Аналитика Telegram-канала
Подписчики
18 276
Охват за 24 ч
993
ER за 24 ч
5,43%
Публикаций
9 954
Динамика подписчиков
7 дней
30 дней
6 месяцев
Больше
28 окт31 окт3 ноя
Показаны последние 7 дней
Больше истории →
Охваты публикаций
29.1029.1030.1030.1001.1102.11
193
Средний охват
444
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале
Больше статистики →
Упоминания
5
Упоминаний
4
Из них репостов
5
Каналов
78
Упоминаний
24
Из них репостов
23
Каналов
Последние посты
3 из 9 954 2 из 9 954
ልጄ ሆይ!
ሙቫይልህን አስቀምጥ 📱
ምክሬን አድምጥ !
ጦርነትን የሚጠምቀው
እድሜውን ብትጠይቀው
የማቱሳላ ገራዥ
የአብርሀም ዣንጥላ ያዥ
በጎሽ ያረሰ
አዳምና ሄዋን ገምጠው የተፉትን በለስ አንስቶ የጎረሰ
የሎጥን ሚስት ሀውልት የላሰ
ሆኖ ታገኘዋለህ ፤
ልጄ ሆይ!
ጦርነትን የሚያውጀው
ያረጀው ነው የጃጀው
ግና ጦርሜዳ ላይ የሚዋጋው
ያንተ ብጤ ነው ለጋው፤
ሜሲ አንደመታት ኩዋስ ወደ መቃብር የሚልለጋው፤
ልጄዋ!
በጀግኖች ዘመን እንኩዋ-“ከመሞት መሰነበት” ይባላል
የሰማእት ሀውልት ሆኖ ተመቆም
ህያው ሆኖ መተኛት ይሻላል
ልጄ ሆይ!
በሀያላን እንዳትታፈስ
ሁንባቸው መንፈስ
መንፈስ መሆን ቢሳንህ ; ሁንባቸው የጎመን ፈስ
ቀን እስኪያልፍ ድረስ ወደ ጎረቤት አገር ንፈስ፤
ልጄ ሆይ!
ጦርነት ማለት
አንድ ሀሙስ የቀራቸው ሸባዎች፣
አንድ ሀሙስ ብቻ የኖሩትን አበባዎች
የሚያስቀጥፉበት አዝመራ ነውና
በሰማእትነት ስም
ምትክ አልባ ሕይወትህ ሳይከስም
እሸት አካልህን ሳይለውጡት ወደ ፍግ
ተግተህ አፈግፍግ፤
ልጄ ሆይ!
ለማንም ኩስለመናም
ነፍስ ይማር ለማለት አንኩዋ ጊዜ ለሌለው
የሙቫይልህን ካሜራ አንጂ ጠመንጃህን አትወልውለው፤
አለቃ ክንፌ
ለለጅ ምክር የአባት መታዘቢያ
ሁሌም ማንበብ📖✨
ещё
126
3
3 2 ноя, 20:16
አባቴ መጠጥ ወዳጅ ነው... ግን ሰክሮ የረበሸበትን አንድም ቀን አላስታውስም። ሲጠጣ ትንሽ ፈነሽነሽ ያለ ፊት ያሳየናል፣ በየመሃሉ ስማችንን እየጠራ...
'አጠፋሁ? ' ይላል ...
'ተመስገን!' ይላል ....
አደጉልኝ እያለ፥ ይወዱኛል እያለ፥ ጠጅ መጠጫ አላጣሁም፥ ሚስቴ ትወደኛለች፥ እያለ ነው መሰለኝ...!
አምሽቶ ከገባ ዘው አይልም፤ እናቴን "ዓለም ሆዴ ልግባ ?" ብሎ ነው። እናቴን ያከብራታል። ይወዳታል። ለኹለት አመት ከስድስት ወር የአልጋ ቁራኛ ሁናበት ታውቃለች። ጨቅላ ነበርኩ፤ ሌሎቹም ከኔ ብዙ አይበልጡም ነበር ...
እናቴ "እኔ ከታመምኩት በላይ ተጎሳቁሎ፤ ልብሱ ላዩ ላይ አልቆ ነው ያስታመመኝ" ትላለች።
እንደሚወዳት አሳይቷታል ፣እንደምትወደው ሲገባ ሲወጣ እየተንከባከበች አሳይተዋለች ።
"መርቀኝ እለዋለሁ..."
'እንደኔ የምትወድህ እኔ እንደምወዳት ዓይነት ሚስት ይስጥህ፤ ፍቅር ካለ ኑሮ ብዙ አይከብድህም። ስታጠፋ ከታረምክ ህይወት አታሸንፍህም።' ይላል።
መርቀኝ እንጂ ስለው።
'ደስ ብሎህ ኑር' ይላል ። ጌታዬ ለኔ እንደራራው ይራራልህ ይለኛል ።
"ትወደኛልህ እንዴ" ስለው።
ዝም ብሎ በስስት እያየኝ 'ጅል ነህ እንዴ?' ይላል።
ከዚህ ቤተሰብ ተወልደን እንዴት ፍቅር አያንበረክከንም ታድያ!?
© Adhanom Mitiku
ሁሌም ማንበብ!
ещё
317
3
12 1 ноя, 14:05
አለቃችን ሴት ይወድ ነበር። ሁሉም ይወዳልኮ የእርሱ ግን ትንሽ ወደአምልኮ ይወስደው ነበር። በምሳሌ ላሳያችሁ...ድርጅቱ ውስጥ የሆነች ቆንጆ የፅዳት ሰራተኛ ነበረች። የሆነ ቀን አዳራሽ ውስጥ ቡና ተደፍቶ እግራችን ስር እየወለወለች ሁላችንም እግራችንን በየተራ በአክብሮት ስናነሳ እሱ በሁለት እግሩ ዘለለ እስከምታፀዳ በአየር ላይ ሊቆም ማለት ነው። እዚህ ድረስ ነው ሴቶች ልቡን የሚነሱት። ምኑ ነው በፈጣሪ!
እና የሆነ ጊዜ አንዲት የከተማችን ታዋቂ ቆንጆና ባለሃብት ሴት እኔ የምሰራበት ድርጅት ጋር በጋራ የሆነ ስራ ለመስራት ጠየቀች። አለቃችን የሚመለከተንን 9 የክፍል ሐላፊወች ሰበሰበንና ሙያዊ አስተያየት ጠየቀን። ነገሩ የሴትዮዋ ድፍረት ገረመን። ዝም ብላ ልዝረፍ አትልም? ዘጠኛችንም ከበቂ ማብራሪያ ጋር ስራው ፈፅሞ ድርጅቱን እንደማይጠቅም ገለፅን።
አለቃችን ለሁለት ሰዓት ማስታወሻ እየወሰደ አዳምጦን "አርኪ ውይይት ነበር አመሠግናለሁ" ብሎ ተለያየን። ከወር በኋላ ካሳንችስ በሚገኝ ትልቅ ሆቴል ድል ያለ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ተጠራን። ይሄ ኩርፍድ አለቃችን እዛች ቆንጆ ፣ ሐብታም እና ታዋቂ ሴትዮ ጋር አይሆንም ያልነውን ተስማምቶ ተፈራረመ። ሴትዮዋ በሚስለመለም እና በሚሟዘዝ ፈገግታ " ለመጣመር ያደረግነው ውይይት አርኪ ነበር" ብላ ወደአለቃችን ተመለከተች፤ ራሱን በመስማማትና በጉጉት ነቀነቀ። ቀጥሎ ወደእኛ ዙራ ገላመጠችን። በብስጭት ጦፍን። በተለይ አንዱ የስራ ባልደረባችን ብስጭቱ ከመጠን ያለፈ ነበር። ለኮክቴል የተዘጋጀውን መጠጥ እያነሳ ገሰረተውና በብስጭት😀
ከዚህ በኋላ ሴት ፣ መጠጥ፣ በርበሬ፣ ዘፈን፣ ሹራብ፣ ሽቶ፣ ስብሰባ፣ አበባ፣ ሂል ጫማ፣ ቡና፣ ቋንጣ ፍርፍር፣ መፅሐፍ፣ ፊልም የሚወድ ሰው ጋር ብሞት አብሬ አልሰራም አለ። እና ስራ ለቀቀ፤ ቋንጣ ፍርፍር ሹራብ እና ቡና የእኔ ነው ሌላውን እንጃ።
ሁሌም ማንበብ📖✨
ещё
31
0
2 30 окт, 15:13
Продолжить анализ этого канала
- История роста подписчиков
- Просмотры и охваты публикаций
- Кто упоминает канал и кого упоминает он
- Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней