Аналитика Telegram-канала
Подписчики
1 414
Охват за 24 ч
67
ER за 24 ч
4,74%
Публикаций
836
Динамика подписчиков
7 дней
30 дней
6 месяцев
Больше
15 ноя18 ноя21 ноя
Показаны последние 7 дней
Больше истории →
Охваты публикаций
02.1105.1110.1118.1120.11
67
Средний охват
207
Лучший результат
Показаны 5 публикаций — последние в канале
Больше статистики →
Упоминания
34
Упоминаний
11
Из них репостов
9
Каналов
3
Упоминаний за 90 дней
2
Из них репостов
3
Каналов за 90 дней
Последние посты
3 из 836 2 из 836ቅዱስ ሚካኤል🪽
#ይረዳል ዳን.10፥13-21
#ያጽናናል ዳን. 10፥21
#ለእግዚአብሔር ሕዝብ ይቆማል ዳን.12፥1
#ሰይጣንን ይገስጻል ይሁዳ ቊጥር 9
#ዘንዶውን ይዋጋል ራእ.12፥7
#በመንገድ ሁሉ ይጠብቃል ዘጽ.23፥20
እንደጋሻ እግዚብሔርን በሚፈሩ ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል መዝ.33፥7/2ነገ.6፥14
እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን!
ещё
21
1
20 ноя, 20:57
(በኤርምያስ መለሰ የተጻፈ እንዳለ የቀረበ)
https://youtu.be/lFZmDcKQ_JI?si=kSVhMiUGtx7AYh3S
👆
ይኽንን ቪዲዮ ደጋግሜ ሰማሁት። ሦስት ነገሮችም ገርመውኛል።
አንደኛ:- ብፁእ አቡነ ኤርምያስ የመጋቤ ሐዲስ እሸቱ የቀለም ልጅ መኾናቸው።
፪ኛ. መጋቤ ሐዲስ እሸቱ ያነሷቸው ጥያቄዎች ከአንድ የጋዜጠኝነት ሙያ ካለው ፕሮፌሽናል ጋዜጠኛ የመነጩ ስለመሰሉኝ መጋቤ ሐዲስ እሸቱ ሌላ ሰው ኹነው ስለታዩኝ እጅግ አስገርመውኛል።
፫ኛ. ብፁእ አባታችን ሥለ ሕዝበኝነት አስተያየቶች እና ሥለ ተቋማዊ ውሳኔ አሰጣጥ በሰጡት ሐሳብ ምክንያት የራሳችን ወጣት ፎቷቸውን ዘቅዝቆ ሲዘምትባቸው ሳይ መንጋነታችን ገርሞኛል።
እኔ ግን የትኛው ክትባት ነው ያለፈኝ ። ይቅርታ ኣድርጉልኝና እንድታስረዱኝ እፈልጋለሁ። ምናልባትም ክትባት ካስፈለገኝም ክተቡኝ 😁
እግዚአብሔር ውዴታው የምንፈልገውን ሳይኾን የሚያስፈልገንን ይሰጠን ዘንድ ነው ብየ አምናለሁ።
በችግር ግዜ አንድ ብልህ መሪ ሚዲያ ላይ የሚያወራው የሚመራው ሕዝብ የሚፈልገውን ሳይኾን ለጠላት መስማት የሚገባውን ነው። መሬት ላይ ደግሞ ለሚመራው ሕዝብ የሚያስፈልገውን ይሰራል። በእኔ ክትትል እና ዕይታ ብፁእ አቡነ ኤርምያስ እስካሁን ይኽንን የመሪነት መልክ የተላበሱ ናቸው።
#ወደ ዋናው ጉዳይ ስገባ
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ በቪዲዮው ላይ የገለጹት እና አጀንዳ የኾነባቸው ሐሳብ እኔ እንደገባኝ...
የቤተክርስቲያን አመራር ውሳኔ ሰጭነት ከማኅበራዊ ሚዲያ አስተያየት (populism) ይልቅ ተቋማዊና መርሕ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ መወሰን እንዳለበት ለማሳየት ነው እንጅ የሕዝብን ሐሳብ ሪጀክት ማድረግ አይመስለኝም። ይኽንን ሐሳብ ከተለያዩ አስተምህሮዎች አንጻር እንደሚከተለው መተንተን ይቻላል።
👉 ከክርስትና አስተምህሮ አንጻር... መሪዎች የተመረጡት ሕዝቡን በጅምላ ለማስደሰት ሳይኾን፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሖችን ለመጠበቅ ነው። ብፁዕ አባታችን እንደገለጹትም መሪዎች ለሰዎች ጭብጨባ ሳይኾን፣ ለሚያሳልፉት ውሳኔ ይበልጥ ተጠያቂነት አለባቸው። ስለዚህም አንድ መሪ ዛሬን ሳይኾን ነገን አሻግሮ አይቶ ይወስናል።
👉 ከደኅንነት እና ከሰርቫይቫል አንጻር ... መሪዎች በሥሜታዊነት የሚነዱ አስተያየቶች ላይ ብቻ ተመስርተው ውሳኔ ቢወስኑ፣ የጋራ መረጋጋት እና የሀገር ሕልውና አደጋ ውስጥ ይገባል። አባታችን “በሕዝብ አስተያየት ልክ ብንወስን ሀገር ይፈርሳል” ያሉት፣ ውሳኔዎች በጥልቅ መመርመር እንዳለባቸው ለማስገንዘብ ነው ብየ አምናለሁ። ምናልባትም የሶሪያን ክርስቲያኖች ጥፋት ብናስታውል ይኽ ሓሳባቸው ይገባናል ብየ አስባለሁ። እንጅ ራሳችሁን አትጠብቁ ዝም ብላችሁ ሙቱ ለማለት ፈልገው አይደለም።
👉 የፖለቲካ ፍልስፍና እንደሚያስተምረው መሪነት አድማጭ መኾንን የሚጠይቅ ቢኾንም፣ የረጅም ጊዜ ጥቅምን ከሚጎዳ የሕዝብ ግፊት (mob mentality) የመከላከል ኃላፊነትም አለበት። ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የጠቀሱት ተቋማዊ ውሳኔ (institutional decision) የአንድን ማኅበረሰብ መረጋጋት የሚጠብቅ የመሪዎች የሞራል ግዴታ ነው።
👉 ከሳይንስ አንጻር... ሳይንሳዊ አስተዳደር ውሳኔዎችን የሚወስነው በመረጃ፣ በትንተና እና በጥንቃቄ ነው። ማኅበራዊ ሚዲያ በሚፈጥረው ፈጣንና ሥሜታዊ ጫና ላይ ብቻ የተመሠረተ ውሳኔ ለከፋ ችግር የሚያጋልጥ መኾኑን አባታችን በመግለጽ፣ ውሳኔዎች ችግሩን አብላልቶ መፍትሔ ከመፈለግ ጋር መያያዝ እንዳለባቸው ይናገራሉ።
👉 አባታችን “ሕዝበኛ” (populist) አስተሳሰብ የሚያመጣውን አሉታዊ ተጽእኖ በማንሳት፣ መሪዎች ሕዝቡን ደስ በሚያሰኝ መንገድ ብቻ መመራት እንደሌለባቸው ነው ያብራሩት።
ለምሳሌ በአርሲ ጉዳይ ውጡና ተበቀሉ ቢሉ ምን ሊፈጠር ይችላል? ለመበቀልስ ዝግጁ ነን ወይ? እንኳን የመበቀያ አቅሙ ይቅንርና ክርስቲያናዊ ሕብረት እንኳን የለንም። በዚያ ላይ አርሲ ላይ ስለሚደረገው ነገር የተጠና እና የተደራጀ መረጃ የለንም። ባልተደራጀ ማኅበረሰብ፣ ባልጸና ተቋም፣ ያለ ጠንካራ መዋቅር ፊሽካ ቢነፉ እንደ ሶሪያ እንበተናለን እንጅ አንድ ነገር መፍጠር አንችልም። መፍትሔው ድምፅን አጥፍቶ መረጃ እየተለዋወጡ እየተደጋገፉ በየዘርፉ መስራት ነው።
የኾነው ኹኖስ እንዴው እሳቸው ላይ የዘመተው ኹሉ ውጣ ልምራህ እንዋጋ ቢሉ አንድ ሰው ይዘምት ይኾን?
እግረ መንገዴን ዐውደ ምሕረት ላይ ቁመው " ሊገድልህ ሲመጣ ሚስትህን ሊደፍራት ሲመጣ ጆሮ ግንዱን በለው " ብለው ያስተማሩትን አባት ሐሳብም ላንሣው። እጅግ በጣም ወቅታዊ ትምህርት ነው የሰጡት። የእኔ አቋሜም ይኸው ነው። ቁመህ ሰማዕትነትን ተቀበል የሚባል የጅል ትምህርት አያስፈልገንም። ሰማእት ኹን የተባለው ለመመከት አቅም ብታጣ እና " ሃይማኖትህን ቀይር" ብትባል ነው። እንጅጅ ለመመከቱ አቅሙ እያለህ ዝም ብለህ ታረድ የሚባል ስብከት የለም። ይኽንን የሚሰብክ ካለም ጠላት ነው።
ለማንኛውም ሓሳባቸውን ባንደግፍ እንኳን ፎቷቸውን ዘቅዝቀን ልናራክሳቸው አይገባም። ሲኾም እናንተ ካልተረዳችኋት ( በራሳችሁ መንገድ ከተረዳችኋት) አንዲት ቃል በላይ የሲኖዶሱን የቤተክህነቱን ችግር በደንብ አብራርተው ስለነገሩንም ሊመሰገኑ ይገባ ነበር።
https://www.facebook.com/share/1FLe4gnfoK/?mibextid=wwXIfr
ещё
23
0
18 ноя, 13:50
በሮሜ መልእክት ጥናት ላይ ለተጠየቁ ጥያቄዎች የተሰጠ ምላሽ
1) ምግብን በተመለከተ የተነሳ ጥያቄ
2) <<ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ።>> ሮሜ 5:14 ኃጢአት ባልሰሩት ላይ ለምን ሞት ነገሰ ? ኃጢአት ያልሰሩት የተባሉትስ እነማን ናቸው ? ከሙሴ በኋላስ ሞት መንገሱን አቁሟል ወይ ?
3) <<የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።>> ሮሜ 8:34 በዚህ ጥቅስ ላይ ሁለት ጥያቄ ተነስቷል። በአንዳንድ መጻሕፍት የሚማልደው የሚለውን የሚፈርደው ይለዋል። የመጽሐፍ ቅዱስ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ መተርጎሙን በተመለከተ የተነሳ ጥያቄ 1ኛው ነው። ሌላው የሚማልደው የሚለው ቢብራራልን ለሚል ጥያቄዎች በዚህ ሪከርድ መልስ ተሰጥቷል።
ሽር አድርጉ ለጓደኞቻችሁ
https://t.me/Stpoulos
ещё
55
1
10 ноя, 13:34
Продолжить анализ этого канала
- История роста подписчиков
- Просмотры и охваты публикаций
- Кто упоминает канал и кого упоминает он
- Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней