Аналитика Telegram-канала
Подписчики
4 204
Охват за 24 ч
348
ER за 24 ч
8,28%
Публикаций
317
Динамика подписчиков
7 дней
30 дней
6 месяцев
Больше
26 окт29 окт1 ноя
Показаны последние 7 дней
Больше истории →
Охваты публикаций
26.1026.1026.1026.1026.1027.10
20
Средний охват
54
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале
Больше статистики →
Упоминания
31
Упоминаний
25
Из них репостов
5
Каналов
0
Упоминаний
0
Из них репостов
0
Каналов
Последние посты
3 из 317 2 из 317🟠 የአደባባይ ሰው አለመሆን
• ሚስጥራዊ ስፍራ ከእግዚአብሔር ጋር
ещё
54
1
27 окт, 11:55
🟠 እምነታችሁን የሚያስጥሉ ነገሮች ደግሞ አሉ። ሁለት ናቸው። አንደኛው ሀጢያት ነው፥ ሁለተኛው አለመፀለይ ነው። ስለአለመፀለይ ባለፈው ፅሁፍ ስላነሳሁ ዛሬ ሀጢያት እንዴት እምነትን እንደሚያስጥል ልንገራችሁ። እኛ ሰው በሀጢያት የዘላለም ሀጢያቱን ሊያጣ አይችልም ስንል ሰው በተለያየ ድካም ውስጥ ሆኖ እንኳን እምነቱን መጠበቅና በእግዚአብሔር መደገፍ እስከቻለ ብቻ ነው። ምክንያቱም ሀጢያት ሲደጋገም የሚያመጣው ትልቅ አደጋ አለ። “ወንድሞች ሆይ፥ ምናልባት ሕያው እግዚአብሔርን የሚያስክዳችሁ ክፉና የማያምን ልብ ከእናንተ በአንዳችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልከኛ እንዳይሆን፥ ዛሬ ተብሎ ሲጠራ ሳለ፥ በእያንዳንዱ ቀን እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ” (ዕብ 3፡12-13)። ሀጢያት በመጀመሪያዎቹ ጊዜዎች ያታልላል። በሀጢያት የሚፀና ሰው ግን ልቡ እልከኛ ይሆናል። ያ አልከኝነት በእርሱ ውስጥ ክፉና የማያምን ልብ ይፈጥራል። አስተዋላችሁት? አንድ እያለቀሰ ጌታን የተቀበለ ሰው በሀጢያት እየተታለለና በታለለው ሀጢያት እየፀና ሲሄድ ኢየሱስ አያስፈልገኝም፤ እግዚአብሔር የሚባል የለም ወደሚል ደረጃ ሊደርስ ይችላል። ይሄን መፅሀፍ ቅዱስ ይነግረናል። በሌላ ቃልም ላስረዳችሁ። በዕብራውያን ላይ ህሊናችን ከሞተ ስራ ወይም ከሀጢያት እንደነፃ ይናገራል። “የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?” (ዕብ 9፡14)። ከቃሉ እንደምንረዳው ይሄ ህሊና የተጎዳው በሀጢያት ነበር፤ ከዚያም በክርስቶስ ደም ነፃ። አንዳንድ ሰዎች ተመልሰው ይሄን ህሊና በሀጢያት ማቆሸሽ ይጀምራሉ። ይሄ ልክ ቆዳችሁን በጋለ ብረት እንደመተርኮስ ነው። ህሊና በሀጢያትና ባለመታዘዝ ይቆስላል። ቆዳችሁን ደጋግማችሁ በጋለ ብረት ከተረኮሳችሁት ቆዳችሁ ምንም አይነት ስሜት የማይሰማው ይሆናል። ልክ እንደዚህ ጳውሎስ እንዲህ አለ “በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ ይላል፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው…” (1ጢሞ 4፡1)። እነዚህ ሰዎች ሃይማኖትን የካዱት ህሊናቸው ተቃጥሎ፤ ከዚያም ደንዝዞ ነው። ሕሊና ሲጣል ደግሞ እምነት ይጠፋል። “እምነትና በጎ ሕሊና ይኑርህ፥ አንዳንዶች ሕሊናን ጥለው፥ መርከብ አለ መሪ እንደሚጠፋ፥ በእምነት ነገር ጠፍተዋልና” (1ጢሞ 1፡19)። አስተዋላችሁት? እነዚህ ሄሜኔዎስና እስክንድሮስ የተባሉ ሰዎች ህሊናዬን ጥዬ በሀጢያት እያቆሰልኩት ልኑር ብለው ሲያስቡ እምነታቸው ጠፋ። መርከብ አለመሪ እንደሚጠፋ ማለት መርከብ የሌለው መሪ ከድንጋይ ይጋጫል በማዕበሉና ንፋሱ ይገለበጣል፤ ወዳልፈለገው አቅጣጫ ይወሰዳል። ከዚያም ያ መርከብ ይጠፋል። እንዲሁ ደግሞ ህሊናቸውን ከሀጢያት የማይጠብቁ ሰዎች ድንገት የሆነ ቀን እምነታቸው ጠፍቶ፤ እግዚአብሔር ላይ ሲያፌዙ ታገኟቸዋላችሁ። ስለዚህ ሀጢያት በቀጥታ የዘላለም ሕይወትን ማጥፋት አይችልም። ከሰው ድካም ሁሉ የእግዚአብሔር ምህረትና ፀጋ ይበረታል። የዳንነውም በስራ ሳይሆን በፀጋ ነው። ነገር ግን ፀጋውና ምህረቱ የተሰጡን በፅድቅ ለመኖር እንጂ በሀጢያት በርትቶ ለመኖር አይደለም። ጨክኖ ክርስቶስን መከተልና ከድካም መውጣት ያስፈልጋል እንጂ በድካም ለሚኖሩ ሰዎች ሁልጊዜ በድካም ብትኖሩ ችግር የለውም የሚል የመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርትና እንደዛ የሚመስል ሃሳብ እንኳን የለም። ያ የሀጢያት ድካም ህሊናን ወደ ማደንዘዝና ወደ ልብ እልከኝነት መርቶ ጌታ ክርስቶስን እንዳያስክድ መጠንቀቅ እጅግ ወሳኝ ነው።
📱 የአምላኬ ቃል አፕሊኬሽንን በማውረድ የየእለት ዲቮሽኛል ታገኛላችሁ @Lovedface
ещё
1
0
26 окт, 15:56
🟠 በእግዚአብሔር ዘንድ መስፈርት ያላቸውና የሌላቸው ነገሮች አሉ። ይሄን አስረግጦ ማወቅ እጅግ ወሳኝ ነው እላለሁ። ለምሳሌ፡ የእግዚአብሔር ፍቅር መስፈርት የለውም። አለሙን ሁሉ እንዲሁ ወዷል። በእግዚአብሔር ለመወደድ ማመን አያስፈልግም። ፍቅር ከአንድ ወገን ብቻ መምጣት ስለሚችል ያለሁለተኛው ወገን ተሳታፊነት ማፍቀር ይቻላል። ስለዚህ ጌታ ጠላቶቻችሁን ውደዱ ብሎ ነገረን። ጠላቶቻችን ከእኛ ጋር መስማማት ሳይጠበቅባቸው እየጠሉን እንወዳቸዋለን። በተቃራኒው ለመጀመሪያ ጊዜ ከእግዚአብሔር ምህረትን መቀበል መስፈርት አለው። መስፈርቱም ንስሃ ነው። ጌታ ኢየሱስ “በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል” ነው ያለው (ሉቃ 24፡47)። የሀጢያት ስርየት ብቻውን አይሰበክም። ዮሐንስ ደግሞ “በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው” ይላል (1ዮሐ 1፡9)። ይሄ ገና ወደ ጌታ ስንመጣ የምናደርገው ንስሃ (የልብ መመለስ) ነው። ልክ ጴጥሮስ “ምን እናድርግ?” ሲሎት ንስሃ ግቡ እንዳላቸው ማለት ነው (ሐዋ 2፡37-38)። ሰው ግን ልክ ወደ ጌታ ኢየሱስ መጥቶ ዳግመኛ ሲወለድ ምህረትን ያገኘ ስለሚሆን ሳያውቅ በሚሰራቸው ሃጢያቶችና ከሌሎች ለሚራገፍበት ሃጢያት ንስሃ ሳይገባ እንኳን ምህረትን ያገኛል። ይሄን የሚያሳዩ ሁለት ቃሎች ልንገራችሁ “እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል” (1ጴጥ 2፡10)። ምህረት አሁን ርስታችን ነው። “ይሄ ነገር ስህተት ነው ወይስ አይደለም?… ተሳስቻለሁ ወይስ አልተሳሳትኩም?…” እያልን መጨነቅ አይጠበቅብንም። ባወቅነው የእግዚአብሔር ቃል እውቀትና ብርሃን እንደገባን ስንመላለስ መጨነቅ ሳያስፈልገን የክርስቶስ ደም ያጥበናል። ደግሞ ተሳስተን እንኳን መሳሳታችንን ያላወቅናቸው ብዙ ነገሮች አሉ። እነሱ የሚነፁት በዚህ መንገድ ነው። ዮሐንስ “እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል” ያለው ይሄንን ነው (1ዮሐ 1፡7)።
🟠 ባወቅነው ብርሃን በእምነት ስንጓዝ የኢየሱስ ደም ከተሳሳትናቸው ሁሉ፤ ንስሃ እንኳን ሳንገባ ያነፃናል። ነገር ግን ንስሃ መግባት እንዳለብን ስናውቅ ንስሃ (ከስህተት መንገድ መመለስ) ያስፈልገናል። አውቀን ለተሳሳትነውና ለደከምንበት ደግሞ “ምህረትን እንድንቀበል… ወደ ፀጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ” ተብሎ እንደተፃፈልን በንስሃ ወይም በመቅረብ ምህረታችንን እንቀበላለን። አንዳንድ ሰዎች ይሄ ምህረት የሀጢያት ይቅርታ አይደለም ርህራሄ ወይም መልካምነት ነው ይላሉ። ይሄን የሚሉት ደም ሳይፈስ ስርየት የለም የሚለውን ቃል በመጥቀስ ነው (ዕብ 9፡22)። ነገር ግን ይህ አተረጓጎም ስህተት ነው። ኢየሱስ ላለፈ፥ ለአሁንና ለወደፊት ሃጢያት ሁሉ ደሙን ስላፈሰሰ እኛ ንስሃ በገባን ጊዜ ያነፃናል። እንደገና ደም ማፍሰስ አይጠበቅበትም። ከብሉይ ኪዳን ካህናትም የሚለየው በዚህ ነው። እነርሱ ሀጢያት በተደረገ ጊዜ ማቅረብ ሲጠበቅባቸው። እሱ ግን አንድን መስዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጧል (ዕብ 10)። መስፈርቱ ደግሞ ንስሃ ነው። “ወደ ፀጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ” የሚለው ለዚህ ነው። እያወቅን ለተሳሳትነው ስህተት ወደ ፀጋው ዙፋን ቀርበን ነው ምህረት የምንቀበለው። አንድ ሰው እያወቀ ተሳስቶና እየተሳሳተ በመቀጠል “ንስሃ ሳልገባ ምህረት ይገባኛል” ካለ ሞኝነት ነው። እግዚአብሔር በፍፁም የሀጢያት አገልጋይ አይደለም። ለሞትንበት ሀጢያት እንደገና እንኖር ዘንድ አይገባም ብሎ ጳውሎስ ይነግረናል (ሮሜ 6)።
🟠 መፅደቅና መዳን መስፈርት አለው። ያ መስፈርት ደግሞ እምነት ነው። በእምነት መቀበል! ስራ አላልኩም። መስፈርቱ እምነት ነው። የዳነው ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም ለመኖር ነው። “በውኑ ሁለት ሰዎች ሳይስማሙ በአንድነት ይሄዳሉን” እንደሚለው በእምነት መቀበል፤ እግዚእሔር በክርስቶስ ከሰራው የደህንነት ስራ ጋር መስማማት ያስፈልጋል (አሞ 3፡3)። ይሄ የተቀበልነው የዘላለም ሕይወት እንደማይጠፋ እግዚአብሔር ዋስትና እንደሰጠበት በተለያዩ ቃሎች ከዚህ በፊት ተምረናል። ያ የዘላለም ሕይወት ዋስትና ግን መስፈርት አለው። ያ መስፈርት ደግሞ መጀመሪያ ያመንንበትን እምነት ጠብቆ መቆየት ነው። የዘላለም ሕይወት ዋስትና ከእግዚአብሔር ቢመጣም ከእኛ የመጀመርያና እስከመጨረሻ የሚፀና እምነት ይፈልጋል። መፅሀፍ ቅዱስ “ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል” የሚለው ለዚህ ነው (1ጴጥ 1፡3-5)። በዚህ ስፍራ ላይ “በእምነት በእግዚአብሔር ሃይል ለተጠበቃችሁ” እንደሚል እግዚአብሔር በልጁ ያመንነውንና እምነታችንን እየጠበቅን የምንቀጥለውን እኛን በሃይሉ ይጠብቀን ዘንድ የእርሱ መሃላ ነው (ዕብ 6፡17-18)። ሰው ግን እምነቱን ከጣለ የእግዚአብሔር ሃይል ሊጠብቀውም ሆነ የዘላለም ሕይወት ዋስትና ሊኖረው አይችልም። ዮሐንስ ወንጌል 3፡16 ላይ ሁላችን የምናውቀውና ስለዘላለም ሕይወት የተፃፈውን ቃል በጥልቀት ብንመረምር እንዲህ ይላል… “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” በእርሱ የሚያምን በፍፁም አይጠፋም። በሀጢያት አይጠፋም፤ ምንያቱም ላለፈና (Past) ለወደፊት (Future) ሀጢያቱ ኢየሱስ መስዋዕት አቅርቦለታል። ያለፈና የአሁን ሀጢያቱ ተሰርዮለታል፤ የወደፊት ሀጢያቱ ደግሞ አይቆጠርበትም። እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ “ዓመፃቸው የተሰረየላቸው ኃጢአታቸውም የተከደነላቸው ብፁዓን ናቸው (ያለፈ ሀጢያት)፤ ጌታ ኃጢአቱን የማይቆጥርበት ሰው ብፁዕ ነው (የወደፊት ሀጢያት)” (ሮሜ 4፡7-8)። በሀጢያት ባይጠፋም የማይጠፋው ግን በእርሱ የሚያምን ብቻ ነው። ይሄ ማለት እምነቱ የአሁን አምነት መሆን አለበት። “በእርሱ የሚያምን” የሚለው ቃል አፃፃፉ ያልተቋረጠ አምነትን ያሳያል። የቃሉ tense (ሰዋሰው) Present Acttive Participle ነው። ያ ማለት አንድ ስፍራ ላይ የጀመረና ያልተቋረጠ እምነት ማለት ነው። አንድ ሰው ኢየሱስን ካመነ በኋላ ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አያስፈልገኝም ቢል በፍፁም የዘላለም ሕይወት ዋስትና የዘላለም ሕይወቱን ሊጠብቅለት አይችልም። ጌታ ኢየሱስ “ድል ለነሣውና እስከ መጨረሻም ሥራዬን ለጠበቀው…” የሚለው ለዚህ ነው። የገዛ ራሳችንን ስራ ሳይሆን እርሱ በመስቀል ላይ የሰራልንን ስራ በድካም ይሁን በብርታት እስከመጨረሻው በማመን መጠበቅ አለብን። “ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል ወደ ኋላም ቢያፈገፍግ፥ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም። እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑቱ ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉ አይደለንም” ተብሎ እንደተፃፈ ከእምነት ወደኋላ የሚመለስ ነፍሱን ሊያድን አይችልም (ዕብ 10፡38-39)።
ещё
1
0
26 окт, 15:56
Продолжить анализ этого канала
- История роста подписчиков
- Просмотры и охваты публикаций
- Кто упоминает канал и кого упоминает он
- Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней