Аналитика Telegram-канала
Подписчики
4 188
Публикаций
1 456
Динамика подписчиков
7 дней
30 дней
6 месяцев
Больше
12 ноя15 ноя18 ноя
Показаны последние 7 дней
Больше истории →
Охваты публикаций
24.1030.1001.1102.1103.1105.11
47
Средний охват
158
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале
Больше статистики →
Упоминания
75
Упоминаний
37
Из них репостов
14
Каналов
31
Упоминаний за 90 дней
21
Из них репостов
5
Каналов за 90 дней
Последние посты
3 из 1 456 2 из 1 456
ናፈቅከኝ......
ስንኖር በሰው ሀገር፤ ሆኜ መንገደኛ
ስለፋ ስንደክም፤ ሳልሆን በተኛ
እንባዬ በዛብኝ፤ ተስቃየሁ በዛ
የባዕድ ሀገር ኑሮ፤ ምንም አያወዛ
ጽናተም ሁሉ አልቆ፤ ጉልበም ተዳክሞ
መራመድ አቃተኝ፤ ስቃይ ተሸክሞ
ላይጠቅመኝ ላይረባኝ፤ ሁሉም ተከምሮ
መላመድ አቃተኝ ፤ የሰው ሀገር ኑሮ
ስተኛ በህልም፤ ኑሮየ ካገሬ
ስቃይ በለለበት፤ በሰላም አድረ
ስነቃ እዛው ነኝ ፤ በባዕዱ ምድር
ምንስ ይሻለኛል ፤ ናፈቀኝ ያ ሀገር
ኑሮን ለማሸነፍ፤ ሩጫየን ስጀምር
ብልጭ የምልልኝ፤ የተስፋዬ ምድር
እየሮጥኩኝ ውዬ፤ ስመለስ ለማረፍ
እረፍት የላት ነፍሴ ፤ ከንፋለች በክንፍ
በእንባ ታንቄ፤ ዓይኖቼ ስቀሉ
በድካም በሩጫ፤ እግሮቼ ስዝሉ
አሁንስ ከበደኝ፤ መኖሩ በትግል
በባዕዳን ምድር፤ ራስን በማታለል
ይብቃ በለኝ ይብቃ፤ መኖሩ በህመም
መሄድ የሻለኛል፤ እነስ ከዚህ ዓለም
አንተም ተናፍቀሃል፤ ለምን አትመጣም
ና ና እነም ልረፍ፤ እዛ ለዘላለም
በቃ ጨርሻለሁ 😭😭😭😭😭😭
https://t.me/MareJesus
https://t.me/MareJesus
https://t.me/MareJesus
ещё
17
1
1 5 ноя, 22:42
የውርደቱ መስቀል - የዘላለም ክብራችን
የታሪክ ጸሐፊው ጆሴፈስ፣ በዘመኑ ይፈጸም የነበረውን የስቅላት ሞትን “እጅግ አሳዛኝ ሞት” በማለት ገልጦታል፤[1] ስቅላት አስከፊና እጅግ የሚሰቀጥጥ የመሞቻ መንገድ ነበርና። ስቅላትን ለዓለም ያስተዋወቁት ፋርሳውያን ቢኾኑም፣[2] አይሁድ፣ ሮማውያንና ሌሎችም ግን ወደውና ፈቅደው ስቅላትን እንደ ተቀበሉ የታሪክ መዛግብት ይመሰክራሉ፤[3] ይህም የመቀጣጫ መንገድ እጅግ ከባድና አስከፊ ከመኾኑ የተነሣ፣ በአገር ክህደት የተያዙ ወንጀለኞች፣ ወንበዴዎች፣ ቄሣርን የሚቃወሙ ፖለቲከኞች ወይም እስረኞች ኹሉ የሚቀጡበት ቅጣት ነው። ቅጣቱ ረጅም ጊዜ የሚቆይ ወይም የሚቀጣው ሰው እስኪሞት ድረስ በመስቀሉ ላይ መቈየቱ አስከፊነቱን ከማሳየቱ ባሻገር፣ በሕዝብ ፊት የሚፈጸምና ከፍ ያለ ውርደትንም ጭምር በውስጡ የያዘ ነው።[4]
በቅዱሳት መጻሕፍት አራቱም ወንጌላውያን፣ የክርስቶስን የስቅለት ሞት በአንድነት ይገልጣሉ። “ከዘበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፥ ልብሱንም አለበሱት ሊሰቅሉትም ወሰዱት። … ከሰቀሉትም በኋላ ልብሱን ዕጣ ጥለው ተካፈሉ፥” (ማቴ. 27፥31፡ 35)፣ “ትርጓሜውም የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሆን ጎልጎታ ወደተባለ ስፍራ ወሰዱት። … ሰቀሉትም” (ማር. 15፥22፡ 24)፣ “ቀራንዮም ወደሚባል ስፍራ በደረሱ ጊዜ፥ በዚያ እርሱን ክፉ አድራጊዎቹንም አንዱን በቀኝ ሁለተኛውንም በግራ ሰቀሉ።” (ሉቃ. 23፥33)፣ “በዚያም ሰቀሉት፥ ከእርሱም ጋር ሌሎች ሁለት፥ አንዱን በዚህ አንዱን በዚያ ኢየሱስንም በመካከላቸው ሰቀሉ።” (ዮሐ. 19፥18) በማለት ነገረ መስቀሉን በአንድነት ይመሰክራሉ።
ከጥንት እስከ ዛሬ ክርስቶስ በዚህ መንገድ ለእኛ ራሱን አሳልፎ መስጠቱ፣ አጠያያቂና አነጋጋሪ ነው። በደል የሌለበት መሲሕ ፍጹም ከኾኑ ወንጀለኞች ጋር መሰቀሉ፣ ዐሳቡን ለመቀበል ብዙዎች የተቸገሩበት መንገድ ነው። ነገር ግን ይህ የኾነበትን ምክንያት ቅዱስ ጳውሎስ ሲያብራራ፣ “በእንጨት የሚሰቀል ኹሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ኾኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤” (ገላ. 3፥13) በማለት፣ መሰቀሉ ለእኛ ታላቅ ጥቅም እንደ ኾነ ተናግሮአል። ነገር ግን የክርስቶስ የመስቀል ሞት ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብ ደግሞ እጅግ ሞኝነት ወይም መሳለቂያ እንደ ነበር መዘንጋት አይገባም። አዎን፤ ስቁዩ መሲሕ ለአይሁድ መሰናከያ ለአሕዛብ ሞኝነት ነው፤ (1ቆሮ. 1፥23)።
እግዚአብሔር ኀይልና ጥበቡን ግን መግለጥ የወደደው በመስቀሉ በኩል ነው (1ቆሮ. 1፥24)፤ ይህም ማለት እግዚአብሔር ሥራውን መሥራት የፈለገው፣ እንደ ሰው ጥበብ ሳይኾን፥ ሰው ጨርሶ ሊጠብቀው በማይችለውና ጨርሶ ሊኾን ይችላል ብሎ በማይገምተው መንገድ ነውና፤ በዚህም ክብሩንና ውዳሴውንም ራሱ ብቻ ይወስዳል እንጂ ማንም ፍጥረት ሊጋራው አይችልም። ሐዋርያት ለዚህ ነው ከተሰቀለው መሲሕ በቀር ሌላ ርዕስና ሌላ ስብከት ያልነበራቸው (1ቆሮ. 1፥23፤ 2፥2)።
ኀጢአት በእግዚአብሔር ፊት ወራዶችና ክብር ዐልባዎች እንዳደረገን ብዙዎቻችን አናስተውልም ወይም ሌሎችም አያስተውሉም (ሮሜ 3፥23)፤ የክርስቶስ በመስቀል ላይ መሞትን ግን እኛ በኀጢአታችን ከተዋረድንበት በላይ አድርገን ስናቀርብ ይስተዋላል። ነገር ግን እኛ በኀጢአታችን ከተዋረድንበት የውርደት አዘቅት ሊያወጣንና በክብር ሊያቆመን፣ ከውርደታችን በማይተናነስ መንገድ፣ መሲሑ በፍጹም ውርደት ከኀጢአተኞች ጋር ተቈጥሮ ተጠመቀ፤ በመስቀል ተሰቅሎ ዋለ፤ በመቃብር ውስጥም ዐደረ። ክብር ይኹንለት፤ አሜን።
ልንረገም የሚገባንን ከእርግማናችን ይዋጀን ዘንድ፤ በኀጢአታችን ሊፈረድብን የሚገባንን ፍርዳችንን ያስወግድና ይደመስስ ዘንድ መጣልን። ውርደታችንን በውርደቱ ሊሽር፣ ይልቁን የመሳለቂና የሞኝነቱን መንገድ የክርስትና ዋና ትምህርት፤ ለመዳን ታላቅ መንገድ፤ ወደ ሰማይ የሚያደርስ የሕይወት ድልድይ፤ አሕዛብን ኹሉ ወደ መንግሥቱ መሰብሰቢያ ገመድ፤ አማኞችን ኹሉ በአንድ የሚስብ ከፍታ እንደ ኾነ ሊያሳይ … ክቡሩና ቅዱሱ መሲሕ፣ በፍጹም ውርደትና ሽንፈት በሚመስል መንገድ በመስቀል ላይ ተሰቀለ።
እንኪያስ፣ የዚህ ዘመን የመሲሑ የኾናችኹ ኹሉ ሆይ፤ “የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና።” (1ጴጥ. 2፥21) በዚህ መንገድ መመላለስ ይኹንልን፤ አሜን።
http://t.me/MareJesus
http://t.me/MareJesus
http://t.me/MareJesus
ещё
32
2
3 3 ноя, 21:03
እጁን አንስቶ የሚዘምር ልቡ ግን ገና በግብፅ ባርነት ዉስጥ ያለ ህዝብ ወንጌል እንዳይሰበክለት ከዳኑት ጋር ተቀላቅሏል።ከዚህም የተነሣ የእግዚአብሔር ስም በአደባባይ ይሰደባል።አቤቱ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረን🙏
https://t.me/MareJesus
https://t.me/MareJesus
https://t.me/MareJesus
ещё
32
2
2 2 ноя, 21:31
Продолжить анализ этого канала
- История роста подписчиков
- Просмотры и охваты публикаций
- Кто упоминает канал и кого упоминает он
- Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней