Тарифы до −50% до 30.11
Аналитика Telegram-канала
Подписчики
315
Публикаций
98

Динамика подписчиков

7 дней 30 дней 6 месяцев Больше
22 ноя25 ноя28 ноя
Показаны последние 7 дней Больше истории →

Охваты публикаций

07.1107.1110.1110.1111.1111.11
9
Средний охват
11
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале Больше статистики →

Упоминания

1
Упоминаний
0
Из них репостов
1
Каналов
Нет примеров за последние 90 дней
Все упоминания

Последние посты

3 из 98 2 из 98
Фото
ещё
5 0 11 ноя, 15:40
እውነት መጽሐፍ ቅዱስ አሰልቺ ነው? ደባሪ ነው? ዛሬ ከረፈደም ቢሆን አንድ ልጥፍ አይቼ ነበር። የተወሰኑ ሰዎችም የራሳቸውን ምልከታ ልጥፈው አይቻለሁ። እኔ ሀሳቡን ላይ አልስማማበትም። ግን ቶሎ ምላሼን ለመስጠት ሳስብ፣ ማን ነህ አንተ?፣ ምን አገባ? የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎችም በአዕምሮዬ ተመላልሰው ሲያስቸግሩኝ። መልስ ካገኘሁላቸው በኃላ ነው። ምልከታዬን ላስቀምጥ የወደድኩት። በመጽሐፍ ቅዱስ አምናለሁ። የትምህርቴ፣ የአካሄዴ፣ የእምነቴና የአቋሜ ምንጭ ነው። በእኔና በሕይወቴ የመጨረሻ ባለሥልጣን ነው። በዚህም ምክንያት ሒሴን ለመስቀመጥ እገደዳለሁ። እንግዲህ የተነሳው ሃሳቡ ቃል በቃል እንዲህ ይላል፦ «የአለም ታላቁ መጽሐፍ ''መጽሐፍ ቅዱስ'' ያለ መንፈስ ቅዱስ ሲነበብ የዓለም አሰልቺና ደባሪ መጽሐፍ ይሆናል።» ይህን ያገራን ወንድም፤ ''Some one said it.'' ስላለ እንደው የሰው ሀሳብ ነው ብዬ ላልፈው ነበር። ግን ወንድሜ በሁለተኛ ልጥፉ ''እደግመዋለሁ'' ብሎ በፈረጅንኛ የምያምንበት ሀሳብ መሆን አስቀምጦልናል። የእግዚአብሔር ቃል [መጽሐፍ ቅዱስ] ሕይወትም መንፈስ ነው። መንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስን በምናነብበት ጊዜ አስተዋጽኦውን፣ እንዲሁም መንፈስ ቅዱስና መጽሐፍ ቅዱስ ያላቸውን አንድነትና ልዩነት በዚህ ልጥፌ ለማስረዳት አልደክምም። እውነት መጽሐፍ ቅዱስ አሰልቺ ነው? ደባሪ ነው? ለማን ነው አሰልቺ የሆነው? በርግጥ እውነት ነው፤ ብዙ አማኞች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ያለን ሕብረት የሳሳ ነው። ምናልባትም በዓመት ውስጥ ራሱ ለማየት የሚከብዳቸው ሰዎች ይኖራሉ፣ ግን መጠየቅ የምፈልገው ጥያቄ፦ አሰልቺ ነው ባዮች እነማን ናቸው? አንድ አማኝስ መጽሐፉ ''አሰልቺ ነው''ብሎ እንደሆን መንፈስ ቅዱስን አልተቀበለም ወይም መንፈስ የለውም ለማለት መብት አለን?! አመክንዮአዊስ ነው?! ችግሩ ከቋንቋው አለመግባባትና የተጻፈበትን ዓለማ ካለመረዳት ሊሆን አይችልም? ​ኢ-አማኞችና የሥነ ጽሑፍ ባለሙያዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት ይመለከቱታል? ​ መጽሐፍ ቅዱስ ከሃይማኖታዊ ይዘቱ ባሻገር የሰው ልጅን ታሪክ፣ ፍልስፍና እና የቋንቋ ጥበብ ከፍ አድርጎ የሚያሳይ ግዙፍ የሥነ ጽሑፍ ቤተ-መጻሕፍት ነው። ዓለማዊ ምሁራንና ጸሐፍት መጽሐፉን በውበት እና በታሪክ አንጻር ሲመረምሩት፦ ከታሪካዊና ቋንቋ አንጻር ጆርጅ ኦርዌል «1984» እና «የእንስሳት እርሻ» (Animal Farm) የተባለ ታዋቂ የፖለቲካ ልብ ወለድ መጻሕፍትን የጻፈ እንግሊዛዊ ጸሐፊና ጋዜጠኛ ነው። እንዲህ ይለናል " የኪንግ ጄምስ መጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋ (ቀላልነቱና ውበቱ) ለምዕራባውያን ሥነ ጽሑፍ እድገት መሠረት ነው" ሮበርት አልተር: (Robert Alter) የመጽሐፍ ቅዱስን የዕብራይስጥ ጽሑፎች በሥነ ጽሑፍና በውበት አንጻር በመተንተን የሚታወቅ ታዋቂ አሜሪካዊ የሥነ ጽሑፍ ምሁርና ተርጓሚ ነው። ጸሐፊዎቹ (የመጽሐፉ) ቃላትን በመምረጥና ስሜትን ከሐሳብ ጋር በማጣጣም ረገድ የነበራቸውን ከፍተኛ የቋንቋ ጥበብ ያደንቃል። ከግጥም ጥበብና ትይዩነት (Parallelism)፦ እንደ መዝሙረ ዳዊትና መክብብ ያሉ ክፍሎች በውስጣቸው የያዙት የሐሳብና የድምፅ ትይዩነት (Parallelism) የሰው ልጅን ጥልቅ ስሜት (ስቃይ፣ ደስታና ፍርሃት) ያለ አንዳች ማጣሪያ በግልጽ የሚያሳዩ የኪነ ጥበብ ውጤቶች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስን ከማንበብና ከመተንተን ባሻገር፣ በውስጡ ባለው የቋንቋ ሀብት፣ ዘይቤ እና ጥልቅ የሰው ልጆች ሥነ ልቦናዊ ነጸብራቅ መነጽር ማየት የሥነ ጽሑፍ አድማሳችንን እንደሚያሰፋው አያጠራጥርም። በመሆኑም ለማለት የፈለገውን በየዋህነት እንረዳው ወይስ በጭፍንነት እንቀበል? አላውቅም። ምንም ቢሆን መጽሐፍ ቅዱስ እንደዚህ መባል አይገባውም።(ጠብቆ ይነበብ)
ещё
10 0 11 ноя, 15:39
ለራስ ስብከት ለመጀመሪያ ጊዜ የሰበኩት አምስተኛ ክፍል እያለሁ ይመስለኛል። በዚያን ጊዜ በየትምህርት ቤቱ ደስ የሚል መንፈሳዊ መነቃቃት ተከስቶ ነበር፤ በሚገርም ሁኔታ በሆሳዕና ሁሉም ትምህርት ቤት ማለት ይቻላል የክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት (Fellowship) ተጀምሮ ነበር። ተጽዕኖው በጣም የጎላ ከመሆኑ የተነሳ "ወጣ ያለ ባህርይ ያላቸው ልጆች ጭምር መሳተፍ ጀምረው ነበር። ​ እንግዲህ ይህ ሕብረት በትምህርት ቤት ብቻ ሳይሆን በየሰፈሩም ይካሄድ ነበር። በየተራ ፕሮግራም እንመራ ነበር፤ መዝሙርና ስብከትም ይደርሰን ነበር። ​አንድ ቀን እጣው በእኔ ላይ ወደቀ። «ቀጣይ ሳምንት ጆሲ ይሰብካል» ተባልኩ። መንቀጥቀጥ ያዘኝ፤ የምገባበትም አጣሁ። «ኧረ ቀላል ነው ጆሲ፣ ጌታ ይረዳሃል» ብለው አበረታቱኝ። ​ቀኑ ማክሰኞ ነበር። ከማክሰኞ ጀምሮ እስከ ማክሰኞ ጥቂት ሰዓት ብቻ ነበር እንቅልፍ ወስዶኝ የነበረው። ያንን ሁሉ ምሽቶች ስጸልይ እንደነበር አስታውሳለሁ። ይገርማችኋል፤ ከዚያ ቀን በፊት ሰብኬ አላውቅም ነበር፤ እንዴት እንደሚሰበክም ራሱ አይገባኝም ነበር። በጣም ብፈራም እንኳን፣ በሰፈር ልጆች ፊት ፈርጥጬ ከምዋረድ የምችለውን መሞከር ነበረብኝ። ​ሐሙስ ቀን «እንደገባኝ ልሁን» አልኩና ተንበርክኬ ጸለይኩ፤ «የልብህን ተናገረኝ» አልኩት። ዓይኔን ስከፍት እንደ በርገር ዳቦ፣ መጽሐፉን ለሁለት ከፈልኩት፤ ኢሳያስ 61 ላይ ዓይኔ አረፈ። በደስታ ጮቤ ረገጥኩ! ​ ቀጥሎ ያደረኩት ነገር ቢኖር መስታወት ፊት ቆሜ ራሴን መስበክ ነበር። ሰው ሁሉ ከቤት መውጣቱን ጠብቄ ለራሴ ስብከት (ለራስ ስብከት) ማቅረብ ጀመረኩ። ​«ለራስ ስብከት» ሰሞኑን ፌስቡክ ላይ አንድ ጽሑፍ አይቼ ነበር፤ እንዲህ ይላል፦ «ሌሎችን ከመስበክህ በፊት ቃሉን ለራስህ ስበክ።» ​ እኔ ቀደም ሲል ያደረኩት ለመድረክ ዝግጅት ብቻ ነበር። ይህ አባባል የሚነግረን ግን ቃሉን ለራሳችን የመስበክን ልማድ ነው። ቃሉን ከራሳችን ጋር እየተጫወትን ማውራትንና ራሳችንን የማስተማርን ልማድ ነው። አስተማሪዎች ብቻ ከሆንን የቃሉ ባለቤት ደስ አይሰኝም። ለራስ ስብከት፣ ለራስ ትምህርት፣ ቃሉን የምናወራበት ጊዜ ያስፈልገናል። የምናውቀውን ቃል ማካፈልና ማዜም እንዴት ደስ ይላል! ​እንደዚህ ስል በአገልግሎቱ ላይ የተሰማራነውን ብቻ ማለቴ አይደለም፤ በእግዚአብሔር ቃል የሚያምን ሁሉ ይህ ልምምድ ሊኖረው ይገባል ብዬ አምናለሁ። ምክንያቱም በክፉ ቀን ለብቻችን ስንቀር አብሮን የሚቆየውና የሚረዳን ያ የምናውቀው ቅዱስ ቃል ብቻ ነው። ከቃሉ ጋር እንድንሰነብት ጸጋ ይብዛልን። ​___ ቅዳሜ ሲደርስ ግን በጣም ልበ ሙሉ ነበርኩ፤ ጥቅሱንም መሸምደድ ችዬ ነበር። ደግሜ ደጋግሜ በቃሌ ማለት ችዬ ነበር። ​ቀኑ ደረሰ፤ 11 ሰዓትም ሆነ። ጸሎት ቢጀምሩም እኔ መጸለይ አልቻልኩም ነበር። ብቻ በፍርሃት ተውጬ ጌታን አንድን ነገር ብቻ ነበር የለመንኩት፦ «ጌታ ሆይ፣ ከዚህ ጉድ ብቻ አውጣኝ!» 😂 ​ጊዜዬ ደርሶ ቆምኩኝ። ቤቱ በልጆችና በአዋቂዎች (ታላላቅ ወንድሞች) ሞልቶ ነበር። የሁሉም ዓይኖች በእኔ ላይ ነበሩ። ​ልቤ ወረደብኝ፤ «ቶሎ ብዬ እንጸልይ» አልኩኝ። ምን እንደጸለይኩ ትዝ አይለኝም፤ በርግጥም 60 ሰከንድ እንኳ አልቆየሁም። ያን ሁሉ ቀን የሸመደድኩት የት ጠፋ? 😂 ​ዓይኔን ስከፍት ቀጥ ብዬ መቆም አቃተኝ፤ እግሬ መንቀጥቀጥ ጀመረ፣ እጄም እንደዚሁ። የደረሰበት ያውቀዋል! 😭 ​አንዱ ወንድም በእኔ ቦታ እፍረት ተሰምቶትና ሳቁን መቆጣጠር እያቃተው የገዛ ጭኑን ሲቆንጥጥ አየሁት። «እናቴ ድረሽልኝ!» አልኩ። (በልቤ) ​ለ6 ቀናት ሙሉ ለ30 ደቂቃ የሚቆይ ስብከት ባዘጋጅም፣ ክፍሉን አንብቤ የመጣልኝን ብቻ ተናግሬ 5 ደቂቃ ያህል መቆየት ችያለሁ።😂 እግዚአብሔር ይመስገን! መልካም ቀን!
ещё
11 0 10 ноя, 07:48
Больше постов

Продолжить анализ этого канала

  • История роста подписчиков
  • Просмотры и охваты публикаций
  • Кто упоминает канал и кого упоминает он
  • Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней