን ብር ከኪሱ አውጥቶ ሰጠው። አባ አያሌው ብሩን ተቀብሎ "አይይ ደግ መቼም ደግ ነው የሚወልደው። ይሄው ሳልሞት አሳየኝ። በኸፍት እድግ በልልኝ ጌታዬ ዘርህ አንደ ምድር አሸዋ ይብዛ! የተከልከው ሁሉ ይለምልም፣ ያረብከው ሁሉ ይሳካ፣ ችግርህና ምቀኛህ እንደ ወራጅ ውሃ እብስ ብሎ ይሂድ። ክፉ አይንካህ ልጄ"ብሎሀል በልልኝ"ብሎ እረኛውን ሸኝቶ ምርቃቱን ቀጠለ።

ሙሉቀን ወንዙ ዳር ከዋና ወጥቶ እያቅራራ ከገደል ማሚቶው ጋር ይነጋገራል። የሚያወጣውን ቃል መልሶ እየሰማ አሸዋውን በእጁ እያፈሰ ከእንደገና ያዘራዋል። ትንሽ አሸዋው ላይ እንደ ልጅነቱ ከተንከባለለ በኋላ ባህሩ ውስጥ ለመዋኘት ተወረወረ። እስኪበቃው ዋኝቶ ልብሱን ለባብሶ ትከሻው ላይ መጥረቢያውን አስቀምጦ ወደ ጫካው ሊገባ ሲል "ጋሻዬ ሙሉቀን!" ብሎ አንድ እረኛ ተጣራ። በመጀመሪያው ጥሪ እሱን ስላልመሰለው ቸል ብሎት ቢያልፍም ልጅየው ግን በተደጋጋሚ ይጠራው ጀመር በመጨረሻ "ምን ሆነህ ነው እዚህ ነኝ!"አለ ድምፁን ከፍ አድርጎ "ሙሽሪት ዳሳሽ እንዳለችህ እንግዳ መጥቷል ፈጠን ብለህ ና ብላሀለች"አለ የጉሮሮው ላንቃ እስኪዘጋ በደንብ እንዲሰማው። ሙሉቀን መልስ አልመለሰለትም። "ማን መጥቶ ነው? መቼም ለየት ያለ እንግዳ መሆን አለበት እንደዚህ በአስቸኳይ ያስጠራችኝ...."አለና ወደ ቤት መንገድ ጀመረ። ቀዳማዊና መልካሙ ከዳሳሽ ጋር ለረጅም ደቂቃ እየተጫወቱ ባለበት ዳሳሽ የእጅ ውሃ ይዛ ቀረበች። መልካሙ "ኧረ አንቺ ተጎንብሰሽማ አንታጠብም። ቀዳማዊን እኔ አስታጥበዋለሁ"አለና ጆጉን ሊቀበላት እጁን ሲሰድ ዳሳሽ "ይሄማ በጭራሽ አይሆንም "ብላ አሻፈረኝ አለች። ቀዳማዊ የሁለቱን መገላገል ትንሽ ካዬ በኋላ "በቃ ሁላችንም ራሳችንን እናስታጥብ"የሚል ምክረሀሳብ አቀረበ። ሁለታቸውም ወደ ቀዳማዊ በመዞር "ይሄማ አይሆንም"አሉ። "እሺ እንደዛ ካልሆነ ቤቢ ያስታጥበኝ"አለና ወደ ዳግማዊ ተመለከተ። ዳሳሽ ሳቅ አለችና "ዳግማዊ ያስታጥባል ብለህ ነው?"ብላ ሳቅ አለችና "ዳጊዬ ና አጎትህን አስታጥበው"አለች..
                  🖎​✐✎ ይቀጥላል...​ ✎​✐✍︎
            ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ like...
@quoteopia
@quoteopia
❤ 1
Пост от 25.10.2026 20:08
18
0
0
𝓦                   ❀༉‧₊˚. ኤሴቅ .˚₊‧༉❀
                         𖤣𖥧 #ክፍል_225 𖥧𖤣

..... ከተለያየን በኋላ ራሱ አሁንም አሁንም ነው የሚደውለው። በዛ ላይ ጥርሴን ግጥም አያደርገውም እንዳሳቀኝ እንዳዝናናኝ ነው" "በጣም ጥሩ ላይ ናችኋ። ደስ ይላል። በደንብ ጠበቅ አድርገሽ ወደ ትዳር ቀይሪው!"አለች ደሐብ ከንፈሯን ነከስ እያደረገች። "ኧረ ደሐብ ምን ሆነሽ ነው አሁን ይበልጥ ማወቅ ፈለኩኝ።" "ምንድነው ማወቅ የፈለግሽው?"....
○●○●
"ሰላም እንዴት አረፈዱ አባ አያሌው " ደህና እንዴት አረፈድክ ልጅ መልካሙ"አሉ በበስልሳዎቹ መጨረሻ ዕድሜ ላይ የሚገኙት አቶ አያሌው። "እንደው አንድ ነገር ላስቸግረዎት ነበር አመጣጤ። የማውቀው ሰው ያገኘሁት እርሰዎን ነው" "ምንድነው የምታስቸግረኝ መቼም የዛሬ ልጆች እኮ የምታስቸግሩትንና የማታስቸግሩትን ለይታችሁ አታውቁም በል እስኪ ልስማህ"አሉ አቶ አያሌው በፂም የተሸፈነ ከንፈራቸውን ገልጠው ጥርሶቻቸው እያሰጡ " አህያዎን ያበድሩኛል? እንደው የሆነ እንግዳ አምጥቼ እቃውን በምን ይዤው ልሂድ" አለ መልካሙ (አቤል) "አይ መልካሙ እውነትም ላስቸግርህ ያልከው እውነትህን ነው ልጄ እህል ሸምቼ እኮ ይዤባት ልሄድ ነው" አሉና "ግን የማንን እንግዳ ይዘህ ነው?" አሉ አቶ አያሌው "አልናገርም። አህያዎን የሚፈቅዱልኝ ከሆነ ነው የምነግረዎት"አለ መልካሙ " ኧረ ኧረ አንተ ሞላጫ ልጅ ብለህ ብለህ በወሬ አህያየን ልቀይር ነው? በል ሂድ ነገ ለምሰማው ወሬ ምን አህያየን አስገበረኝ"አሉ አቶ አያሌው። መልካሙም አቶ አያሌውን ባሉበት ትቶ ሌላ ሰው ፍለጋ መዟዟር ጀመረ። አንዳንድ ሰዎችን ቢያገኝም ነገር ግን አህያ ባለመያዛቸው ከእንደገና ወደ አቶ አያሌው ጋር ሄደ። "ዙረህ ዙረህ መጣህ?"አሉና " ለመሆኑ የማን እንግዳ ህኖብህ ነው እንደዚህ መኪናህን መወወር ትተህ አህያ የምትፈልግ?"አሉ ከዘራቸውን በክንዳቸው ተመርኩዘው " ቀዳማዊን ያውቁታል አባ አያሌው?" ቀዳማዊ ቀዳማዊ?" " የአባ ታረቀኝን ልጅ" " ኧረ እዝጎ ኧረ አፈር በሆንኩ የደጃዝማች ታረቀኝ ልጅ ብቸኛ ወንድ ልጁ?"አሉ አቶ አያሌው በድንጋጤ ከዛራቸውን ጥለው ራሳቸውን እየጨበጡ "አዎ አባ አያሌው ከአማሪካ መጥቶ ነው"አለ መልካሙ ከአሜሪካ ማለት እየቻለ በገጠርኛ አቀላለፅ " ኧረ እዝጎ በህይወት ኖሮ መጣ?" አሉ አቶ አያሌው "አዎ አባባ በህይወትማ እንዳለ ከዘጠኝ አመት በፊት በቴሌቭዥን ቀርቦ ሰምተነው ነበር"አለና መልካሙ አቶ አያሌው ወሬ እንዳይቀጥል "እና አሁን መኪና ውስጥ አስቀምጨው ነው የመጣሁት። አህያዎትን ቢሰጡኝ ቶሎ በሸኘሁት መንገድ ስለመታው ደክሞታል"አለ መልካሙ "ኧረ ውሰዳት ልጄ "አሉና ከሞጨሞጩ አይኖቻቸው እንባ እንደ ጠበል ቀስ ብለው ይንከባለሉ ጀመር። መልካሙ (አቤል) አህያይቱን ከታሰረችበት ዛፍ ፈትቶ ይዞ ሄደ። ሁሉንም እቃዎች በደንብ ከጫነ በኋላ። ታብሌቱንና ላፕቶፑን እንዲሁም ተሰባሪ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎቹን በሻንጣ አድርጎ በጀርባው አዝሎ መንገድ ጀመሩ። መልካሙ "ልጄ " የሚል ድምፅ ሲሰማ ወደ ኋላ ዞሮ ሲመለከት አቶ አያሌው ነበረ። " አባ አያሌው " "አቤት ልሳመው ብዬ አይደል"አለ " ቀዳማዊ የሚገናኝህ ሰው አለ" አቶ አያሌው ቀዳማዊን እያዟዟረ ከሳመው በኋላ " አይ ሲመሽ ወደ ዱሩ የተባለልህ ልጅ"አሉና ከእንደገና ሳሙት "አሁን አባትህ ቢኖር ምንኛ ይኮራ ነበር። ኩሩ የኩሩ ልጅ መቼም ደግ መሆን ጥሩ ነው ይሄው ለዚህ በቃህ"አሉና "በል ሂድ ልጄ የሽማግሌ ወሬ እንደሁ አያልቅም እዛው ቤት መጥቼ አነጋግርሀለሁ"አሉ " አብረውን አይሄዱም? አባ አያሌው"አለ መልካሙ " ቅድም ነግሬህ የል ልጄ ለምን ታደናቁረኛለህ። እህል ልሸምት ነው አላልኩህም"አሉና "ጭነቷን አራግፈህ በሰው ላክልኝ" "እሺ አባባ እልክለዎታለሁ" ብሎት መንገዳቸውን ቀጠሉ። "የኛ አካባቢ ሰው ለአባትህ ያላቸውን ፍቅርና አክብሮት ያወኩት እያደኩ ስመጣ ነው። በየማህበሩ በየ ፅዋው በየ ሰንበቴው። እንዲሁም ሰው በተጣላ ቁጥር ሁሌ እንዳስታወሷቸው ነው። በስህተት እንኳ ስለ አባትህ መጥፎ ነገር የሚያነሳ ሰው አጋጥሞኝ አያውቅም"አለ መልካሙ። ቀዳማዊ ሄድ ሴቱን አንገቱ ላይ አድርጎ ካዳመጠው በኋላ "ልክ ነህ አባቴ በጣም ጥሩ ሰው ነበር። ወደ ትምህርት ቤት እንድገባ የተናዘዘውም እሱ ነበር። ነፍሱን ይማረውና አሁን ላይ ቢያየኝ ደስ ይለኝ ነበር። ግን ምን ታደርገዋለህ አንዳንድ ጊዜ በሕይወት ትቀደማለህ። አስተዳደጌንም አኗኗሬንም ሳያይ ዝም ብሎ ባዶ በረሃ ላይ ብቻየን ትቶኝ ሄደ"አለና አይኖቹ ላይ የሞሉትን እንባዎች ጨምቆ አፈሰሳቸው። " አይዞህ ፈጣሪ እኮ በአንዱ ሲነሳ በአንዱ ደግሞ ይለግሳል"ብሎ ሊያፅናናው ሞከረ። "አይ አቤል በእርግጥ ከዚህ ከወጣሁ ጀምሮ ለተወሰነ ብቸገርም ብሰቃይም የአዲስአበባ ቤተሰቦቼን ካገኘሁ በኋላ ጉድለቴን ሞለተውልኝ ሙሉ ሰው ሆኜ በደስታ ኖሪያለሁ። ግን አንድ የማይቀየር የተፈጥሮ እውነት አለ አቤል። ቤተሰብ ሁሌም ጉድለትህ ነው። ሁልጊዜም እውነተኛ ቤተሰብ እንደሌለህ ስታስብ ትንሽ ይከፋሀል። ይህን የምልህ ባልተመቻቸ ኑሮ ውስጥ ሆነህ ብቻም ሳይሆን የምትኖረው ሕይወት ምንም እንኳ በድሎት ቢሆንም ነው። እና ለእኔ ደግሞ ያጎደለኝ የአባቴ በሕይወት አለመኖር ነው። እና አሁን ላይ የደረስኩበትን የሕይወት ከፍታ ቢያይና ጉልበቱን ስሜ ምርቃት ባገኝ ምንኛ ደስ በተሰኘሁ ነበር" " ልክ ነህ የአባት ምርቃት በጣም ጥሩ ነበር። ግን እላይ ሆኖ የመረቀኽ ይመስለኛል አይዞህ በል አሁን የባልንጀራህ ቤት ደርሰሀል"አለ መልካሙ " በእውነት!?" መልካሙ በአዎንታ ራሱን ነቀነቀና "ቤቶች እንደምን አረፈዳችሁ ዋላችሁ?" አለ መልካሙ (አቤል)። ቀዳማዊ የልብ ምቱ ጨመረ። ማንም የሰማው ስላልነበር ከእንደገና ድምፁን ጨመር አድርጎ "ቤቶች"ብሎ ተጣራ። የሳር ጎጆዋ በኩበት ጭስ እየተጓፈጠች መሆኑን ሲመለከት መልካሙ "ጓዳ ውስጥ ሆና ነው ያልተሰማት አለና ወደ ደጃፉ ቀረብ በማለት ድምፁንም ጥላውንም አሳያትና "ኧረ እናንተ ቤተኞች"አለ መልካሙ ለሶስተኛ ጊዜ። "አቤት አቤት"አለች በጥላሸት የወዛ ፊቷንና እና በጭስ የታፈነ አይኗን እያጨናበሰች እንዲሁም እጇ ላይ ያለውን ሊጥ ሳፋው ላይ እየታጠበች። "በመጥራት ደከምን እኮ"አለ መልካሙ " ምን ስራ ይዤ በዛ ላይ ልጁ ፋታ አይሰጥ ምን ላርግ ብለህ ነው " ብላ ከውስጥ ስትወጣ ከመልካሙ ኋላ እንግዳ የሆነ ሰው ተመለከተች። "እንዴት ነህ መልካሙ " " ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን አንቺ እንዴት ነሽ ዳሳሽ?" " ደህና ነን ክብሩ ይስፋ " ብላው ትኩረቷን ከቀዳማዊ መንቀል ተሳናት። "ግራ የተጋባሽ ትመስያለሽ" አለ መልካሙ አይኖቿን ተከትሎ ቀዳማዊ ላይ እያረፈ። " እንግዳ አንተዬ አላውቀው ብዬ አይደለ"አለች ዳሳሽ ግራ መጋባቷን ሳትደብቅ "እንግዳ ነው" " እሺ እንግዳ መሆኑንማ እያየሁኝ ነው። ለማንኛውም ግቡና አረፍ በሉ። እየተነጋገርን እንጠያየቃለን። አለችና ወደ ቤት ገብታ መደቡን በአጎዛ አልብሳ "ግቡ ግቡና አረፍ በሉ"አለች። መልካሙ የቀዳማዊን ዕቃ ተቀብሎ የእሱንም አስገብቶ ካስቀመጠ በኋላ አህያዋ ላይ የተጫነውን ዕቃም አውርዶ ውስጥ አስገባው።........
                  🖎​✐✎ ይቀጥላል...​ ✎​✐✍︎
            ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ like...
@quoteopia
@quoteopia
❤ 5
Пост от 24.10.2026 20:49
28
0
1
𝓦                   ❀༉‧₊˚. ኤሴቅ .˚₊‧༉❀
                         𖤣𖥧 #ክፍል_224 𖥧𖤣

..... እስኪ ስለ አንተ ንገረኝ ምን ላይ ነው ያለኸው የት ነው ስራ ቦታህስ?" "እኔ ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት ከዘጠኝ አመት በኋላ ነው። የዩኒቨርስቲ ትምህርቴን በአሜሪካን ሀገር ነው ያጠናቀኩት። እንደጨረስኩ እዛው ኢንተርናሽናል ካምፓኒ በዋና መሀንዲስነት እየሰራሁ እገኛለሁ። ወደ አምስት አመት ሆኖኛል ስራ ከጀመርኩ!" " የዛው ሀገር ሰው ሆኛለሁ በለኛ! አይ የእጣፈንታ ነገር ይገርማል። ሕይወት መነሻዋም መዳረሻዋም አይታወቅም። ከዚች የገጠር ቀበሌ ተወልደህ ለዚህ ክብር መብቃትህ የሚገርም ነው። ለአንተ ስኬት በጣም ደስ ብሎኛል። ያኔ በቴሌቪዥን ስንከታተልህ እንዴት እንደኮራን አትጠይቀኝ። ከመላው ሀገራችን አንደኛ ስትወጣ ብታይ የኛ አካባቢ ሰው በደስታ ልቡ ቀልጦ ነበር። ከማናችንም በላይ ሙሉቀን ከመደሰቱ ብዛት የሚናገረው ቃል ሁሉ ጠፍቶበት አፉ ተያያዘ። ይዞራል ሰውን ያያል ከእንደገና ወደ አንተ ይመለከታል። ብቻ ሁሉም ነገር በህልም ነበር የሚመስለው።"ቀዳማዊ ዝም ብሎ እያዳመጠው በመሀል "እኔ ምልህ ስምህ ማን ነበረ? " ያው አሁን አቤል ነው የምባለው ስሜን አስቀይሬ ግን መልካሙ ነበር የምባለው" "እሺ አቤል እና ከይቅርታ ጋር ሙሉቀን ጋር ይዘኸኝ አትሄድም?" " ኧረ ይሄ ምንም ጥያቄ የለውም ወንድሜ በስንት ዘመንህ መጥተህ ወትሮስ ትቸህ አልመለስ። መኪናይቱን ራስ አምባ አስገብተን እንሄዳለን። በደንብ ደስ እያለኝ ደግሞም እኮ አባቴ ሁሌም ይላል "አባ ታረቀኝ እንዴት ያለ መልካም ሰው ነበር። አስታራቂያችን መካሪያችን ነበረ"ይላል። በአንተ አወጣጥም በጣም ነበር ያዘንነው ድምፅህን እስክንሰማው ድረስ በሕይወት ያለኽም አልመሰለን ነበረ"አለና ወሬውን አቆሞ መኪናውን ነዳጅ በመስጠት አቀበቱን በአንደኛ ማርሽ ወጣ። ቀዳማዊ ወደ ራስ አምባ እየቀረበ በሄደ ቁጥር ልቡ እየፈራ ሄደ። ፊቱ ላይ ቅፅበታዊ ጭንቀት ይታያል። ልጅነቱ ያያቸው ኮረብታዎችን ተመለከታቸው። አንዳች ስሜት ውስጡን አናውጦ ረበሸው። "ደርሰናል ጥሩ ቀን ነው የመጣኸው። ዛሬ የራስ አምባ ቀበሌ ገበያ ስለሆነ እቃህን የሚጭንልን ባለ አህያ አባወራ አይጠፋም"አለ አቤል (መልካሙ)" ኧረ ደረስን እንዴ"ብሎ ጠይቆ ሳይጨርስ.. መልካሙ መኪናውን አቁሞ "በል ውረድ ደርሰናል። እንኳን ለሀገርህ አበቃህ በሰላምም መጣህ!"
○●○●
ለረጅም ስዐት እያሰበች እያወላወለች ከቆየች በኋላ ስልኳን አንስታ ደወለች። "አቤት"አለች ሔዋን ስልኩ አዲስ ሆኖባት " እትዬ ሰላም ነው? ሐምራዊ ነኝ!" "አንቺ ነሽ እንዴ? ስልኩ አዲስ ሲሆንብኝ ጊዜ"አለች ሔዋን ቀዝቀዝ ባለ አነጋገር ና ቅሬታ በተሞላበት መንፈስ። ሐምራዊ የሔዋን አነጋገር ምቾት ባይሰጣትም የደወለችበትን ጉዳይ አዘግይታ እሷን ለማውራት ብትፈልግም ሔዋን ግን በአጭር በአጭር እየመለሰች ለሌላ የወሬ ርዕስም ሆነ መንገድ አልከፍትላት አለች። "ይልቅ ለምን ጉዳይ ነበር የደወልሺው? የሆነች ስራ አለችብኝ"አለች ሔዋን ሐምራዊን ላለማውራት የሌላትን ስራ እንደምክንያት እየተጠቀመች። "እትዬ ቀዳማዊን ፈልጌው ነበር። ላገኘው እችላለሁ?" " አሁን ከእኔ ጋር የለም። ወደ የት እንደሄደ አላውቅም" "እሱን ላገኝበት የምችልበት ስልክ ልትሰጪኝ ትችያለሽ?" "አላውቅም እያልኩሽ! እስካሁን አዲስ ስልክ ቁጥር አላወጣም እስከማውቀው ድረስ"አለች ሔዋን እየተቆጣች። " እሺ ስለረበሽኩሽ በጣም ይቅርታ መልካም ቀን"አለች ሐምራዊ ሐዘን ፊቷ ላይ እያጠላ "ሙልጭ አድርጎ መስደብ ነበር። ደግሞ ቀዳማዊ ማለት ጀመረች" አለች ሔዋን " አይ እማዬ ታስቂኛለሽ ያን ጊዜ ከማንም አስበልጠሽ ነበር የምትወጃት ከዛ ደግሞ ቀዳማዊን አስቀየመችው ብለሽ እንደዚህ አክ እንትፍ ማለት ምንድነው? ስትወጂም ስትጠይም ስፍር የለሽም" አለች ሔመን " እኔማ በእናቷ ትህትና እሷን መዝኛት እንደ እናቷ ደግና ጥሩ ሰው መስላኝ ነበር። ግን ግምቴም ሆነ አረዳዴ ልክ አልነበረም።"
○●○●
" መጣሁ ቀዳማዊ እዚሁ መኪና ውስጥ ተቀምጠህ ጠብቀኝ። እኔ በገበያው ዘወር ዘወር ብዬ አህያ የያዘ የማውቀው ሰው ፈልጌ ይዤ ልምጣ" " እሺ ጥሩ በቃ እኔ እዚሁ እጠብቅሀለሁ!"አለና በፈገግታ ተመለከተው። ቀዳማዊ ውስጥ መቀመጥ ስላልፈለገ የመኪናውን በር በጀርባው ተደግፎ እጁን በደረቱ አጣምሮ ከገበያ የሚወጣውን ገቢያተኛና ወደ ገቢያ የሚገባውን ሰው ይመለከታል። "ከየት የመጣ ነው ይሄ ደግሞ የከተሜ ቀለጤ" አለ አንደኛው ገበሬ ትከሻው ላይ የሆነች ሸክም ነገር ይዞ አንገቱ እስኪበጠስ ዞሮ ቀዳማዊን እየተመለከተ። "አይ አያ ገብሬ የመንግስት ባለሟል ጉዳይ አስፈጣሚ ይሆናልይ"አለ አብሮት ያለው ነቃ ያለ ወጣት ገበሬ። "ደግሞ መኪናይቱ መልካሙ የሚዘውራት ናት!" አለና ለመጨረሻ ጊዜ ቀዳማዊን ዞሮ ተመለከተው። አላፊ አግዳሚው በትኩረት እየተመለከቱት ያልፋሉ። ካለፉ በኋላም የማን ሰው ነው? እየተባባሉ ይጠያየቃሉ። ቀዳማዊ የሁሉም ሰው ትኩረት ሲበዛበት መኪናው ውስጥ ገብቶ ተቀመጠ።
○●○●
ታካሚዎቿን በየተራ ካስተናገደች በኋላ ለትንሽ ጊዜ ፋታ አገኘች። ለብዙ ደቂቃ በሀሳብ ሰጥማ የታሮስን ንግግር እንደ ዳዊት ደጋግማ እያስታወሰች ሳለ ስልኳ ጠራ ከእንቅልፏ የመባነን ያህል በመንቃት "አቤት ቤርሲ" "ደህና ነሽ? በጣም ጠፋሽብኝ እኮ የኔ ቆንጆ" አለች ቤርሳቤህ " ኧረ አለሁ አንቺ ነሽ እንጅ ፍቅረኛሽ ጋር አለምሽን እየቀጨሽ እኔን የረሳሽኝ"በማለት ቅሬታዋን አቀረበች። "ኪሩ ጋርማ ምን ልበልሽ በቃ ሁለታችንም ነፍሳችንን አናውቅም። ብቻ ሁለታችንም በፍቅር ክንፍ ብለንልሻል" "እንኳን ደስተኛ ሆንሽ ጓደኛዬ ደስታ ይገባሻል" አለች ደሐብ ቅሬታ ባዘለ አነጋገር። "ግን ይበልጥ ደስታዬ እጥፍ የሚሆነው አንቺ ከቀዳማዊ ጋር ስትሆኝልኝ ነው" "እንጃ አላውቅም ቤርሲ በጣም ግራ ተጋብቻለሁ። እስካሁን እኮ ቀዳማዊን አላገኘሁትም" "ለምን ምን ሆነሽ?" ደሐብ መልስ አልመለሰችላትም "እኔ የማላውቀው ነገር አለ?" ደሐብ ምንም አልመለሰችላትም። "አታስጨንቂኝ እንጅ ደሐብሻ። ምን ሆንሽ?"ቤርሳቤህ በሚያሳዝን ቅላፄ ጠየቀቻት። "በስልክ የሚሆን ነገር አይደለም በአካል ተገናኝተን በደንብ እነግርሻለሁ።"አለች ደሐብ ቅርዝዝ ባለ አነጋገር። ቤርሳቤህ ይበለጥ ተረበሸች።"ደሐ እባክሽ ምን እንደሆንሽ በትንሹም ንገሪኝ "ቤርሳቤህ እንድትነግራት መለመን ጀመረች። ደሐብ ግን በአካል ካልሆነ በስልክ እንደማትነግራት በድጋሚ ነግራት ድርቅ አለች። ቤርሳቤህም ምንም እንኳ የማወቅ ፍላጎት ቢኖራትም ደሐብ እንደማትነግራት ስትረዳ ተስፋ ቆርጣ መጠየቋኖ አቆመች። "ይልቅ ስለ ፍቅራችሁ ጅማሬ ንገሪኝ የኔን እንደርስበታለን"አለች ደሐብ። "የኔማ በቃ እሱም ጋር ተመሳሳይ ፍቅር ስለነበር። ከእኔ ሲቀርብና ሲሆንለት በጣም ደስ ብሎታል። የሚገርምሽ ጓደኛውን ታሮስን ራሱ የረሳው ይመስለኛል። ከተለያየን በኋላ ራሱ አሁንም አሁንም ነው የሚደውለው። በዛ ላይ ጥርሴን ግጥም አያደርገውም እንዳሳቀኝ እንዳዝናናኝ ነው.......
                  🖎​✐✎ ይቀጥላል...​ ✎​✐✍︎
            ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ like...
@quoteopia
@quoteopia
❤ 2
Пост от 24.10.2026 19:31
8
0
0
𝓦                   ❀༉‧₊˚. ኤሴቅ .˚₊‧༉❀
                         𖤣𖥧 #ክፍል_223 𖥧𖤣

..... አሁን ላይ አይደለም ተፎካካሪ ተማሪ ልሆን ሴሚስተር ፓስ ራሱ ይከብደኝ ነበር።" " ልክ ነሽ ልጄ የሰው ልጅ መሰረቱን ካልረሳ መድረሻውም የተቃናና ጥሩ ይሆናል። እኔ አሁን ቀዳማዊን ዝም ብዬ ሳስብ እንጅ የሌላ ልጅ እንደሆነ የማውቀው አብሬው ስሆን የወለድኩት ልጄ ነው የሚመስለኝ። እሱም ስርአቱና ባህሪው ከአመት አመት አይለወጥም። አይተሽዋል አሜሪካ የኖረ አይመስልም። አክብሮቱና ትህትናው አጀብ ነው። እና በዛ ላይ ቅን እና የዋህ! አሁን ግን ወደ ክፍለ ሀገር ሲሄድ ትንሽ ፈርቻለሁ።"ለምን ፈራሽ እማዬ "አለች ሔመን ፊቷን ወደ እናቷ እያዞረች። "ሕመሙን እንዳያስታውሱትና ፀባዩን እንዳይቀይሩት እበቀላለሁ እንዳይል ነው የምፈራው ልጄ" አለች ሔዋን በሀሳብ አይኖቿን ከደን እያደረገች።" እና መበቀል ከፈለገ ይበቀላ እማዬ ይሄን ልጅ እኮ ያላደረጉት ነገር የለም።" "እንደዛ ካደረገ ከአምላኩ ጋር ነው የሚጣላው በደለኞችን የሚቀጣ ተበዳዮችን ደግሞ የሚጠብቅ እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ ለእግዚአብሔር መስጠት እንጅ ያለበት እሱ ምንም ማድረግ የለበትም። ለሰይጣን ድርጊት ሰይጣናዊ ምላሽ አያስፈልግም። አንቺነትሽን ይቀይረዋል። በቀል ውስጥሽ ላይ ሲያድር ባህሪሽ ይቀየራል። ደስታ ይርቅሻል። ብቻ ብዙ ብዙ ችግር አለው"አለች ሔዋን በረጅሙ እየተነፈሰች።" ማለት እንዲህ ነው ማለት ይከብዳል። ግን ሁሉም ነገር ያለው እሱ ጋር ነው። ልቡ ላይ እንደተቀመጠው የጥላቻ መጠን ነው የሚለካው። እኔ በቀላሉ ይተወዋል ብዬ አላስብም እማዬ። ምክንያቱም በልጅነቱ ነው የተቀረፀበት ምን አልባት እስካሁን ስላላወጣው ንዴቱን ብስጭቱን ብሶቱን ምንም አያደርግም ለማለት ይከብዳል። ምክንያቱም ማንም ሰው ስላለፈበት ስቃይም ሆነ ግፍ ሊያገባውም ሆነ ሊወስንለት አይችልም። እማዬ እኛ እኮ ሰሚዎች ነን። የነገረንን ነው የምናውቀው ያልነገረንን የሆነውን እንዴት ነው የምናውቀው? ስሜቱን የሚያውቀውና የሚሰማው እሱን ብቻ ነው ምን አልባት ለእኛ ያልነገረን እሱ ብቻ የሚያውቀው ለዘላለም በልቡ የያዘው ሀዘን ቢኖርስ? ስለዚህ እኔን ከጠየቅሽኝ የልቡ ሀዘን የሚወጣለትን ማንኛውንም ነገር ያድርግ ነው። ምክንያቱም ለዘላለም ሲሰቃይም ሲፀፀትም እንዳይኖር!"አለች ሔመን " ልጄ እሳትን በሳት እያልሽ ነው? እሺ እሱ ይበቀል እንበል ይህ ሁኔታ የት ላይ ያበቃል? ንገሪኝ በቀሉም ግፉም ይቀጥላል። እሱም ቀስ በቀስ ራሱን እያጣ ይሄዳል። የሚሆነውና መልካሙ ነገር እሱ ቢያቋርጠውና እንደ ልጅም እንደ ታናሽም ተሸንፎ ይቅር ለእግዚአብሔር ብሎ ቢተወው ነው። ካልሆነ እስከ ልጅ ልጅ ይዳረሳል!" "በርግጥ እማዬ ልክ ነሽ። ብቻ ፈጣሪ ጥሩውን ነገር ብቻ እንዲያደርግ የሰይጣን ሀሳቡን ከልቡ ከውስጡ እንዲያርቅለት አይለየው። " "አሜን የኔን ምስኪንና የዋህ ልጅ ሌላ ስቃይ እንዳያሳልፍ እሱ በቸርነቱ ይርዳው! ከዚህ በኋላ ደስታና የተመቻቸ ሕይወት እንጅ ሀዘን አይገባውም" አለች ሔዋን።
○●○●
" እንደው ጥያቄዬ አግባብ ካልሆነ ይቅርታ ግን አዲስ ሰው ስለሆንክ ልጠይቅህ ብዬ ነው! ወደ ቀበሌያችን ምን እግር ጣለህ?" አለ ሾፌሩ ከብዙ የዝምታ ጉዞ በኋላ " አይ መጠየቅማ አለብህ። ጥሩ ጥያቄ ነው ጥያቄህ። የማታውቁት ሰው ሲገባ መጠየቁ አግባብም ልክም ነው። ልክ የማይሆነው በይሉኝታ ዝም ብለህ ስታልፍ ነው። ለማንኛውም ጥያቄህን ልምልስልህ... የተወለድኩት እዚህ ነው እስከ አስራ ሶስት ምናምን አመቴም እዚህ ነው ያደኩት። እና ከዛ በኋላ መጥቼ ስለማላውቅ ናፍቆትም ትዝታም ነው ያመጣኝ! "አለ ቀዳማዊ። ሾፌሩ በመገረም "እዚህ እኛ ጋ ራስ አምባ?"አለ በመገረም "አዎ ራስ አምባ ነኝ ምነው ተገረምክ?" "አልጠበኩም ለዛ ነው። እና ማን ነው የምትባለው የማንስ ወገን ነህ?"አለ። ቀዳማዊ በሾፌሩ ጥያቄ እንደመሳቅ ብሎ "እንግዲህ ወገኔን አላውቀውም ግን ቀዳማዊ ታረቀኝ እባላለሁ!" "ምን ቀዳማዊ?" በድንጋጤ የመኪናውን ፍሬን ያዘው። ወደፊት ሄደወ ተመለሱ። ቀዳማዊ ቀበቶ ባያስር ኖሮ ከመስታውቱ ጋር ተላትሞ ነበር። " የአባ ታረቀኝ ልጅ የወይዘሮ አትጠገብ ልጅ? የነ ርብቃ ወንድም የነ ማለፊያ ወንድም"አለ እጁን አፉ ላይ ጭኖ "አዎ"አለ ቀዳማዊ "አይ ቀዳማዊ መከረኛ ልጅ ነበርህ። ሁላችንም ነበር የምናዝንልህ። እናትና አባቶቻችን ስለማይፈቅዱልንና ከአትጠገብ ጋር እንዳታጣሉን ብለው ስለሚያስፈራሩን ነው እንጅ እኮ እኛም እንደ ሙሉቀን ጓደኛ ልናረግህ እንፈልግ ነበር"አለና ከእንደገና አቅፎ ሰላም አለው። ትንሽ ቆይቶ መኪናውን አስነስቶ መንገድ እየጀመረ "ታስታውሳታለህ ዳሳሽን?" "ማነች እስኪ አስታውሰኝ" "ያውም የእሽውላሌ ጊዜ እሽው እያለይ ብዙ አስግረዋት አውርዱኝ ስትል ማነው ባልሽ አሏት። ከዚያ እሷ ቀዳማዊ ነው አለች። ያን ጊዜ እኛ እኮ ታዲያ እያባጨጭናት እሷንም አንተንም እያሳፈርናችሁ ነበር።" "አ አዎ አሁን ትዝ አለኝ። እንደውም ሙሉቀን ዝምበላቸው አትስማቸው ብሎ አባብሎኝ ነበር። " "ልክ ነህ በጣም ተናድጄ ነበር አስታውሳለሁ። " አዎ አልረሳውም የቀለም ተማሪም ስለነበርህ ቀዳማዊ ተምሮ መምር ስለሚሆን መምር ለማግባት ነው እያልን እናሾፍባት ነበር። አንተ ከኸደህ በኋላ ራሱ ብዙ ጊዜ የቀዳማዊ ሚስት እየተባለይ ትበጨጭ ነበር። አሁንማ የሙሉቀን ሚስት ሆና የአራት አመት ወንድ ልጅ ሁሉ አድርሰዋል" " ኧረ ባክህ እንዴት ነው ደስ የሚለው እና ጓደኛዬ አሁን የልጅ አባት ሆኗላ?"አለ በፍፁም ደስታ ፈገግ ብሎ "አዎ ሆኗል። ነገር ግን ሰርክ ከአፉ አትጠፋም ነበር። በተለይ ድምፅህን ከሰማው በኋላ እንባው እንደ ሴት ልይ ነበር ሲወርድ የነበረው። ስለ አንተ ሲያስብ ሆድ ይብሰዋል። ሲዳር ራሱ አንተ አጠገቡ ባለመኖርህ በጣም አዝኖ ነበር። ሁሌም የምትመጣና የሚያይህ እየመሰለው ለገበያ ወደሀመረ ኖህ በመጣን ቁጥር ቴሌቪዥን ቤት ይቀመጥ ነበር። ብቻ ባጭሩ ከእኛ ጋር እንኳ አያሳልፍም ዝም ብሎ በአንተ ጉዳይ እንደተብሰለሰለ ነበር ጊዜውን የሚያጠፋው። ስንት ጊዜ መሰለህ እህቶችህን ሁሉ እየተማታ ስሞታ የቀረበበት። እንደውም ብዙ ጊዜ ካሳ ሁሉ እያስከፈሉት ነበር። ሙሉቀንም ትንሽ ነበር የሚበቃው ሲናገሩት ንቆ መተው እየቻለ ስስ ሆነ አልችል እያለ በተለይ ማለፊያን ሰርክ እንደቀጠቀጣት ነበር። ብቻ የኛ አገር ኑሮ የገጠር ኑሮ ከድጥ ወደ ማጡ ነው። ትንሽ ከባድ ነበር። በአንተ ሁኔታ የተበሳጩ ሰዎችም እናትህን ለአመታት አያናግሯትም። የአንተ ሁኔታ እንደ እግር እሳት የሚያቃጥላት ደግሞ የሙሉቀን እናት ነበረች። ሲበዛ ጥሩ መከታ ነበረች። በስተመጨረሻ ሁሉም እህቶችህ ሲያገቡ ፀቡም ክሱም ስሞታውም ቀረ እንጅ ሁሌ ነበር የሚጣሉት። እና እናትህና እህቶችህ.... ቀዳማዊ ሳያስጨርሰው " ስለ እነሱ እንዳትነግረኝ! " ብሎ ኮስተር አለ። " ይቅርታ ወንድሜ በጣም ይቅርታ!" " ምንም አይደል ዝም ብለህ ስለ ሙሉቀን ንገረኝ ስለ እናቱና ስለ ሚስቱ በቃ ስለ እሱ ብቻ"አለ ቀዳማዊ "ያው የአስራ አምስት አስራ አራት አመት ታሪክ በአጭር ጊዜ አያልቅም ብነግርህስ። ከብዙ በጥቂቱ የነገርኩህ ነው። እስኪ ስለ አንተ ንገረኝ ምን ላይ ነው ያለኸው የት ነው ስራ ቦታህስ?..
                  🖎​✐✎ ይቀጥላል...​ ✎​✐✍︎
            ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ like...
@quoteopia
@quoteopia
❤ 2
Пост от 23.10.2026 20:30
29
0
0
𝓦                   ❀༉‧₊˚. ኤሴቅ .˚₊‧༉❀
                         𖤣𖥧 #ክፍል_222 𖥧𖤣

..... አንቺ የደስታዬ ምንጭ ሳትሆኝ ደስታዬ ነሽ።"አለና ታሮስ አይኖቿን በስስትና በድፍረት ቀና ብሎ ተመለከታቸው። ደሐብ ውስጧ በደስታ ሲሞላ ታወቃት። ለምን እንደሆነ ባታውቅም ነገር ግን አይኗን እያዬ ስለ እሷ የሚሰናውን ስለነገራት ኩራትም ሀሴትም ተሰማት።" ይሄን ያህል ነው የምትወደኝ?"አለች ደሐብ። ይሄን ያህል ስላፈቀራት ደስታ እየተሰማት። ታሮስ መልስ እስክትመልስለት ይጠበቅ ጀመር። አይኖቿንና ከንፈሮቿን ያለመታከት ቢጠብቅም ደሐብ ከፈገግታ ውጪ ምንም ልትሰጠው አልቻለችም።
○●○●
ቤርሳቤህ ከእንቅልፏ ስትነቃ ኪሩቤል ከአጠገቧ ጀርባው ተገልጦ እንቅልፍ ይዞታል። ፀጉሯን እያስተካከለች ትንሽ ከተመለከተችው በኋላ ጀርባውን ሳም አደረገችና አንሶላውን ከፍ አድርጋ ሙሉ በሙሉ ካለበሰችው በኋላ " የኔ ፍቅር እወድሀለሁ! አንዳንድ ጊዜ መጠጥ ፍቅርን ለመግለፅ ጥሩ አጋጣሚ ይሆናል። ዝም ብሎ ፍቅሩን መናገር ለማይችል በመጠጥ ሽፋን ወይም የሰከረ መስሎ የሆዱን ይዘረግፋል። ሁሌም የምደሰትበትንና ያመንኩበትን ምሽት ከአንተ ጋር ስላሳለፍኩ ደስ ይለኛል።"አለችና ጀርባው ላይ ፀጉሯን በትና ተኛች። ኪሩቤል እንቅልፉን ጨርሶ ሊነሳ ሲል ቤርሳቤህ ላዩ ላይ ተኝታበታለች። እሷን ላለመቀስቀስ ከእንደገና ተመልሶ ተኛ
○●○●
"እስካሁን ምን ሆኖ ነው እማዬ ያልነቃው?"ሔመን የቀዳማዊን መኝታ ክፍል በተደጋጋሚ እየተመለከተች ሔዋንን ጠየቀች። ሔዋን ኮስተር ብላ "ምን አስር ጊዜ ትጠይቂኛለች። ለምንድነው ቀዳማዊ ዝም ባለ ቁጥር ከእንቅልፉ ባልነቃ ቁጥር እኔን የምትጠይቂኝ ልጄ?"ብላ በመገረም መልሳ ጠየቀቻት። ሔመን የእናቷን ጥያቄ ከቁብም ሳትቆጥር ዝም ብላ የቀዳማዊን ክፍል ትመለከት ያዘች። ፊቷ የተወዛገበ ይመስላል። ለምን እንደሆነ ለእራሷም ባልገባት ልክ ለቀዳማዊ ትጨነቃለች። አብዝታ ስለ እሱ ጉዳዮችም ማወቅ እንዳለባት ለምን እንደምትፈልግ አታውቅም። ግን ቀዳማዊ የሆነ ነገር እያሰበ ነው ከተባለች ምንድነው የሚያስበው የሚል ጥያቄ ሁሉ ትጠይቃለች። ይህ እሳቤዋ እያደገ ቁጥጥር ላይ የደረሰ ይመስላል። "ሔመን በጥያቄ ሳታጨናንቀን ነው የደረስክልን "አለች ሔዋን ቀዳማዊ ከክፍሉ ሲወጣ እየተመለከተች። ሔመን የእናቷን ቃል ተከትላ ስትዞር ቀዳማዊን ተመለከተችው በደስታ ፈገግ አለች። "እትዬ ነገ ጠዋት ወደ ክፍለ ሀገር እሄዳለሁ። "አለ ቀዳማዊ ቁርስ ተሰብስበው እየበሉ ባለበት "ኧረ ይሻላል? ትንሽ አረፍ ብለህ አትሄድም?" "አይ ስመለስ በአንድ ልቤ እስከምሄድበት ጊዜ ብቆይ ይሻላል።" "እሽ እንዳልክ። ግን ብዙ አትቆይ!" " የተወሰነማ እቆያለሁ። ወንድሜን ጓደኛዬን ከስንት አመት በኋላ አይደል የማገኘው" "ብቻ ከማንም ጋር እንዳትጣላ። ሁሉንም ለእግዜር ነው የሚሰጠው። በእኛ አቅም የሚሆን ነገር የለም። በዛ ላይ ጊዜ ለሁሉም ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል። እና በተነጋገርነው መሠረት እሺ ልጄ "አለች ሔዋን ራሷን ዘንበል አድርጋ። ቀዳማዊ መልስ አልመለሰላትም "ምንድን ነው የተነጋገራችሁት?"አለች ሔመን ሔዋንና ቀዳማዊን በግራ መጋባት ስሜት በየተራ እየተመለከተች። ቀዳማዊም ሆነ እናቷ ሔዋን ምንም አልመለሱላትም። "ልጄ አሁን አሁን በጣም እያስፈራሽኝ ነው።ሁሉንም ነገር ካላወኩት የምትይው ነገር አልተመቸኝም። ለአንቺም ጥሩ አይደለም። ቀስ በቀስ ይጎዳሻል። በዛ ላይ ሰዎችን በግድ እንዲነግሩሽ የማስገደድ ያህል ስሜት ያመጣል። ሰዎችን ካስገደድሽ ደግሞ ያሰው ሳይፈልግ ሊዋሽሽ ይችላል። በኋላ ውሸት ሆኖ ስታገኘው ደግሞ አንቺ ትጎጃለሽ። ስለዚህ አንዳንድ ነገሮችን ለቀቅ ማድረግ አለብሽ ባይ ነኝ"አለ ሙሉሰው። ሔመን የአባቷ ንግግር ምቾት ያሳጣት ትመስላለች። አኮረፈች......
○●○●
"አሁን ነው ትክክለኛ የመሄጃ ስዐቴ "አለች ሐምራዊ የእጅ ስአቷን እየተመለከተች። " ዛሬ ደስ ብሎሻል። በፈገግታ ነው የነቃሽው። ሁኔታሽም ደስ ይላል"አለች ፊደላዊት ከወትሮው በተለዬ ካለፉት ብዙ አመታት የጧት ጊዜዋ ጋር በማነፃፀር እና የዛሬው ሁኔታዋ ከእነዛ ጊዚያት ፍፁም ተቃራኒና የተለዬ እንደሆነ እያየችና በቃላት ለልጇም ወጋ እያደረገች።። "ከዚህ በኋላ እማዬ ከዚህ በበለጠ በፈገግታ ታጅቤ የምነሳባቸውና የምቀበላቸው ጠዋቶች እንጅ በሀዘን በድብርት የምቀበላቸው ጠዋቶች አይኖሩም "አለች ሐምራዊ። "ደስስስስ ይለኛል የኔ መላዕክ ልጅ። ሁሌም ፈገግ ሳቅ እንድትይልኝ ነው የምፈልገው። ካልሆነ በአንቺ መከፋት እና ደስተኛ የማልሆነው እኔም ነኝ።"አለችና ጉንጯን ሳመቻት። "እሺ እማዬ ደህና ዋይልኝ በጣም ውድድ ነው የማደርግሽ"ብላት ወጣች። ፊደላዊት በአይኗ እስከበር ድረስ ሸኘቻት። ከልጆቿ አስበልጣ ሐምራዊን ለምን እንደምትወዳት እስከማይገባት ድረስ ትወዳታለች። ለሐምራዊ ለየት ያለ ስሜት በመኖሩ ከሌሎቹ ልጆቿ ጋር ራሱ ቅራኔ ውስጥ ገብታለች። ብዙ ጊዜ "እኛማ ልጅሽ አይደለንም። ለአንቺ ልጅ ሐምራዊ ብቻ ነች። በማለት ወቅሰዋታል። አኩርፈዋታል። እሷም ለወዲያው እነሱን አባብላ በማግስቱ ከሐምራዊ ጎን ያገኟታል። ቀስ በቀስ አሁን ላይ እየለመዱት መጡ እንጅ። ሐምራዊ በፈገግታ ታጅባ ከወትሮው በተለዬ መነቃቃት ላይ ሆና በጊዜ የስራ ገበታዋ ተገኝታለች።
○●○●
የአገር ውስጥ ኢት 328 በራሪ አውሮፕላን ከ 2 ስአት በረራ በኋላ ተሳፋሪዎቹን የጉዞው መዳረሻ ወደ ሆነችው ሀመረ-ኖኅ ከተማ አደረሰ። ተሳፋሪዎች ወርደው እቃቸውን ወደ ሚያገኙበት ተርሚናል አመሩ። ቀዳማዊ ከተሳፋሪዎች መጨረሻ ወርዶ ዕቃውን በየተራ ካወረደ በኋላ በተሽከርካሪ ካርጎ እየገፋ ታክሲዎች ጋር ደረሰ። ባለታክሲዎቹ ለመጫን እየተሻሙ ያጣድፉት ያዙ " ወደ ራስ አምባ ቀበሌ ነው የምሄደው ኮንትራት የሚወስደኝ ነው የምፈልገው"አለ ረጋ ባለ አነጋገር። እኔ ካልወሰድኩህ እያሉ ሲሻሙት የነበሩ የታክሲ ሾፌሮች ማፈግፈግ ጀመሩ። ቀዳማዊ ግራ በመጋባት "ምነው ምን ሆናችሁ ነው?" አለ። " መንገዱ አይመችም ባባዬ እና ዋጋ ብንተምንልሽ ደግሞ ልትጎጂ ትቾያለሽ!"አለ አንደኛው ወጣት እግር ሾፌር ፀጉሩን እያፍተለተለ "እሺ ስንት ነው የምትለኝ "አለ ቀዳማዊ የሆነ ነገር ቅልል እያለው " 400 ብር ነው ባባ"አለ ሾፌሩ አንገቱን እንዳቀረቀረ። "እሺ አመሰግናለሁ ወንድሜ ችግር የለውም እከፍላለሁ! "አለና ጋቢና ገብቶ ተቀመጠ። "ዛሬ በቀኝህ ነው መሰል የተነሳኸው "ብሎ ሾፌሩን አንዱ ጓደኛው ትከሻውን ቸብ አደረገው። ሾፌሩ በደስታ ከጓደኞቹ ጋር የቀዳማዊን እቃ አንድ በአንድ ከጋቢና ኋላ ካሉት ወንበሮች አስገብተው ካስቀመጡ በኋላ መኪናውን አስነስቶ መንገዱን ጀመረ።
○●○●
"እማዬ ቀዳማዊ ተመልሶ ባይሄድ ደስ ይለኝ ነበር!"አለች ሔመን አንገቷን ሰበር አድርጋ ፀጉሯን ለእናቷ እያስያዘች። " እኔም ደስ ይለኛል ልጄ እዚሁ አገሩ ላይ ቢሰራ ነው የምመርጠው። ግን የሚወስነው ቀዳማዊ ነው" "እሱማ ልክ ነሽ ግን "አለችና ሐሳቧን ሳትጨርስ ዝም አለች። " ግን ትምህርት እንዴት ነው?" ""ቆንጆ ነው እማዬ እድሜ ለቀዳማዊ ያኔ በደንብ እያስረዳ ቤዝ ባያስይዘኝ አሁን ላይ አይደለም ተፎካካሪ ተማሪ ልሆን ሴሚስተር ፓስ ራሱ ይከብደኝ ነበር። ........
                  🖎​✐✎ ይቀጥላል...​ ✎​✐✍︎
            ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ like...
@quoteopia
@quoteopia
❤ 7
Смотреть все посты