Аналитика Telegram-канала
Подписчики
266
Охват за 24 ч
61
ER за 24 ч
22,93%
Публикаций
62

Динамика подписчиков

7 дней 30 дней 6 месяцев Больше
14 ноя17 ноя20 ноя
Показаны последние 7 дней Больше истории →

Охваты публикаций

07.1109.1110.1118.1119.1119.11
47
Средний охват
107
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале Больше статистики →

Упоминания

1
Упоминаний
0
Из них репостов
1
Каналов
Нет примеров за последние 90 дней
Все упоминания

Последние посты

3 из 62 2 из 62
ещё
80 0 19 ноя, 22:26
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዳዲስ የፋይናንስ ፈጠራዎች ሙሉ ፈቃድ ከማግኘታቸውና ወደገበያ ከመግባታቸው በፊት በክትትል የሚሞከሩበት መመሪያ ተግባራዊ አደረገ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በፋይናንስ ዘርፉ የሚቀርቡ አዳዲስ ፈጠራዎችን (Innovations) ሙሉ ፈቃድ ከማግኘታቸው በፊት በተወሰነ ጊዜና ቁጥጥር ስር እንዲሞከሩ የሚያስችል መመሪያ አውጥቶ ተግባራዊ አደረገ። በባንኩ ገዥ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ተፈርሞ ከኅዳር 8 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ተፈጻሚ የሆነው ይህ መመሪያ፤ የፋይናንስ አካታችነትን ለማሳደግ፣ ውድድርን ለማበረታታት እና ዘመናዊ የፋይናንስ አገልግሎቶችን በኃላፊነት ለማስፋፋት ያለመ ነው ይላል። በመመሪያው መሠረት ፈቃድ ያላቸው የፋይናንስ ተቋማት (ባንኮች፣ ኢንሹራንሶች፣ ማይክሮ ፋይናንሶች፣ የክፍያ ሥርዓት ኦፕሬተሮች ወዘተ)፣ የፋይናንስ ተቋም ፈቃድ ለማግኘት ያመለከቱ አካላት እንዲሁም አዲስ ዓይነት የፋይናንስ ተቋም ሆነው ለመሰየም ጥያቄ ያቀረቡ አካላት በተናጥል ወይም በጥምረት (Consortium) በሙከራ ማዕቀፉ ለመሳተፍ ማመልከት ይችላሉ። ሆኖም የሚቀርበው ፈጠራ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ቀደም ሲል ያልነበረ ወይም አሁን ያለውን አገልግሎት በከፍተኛ ደረጃ የሚያሻሽል፣ ለተጠቃሚዎች ተጨባጭ ጥቅም የሚያስገኝ እና በነባር ሕጎች ምክንያት በቀጥታ ወደ ሥራ ለመግባት ተግዳሮት የገጠመው መሆኑን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል። ብሔራዊ ባንክ በዓመት ቢያንስ ሁለት ጊዜ በይፋ ጥሪ የሚያደርግ ሲሆን፣ አመልካቾች የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ እና የሙከራ ቡድን መሰየም ይኖርባቸዋል። ቡድኑ በወንጀል ያልተከሰሰ፣ መልካም ሥነ-ምግባር ያለው እና የፖሊስ የንጽሕና ማረጋገጫ (Police Clearance) ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት። እንዲሁም ተመላሽ የማይሆን የማመልከቻ ክፍያ የተቀመጠ ሲሆን • ለባንኮች 100 ሺ ብር፣ • ለኢንሹራንስ ኩባንያዎች 75 ሺ ብር፣ • ለማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት 50 ሺ ብር እንዲሁም • ለሌሎች ተቋማት 35 ሺ ብር እንዲከፍሉ ተደንግጓል። የሙከራ ፈቃድ ያገኘ ተቋም ፈቃዱ በደረሰው በ30 ቀናት ውስጥ ሙከራውን መጀመር ያለበት ሲሆን፣ የሙከራ ጊዜው ከ12 ወራት አይበልጥም። አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ግን ለአንድ ጊዜ ብቻ እስከ ተጨማሪ 12 ወራት ሊራዘም ይችላል። በሙከራው ወቅት ብሔራዊ ባንክ ለፋይናንስ መረጋጋትና ለተጠቃሚዎች ደህንነት ስጋት እስካልፈጠረ ድረስ ጊዜያዊ የደንብ ማቅለያ (Rule Waiver) ሊፈቅድ ይችላል። ሆኖም ፀረ-ሕገወጥ ገንዘብ ዝውውር (AML/CFT)፣ የመረጃ ጥበቃ፣ የሳይበር ደህንነት እና የተጠቃሚዎች መብት ጥበቃ ሕጎች በማንኛውም ሁኔታ አይታለፉም። ተሳታፊ ተቋማት ለደንበኞቻቸው አገልግሎቱ በሙከራ ደረጃ ላይ ያለ መሆኑን በግልጽ በጽሑፍ ማሳወቅና የደንበኞችን ፈቃድ ማግኘት አለባቸው። በሙከራው ምክንያት በደንበኞች ላይ ለሚደርስ ማንኛውም ኪሳራ ወይም ጉዳት ተቋሙ ሙሉ ኃላፊነት የሚወስድ ሲሆን፣ ነጻ የቅሬታ ማቅረቢያ ሥርዓት በመዘርጋት የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ቢበዛ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ መፍታት ይኖርበታል። በተጨማሪም የሳይበር ጥቃት፣ የመረጃ መመንተፍ ወይም ከፍተኛ የአሠራር ችግር ሲያጋጥም በ24 ሰዓት ውስጥ ለብሔራዊ ባንክ ሪፖርት ማድረግ ግዴታ ነው። የሙከራ ጊዜው ሲጠናቀቅ ተቋሙ ወደ ሙሉ ፈቃድ ሊሸጋገር፣ በቅድመ ሁኔታ እንዲቀጥል ሊደረግ፣ የሕግ ማሻሻያ እስኪደረግ ሊጠብቅ ወይም ፈቃድ ሳያገኝ ሊሰናበት ይችላል። ከሙከራው በኋላም እስከ አንድ ዓመት የሚደርስ የድህረ-ሙከራ ክትትል (Post-Exit Monitoring) ይደረግበታል። መመሪያውን በመተላለፍ ሐሰተኛ መረጃ በሚሰጡ፣ የተጠቃሚዎችን መረጃ ያለፈቃድ በሚጠቀሙ ወይም ከተፈቀደው ወሰን ውጭ በሚሠሩ ተቋማት ላይ 50 ሺ ብር እንዲሁም ማጭበርበር በሚፈጽሙ፣ ያለፈቃድ ተቀማጭ ገንዘብ በሚሰበስቡ ወይም ሙከራው ከታገደ በኋላ ሥራ በሚቀጥሉ ላይ 100 ሺ ብር የገንዘብ ቅጣት እና ከቀጣይ ተሳትፎ እስከመታገድ የሚደርስ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ መመሪያው ይደነግጋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ/ም
ещё
62 0 19 ноя, 22:26
ጮቄ flying ዛሬ ከጮቄ አቡጊዳ ቁጠባ እና ብድር የህብረት ስራ ማህበር (SACCO) አመራሮች ጋር እንደ አንድ ቤተሰብ ሆነን በምንሰራበት ጉዳይ በጣም ብዙ ሰአት ወስደን አውርተናል ። በተቋም ምስረታ እና አመራር ዙሪያ ልምዳችንን አጋርተናል ። በቃ LSACCO ቀርቷል እና ጮቄ SACCO ሆኗል ። ጮቄ SACCO በቃ ሰማይ እናደርሰዋለን ደግሞ ለዚህ ማን ብሎን ! ጮቄ will be the famous brand in various economic sectors. I told you እኮ አትሰሙም እንጅ 😂 More info loading soon.. በቃ አዳሜ እና ሄዋኔ ተሰልፋችሁ ጠብቁኝ ! ጮቄ ትዕስር 🙏
ещё
107 1 3 18 ноя, 16:14
Больше постов

Продолжить анализ этого канала

  • История роста подписчиков
  • Просмотры и охваты публикаций
  • Кто упоминает канал и кого упоминает он
  • Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней