Аналитика Telegram-канала
Подписчики
319
Охват за 24 ч
33
ER за 24 ч
10,34%
Публикаций
16
Динамика подписчиков
7 дней
30 дней
6 месяцев
Больше
7 ноя10 ноя13 ноя
Показаны последние 7 дней
Больше истории →
Охваты публикаций
01.1102.1107.11
13
Средний охват
22
Лучший результат
Показаны 3 публикации — последние в канале
Больше статистики →
Упоминания
90
Упоминаний
52
Из них репостов
2
Каналов
1
Упоминаний за 90 дней
1
Из них репостов
1
Каналов за 90 дней
Последние посты
3 из 16 2 из 16. ╔═══ ೋ 𔘓 ೋ ═══╗
𝙼ҽɾℓỉɳ
ፀሐፊ « 𝙰ϝ𝚗α𝚗 »
╚═══ ೋ 𔘓 ೋ ═══╝
. ━─━─ 𓍯 ─━─━
ραɾƚ 0:04
━─━─ 𓍯 ━─━─
ከሰከንዶች የደስታ ገለፃ ቡሀላ ጨዋታው በድጋሜ ቀጠለ አሁንም ቢሆን የ 11 ክፍል ተማሪዎች የአጨዋወት ስልታቸው ለተቃራኒ ተጋጣሚ ቡድን ከባድ ሆነባቸው
« ለ 12 ክፍሎች ጨዋታው ከባድ የሆነባቸው ይመስላል ኳሷን ከራሳቸው የጨዋታ ክልል ማሳለፍ እንደተሳናቸው እያስተዋልን ነው »
« ልክ ብለሀል መምህር እዩኤል 11 ክፍሎች በጣም አሪፍ የሚባል የአጨዋወት ስልት እየተጠቀሙ ነው ኳስ አያያዛቸው የዃላ አሰላለፍቸው ብቻ ምን አለፋህ ጨዋታውን በመቆጣጠር የበላይነት ይዘዋናል በድጋሜ አሊ ያሻማው ኳስ ለ ሮቤል ሮቤል ማለት እንግዲህ የ 11 ክፍል natural ተማሪ ነው በትምህርት ቤታችን ውስጥ አሉ ከሚባሉ ጎበዝ ተማሪዎች አንዱ ተማሪያችን ነው ሮቤል ሮቤል ለመሀል መስመር አጥቂው ለበምነት በረዥሙ ካሱን አሻምቷል በምነት በፍጥነት ኳሷን ወደ ተቃራኒ ቡድን የግብ መስመር ይዟት እየሄደ ነው በእምነት ጎልልልልልልል አልገባም ለትንሽ የበእምነት ሙከራ ምንም አይልም የጎሉን አንግል መቶ ተመልሷል »
«የተሰጣቸውን 45 ደቂቃ ጨርሰው ጭማሬ 5 ደቂቃ ነው የሚቀራቸው ይህ ዙር በ 11 ክፍሎች መሪነት ሊጠናቀቅ ይመስላል ሁኔታው 11 ክፍል ተማሪዎች በጣም ጫና እያደረጉ ነው ከመሀል ሜዳ የተሻማው ኳስ አሊ ዙሩን እያከረረው ነው እንደ ቅድሙ አይነት ቴክኒክ ሊጠቀሙ ይመስላል አሊ ኳሱን ለመርሊን አቀብሏል ጎልልልልልልልልልልል በድጋሜ መርሊን በሚያስደንቅ ሁኔታ ጎል አስቀጥሯል » በዳኛው የፊሽካ ጩኸት የጨዋታው መጠናቀቅ ታወቀ ዙሪያውን ከበብው የነበሩት ተማሪዎች በጩኸት ራሳቸውን ስተዋል የቡድኑ አባላት እና መርሊንን አቅፈው ደስታቸውን እየገለፁ ነው በድጋሜ አይኑን ፊት ለፊት ወደአለው ፎቅ ላከው ግን በቦታው አልነበረችም ዙሪያውን አየ ግን ድጋሜ አላገኛትም
─── ⪩⪨ ───
የአላርሙ ጩኸት ከእንቅልፌ አባነነኝ እየተገላበጥኩ ተነሳው ከተኛውበት የስራ ሰዓት እየደረሰ ስለነበረ ምግብ ቀማምሼ ከአፓርታማው ወጣሁ
« ቆየሽ እኮ ?» አለኝ እየሳቀ
« ዛሬ ተሳክቶልህ አምስት ደቂቃ ብትቀድመኝ አቤቱታ ልታቀርብብኝ ነው ሆ በል አሁን እንሂድ »
የመኪናውን መሪ እየዘወረ « ወደ ስራ ቦታ ነው አይደል ?»
« ታድያ የት ልትወስደኝ ፈለክ አንተ »
« ግን እዚህ ሀገር ከመጣሽ ስንት ጊዜ ሆነሽ »
5 አመት ሆነኝ መሰለኝ ግን ለምንድነው ብዙ ጥያቄ የምትጠይቀኝ የለሊቱ የፓሊስ ምርመራ አይበቃኝምእንዴ
« ኧረ እኔ ለጨዋታ ያህል ነው ይኸው ከተገናኘን ከአፓርታማ ወደ ስራ ቦታ ወይም ደሞ ከስራ ቦታ ወደ እቤት የሁልጊዜ ተግባርሽ ነው ጓደኛ ምናምን የለሽው ደሞ ገና ልጅነሽ ሲቀጥል የዚህ ሀገር ሰው እንዳልሆንሽ ያስታውቃል »
« አዎ እዚህ ለስራ እና ለትምህርት ነበር የመጣሁት አሁን ግን ትምህርቴን ጨርሻለሁ እና እዚሁ ስራ ስላገኘው ነው የምሰራው »
« ደስ ይላል እኔም ለስራ ነው እዚህ ሀገር የተገኘውት ደረስን መሰለኝ » አለኝ መኪናውን እያቆመ
« እሺ ቻው መልካም ስራ ነገሩ መልካም አዳር ልበል እንጂ » ከመኪናው ወርጄ ወደ ውስጥ ገባሁ
« ረዒፍ » የስሜ ጥሪ እርምጃዬን ገታው እና ወደ ላይ ቀና አልኩኝ ሁለተኛው ፎቅ ሊይ ኮስተር ብሎ ቁሟል
ዛሬ ደሞ ምን አቤቱታ ሰምቶ ይሆን ብስጭትጭት እያልኩ ተከትዬው ወደ ቢሮው ገባው ከጠረንጴዛው ላይ ያለውን የማእረግ ስሙን ካስተካከለ ቡሀላ ከጠረንጴዛው ዙሮ ተሽከርካሪው ወንበር ላይ ተቀመጠ።
« ወይዘሪት ራዒፍ ግን ስራሽ አግባብ ነው ?» በትኩረት እያየኝ
« ምን አደረኩኝ » የዛን ሰውዬ ጉዳይ መሆኑ ገብቶኛል እንዳላወቀ ሳስመስል እኮ ነው
« ትላንት ለሊት የተፈጠረው ነገር እራስሽንም እኔንም ሆቴላችንንም በጣም ያሳፈረ ስራ ነው »
« አዎ ትልቅ ጥፋት አጥፍቻለሁ ግን አውቄ ያጠፋውት ነገር አይደለም አጋጣሚ ነው ለእኔ ጥሩ የመሰለኝን ነገር ነው ያደረኩት » ስልምልልም እያልኩ ነው የማወራው
« ራዒፍ እዚህ ካሉ በጣም ጎበዝ እና የምወድሽ ሰራተኛ ነሽ ግን የአሁኑ ጥፋትሽ እኔ ባልፍሽ እሱ የሚያልፍሽ አይመስለኝም » ሁለት ወረቀቶች እንዳነባቸው አቀበለኝ
ወረቀቶቹን አነበብኳቸው አንዱ የፍርድቤት ክስ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እሱ ወረቀቱ ላይ ካልፈረመ ከስራዬ እንደምታገድ የሚያሳውቅ ፁሁፍ ነበር « ከሰሰኝ ማለት ነው » አልኩት « አዎ እንደ እኔ በተረጋጋ መንፈስ ከእሱ ጋር ይሄንን ጉዳይ ብትጨርሺው ለራስሽ ስትይ ትግስተኛ መሆን አለብሽ አሁን መሄድ ትችያለሽ »
ምንም ቃል ሳልናገር ከቢሮው ወጣው እና ወደ ልብስ መቀየሪያው ክፍል ገባሁ።
« ረዒፍ ምን አለሽ እ ሲጠራሽ እኮ እያየሁ ነበር »
ሎከሩን ከፍቼ ልብሴን አወጣሁት « ውድ ረዒፍ ትላንት ለሊት የሰራሽው ትልቅ ጀብድ አስደምሞናለ ለዚህ ሆቴል ትልቅ እውቅና ሊያስገኝ ስለሚችል የስራ ማሻሻያ እድገት እና የደሞዝ ጭማሪ ተደርጎልሻል » እንደዚህ ነው ያለኝ አልኳት ያወጣሁትን ልብስ እየቀየርኩኝ
« አንቺ እንደዚህ አጣብቂኝ ውስጥ ሁነሽም ትቀልጂያለሽ እንዴ ቆይ የምር ምንድነው ያለሽ ጠዋት ብታይው እኮ ሊፈነዳ የደረሰ እሳተጎሞራ መስሎ ነበር ያ ቀይ ፊቱ ይበልጥ ሲቀላ ብታይው የሚረጋጋም አይመስልም ነበር ተቀናቃኝሽን ደሞ ታቂያታለሽ ከዛ ከዚህ ስታራግበው መላዐክ መስላ ለመታየት ስትጥር ነበረ »
« እሷ ሴትዮ ለምን ከህይወቴ እንደማትወጣ ነው የማይገባኝ አሁንስ ከሷ ጋር መፎካከሩ ደክሞኛል የፈለገችውን ታድርግ » መሰላቸቴን ለመግለፅ ፊቴን ኩስምን አደረኩት
« ይሄ ስራ እኮ ላንቺ በጣም አስፈላጊ ነው ረዒ እናትሽን አስቢ እንጂ ይሄን ስራ አጣሽ ማለት እኮ ላንቺ ከባድ ነው»
« ምን ላድርግ እስኪ ንገሪኝ እኔ እሱ ላይ ጉዳት ያደረስኩት ከሱ ጋር ችግር ኑሮብኝ ነው ? ማንም ግን አልተረዳኝም ሁሉም እኔን ጥፋተኛ ነው ያደረገው እኮ ሰውዬውም ክስ መስርቶብኛል እሱ ይሄን ክስ ካላነሳ እስከዘላለሙ ነው ስራዬን የማጣው»
« ከባድ ነገር ነው ያለሽ አማራጭ ክሱን እንዲያነሳልሽ ማድረግ ነው ካልሆነ እኮ ከስራሽ በዲሲፕሊን ነው የምትታገጂው ከዚህ ብትወጪ እንኳን የትም መቀጠር አችይም እኮ እዚህ ሀገር ላይ » ሀዘኔታው ፊቷ ላይ ያስታውቃል
« አታስቢ ሁሉንም ፈጣሪ ያስተካክለዋል አሁን ወደ ስራ እንግባ ደሞ ሌላ ጣጣ እንዲይመጣብን » አልኳት ሰነዶቹን ያዝኩህ
« እሺ ራዒ በቃ አይዞሽ ግን ለምታደርጊያቸው ነገሮች አስቢ ቶሎ አትወስኚ እሺ ውዴ ተጠንቀቂ ደሞ «room 102 » የሆነ ችግር አለ ብለው ነበር ከእንግዳ ተቀባዮ ነው መልእክት የደረሰኝ »
« እሺ አሁን ወደዛው ልሂድ » አሳንሰሩን ተጠቅሜ ወደ room 102 አመራሁኝ የበር መጥሪያውን ነካውት
ምላሽ ግን አላገኘውም በድጊሜ መጥሪያውን ተጫንኩት “ ጧ ..ጧ ” የሚል ኮቴ ሰማው እና አይኖቼን ወደያዝኩት ወረቀት አደረኩት በሩ ተከፈተ በፈገግታ ቀናል ስል ድንግጥ አልኩ
┎┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┒
ይቀጥላል ....
┖┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┚
ещё
3
0
1 7 ноя, 21:28
. ╔═══ ೋ 𔘓 ೋ ═══╗
𝙼ҽɾℓỉɳ
ፀሐፊ « 𝙰ϝ𝚗α𝚗 »
╚═══ ೋ 𔘓 ೋ ═══╝
. ━─━─ 𓍯 ─━─━
ραɾƚ 0:03
━─━─ 𓍯 ━─━─
« ይሄን ማድረግ ካልቻልሽ ምንም ማድረግ አልችልም » አልፎኝ ሄደ በቆምኩበት ድርቅ ብዬ ቀረው
~ ~ ~
« የምርህን ነው ግን ከስራዋ ሊያስባርራት ይችላል እኮ ነገሩ ልክ ነህ እንደዚህ አይነት ስርአት አልበኝነት መማር የለበትም »
« ሆስፒታል መሄድ ነው የምፈልገው ቅድሚያ አናቴ ውስጥ ያሉት ነገሮች ሳይበጠበጡ አልቀረም » መኪና ውስጥ ቀድሜው ገባው « በፈጣሪ ቸርነት ነው ለሁለት አለመከፈሉ ጭንቅላትህም ግን ደምህ ከጭንቅላትህ ብቻ ነው ይሄ ሁሉ » እሱም ተከትሎኝ እየገባ መኪናውን አስነሳው
─── ⪩⪨ ───
« ምን አይነት የተረገመ ቀን ነው » ከስንት ጥበቃ ቡሀላ የጠራሁት ታክሲ መጣልኝ « ስንት ሰአት እንደጠበኩህ ታውቃለህ » እየተነጫነጭኩ በሩን ከፍቼ ገባሁ
« ይቅርታ የእኔ እህት ትንሽ መንገድ crowded ሁኖ ነው »
« ወደ ፓራዳይዝ አፓርትመንት ውሰደኝ
« ዛሬ ስራ የለም እንዴ ? ወይስ እረፍት ነሽ ?» በከፊል መንገዱን በከፊል እኔን እያየ « የለሊት ፈረቃ ነበርኩኝ እረፍት ነኝ አሁን ደክሞኛል ብዙ ጥያቄ አትጠይቀኝ » ለመተኛት ወንበሩ ላይ እየተመቻቸው ስልኬ ጠራ
📞 ሄሎ አንቺ ጉደኛ ማታ ምንድነው ያደረግሽው
📞 ሰላምታ አይቀድምም እንዴ ደሞ ምን አደረገች አሉ
📞 ኧረ ምን ያልተባለ አለ ሰውዬው ይኸው ሊያብድ ነው ታውቂያለሽ ተቀናቃኝሽ ደሞ ከጎኑ ሁና እያራገበች ነው እሳቱ በደንብ ትቀጣጥሏል
📞 ኧረ ተያቸው የፈለጉትን ያድርጉ እኔ ደክሞኛል ወደ እቤት እየሄድኩ ነው ማታ እመጣለሁ
📞 ደክሞኛል ትያለሽ እንዴ ያንን የተከበረ ሰው እንደዛ አዋርደሽው
📞 የምን የተከበረ ነው ማንን ነው ያዋረድኩት
📞 ዶ/ር ዛቪያርን እኮ ነው የፈነከትሽው
📞 ዛቪያር ይሄ ነው እንዴ እኔ መች አወኩኝ ግን ደግ አደረኩት ፀባይ የለውም ለማንኛውም ማታ ሁሉንም እናወራለን
📞 ሆ አንቺ ቀልጂ ጭራሽ ደግ አደረኩት እስከ ማታ ስራሽ ላይ የመቆየት እድል ካገኘሽ እናወራለን በይ ቻው
« ደርሰናል » አለኝ አስፓልቱ ዳር መኪናውን አቁሞ ከመኪናው ወረድኩኝ « ማታ እንዳታረፍድ ቶሎ ና » አልኩት እና በሩን ዘግጄ ወደ ህንፃው ገባሁ አሳንሰሩ ተበላሽቷል ተብሎ ይኸው ስንት ጊዜያችን በደረጃ ስንወጣ እኔስ ቅርብ ነኝ እላይ ላሉት ሳስበው ግን ዝግንን ይለኛል ፈጠን ፈጠን ብዬ ደረጃውን ወጣሁት እኔ ብሎክ ላይ ስደርስ ከቦርሳዬ ውስጥ የበሬን ቁልፍ አውጥቼ ከፈትኩት
ልምዴ ነው ወደ ስራ ከመሄዴ በፊት ቤቴን ፅድት አድርጌ ነው የምሄደው ስመለስ ድስ ብሎኝ ነው እረፍት የማደርገው በልቤ ድፍት አልኩ አልጋዬ ላይ
─── ⪩⪨ ───
« ምንም ጉዳት የለውም እራስ የማዞር ስሜቱም አሁን ይተውሀል እረፍት አድርግበት » እቃዎቹን ሰብስቦ ብድግ አለ « ዶክተር እናመሰግናለን እዚህ ድረስ መተህ ስለተባበርከን » እስከ በሩ ድረስ ተከትሎ ሸኝቶት ተመለሰ
« ኒያዝ ግን እንደ ትላንት ማታ በህይወቴ ተዋርጄ አላውቅም የምር በህይወቴ » የያዘውን አፕል እየገመጠ « አጋጣሚ ነው ያቺ የተንቀለቀለች ልጅ ነች እኮ ዙሩን ያከረረችው ምላሷ ከቁመቷ በላይ ነው የፈጣሪ ያለህ » ሶፋው ላይ እየተቀመጠ
« የሷን ጉዳይ ለእኔ ተወው ዋጋዋን ነው የምሰጣት እቅዶቼን አበላሸቻቸው » ከተኛውበት ቀና ብዬ ተቀመጥኩኝ እና ከፍራፍሬዎች ውስጥ አፕል አነሳው
« ምን ልታደርጋት ነው ቀለሟ የኛው ሰው እንደሆነች ያስታውቃል የለበሰችው ዩኒፎርም ላይም የሆቴሉ ማናጀር እንደሆነች ይናገራል »
የቀሩት ስን ቀናት ናቸው እዚህ ሀገር ለመቆየት ?»
« 4 ወይም 5 ቀን ቢሆን ነው የቀረን ምን እያሰብክ ነው አንተ እ ... ምን ልታደርግ ነው » ይበልጥ ወደ እኔ ዙሮ ሀሳቤን ለማዳመጥ እንዲመቸው
« ምንም አላደርግም የቀሩትን 5 ቀናት በእኔ ቁጥጥር ስር ትሆናለች እንግዲህ ብዙ ልምድ ይኖራታል የማስጎብኘት እና ይቺን ውብ ሀገር ብታስጎበኘንስ ምን ይመስልሀል ?» አልኩት « አሪፍ ሀሳብ ነው ለሷም ጥሩ እውቀት ይሆናታል እንዴት እንግዳ ትሪት እንደሚደረግ እናስተምራታለን ያው መፈንከቷን ብታቆም » ሁለታችንም ተሳሳቅን « አዎ ጉብኝታችንን ስንጨርስ የጣልኩባትን ክስ አነሳላታለሁ እሷም ወደ ስራዋ ትመለሳለች
« ደሞ ሳልነግርህ አንድ ስልክ ተደውሎልኝ ነበር እና እራት ግብዣ ዶክተር ዛቪያርን የሚል መልእክት የያዘ ጥሪ ነው » እና ምን ትላለህ ?
« ኧረ ይቅርብኝ በዚህ ሁኔታዬ እንዴት ነው እራት ግብዣ ላይ የምገኘው አይመቸውም ምናምን ብለህ አስተባብለው
« እሺ እንዳልክ በቃ እረፍት አድርግ ብሎሀል ዶክተሩም » ብድግ አለ ከተቀመጠበት
« ኒያዝ » አልኩት « እ ..» ፊቱን ወደ እኔ እያዞረ
« ዲያሪውን አቀብለኝ » አልኩት ወደ ተደረደሩት ወረቀቶች እየጠቆምኩት
« እረፍት እንድታደርግ እኮ ነው የተነሳውልህ » ብሎ ሰጠኝ
« የእኔ እረፍት እኮ እሱ ነው እያወክ » ተቀበልኩት እሱም ፈገግ ብሎ ምንም አላለኝም ወደ ክፍሉ ሄደ ።
የመጀመሪያውን ገፅ ስገልጠው
« ራዒና »
ትልቅ ቀን ነው ዛሬ ለ8 ወራት ሲካሄድ የነበረው የኳስ ግጥሚያ የፍፃሜ ውድድር የሚካሄድበት ቀን ነው 11 ክፍል ተማሪዎች ከ 12 ክፍል ተማሪዎች ጋር የሚካሄደው ውድድሩ ነው ተጋጣሚ ቡድኖች ልብሶቻቸውን ቀይረው እያሟሟቁ ነው በሜዳው ዙሪያ ሁሉም ተማሪ የሚደግፈውን ቡድን ለማየት ቦታ ቦታቸውን ይዘዋል ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ አስተማሪዎቹን ጨዋታውን ለማየት በሜዳው ተሰይመዋል የትምህርት ቤቱ ምክትል ዳይሬክተር መሀል ዳኛ ሲሆን ሌሎች በዳኝነት ቦታ የተሰየሙ መምህራን አሉ በትምህርት ቤት ውስጥ የሚኒሚድያ ተጠሪ የሆነው መምህር ሚኒ ሚዲያውን እንደ ኮሚታተር ተቆጣጥሮታል ስለ ተጨዋቾች እንዲሁም አሰላለፋቸው ሰፊ ዘገባ የሰጠ ነው ።
በዳኛው ፊሽካ የጨዋታው መጀመር ተበሰረ ሁሉም የሚደግፈውን ቡድን የሚያበረታታ ነገሮች እየተናገሩ መጮሀቸውን ተዪያዙት ጨዋታው እየደራ ነው
« ኦ የ 11 ክፍል ተማሪዎች አልተቻሉም የሚገርም ብቃት እያሳዩን ነው እንደሚታወቀው እስከዛሬ ብዙ ጨዋታዎችን በማሸነፍ የምናውቀው የ 11 ክፍል ተማሪዎች ቡድን መሀል ሜዳውን ተቆጣጥሮታ ል አሊ በረዥሙ ኳስ አቀበለው መርሊን መርሊን መርሊን ኳሱን ይዞታል ጎልልልልልልልልልልልልልልል ጎል መርሊን የመጀመሪያውን ጎል በ 15 ደቂቃዎች ውስጥ አስቆጠረ አጃኢብ ነው »
11 ክፍል ሲደግፉ የነበሩ ተማሪዎች በጩኸት እና በፉጭት ዘለሉ የቡድኑ አባላትም እየሮጡ መርሊን ላይ ተደራረቡበት እሱ ግን ከዚህ ሁሉ ጓጓታ መሀል እሷን በአይኖቹ እያማተረ ፈለጋት ሁሌም ከምትቆምበት ቦታ ሁና እንደሁሌዋ እየተመለከተች ነበረ ከዛ ቡሀላ ጫጫታ መሀል የእሷ እይታ ልቡ ላይ ትልቅ ደስታ ፈጠረለት
┎┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┒
ይቀጥላል
┖┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┚
ещё
15
0
2 2 ноя, 19:56
. ╔═══ ೋ 𔘓 ೋ ═══╗
𝙼ҽɾℓỉɳ
ፀሐፊ « 𝙰ϝ𝚗α𝚗 »
╚═══ ೋ 𔘓 ೋ ═══╝
. ━─━─ 𓍯 ─━─━
ραɾƚ 0:02
━─━─ 𓍯 ━─━─
እራሱን ስቶ ወደቀ ቶሎ ብዬ ልጅቷን ሳያት እስትንፋሷ አለ ግን ራሷን ስታለች ከጎና ከወደቀው ቦርሳዋ ውስጥ ስልኳን አውጥቼ ለፓሊስ ደወልኩኝ በአቅራቢያችን የነበሩት ፓሊሶች ወዲያው በቦታው ደረሱ ሶስታችንንም ወደ ፓሊስ ጣቢያ ይዘውን ሄዱ እኔ በገጠመኙ እጆቼ ይንቀጠቀጣሉ። እሷም ስለነቃች ቃሏን እንድትሰጥ ከእኔ አጠገብ ተቀመጠች
« ምን ተፈጥሮ ነው ?» አለችኝ
« ውስጥ ያለው ሰውዬ የሆነ ነገር ሊያደርግሽ ሲል ደርሼ እሱን በጠርሙስ መታሁት እና ፓሊስ ጋር ደወልኩ
« ምን እኔ ምን ሆኜ ነው እንዴ ጓደኞቼስ የት ሄዱ ?»
« የተፈጠረውን አታስታውሺም እንዴ እኔ የመዋኛው ገንዳ ጋር ወድቀሽ እሱ ደሞ እላይሽ ላይ ነበረ ይሄን ነው ያየሁትም የደረስኩበትም
─── ⪩⪨ ───
እራሴን ወጥሮ ይዞኛል የለበስኩት ነጭ ሸሚዝ በደም ተጨማልቋል በተሰጠኝ በረዶ እናቴን እያሸው ከመርማሪው ፊት ለፊት ወንበር ተቀምጫለሁ
👮♂ « አቶ ዛቪያር በቅድሚያ እዛ ቦታ ላይ ምን ይሰራሉ ?ብሎ ጠየቀኝ ስለ ራሴ ብዙ መረጃዎችን ከመዘገበ ቡሀላ
« የድርጅታችን 20 አመት ክብረ በአል ነበር ለዚሁ ፕሮግራም ነበረ የተገኘውት »
👮♂ « እሺ ታድያ ሁሉም እንግዶች ከሄዱ ቡሀላ እርሶ እዛ ምን ይሰራሉ »
« ሁኔታዎችን እያየሁ ነበረ ድንገት የሆነች እንስት መታ እጄን ያዘችን በጣም መጠጥ ጠጥታ ስለነበረ በስትክክል መራመድ ቀርቶ መቆም አቅቷት ነበረ ከዛ ራሷን ሳተች »
👮♂ « እሺ ከዛስ ምን ተፈጠረ ?» በጥሞና ነበር የሚያዳምጠኝ
« ከዛ ዶክተር ስለሆንኩ ሁኔታዋ ገብቶኝ ቀስ ብዬ ቀጥ አድርጌ አስተኛዋት እና ልቧን ጫን ጫን ስልላት እንዳለ የጠጣችው ወጣ ከዛ በቀበቶዬ ሆዷን አጥብቄ ይዤ እንዲወጣላት አደረኩኝ በዚህ መሀል ነው ድምፅ ሰምቼ ብድግ ስል አናቴ ላይ አንድ ነገር ያረፈብኝ ከዛ ቡሀላ የተፈጠረውን አላስታውስም ስነቃ ፓሊስ ጣቢያ ውስጥ ነኝ » አልኩት
👮♂ « እሺ ለዛሬ እዚህ ማደር ግዴታ ሁኔታዎች ተጣርተው ነፃ ከሆኑ በነፃ ይለቀቃሉ » ብሎኝ ተነስቶ ውጣ
« ለአንድ ቀን ጥዬህ ብሄድ እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ ትገባለህ ? » አለኝ መርማሪው ከመውጣቱ በሩን ከፍቶ እየገባ
« አልቻልኩም ራሴን በጣም አሞኛል » ወንበሩ ላይ ወደ ዃላ ተደግፌ ተቀመጥኩ
« ይሄ ሁሉ ደም ምንድነው ተጎድተሀል እንዴ ቆይ ምንድነው የተፈጠረው ውጪ እኮ ልጅቷን ሊደፍራት ነበር ብላ ቃሏን የሰጠች የእይን እማኝ ምስክር አለች »
ቀስ ብዬ እይኔን ገለጥኩ « የምን መደፈር ነው ልጅቷ እርዳታ ያስፈልጋት ነበር እርዳታ አደረኩላት በቃ ከዛ ድምፅ ሰምቼ ዞር ስል አናቴ ላይ የሆነ ነገር አረፈብኝ
« እሺ አሁን እንዴት ነህ cctv ካሜራዎች ስላሉ ማስረጃ እውነታው ይታወቃል »
« ደህናነኝ አታስብ ትንሽ ራሴን ብቺ ነው ያመመኝ » አልኩት በድጋሜ በረዶውን አናቴ ላይ እያደረኩኝ
« እዚህ ውስጥ አሁን ምንም ላደርግልህ አልችልም እኔ ውጪ ያለውን ጉዳይ እጨርሳለሁ »ብሎኝ ወጣ ።
─── ⪩⪨ ───
« ሆቴል ውስጥ ካሜራዎች አሉ ስለዚህ መታየት አለበት » የሚል የክርክር ድምፅ ከክፍሉ ውጪ ይሰማል። እኔ ባደረኩት ድርጊት በጣም እርግጠኛ ነበርኩኝ
👮♂ « ቃልሽን ሰተሽ ስለጨረሽ አሁን መሄድ ትችያለሽ አለኝ » ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ከቢሮ ስወጣ ግጥምጥም አልን « ይቺ ነች የአይን እማኝ ተብየዋ » አለ በንቀት እያየኝ
« በአይኔ ያየሁትን ነው የመሰከርኩት ልጅቷን ሊደፍራት ሲል በአይኔ በብረቱ ተመልክቻለሁ አለቀ » በንዴት ነበር የተናገርኩት
« ተናግረሽ ሙተሻል ምን ትመስላለች ይቺ አይጥ »
« ሲጀመር አንተም ተባባሪ ነህ መሰል እንደዚህ የሚያንጨረጭርህ » አልኩት ፈገግ ብዬ
« ሴት ነሽ ብዬ ዝም ስልሽ አናቴ ላይ ትወጪያለሽ እንዴ ድንጋይ ራስ በጥፊ እንዳልጥልሽ እዚ »
👮♂ « እባካችሁ ተረጋጉ አትጨቃጨኩ ሰዎች እየረበሻችሁ ነው መረጃዎች እየተጣሩ ነው እውነቱ ይወጣህ አሁን አረፍ አረፍ በሉ » አለን እሱን ጎትቶ ወደ መቀመጫ እየወሰደው እኔም መቀመጫው ሊይ በጫፍ በኩል ተቀመጥኩኝ ሰአቱ 12:00 ሆኗል ነግቷል ፓሊሶች ብዙ ሰዎችን ወደ ፓሊስ ጣቢያ ይዘው ይገባሉ አንዳንዶች በሱስ ራሳቸውን ስተዋል ምንም ቢዪደርጓቸው አይሰሙም በተለይ ሴቶች ይብሳሉ ከወንዶች
በጣም ርቦኝ ስለነበረ ውስጥ ከሚያስተናግደው ልጅ እርጎ እና ብስኩት ገዛው ። ከምርመራ ክፍሉ ውስጥ ጭንቅላቱን እያሻሸ ከፓሊሱ ዃላ ተከትሎ ወጣ ።
👮♂ « ሙሉ መረጃ ከሆቴሎ ወደ እኛ ተቋም ተልኳል በምስሉ ላይ እንደሚታየው ለልጅቷ እርዳታ እያደረገላት እንደነበረ በግልፅ ይቲዪል ልጅቷም ምንም አይነት ቅሬታ ስላላቀረበችበት በነፃ ተለቋል » አለ
የጎረስኩት እና የተጎነጨውት እርጎ ከጉሮሮዬ አልወርድ አለ « ማለት ምን »አልኩኝ እየተንተባተብኩ
« እሺ የእኛ ምስክር በአይንሽ በብረቱ ነው ያየሽው እንዴ ይመስለኛል አይንሽ ብረት የለውም ለማንኛውም ለዚሁ ሁሉ መንዛዛት ሀላፊነት ትወስጃለሽ እሺ » አለሽ የተንኮል ፈገግ እያለ
ምንም መልስ አልሰጠውትም አንገቴን ደፍቼ ዝም አልኩ ጉዳት ያደረስኩበት አንድ ቃል ሳይተነፍስ የዚህኛው መንጨርጨር ነው ያልገባኝ ምን አይነት አሽቃባጭ ሰው ነው አልኩ በውስጤ ጠጋ ብዬ ወደ እሱ « ይቅርታ አለቃዬ በሰአቱ እኔ የመሰለኝ አደጋ እያደረስክባት ነው እንጂ ህይወቷን ለማትረፍ እየታገልክ እንደነበረ አልገባኝም በጣም ይቅርታ » አልኩት ድምፄን ልስልስል እና ልምምጥ በሞላበት መንገድ
« አይ ችግር የለውም አጋጣሚ ነው ይፈጠራል ይቅርታ አድርጌልሻለሁ ግን ከሆቴሉ አስተዳደር ጋር ያንቺን ጉዳይ የምጨርሰው እንደዚህ በቀላሉ ዝም አልልሽም » ብሎ ጥሎኝ ሄደ
ረጋ ያለ ነው ከእዚህኛው ይሻላል ብዬ ብጠይቀው ጭራሽ ይሄ ባሰ ከስራዬ ሊያስባርረኝ ነው እንዴ ሮጥ ብዬ ሂጄ ከፊቱ ቆምኩ « እባክህ እንደዚህ አታድርግ ከስራዬ እባረራለሁ ሌላ የፈለከውን ጠይቀኝ አደርግልሀለው እባክህን ጌታዬ »
« እሺ ላደረሽብኝ ጉዳት ጊዜዬን ለገደልሽብኝ እንዲሁም ለተጉላላሁበት 1million $ ካሳ ትከፍይኛለሽ ?» አለ
« እ » ጆሮዬ መስማቱን ተጠራጠርኩ
┎┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┒
ይቀጥላል
┖┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┚
ещё
22
0
1 1 ноя, 20:29
Продолжить анализ этого канала
- История роста подписчиков
- Просмотры и охваты публикаций
- Кто упоминает канал и кого упоминает он
- Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней