Аналитика Telegram-канала
Подписчики
261
Охват за 24 ч
15
ER за 24 ч
5,75%
Публикаций
197
Динамика подписчиков
7 дней
30 дней
6 месяцев
Больше
5 ноя8 ноя11 ноя
Показаны последние 7 дней
Больше истории →
Охваты публикаций
09.1109.1110.1110.1111.1111.11
3
Средний охват
6
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале
Больше статистики →
Упоминания
106
Упоминаний
102
Из них репостов
2
Каналов
15
Упоминаний за 90 дней
14
Из них репостов
1
Каналов за 90 дней
Последние посты
3 из 197 2 из 197ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፤ ጌታ እግዚአብሔርን መጠጊያዬ አድርጌዋለሁ፤ ስለ ሥራህም ሁሉ እናገር ዘንድ። መዝሙረ ዳዊት 73:28
✍️ዓለም ማለቂያ በሌለው ሩጫ፣ በሚያደነቁር የሐሳብ ውዥንብር እና ትኩረታችንን በሚሰርቁ ሁኔታዎች የተሞላ ነው። በየዕለቱ ከፊታችን የሚደቀኑ ፈተናዎች፣ የኑሮ ውጣ ውረዶች እና የነገ ስጋቶች ልባችንን ይወጥሩታል። ከዚህ ግርግር መሃል ቆም ብንል፣ ነፍሳችን እውነተኛ ዕረፍት የሚሰማት የት ነው? ስንል እንጠይቃለን። መዝሙረ ዳዊት 73:28 ላይ ባለቤቱ አስራ አንደኛው ሰዓት ላይ ሆኖ እንዲህ ይላል፡- ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፤ ጌታ እግዚአብሔርን መጠጊያዬ አድርጌዋለሁ፤ ስለ ሥራህም ሁሉ እናገር ዘንድ። ይህ ቃል በቀላሉ የሚነበብ አይደለም፤ በህይወት ማዕበል ውስጥ ለተቸገረ ነፍስ የሚሆን የሕይወት ተስፋ ነው እንጂ።
ሰዎች በሕይወታቸው ውስጥ መፅናናትን ለማግኘት ብዙ መንገዶችን ይሞክራሉ። በሀብት፣ በዝና፣ በሰው ድጋፍ ወይም በቁሳቁስ መጠጊያ እንፈልጋለን። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል ይላል። ቃሉ ይሻለኛል ማለቱ ከሌሎች አማራጮች ተሻለ ማለት ብቻ አይደለም፤ ከዚህ ውጭ ሌላ እውነተኛ አማራጭ የለም ማለቱ ነው። ከፈጣሪ ጋር ያለን ግንኙነት ሲጠበቅ፣ የዓለም ጫጫታ ደብዛውን ያጠፋዋል። በእግዚአብሔር መቅረብ ውስጥ ፍርሃት ይጠፋል፣ ጥርጣሬ ይተናል፤ በምትኩም ጥልቅ የሆነ ሰላም በልባችን ላይ ይሰፍራል።
በአደገኛና አሰልቺ በሆነው ዓለም ውስጥ እግዚአብሔርን መጠጊያ ማድረግ ማለት ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ በእርሱ እጅ መተው ማለት ነው። ነፋሱ ሲነፍስና ማዕበሉ መርከባችንን ሲያንገላታው፣ በዐለት ላይ የተመሰረተ መጠጊያ ማግኘት የድል ምስጢር ነው። ዳዊት ጌታ እግዚአብሔርን መጠጊያዬ አድርጌዋለሁ ሲል፣ በዙሪያው ያሉ ሰዎች በሐሰተኛ መሠረት ላይ ሲቆሙ እርሱ ግን የማይናወጠውን አምላክ እግዚአብሔርን መርጧል። መጠጊያችን እግዚአብሔር ሲሆን፣ የውጭው ዓለም ውዥንብር ምንም ሊያደርገን አይችልም። እርሱ ምሽጋችን፣ ብቃታችን እና ጋሻችን ነው።
የዚህ አስደናቂ ጥቅስ የመጨረሻ ክፍል ደግሞ ሌላ ጥልቅ እውነትን ያሳየናል፤ ስለ ሥራህም ሁሉ እናገር ዘንድ። ከእግዚአብሔር ጋር መቅረብ እና በእርሱ መጠለል ዝም ብሎ መቀመጥ አይደለም፤ ይልቁንም በእኛ ሕይወት ውስጥ ያደረገውን አስደናቂ ሥራ፣ ያዳነንበትን ኃይልና ያሳየንን ቸርነት ለዓለም መመስከር ነው። የእግዚአብሔርን ርህራሄና ድንቅ ሥራዎች የቀመሰ ሰው ዝም ማለት አይችሉም። በህይወታችን ውስጥ ያጋጠሙንን የጨለማ ጊዜያት ያበራውን የእርሱን ብርሃን ለሌሎች ማካፈል የክርስቲያን ህይወታችን ማዕከል ነው።
ዛሬ ሕይወትዎ ከብዶት ሊሆን ይችላል? ዙሪያዎትን ሲመለከቱ መፍትሔ የጠፋ ይመስልዎታል? መልሱ ቀላል እና ቅርብ ነው። ሩጫውን ትተው ወደ ፈጣሪዎ ይቅረቡ። ሕይወትዎን ለእርሱ አስረክቡ፤ መጠጊያዎ ያድርጉት። በጸጥታና በእርጋታ ከእርሱ ጋር ጊዜ ሲያሳልፉ፣ ነፍስዎ እውነተኛ ዕረፍት ታገኛለች። ያን ጊዜ የፈጣሪን ታላቅነትና ድንቅ ሥራዎች በደስታና በምስጋና ማወጅ ይችላሉ።
✍️ ተመስገን ብርሃኑ (2/3/2019)
#መልካም_ዕለተ_ረቡዕ!
ещё
1
0
11 ноя, 07:32
ещё
3
0
11 ноя, 07:32
ещё
6
0
10 ноя, 08:43
Продолжить анализ этого канала
- История роста подписчиков
- Просмотры и охваты публикаций
- Кто упоминает канал и кого упоминает он
- Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней