Аналитика Telegram-канала
Подписчики
2 178
Охват за 24 ч
308
ER за 24 ч
14,14%
Публикаций
791
Динамика подписчиков
7 дней
30 дней
6 месяцев
Больше
23 ноя26 ноя29 ноя
Показаны последние 7 дней
Больше истории →
Охваты публикаций
26.1127.1127.1127.1128.1128.11
73
Средний охват
176
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале
Больше статистики →
Упоминания
2
Упоминаний
1
Из них репостов
2
Каналов
0
Упоминаний за 90 дней
0
Из них репостов
0
Каналов за 90 дней
Последние посты
3 из 791 2 из 791ይቅርታ የሚያደርግ ሰው የተሰራበትን በደል ክብደት አይደለም የሚያሳንሰው። ጭርሽ የተሰራበትን በደል መጠን በእጥፍ ነው የሚጨምረው።
ይቅርታ ስታደርጉ ግፉን የበለጠ ክፉ እና አረመኔ ታደርጉታላችሁ። ምክንያቱም ያ ግፍ ይቅርታ ማድረግ የሚችል፣ ግፍ የሰራበትን ሰውን ማፍቀር የሚችል ሰው ላይ ተፈጽሟልና። ያ ግፍ ተራ ሰው ላይ የተፈጸመ አለመሆኑን ይቅርታ አድራጊው በይቅርታው አሳየ። በዚህም የግፍ አድራጊውን አረመኔነት ጭራሽ ይበልጥኑ ገለጠ። ከዛ ሁሉ በኋላ እንኳን ይቅር ማለት የሚችልን ሰው በድሏል’ና።
ещё
47
1
28 ноя, 22:50
“እውነት ኃይል ነው። ግን ያን ማየት የሚችሉት ጥቂቶች ብቻ ናቸው ምክንያቱም እውነት በስቃይ እና ስደት ውስጥ ስለሆነ እና እውነት እስከሆነ ድረስ መሸነፍ የግድ ስላለበት።
የሚገርመው ግን አሸናፊ ሆኖ ሲወጣ ብዙዎች ይቀላቀሉታል።
ለምን? እውነት ስለሆነ?
በፍጹም።
ስለእውነትነቱ የተቀላቀሉት ቢሆን ኖሮማ ያኔ በስቃይ እና በስደት ላይ እያለም ይቀላቀሉት ነበረ። ስለዚህ የተቀላቀሉት እውነት ኃያል ስለሆነ አይደለም።
ነገር ግን የተቀላቀሉት አሁን ሌሎችም ተቀላቅለውት ስልጣንን ስለያዘ እንጂ።” ኪርከርጋርድ
ещё
54
0
4 28 ноя, 20:05
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰይጣን ተፈትኖ፤ ፈተናዎቹን ያለፈው በቃለ እግዚአብሔር እውቀቱ ነው።
ማለትም ቃለ እግዚአብሔርን ጠቅሶ ነው ሰይጣንን ያባረረው። ቃሉን ለመከራከር ወይም ልክ ይሆን አይደለም በሚል አይደለም የጠቀሰለት። ማለትም “ቃሉ እኮ ግን እንዲህ ይላል” በሚል ሰይጣንን ለክርክር በሚጋብዝ ሁኔታ አይደለም የጠቀሰለት። ቃሉ ከሚለው ውጪ ፈጽሞ ንቅንቅ አልልም በሚል መንፈስ እንጂ የጠቀሰለት። እንዲህ አድርግ ሲለው ሰይጣን፤ “ቃሉ እንዲህ ስለሚል አላደርግም” ነበር ብሎ የሚመልስለት። ስገድ፣ ውደቅ፣ ብላ ሲለው “ግን እኮ ቃሉ እንዲህ ይላል ፥ ታዲያ ይሄ ምን ይመስልሃል?” በሚል ክፍተት አላናገረውም። ይልቁንስ ቃሉ እንዲህ ስለሚል አላደርግም በሚል እንጂ። ይሄ የሞራል መሠረቴ እውቀት ሳይሆን መታዘዝ ነው የሚል ነው። ቃሉ ስላወቀ ብቻ ሳይሆን ለቃሉ ስለሚታዘዝም ጭምር እንጂ። እውቀቱን ብቻ አይደለም የገለጠው። ከዚህ የቃለ እግዚአብሔር እውቀት ውጪ ያለን እውነት ለመስማት ራሱ ፈቃደኛ አለመሆኑን እንጂ። በዚህም እውቀቱ ለመታዘዝ ብቻ እንደሆነ አሳየን። ማቴ 4 ፥ 1። ሉቃስ 4፥1።
በሰይጣን ተታላ የወደቀችው ሄዋን ግን እውቀቷ ለመታዘዝ ብቻ አልሆነላትም። ይልቁንስ ቃሉን በጥንቃቄ አለማወቋ ብቻ ሳይሆን፤ ከዛ ቃል ውጪ ያለ እውነት ካለም ለመስማት እና ለመከተል ፈቃደኛ መሆኗን ጭምር ነበር የገለጠችው።
ሌላኛው እውነት እስካሳመናት ድረስ ለመከተል ፈቃደኛ ነበረች። ስለዚህ የእባብን ሌላ ምልከታ እና እውቀት ደግሞ ለመስማት ፈቃደኛ ሆነች። ሄዋን ቃሉን በመጀመሪያ በጥንቃቄ አታውቀውም ነበር። ምክንያቱም ለሰይጣን የጠቀሰችለት ቃል እግዚአብሔር አምላክ ያላለውን ጭምር ነበር። ይሄም “ነገር ግን በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ፥ እግዚአብሔር አለ። እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ አትንኩትም።” ዘፍጥረት 3፥3። እግዚአብሔር አምላክ አትብሉ እንጂ አትንኩ አላለም። ዛፉን አትብሉ ነበር ያለው። አትንኩት ግን አላለም። ከዛም ከጌታችን በተለየ ልክ እንደ ሰይጣን እግዚአብሔርን እግዚአብሔር ብላ ብቻ ጠራች። እስከ ዘፍጥረት ሦስት ድረስ እግዚአብሔር አምላክ ተብሎ ሲጠራ የነበረው ፈጣሪ አሁን በሰይጣን አንደበት እግዚአብሔር ብቻ ተብሎ ተጠራ። እርሷም ያን ፈለግ ተከትላ እግዚአብሔር ብቻ አለች።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ቃሉን በአንድ ቦታ እንዳለ ሲጠቅስ እግዚአብሔር ከማለቱ ውጪ ያለው “ጌታ አምላክ” ብሎ ነበር አባቱን የጠራው። በነጠላ ስሙን አልጠራም። ጌታ እና አምላክ ብሎ እንጂ። ምንም እንኳን ሰይጣን እግዚአብሔር እንዲህ ብሏል እንዲህም አድርግ እያለ ለዛ የእግዚአብሔርን ስም ባላከበረ አጠራር እንዲጠራ ቢጋብዘውም።
ሄዋን ቃሉን ፍጹም ለመታዘዝ ብቻ አይደለም ያወቀችው። ሌላ እውነት ካለም ለመስማት ፈቃደኛ ነበረች። አዕምሮዋን እስካሳመነ ድረስ ሌላ እውነት ለመከተል ፈቃደኛ ነበረች። በዚህም ሌላ እውነት አመነች። የዘላለም ሞትም አመጣባት።
ጌታችን ግን ቃሉን ለመታዘዝ ብቻ ነበር ያወቀው። በዚህም በቃሉ ሰይጣንን ድል ነሳው።
የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ነገራችን ምርኩዝ፣ ጋሻ እና ጦራችን ነው። ያንን ካላወቅን ቀድመን ወድቀናል። ያወቅነውም ለአዕምሮ እውቀት ከሆነ አሁንም ከመውደቅ አንድንም። ያወቅነው ለመታዘዝ እና ለመታዘዝ ብቻ ከሆነ ግን ድል ማድረጊያችን ነው።
ещё
27
0
1 27 ноя, 21:53
Продолжить анализ этого канала
- История роста подписчиков
- Просмотры и охваты публикаций
- Кто упоминает канал и кого упоминает он
- Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней