Не попадитесь на накрученные каналы! Узнайте, не накручивает ли канал просмотры или подписчиков Проверить канал на накрутку
Прикрепить Телеграм-аккаунт Прикрепить Телеграм-аккаунт

Телеграм канал «Mohammed Seid - Miftah»

Mohammed Seid - Miftah
57
0
5
5
0
​🛠 Digital Skills | AI | Innovation
📢 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዜናዎች እና መፍትሄዎች።
👇 ፌስቡክ ላይም ያግኙኝ፡
https://www.facebook.com/share/1ANudUpgYu/
Подписчики
Всего
2 643
Сегодня
+3
Просмотров на пост
Всего
597
ER
Общий
22.6%
Суточный
12.18%
Динамика публикаций
Telemetr - сервис глубокой аналитики
телеграм-каналов
Получите подробную информацию о каждом канале
Отберите самые эффективные каналы для
рекламных размещений, по приросту подписчиков,
ER, количеству просмотров на пост и другим метрикам
Анализируйте рекламные посты
и креативы
Узнайте какие посты лучше сработали,
а какие хуже, даже если их давно удалили
Оценивайте эффективность тематики и контента
Узнайте, какую тематику лучше не рекламировать
на канале, а какая зайдет на ура
Попробовать бесплатно
Показано 7 из 57 постов
Смотреть все посты
Пост от 26.10.2026 15:33
55
0
0
ወጣት ሆይ!

እጅህ ላይ ያለው ጉልበት፣ ጊዜና አቅም ተመልሶ የማይመጣ ውድ ሀብት ነው።

ዛሬ ራስህን በእውቀት፣ በጥሩ ስነ-ምግባርና በጠንካራ ክህሎት ከገነባህ፣ ነገ የምትቆምበት ማማ የላቀ ይሆናል።

ጊዜህን በማይረቡ ነገሮች ከማባከን ይልቅ፣ ህልምህን ወደ እውነት ለመቀየር ዛሬን በአግባቡ ተጠቀምበት!
👏 4
Пост от 25.10.2026 16:47
76
0
0
ማስታወቂያዎች እኛን እያነበቡን ይሆን?
የድሮውን ማርኬቲንግ ዘመን ታስታውሳላችሁ? በአንድ የሬዲዮ ወይም የቲቪ ማስታወቂያ በሚሊዮን የሚቆጠርን ህዝብ “በጅምላ” ለማዳረስ ይሞከር ነበር። የእኛ የተለየ ፍላጎት፣ ምርጫም ሆነ ስሜት ቦታ አልነበረውም።

ነገር ግን የዲጂታል ዘመን ሁሉንም ነገር ቀየረው።

እኛ ፌስቡክ እና ቲክቶክ ላይ ስናሳልፍ የተውነው እያንዳንዱ “ላይክ”፣ ኮሜንት እና የቪዲዮ እይታ ተከማችቶ አርተፊሻል ኢንተለጀንስን (AI) ወለደ።
AI ደግሞ የእያንዳንዳችንን የባህሪና ልማድ በደንብ በማጥናት ማስታወቂያዎችን ልክ ለእኛ ብቻ ተለክተው የተሰፉ እስኪመስሉ ድረስ እጅግ ግላዊ (Hyper-Personalized) አደረጋቸው።
አሁን ደግሞ በስልካችን ብቻ ሳይሆን ወደፊት በአካል በምንሄድባቸው ቦታዎችም ጭምር በምናባዊ ቴክኖሎጂዎች (XR) ታግዞ ፍላጎታችንን በቅጽበት እያነበበ የሚያስተናግድበት ጊዜ ሩቅ አይደለም።

አሁንም ነገሮች ከዚህም በላይ ይበልጥ ይራቀቃሉ ተብሎ ይገመታል የኮግኒቲቭ ሳይንስ ውህደት! ኮግኒቲቭ ሳይንስ ይበልጥ አድጎ የ Neuromarketing ዘመንን ይወልድ ይሆን? ኢንሻአላህ አብረን የምናየው ይሆናል!
Пост от 25.10.2026 15:05
61
0
0
Artificial intelligence is getting ready for business, but are businesses ready for AI?
Пост от 24.10.2026 15:38
74
0
1
AI "ዛሬ ምን ላግዝህ?" ሲልህ ወይም ለስህተቱ "ይቅርታ" ሲጠይቅህ፣ ስሜት ኖሮት እያሰበ እንዳይመስልህ። ይህ Anthropomorphism ወይም ማሽኑን እንደ ሰው የማየት ስነ-ልቦናዊ እይታ ይባላል።
ከጀርባው ያለው እውነታ ግን የLarge Language Models (LLMs) ስልተ-ቀመር ነው። AI ቀጣዩን ተስማሚ ቃል የሚመርጠው በ Probabilistic Modeling እንጂ በማስተዋል አይደለም። "ይቅርታው" የሰውኛ ባህሪ ሳይሆን የData ስልጠናው ውጤት ብቻ ነው።
የቴክኖሎጂውን ውስንነትና አሰራር በትክክል መረዳት፣ ከAI ጋር የምናደርገውን መስተጋብር ይበልጥ ውጤታማ እና ምክንያታዊ ያደርገዋል።
#ArtificialIntelligence #DataScience #LLMs
Пост от 23.10.2026 16:14
61
0
0
ብዙ ጊዜ የሀገር መሪዎች ሲናገሩ የምንሰማው ስለ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ ወይም ዲፕሎማሲ ነው። ነገር ግን በጃፓን የሆነው ነገር ሙሉ በሙሉ የተለየ እና ለቴክኖሎጂው ዓለም ትልቅ ማሳያ ነው!

​የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሳናኤ ታካኢቺ (Sanae Takaichi) በPHP ላይ የተገኘውን አደገኛ የደህንነት ክፍተት በማህበራዊ ገጻቸው ላይ ለሕዝብ ያስተላለፉት አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ በጣም አስገርሞኛል።

የሳይበር ደህንነት (Cybersecurity) አሁን ላይ የቴክኒክ ሰራተኞች ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የብሔራዊ ደህንነት አካል መሆኑን እና የከፍተኛ ሀገር መሪዎችን ትኩረት የሚሻ ደረጃ ላይ መድረሱን ያሳያል!

📌 Telegram:
telemetr.me/miftahcode
​#TechNews #CyberSecurity #PHP
👍 1
Пост от 23.10.2026 10:30
135
1
1
አስቸኳይ የሳይበር ደህንነት መልዕክት 🚨

በመላው ዓለም ከ70% በላይ ድረ-ገጾችን (በተለይም WordPress, Drupal እና Joomla እና የውስጥ ሲስተሞችን) በሚያነቀሳቅሰው የPHP የሶፍትዌር እምብርት ላይ እጅግ አደገኛ ክፍተት (php2shell) ተገኝቷል። ይህ ክፍተት አጥቂዎች ያለ ምንም የይለፍ ቃል ሰርቨሮችን በቀጥታ እንዲቆጣጠሩ እና የመንግስት ውሂቦችን፣ የህክምና መዝገቦችን እንዲሁም የባንክ ዳታቤዞችን እና ሌሎች የግል ፣ የተቋም እና የመንግሥት መረጃዎችን እንዲዘርፉ ሙሉ በር የሚከፍት በመሆኑ፤ በሀገራችን የሚገኙ ድርጅቶች እና ተቋማት በአስቸኳይ የሚከተሉትን 3 ወሳኝ እርምጃዎች እንዲወስዱ እንመክራለን፦

1️⃣ የPHP ስሪትን በአስቸኳይ ማሻሻል (Patching)
ይህ አደጋ ሊፈታ የሚችለው በራሱ በPHP ሰርቨር ላይ በሚደረግ ማሻሻያ ብቻ በመሆኑ፤ የዎርድፕረስ አፕሊኬሽንን ወይም ፕለጊኖችን ማዘመን ብቻውን ዋስትና አይሆንም። ሰርቨሮችዎን በአስቸኳይ ወደሚከተሉት ደህንነታቸው የተጠበቁ ስሪቶች ያሳድጉ፦
✔️ PHP 8.5.12 ፣ 8.4.27 ፣ 8.3.36 ወይም 8.2.35 እና ከዚያ በላይ።
(ማሳሰቢያ፦ እንደ PHP 7.4 ወይም 8.0 ያሉ አገልግሎታቸው ያበቃ የቆዩ ስሪቶች ይፋዊ ማስተካከያ ስለማይደረግላቸው ሰርቨሩን ሙሉ በሙሉ ወደ አዲሱ ስሪት ማዛወር ግዴታ ነው)።

2️⃣ ድብቅ መግቢያዎችን መፈተሽ (Audit for Backdoors)
የአለም አቀፍ ተቋማት (እንደ Cloudflare እና Amazon ያሉ) ክፍተቱ ይፋ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የጥቃት ሙከራዎችን መዝግበዋል። ስለዚህ የደህንነት ማስተካከያውን ከመጫንዎ በፊት፤ አጥቂዎች ቀድመው ወደ ሰርቨርዎ የሰገሰጓቸው ድብቅ መግቢያዎች (Backdoors) መኖራቸውን በሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች በጥልቅ ያስፈትሹ።

3️⃣ ማሻሻል ወይም መዝጋት (Fix or Suspend)
እንደ አሜሪካው NSA እና የእንግሊዙ NCSC ያሉ ዓለም አቀፍ የደህንነት ተቋማት እንዳሳሰቡት፤ የደህንነት ማስተካከያውን (Patch) ወዲያውኑ መጫን የማይቻል ከሆነ፤ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑትን የውጭ መስመር ድረ-ገጾች እና ሲስተሞች ለጊዜው ሙሉ በሙሉ ከኢንተርኔት ላይ ማጥፋት (Offline ማድረግ) ተመራጭ እና አስተማማኝ የመከላከያ እርምጃ ነው።
Пост от 22.10.2026 16:19
85
0
0
AI ሁሉንም ነገር ያውቃል ብላችሁ ታምናላችሁ?

Artificial Intelligence (AI) ስንጠቀም ከሚገጥሙን ትልልቅ ፈተናዎች አንዱ "ቅዠት" (Hallucination) ሲሆን የAI ትልቁ ድክመት ነው።

​Hallucination ማለት AI እኛ ከሰጠነው ትእዛዝ (Prompt) ጋር በፍጹም የማይገናኝ፣ የተቀነባበረ ወይም የሌለ ሀሰተኛ መረጃ (ጽሑፍ፣ ኮድ ወዘተ) እንደ እውነተኛ አድርጎ ሲያቀርብልን ነው።

🔖​ስለዚህ ምን ማድረግ አለብን?
የፈለገውን ያህል የላቀ AI ቢሆንም፣ የሚሰጠንን ውጤት ከመጠቀማችን በፊት፡
☑️ ​በጥንቃቄ ማንበብ እና ማረጋገጥ
☑️ ​ዋናውን የመረጃ ምንጭ በSearch Engine like (Google) ፍለጋ ማጣራት
☑️​በሌሎች የAI ሞዴሎች (Cross-checking) ትዕዛዙን ማረጋገጥ
በእነዚህ መንገዶች የምናገኘውን መረጃ አስተማማኝነት መጨመር እንችላለን።

​💬 እናንተስ ከኤአይ ጋር በትብብር ስትሠሩ ያጋጠማችሁ የሚያስቅ ወይም የሚያስገርም "የ AI ቅዠት" አለ? ኮሜንት ላይ አጋሩን! 👇

​📌 ለበለጠ የቴክኖሎጂ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡
👉 telemetr.me/miftahcode
Смотреть все посты