Аналитика Telegram-канала
Подписчики
1 305
Охват за 24 ч
278
ER за 24 ч
21,30%
Публикаций
91

Динамика подписчиков

7 дней 30 дней 6 месяцев Больше
16 ноя19 ноя22 ноя
Показаны последние 7 дней Больше истории →

Охваты публикаций

28.1029.1030.1031.1012.1115.11
86
Средний охват
185
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале Больше статистики →

Упоминания

16
Упоминаний
6
Из них репостов
4
Каналов
Нет примеров за последние 90 дней
Все упоминания

Последние посты

3 из 91 2 из 91
📢 ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ በአዲሱ የአዲስ አበባ የግዥ መመሪያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 197/2019 የብሔራዊ ግልጽ ጨረታን አፈፃፀም በአንቀጽ 54 ደንግጓል። 🔹 የገንዘብ ጣሪያዎች: ግዥው በሀገር ውስጥ ተጫራቾች ሊሟላ የሚችል ሲሆንና ግምታዊ ዋጋው ከሚከተሉት ካልበለጠ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ይፈጸማል ▪️ ግንባታ ሥራ፦ እስከ 3 ቢሊዮን ብር ▪️ ዕቃ ግዥ፦ እስከ 1 ቢሊዮን ብር ▪️ የምክር አገልግሎት፦ እስከ 90 ሚሊዮን ብር ▪️ ከምክር ውጪ ያሉ አገልግሎቶች፦ እስከ 250 ሚሊዮን ብር ከእነዚህ በላይ የሆኑ ግዥዎች በዓለም አቀፍ ግልጽ ጨረታ ይፈጸማሉ። 🔹 ያለ ገንዘብ ገደብ: የሚፈለገው ዕቃ፣ ግንባታ ሥራ ወይም አገልግሎት በሀገር ውስጥ ብቻ የሚገኝ መሆኑ ከተረጋገጠ፣ የገንዘብ ገደብ ሳይደረግበት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ መግዛት ይቻላል። 🔹 ተሳታፊዎች: በሕግ በተለየ ሁኔታ ካልተፈቀደ በስተቀር በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ መሳተፍ የሚችሉት የሀገር ውስጥ ተጫራቾች ብቻ ናቸው። “የሀገር ውስጥ ተጫራች” ማለት የባለቤቶቹ ዜግነት ሳይታይ በኢትዮጵያ ሕግ የተቋቋመ፣ የንግድ ምዝገባ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የንግድ ፈቃድ ያለው ተጫራች ነው። 📢 Join: @procinsightet 📬 Contact: @Procinsight_bot 👨‍🦰 Discussion: @procinsightet2
ещё
45 0 1 15 ноя, 20:30
📢 የአዲስ አበባ የጨረታ ማስከበሪያ ከፍተኛ መጠን ወደ 5 ሚሊዮን ብር ከፍ አለ! 🔴 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ያወጣው አዲሱ የመንግስት ግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 197/2019 የጨረታ ማስከበሪያ ከፍተኛ መጠንን ወደ 5 ሚሊዮን ብር ከፍ አድርጎታል። 2 ሚሊዮን ብር የፌዴራሉ ግዥ መመሪያ 1073/2017 ጣሪያ ሲሆን ማስከበሪያው አሁንም ከግምታዊ ዋጋው ከ0.5% እስከ 2% ድረስ ይሰላል። 🔹በሌላ በኩል “በቁርጥ ነጠላ ዋጋ” የሚፈፀም ግዥ አዲስ አማራጭ ሆኖ ተካቷል። የኮንስትራክሽንና ተያያዥ ሥራዎችን ከመደበኛ የግዥ ዘዴዎች ውጭ በዚህ የቁርጥ ዋጋ ደንብ መሠረት መግዛት ይቻላል። 🟣 መመሪያው ነባሩን የግዥ መመሪያ ቁጥር 3/2002 ሽሯል። 📎 ሙሉው መመሪያ ከዚህ ጋር ተያዟል። 📢 Join: @procinsightet 📬 Contact: @Procinsight_bot 👨‍🦰 Discussion: @procinsightet2
ещё
40 0 2 12 ноя, 21:12
📢 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ተቋራጭ የግንባታ ግዥና የሥራ ስምሪት የአሰራር ደንብ ቁጥር 199/2018 – የምዝገባ ሂደት በአጭሩ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን፣ የመንገዶች ባለስልጣን እና ሌሎች የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በቤቶች፣ በኮሪደርና በወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ሥራ ተቋራጮችን የሚያጫርቱበትና የሚመርጡበት አዲሱ ደንብ ምን ይላል? ይህ ደንብ በነዚህ ዋና ዋና ፕሮጀክቶች ላይ ሥራ የሚሰጠው በቁርጥ ነጠላ ዋጋ ላይ ተመስርቶ እና በድርድር እንዲሆን ይደነግጋል። 📌 1. የምዝገባ ጥሪ (አንቀጽ 5) አሰሪው አካል ጥሪውን በማስታወቂያ፣ በጋዜጣ፣ በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮና በድረ-ገጽ ያደርጋል። የምዝገባ ጊዜው 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ነው። 📌 2. ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ዋና ዋና ሰነዶች (አንቀጽ 6) ✅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ✅ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት ✅ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ✅ የአቅራቢዎች ዝርዝር (Supplier List) ውስጥ የመመዝገብ ማስረጃ 💡 ማስታወሻ፦ ሰነዶቹ ዋናውና አንድ ቅጂ ይቀርባሉ። እያንዳንዱ ገጽ በባለቤቱ፣ በዋና ሥራ አስኪያጁ ወይም በሕጋዊ ወኪሉ ተፈርሞ ማህተም ሊደረግበት ይገባል። የጎደለ ሰነድ ካለ ከምልመላው አንድ ቀን በፊት እንዲቀርብ ሊደረግ ይችላል። 📌 3. የመዝጋቢው ኃላፊነት (አንቀጽ 7): ቅጂዎችን ከዋናው ሰነድ ጋር አመሳክሮ ይመዘግባል። 📌 4. የቴክኒክ ሰነድ አቀራረብ (አንቀጽ 8–10) የቴክኒክ ሰነድ መግዛት የሚችሉት የተመዘገቡ ተቋራጮች ብቻ ናቸው። ተቋራጩ የሚያቀርባቸው ሰነዶች፦ 📍ባለፉት 5 ዓመታት የሰራቸውን ሥራዎች ማስረጃ 📍የባለሙያዎች የሥራ ልምድ (CV) እና ፈቃድ የማሽነሪ ባለቤትነት ወይም የኪራይ ውል 📍በኦዲተር የተረጋገጠ የሂሳብ ሪፖርት 🆓 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) አያስፈልግም። 🛑 ሰነድ ከገባ በኋላ መጨመርም ሆነ መቀየር አይቻልም። 📌 5. ቁልፍ የብቁነት መስፈርቶች (እነዚህን ትኩረት ይስጡ!) 🚫 ቀደም ብሎ የጀመረውን ሥራ ቢያንስ 85% ያላጠናቀቀ ተቋራጭ መሳተፍ አይችልም። 🎯 ወደ ድርድር ለማለፍ ከቴክኒክ ምልመላው ቢያንስ 75% ነጥብ ማግኘት ያስፈልጋል። ❌ ባለፉት 2 ዓመታት በአፈጻጸም ችግር ውል የተቋረጠበት ተቋራጭ አይካተትም። ⛔ ሀሰተኛ ሰነድ ያቀረበ በየትኛውም ደረጃ ከውድድር ይሰረዛል። 📌 6. የቅሬታ አቀራረብ (አንቀጽ 11) ቅሬታ ያለው ተቋራጭ ውሳኔው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በ 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ለአሰሪው የበላይ ኃላፊ ማቅረብ ይችላል። በምላሹ ያልረካ ተቋራጭ አቤቱታውን ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ማቅረብ ይችላል። 📢 Join: @procinsightet 📬 Contact: @Procinsight_bot 👨‍🦰 Discussion: @procinsightet2 Tik Tok: https://vt.tiktok.com/ZSgWsfGQN/
ещё
53 0 1 31 окт, 19:15
Больше постов

Продолжить анализ этого канала

  • История роста подписчиков
  • Просмотры и охваты публикаций
  • Кто упоминает канал и кого упоминает он
  • Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней