Аналитика Telegram-канала
Подписчики
8 328
Охват за 24 ч
743
ER за 24 ч
8,92%
Публикаций
691
Динамика подписчиков
7 дней
30 дней
6 месяцев
Больше
21 ноя24 ноя27 ноя
Показаны последние 7 дней
Больше истории →
Охваты публикаций
01.1101.1107.1108.1114.1124.11
198
Средний охват
726
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале
Больше статистики →
Упоминания
265
Упоминаний
230
Из них репостов
36
Каналов
11
Упоминаний за 90 дней
7
Из них репостов
4
Каналов за 90 дней
Последние посты
3 из 691 2 из 691የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮችን አጣሪ ጉባኤ❓
በማጣራት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል ለተባሉ ጉዳዮች የውሳኔ ሀሳብ መስጠት
አገልግሎቱን ለማግኘት መሟላት ያለባቸው ጉዳዮች፡-✍️
አቤቱታው ስልጣን ባለው ፍ/ቤት ቀርቦ የታየና የጨረሰ ሕገ መንግሥታዊ ጉዳይ ሲሆን፣
ጉዳዩ በየደረጃው ስልጣን ያለው አስፈፃሚ አካል ጋር ቀርቦ የመጨረሻ ውሳኔ ያገኘ ሲሆን፣
አንድ ሦስተኛ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ የፌዴራል ወይም የክልል ም/ቤት አባላት የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ ሲቀርብ፤
አቤቱታ ለማቅረብ መሟላት ያለባቸው ነገሮች✍️
ሀ) የጉባዔውን ስምና አድራሻ፣
ለ) የአመልካች /አቤቱታ አቅራቢው/ ሙሉ ስምና
ሐ) አድራሻ ስልክ ቁጥር፣
መ) የተጠሪ ሙሉ ስምና አድራሻ፣
ረ) የአቤቱታው ርዕስ፣
ሠ) ግልጽና አጭር የሆነ የሕገ መንግሥታዊ መብት ጥሰቱን የሚያሳይ አቤቱታ፣
ረ) የተጣሰውን ሕጋዊ መብት፣ ሕጋዊ ጥቅም ወይም ሕጋዊ ስልጣን እና ከሕገ መንግሥቱ ድንጋጌ ጋር የሚጋጭበትን ምክንያት፣
ሰ) በውክልና ለሚቀርብ አቤቱታ በውክልና የቀረበ መሆኑን የሚገልጽ መሆን አለበት
ከላይ የተዘረዘሩት እንደተጠበቁ ሆነው፡-✍️
ሀ) ትርጉም የተጠየቀበት ሕግ በሆነ ጊዜ የሕጉ አጭር ርዕስ፣ ቁጥር፣ የታተመበት ቀን፣ ዓመተ ምህረት እና ድንጋጌ፣
ለ) ትርጉም የተጠየቀበት የመንግሥት አካል ወይም የባለስልጣን ውሳኔ በሆነ ጊዜ ለመጨረሻው ውሳኔ ምክንያት የሆኑ ሌሎች ውሳኔዎችበቅደም ተከተል፣ የመጨረሻው ውሳኔ፣ውሳኔውን የሰጠው አካል፣ ውሳኔዎቹየተሰጡበት ቀን እና ዓ.ም፣
ሐ) ትርጉም የተጠየቀበት ውሳኔ ከፍርድ ቤት፣ከሌሎች የዳኝነት ስልጣን ካላቸው አካላት የሚላክ የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ እንደ አግባብነታቸው ከላይ የተጠቀሱትን ዝርዝር ጉዳዮች ሊይዝ ይገባል፡፡
ещё
726
6
24 ноя, 21:06
" የተሰረቀ ዕቃ በቅናሽ ዋጋ መግዛት ወይም ይዞ መገኘት እንደ ወንጀሉ ክብደት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት ያስቀጣል " - የሕግ ባለሙያ
አንዳንድ ሰዎች የተሰረቁ ስልኮች፣ ላፕቶፖችና ሌሎች ዕቃዎች በርካሽ ዋጋ የሚሸጡባቸውን ቦታዎች በማፈላለግ ሲገዙ ይስተዋላል።
አንዳንዶች ምንጫቸውን ሳያውቁ ያገለገሉ ዕቃዎችን በርካሽ ስላገኟቸው ብቻ ከሰዎች ላይ ይገዛሉ ፤ ሌሎች ደግሞ እቃውን በትንሽ ብር ገዝተው አትርፈው ይሸጣሉ።
ታዲያ አንድ ሰው " ዕቃው በቅናሽ ዋጋ ስለቀረበልኝ በቅን ልቦና ነው የገዛሁት ፤ የተሰረቀ መሆኑን አላውቅም ነበር " ቢል ከሕግ ተጠያቂነት ያመልጥ ይሆን ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ላይ ዓለም አቀፍ የሕግ ባለሙያና ጠበቃ የሆኑትን አቶ ጥጋቡ ደሳለኝን አነጋግሯል።
የሚያስከትለው የሕግ ተጠያቂነት ምንድነው ?
በአነስተኛ ዋጋ ስለተገኘ ብቻ የተሰረቀ ዕቃ የሚገዙና አትርፈው የሚሸጡ አካላት፣ በቅን ልቦናም ይሁን ሳያውቁ ቢገዙ ከሕግ ተጠያቂነት ነጻ እንደማይሆኑ አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ገልጸዋል።
በሕግ ፊት " የተሰረቀ መሆኑን አላውቅም ነበር " የሚል ምክንያት ተቀባይነት እንደሌለውም አስረድተዋል።
" የተሰረቀ ዕቃ የዋጋ ቅናሽ ስላለውና ደረሰኝ ስለሌለው መግዛት፣ በሕጉ መሠረት የተሰረቀ ዕቃ በመግዛት እና ደረሰኝ የሌለው ዕቃ ይዞ በመገኘት እንደ ነገሩ ክብደት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት ያስቀጣል። ከተጠያቂነት ነጻ መሆን የሚቻለው ከሕጋዊ ነጋዴ በስሙ የተቆረጠ ሕጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ ሲቻል ብቻ ነው " - አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ
የአንድ ግብይት ሕጋዊነት የሚረጋገጠው በደረሰኝ ብቻ መሆኑን ያነሱት ባለሙያው፤ ሻጩ ለሰጠው ዕቃ ወይም አገልግሎት ደረሰኝ የመስጠት፣ ገዢውም የከፈለበትን ደረሰኝ የመቀበል ግዴታ እንዳለበት ተናግረዋል። ግብይቱ በደረሰኝ እስካልተረጋገጠ ድረስ የትኛውም ግብይት የወንጀል ተጠያቂነትን እንደሚያስከትል አሳስበዋል።
የኦንላይን (ማኅበራዊ ሚዲያ) ግብይቶች ተጠያቂነት አለባቸው ?
ከሰው ላይ የተሰረቁ ወይም በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኙ (የወንጀል ፍሬ የሆኑ) ዕቃዎችን ሰዎች ትክክለኛ መስሏቸው በቴሌግራም ቻናሎች፣ በፌስቡክ ገጾች እና በሌሎች የበይነመረብ አማራጮች ተታልለው ቢገዙና በኋላ የተሰረቀ ዕቃ መሆኑ ቢታወቅ፣ የወንጀል ተጠያቂነቱ በቀጥታ የሚያርፈው ዕቃውን ባሻሻጡት የኦንላይን ገጽ ባለቤቶች ወይም አንቀሳቃሾች (ኦፕሬተሮች) ላይ መሆኑን ጠበቃው ገልጸዋል።
አክለውም በማኅበራዊ ሚዲያ " ዕቃ እናሻሽጣለን፣ ሻጭና ገዢ እናገናኛለን፣ የዴሊቨሪ አገልግሎት እንሰጣለን " የሚሉ አካላት በቀጥታ በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ጠቅሰዋል።
እነዚህ አካላት ዕቃውን ከማስተዋወቃቸው በፊት ዕቃው በሕጋዊ መንገድ የተገኘና የወንጀል ፍሬ አለመሆኑን፣ እንዲሁም ከትክክለኛ አቅራቢ ተገዝቶ ለትርፍ የቀረበ መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው።
ዕቃው በፖሊስ ቢወሰድ ገዢው ምን መብት አለው ?
አንድ ገዢ በቅን ልቦና ያገለገለ ዕቃ ገዝቶ የተሰረቀ መሆኑ ተደርሶበት በፖሊስ ከተወሰደበት፣ ዕቃውን ለመግዛት ያወጣውን ገንዘብ ከካሳ ጋር በፍርድ ቤት የመጠየቅ ሕጋዊ መብት እንዳለው አቶ ጥጋቡ ጠቁመዋል። ሆኖም የፍትሕ ሂደቱ እስከ 6 ወር ወይም ከዚያ በላይ ሊወስድ ስለሚችል፣ ዜጎች ገና ከጅምሩ በደረሰኝ በመገበያየት ራሳቸውን ከእንግልትና ከኪሳራ መጠበቅ እንደሚገባቸው መክረዋል።
የተሰረቀ ዕቃ በስጦታ መልክ መቀበል የሚያመጣው ችግርስ ?
" የተሰረቀ ዕቃ መሆኑን ሳያውቁ በስጦታ መቀበል ከሕግ ተጠያቂነት ያድናል ወይ ? " ለሚለው ጥያቄም የሕግ ባለሙያው የሚከተለውን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡
የተሰረቀ ዕቃን በስጦታ የተቀበለ ሰው በሕግ ሲጠየቅ፤ " ዕቃው የተሰጠኝ በማኅበረሰቡ የመሰጣጣት ባህልና ልማድ መሠረት በስጦታ ነው፤ ቀደም ሲል በእኔ እጅ አልነበረም፤ እከሌ የሚባል ሰው ነው የሰጠኝ " ብሎ በሰው ምስክር ማረጋገጥ ከቻለ ከወንጀል ተጠያቂነት ነጻ ይሆናል።
በሰነድ እንኳ ባይሆን በሰው ምስክር ማረጋገጥ ካልቻለ ግን፣ የተሰረቀ ዕቃን ለማሸሽ፣ ለመሸሸግ፣ ለመደበቅ፣ ለመሰወር ወይም አትርፎ ለመሸጥ የተደረገ ሙከራ ነው ተብሎ በወንጀል ይጠየቃል።
በሕግ አግባብ ስጦታ መቀበል የሚቻለው ስጦታ ሰጪው ንብረቱ የራሱ ስለመሆኑ በውልና ማስረጃ መሥሪያ ቤት ሲያረጋግጥ ብቻ መሆኑን የገለጹት ባለሙያው፤ በማኅበረሰቡ ዘንድ በተለመደው መንገድ ብቻ ዝም ብሎ ስጦታ መቀበል ከሕግ ተጠያቂነት እንደማያድን አስገንዝበዋል።
በመጨረሻም ማኅበረሰቡ ለሚፈጽማቸው ማናቸውም ግብይቶች ሕጋዊ ደረሰኝ መስጠትና መቀበልን ባህሉ ሊያደርግ እንደሚገባ አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ አሳስበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia
ещё
120
1
14 ноя, 21:22
ባለፉት አምስት አመታት ከ20 ሺህ በላይ ፍቺ ተመዝግቧል
ከአዲስ አበባ ህዝብ ምዝገባ እና መኖሪያ ፈቃድ ኤጀንሲ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ባለፉት አምስት ዓመታት ከ20 ሺህ በላይ ፍቺ ተመዝግቧል ተብሏል።
ከዚህም ውስጥ ከ5 ሺህ በላይ የሚሆኑት ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ የተመዘገቡ መሆናቸው አሳሳቢነቱን ያሳያል።
በአዲስ አበባ ከተማ እየጨመረ የመጣውን የፍቺ ቁጥር ለመቀነስ እና ጤናማ ቤተሰባዊ ግንኙነቶችን ለመገንባት ያለመ "ቁርስ ከደሚና ጋር" የተሰኘ አዲስ የፍቅር ግንኙነት ትምህርት፣ የሥልጠና እና የምክር አገልግሎት ኢኒሼቲቭ በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል ።
የትዳር አማካሪ ኢብሳ ደሚና "ሀገር የሚመሰረተው ቤት ውስጥ ነው፤ ቤተሰብ ከተረጋጋ ሀገር ይረጋጋል" በማለት የቤተሰብን ወሳኝ ሚና አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።
አክለውም በትዳር ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት እና ትውልድን ለመታደግ መፍትሔው ከራሳችን መጀመር እንዳለበት አመልክተዋል።
አዲስ ተጋቢዎችንና ጥንዶችን የሚያካትተው ይህ መርሃ ግብር፥ውጤታማ ግንኙነት፣ ስሜታዊ ግንዛቤ እና ግጭትን በአግባቡ መፍታት ላይ የሚያተኩር የአንድ ቀን ስልጠና በመስጠት ከ1 ሺህ በላይ ሰዎችን ለመድረስ አቅዷል።
ችግሮች ከመባባሳቸው በፊት መፍትሄ ለመስጠት ያለመው ይህ መርሃ ግብር ጤናማ ቤተሰቦችን ለመገንባት ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ጥቅምት 28 ቀን 2019 ዓ.ም
ещё
67
0
8 ноя, 23:57
Продолжить анализ этого канала
- История роста подписчиков
- Просмотры и охваты публикаций
- Кто упоминает канал и кого упоминает он
- Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней