Аналитика Telegram-канала
Подписчики
9 780
Охват за 24 ч
631
ER за 24 ч
6,45%
Публикаций
1 275
Динамика подписчиков
7 дней
30 дней
6 месяцев
Больше
13 ноя16 ноя19 ноя
Показаны последние 7 дней
Больше истории →
Охваты публикаций
20.1015.11
126
Средний охват
176
Лучший результат
Показаны 2 публикации — последние в канале
Больше статистики →
Упоминания
237
Упоминаний
196
Из них репостов
31
Каналов
6
Упоминаний за 90 дней
3
Из них репостов
3
Каналов за 90 дней
Последние посты
2 из 1 275 2 из 1 275አዲሱ የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ ያመጣቸው አዳዲስ ለውጦች
አዲሱ የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ 🙏#አለሕግ
#መግቢያ
ከስድስት አሥርት ዓመታት በላይ በሥራ ላይ የቆየውን የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓት የተካው አዲሱ የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 ዘርፈ ብዙ ለውጦችን ያካተተ ነው። ይህ ሕግ አዳዲስ አሠራሮችን ከማስተዋወቁ በተጨማሪ በተለያዩ ሕጎች ውስጥ ተበታትኖ የነበረውን የማስረጃ ሕግ በማካተት በኢትዮጵያ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ውስጥ የቆየውን አንድ ትልቅ ክፍተት ለመሙላት አስችሏል። ይህ ጽሑፍ የአዲሱን ሕግ ይዘት፣ አዲሱ ሕግ ከቀድሞው ሕግ የሚለይባቸውን መሠረታዊ ለውጦች እንዲሁም በሕጉ የተጨመሩ አዳዲስ ጉዳዮችን በአጭሩ ይዳስሳል፡፡
የሥነ-ሥርዓት እና ማስረጃ ሕጉ ይዘት አዲሱ ሕግ በአጠቃላይ
👉 የወንጀል ምርመራ፣ ክስ፣ ችሎትና ይግባኝ ሥርዓቶችን
👉 የተጠርጣሪና የተከሳሽ መብቶችን እና የፍትሐዊ ክርክር መርሆዎችን
👉የእስር፣ የዋስትና እና የጊዜያዊ እርምጃዎችን አፈጻጸም 👉 የፖሊስና የዐቃቤ ሕግ የምርመራና የክስ ሥልጣንና ኃላፊነት
👉የማስረጃ ሕጋዊነት፣ ተቀባይነት፣ አቀራረብና ምርመራ መርሆዎችን
👉 የምስክር ማስረጃ፣ የሰነድ ማስረጃ፣ የኤሌክትሮኒክ ማስረጃና የሳይንሳዊ ማስረጃን
👉 ለከባድ ወንጀሎች ጥቅም ላይ የሚውሉ ልዩ የምርመራ ዘዴዎችን
👉 የምስክሮች፣ የተጎጂዎችና ሌሎች የሂደቱ ተሳታፊዎችን የመብት ጥበቃ
👉 የክስ ማቋረጥ፣ ጥፋተኝነትን አምኖ መቀበልን (ድርድር) እና አማራጭ የውሳኔ መንገዶችን
👉 የችሎት ሂደትን፣ የፍርድ አሰጣጥን፣ የይግባኝና የሰበር ሥርዓትን
👉 ልዩ ሥርዓት እና የዓለም ዓቀፍ ትብብርን የተመለከቱ ጉዳዮችን እንዲሁም
👉የመጨረሻ ፍርድ እንደገና የሚታይበትን አግባብ አካቷል፡፡
አዲሱ ሕግ ከቀድሞው ሕግ የሚለይባቸውን መሠረታዊ ለውጦችአዲሱ ሕግ ከቀድሞው የሚለይባቸው የተለያዩ ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው።
እነሱም፡- 👉መሠረታዊ መርሆዎችየቀድሞው ሕግ ለተከሳሹ መብቶች እውቅና የሰጠ ቢሆንም ድንጋጌዎቹ ትኩረት የሚያደርጉት በክስ ማቅረብ እና በመደበኛ ሥነ-ሥርዓት ላይ ነበር። አዲሱ ሕግ በአንፃሩ መሠረታዊ መርሆዎችን (አንቀጽ 4-17) በግልጽ ዘርዝሯል፡፡ ይኸውም እንደ ጥፋተኛ ያለመቆጠር መብት (አንቀጽ 5)፣ በአንድ ወንጀል ድጋሜ ክስ እና ቅጣት መከልከል (አንቀጽ 6)፣ በሕግ ፊት እኩል መሆን (አንቀጽ 7)፣ ስለ መያዝና ማሰር (አንቀጽ 8)፣ የኢሰብዓዊ አያያዝ መከልከል (አንቀጽ 9)፣ በጠበቃ የመወከል መብት (አንቀጽ 10 የገንዘብ አቅም ለሌለው ፍትሕ ሊጓደል የሚችልበት ሁኔታ ሲኖር በመንግሥት ወጪ ጠበቃ የማግኘት መብትን በሰፊው ያስቀምጣል)፣ የተፋጠነ ፍትሕ (አንቀጽ 11)፣ በግልጽ ችሎት መዳኘት (አንቀጽ 12)፣ የተከራካሪዎች እኩልነት (አንቀጽ 13 በዓቃቤ ሕግ እና በተከሳሽ መካከል እኩልነት እንዲኖር)፣ የቋንቋ አጠቃቀም (አንቀጽ 14 የአስተርጓሚ መብትን ያረጋግጣል)፣ እውነትን ማውጣት (የፍርድ ሒደቱ ዋና ዓላማ እውነት ማውጣት መሆኑን ይገልጻል፣ በአንቀጽ 15)፣ ሕጋዊነት (በአንቀጽ 16) እና የወንጀል ክስ የመንግሥት መሆኑ (አንቀጽ 17) ናቸው።
👉 የተከሳሽን መብቶች ማስፋትበቀድሞው ሕግ የተከሳሽ መብቶች ተካተው የነበሩ ቢሆንም አዲሱ ሕግ እነዚህን መብቶች በዝርዝር በማስቀመጥ አስፋፍቷቸዋል።
እነሱም በጠበቃ መወከል (አንቀጽ 10)፣ የአስተርጓሚ መብት (በፍርድ ሒደቱ ሁሉ የአስተርጓሚ መብት በግልጽ ተደንግጓል (አንቀጽ 14)፣ የመናገር እና ዝም የማለት መብት (ተጠርጣሪ ቃል ከመስጠቱ በፊት ያለመናገር መብቱን ማወቅ ይኖርበታል (አንቀጽ 116))፣ የዋስትና መብት (አንቀጽ 132-147) የዋስትና መብት በሰፊው ተቀምጧል፣ ነገር ግን ለከባድ ወንጀሎች የተገደበ ነው)፣ የተከሳሽ ማስረጃ የማቅረብ መብት (ተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃውን የማቅረብ እና ምስክሮችን የመጥራት መብቱ ተረጋግጧል (አንቀጽ 282-284)፡፡
👉 የዐቃቤ ሕግ ሚና እና ኃላፊነትበአዲሱ ሕግ አንቀጽ 20 መሠረት ዐቃቤ ሕግ የሚከተሉትን ማድረግ አለበት፡፡ ምርመራ እንዲጀመር እና እንዲከናወን ክትትል ማድረግ፣ በምርመራ መዝገብ ላይ ውሳኔ መስጠት (ክስ መመስረት ወይም አለመመስረት)፣ አማራጭ መፍትሄዎችን (ዕርቅ፣ የጥፋተኛነት ድርድር) ማደራጀት፣ ለተከሳሽ የሚጠቅም ማስረጃ ለፍርድ ቤት እና ለተከሳሽ ማድረስ፣ ከወንጀል ጋር የተገናኘ ንብረትን በሚመለከት የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰድ፣ የፍርድ ቤት ውሳኔዎች እንዲፈጸሙ ክትትል ማድረግ እና ምስክሮች ጥበቃ እንዲያገኙ ማድረግ ይገኙበታል።
👉 ማስረጃ እና የማስረዳት ኃላፊነት በቀድሞው ሕግ ስለ ማስረጃ አጠቃላይ ድንጋጌዎች የነበሩ ቢሆንም አዲሱ ሕግ በጣም ዝርዝር ጉዳዮችን አካቷል።
5ኛ መጽሐፍ (አንቀጽ 236-291) ሙሉ በሙሉ ለማስረጃ የተዘጋጀ ሲሆን ይህም የሚከተሉትን ያካትታል፡፡ የማስረዳት ኃላፊነት (ዐቃቤ ሕግ ክሱን ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ የማስረዳት ኃላፊነት (አንቀጽ 280)፣ የማስረጃ ዓይነቶች (የሰው ማስረጃ (የምስክር ቃል)፣ የሰነድ ማስረጃ፣ የኤሌክትሮኒክ ማስረጃ እና ኤግዚቢት በዝርዝር ተመድበዋል (አንቀጽ 247-278)፣ ተቀባይነት ያለው እና የሌለው ማስረጃ (አንቀጽ 243-246)፣ በማስረጃ ላይ መቃወሚያ ስለማቅረብ (አንቀጽ 289)፣ ተከሳሽ በዐቃቤ ሕግ ወይም በፖሊስ እጅ ያለ ማስረጃ ለመከላከያነት የማግኘት መብቱ ተረጋግጧል (አንቀጽ 284)።
👉 አማራጭ የውሳኔ መንገዶች (አማራጭ መፍትሄዎች)በቀድሞው ሕግ የዕርቅ አማራጭ የነበረ ቢሆንም በስፋት የተዘረጋ አልነበረም።
አዲሱ ሕግ በምዕራፍ ሁለት (አንቀጽ 156-182) በሚከተሉት ሦስት መንገዶች የአማራጭ መንገዶችን በስፋት ያስተዋውቃል፡፡
1. ዕርቅ (አንቀጽ 158-162)፡- በተጎጂው እና በተከሳሹ መካከል በሚደረግ ስምምነት ጉዳዩን ለመፍታት የሚያስችል ሥርዓት ተዘርግቷል።
2. የጥፋተኛነት ድርድር (አንቀጽ 163-173)፡- ተከሳሹ ጥፋተኛነቱን አምኖ የክስ ብዛት እንዲቀንስለት ወይም ቀላል ቅጣት እንዲያገኝ የሚያስችል አዲስ ሥርዓት ነው።
3. ባህላዊ ሥርዓቶች (አንቀጽ 174-180)፡- ጉዳዮች በባህላዊ መንገድ እንዲታዩ የሚያስችል ሥርዓት ተዘርግቷል፡፡ ነገር ግን ይህ ሰብአዊ መብቶችን የሚጥሱ፣ በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች እና በአገር ደኅንነት ላይ የሚፈፀሙ ከባድ ወንጀሎችን አያካትትም።
👉 የልዩ ሥነ-ሥርዓት ማስፋትየቀድሞው ሕግ ስለወጣቶች እና ደንብ መተላለፍ የተወሰኑ ልዩ ድንጋጌዎች ቢኖሩትም የአዲሱ ሕግ ስምንተኛው መጽሐፍ ግን ሙሉ በሙሉ ለልዩ ሥነ-ሥርዓት የተዘጋጀ ሲሆን የሚከተሉትን ያካትታል፡፡ በወንጀል ነገር ውስጥ ገብተው የተገኙ ወጣቶች (አንቀጽ 351-365) ለወጣቶች ልዩ እና መደበኛ ያልሆነ አያያዝ ሥርዓት ተዘርግቷል። ይህም የወጣቱን ጥቅም እና ማኅበራዊ ተሃድሶ ቅድሚያ ይሰጣል፡፡ ደንብ መተላለፍ (አንቀጽ 366-373) ለትናንሽ ወንጀሎች ቀላል እና ፈጣን የፍርድ ሒደት ተዘርግቷል።
👉 የዓለም ዓቀፍ ትብብር በቀድሞው ሕግ የዓለም ዓቀፍ ትብብር ድንጋጌዎች ውስን ነበሩ። የአዲሱ ሕግ 9ኛ መጽሐፍ (አንቀጽ 374-417) ሙሉ በሙሉ ዓለም ዓቀፍ ትብብርን የተመለከተ ሲሆን የሚከተሉትን ያካትታል፡፡ የትብብር ጥያቄ ማቅረብ እና አፈጻጸም (ከሌሎች አገሮች ጋር የሚደረግ ትብብር ሥርዓት)፣ የፍርድ ሒደትን ማስተላለፍ (የፍርድ ሒደትን ከአንድ አገር ወደ ሌላ ማስተላለፍ የሚቻልበት ሥርዓት)፤ የውጭ ፍርዶች ዕውቅና እና አፈጻጸም (በውጭ አገር የተሰጡ የወንጀል ፍርዶች እውቅና የሚያኙበት እና የሚፈፀሙበት ሥርዓት) (አንቀጽ 381-395) እንዲሁም በወንጀል ተፈላጊ ሰው አሳልፎ መስጠት (ተፈላጊ ሰዎችን አሳልፎ የመስጠት ሥርዓት (አንቀጽ 396-417)) ተደንግጓል።
👉 የምርመራ እና የቅድመ ክስ ሒደት ማሻሻያ በቀድሞው ሕግ የምርመራ እና የቅድመ ክስ ሒደት አነስተኛ ነበር። በአዲሱ ሕግ 2ኛ መጽሐፍ (አንቀጽ 62-122) የሚከተሉትን ጨምሮ ሰፊ ማሻሻያዎችን ያስተዋወቀ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ማጣራት( አቤቱታ ወንጀል መሆን አለመሆኑን ለማወቅ የሚደረግ ሥርዓት (አንቀጽ 70)፤ የእጅ ከፍንጅ ወንጀል ድርጊት በሚፈጸምበት ጊዜ የሚወሰዱ ፈጣን እርምጃዎች (አንቀጽ 71)፤ የምስክር ቃል የመቀበል እና የመመርመር ሥርዓት (አንቀጽ 77-80)፤ ብርበራ እና ዕቃን መያዝ (ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ብርበራ የሚደረግባቸው ሁኔታዎች (አንቀጽ 82)፤ የልዩ የማስረጃ ማሰባሰቢያ ዘዴዎች (ሠርጎ በመግባትና አብሮ በመሆን፣ በምስልና ድምፅ በመቅረጽ እና የስልክ መጥለፍ ያሉ ዘዴዎች (አንቀጽ 100-107)፤ የተጠርጣሪ አያያዝ እና ቃል አቀባበል ሥርዓት (አንቀጽ 108-122) ተጠቃሽ ናቸው። የቅጣት አፈጻጸም እና መሠየም የቀድሞው ሕግ የቅጣት አፈጻጸም ሥርዓት ውስን ነበር። አዲሱ ሕግ 6ኛ መጽሐፍ (አንቀጽ 296-315) የሚከተሉትን አካቷል፡፡ የሞት ቅጣት አፈጻጸም ሁኔታ (አንቀጽ 298-299)፤ የእስራት ቅጣት አፈጻጸም (አንቀጽ 300)፣ የእስራት ቅጣት መተላለፍ (አንቀጽ 302) እና መቋረጥ (አንቀጽ 303) ሁኔታዎች)፤ የገንዘብ ቅጣት አፈጻጸም (የገንዘብ ቅጣት የሚከፈልበት እና የክፍያ ቅደም ተከተል (አንቀጽ 304-305)፤ ንብረትን መውረስ ( ንብረት እንዲወረስ የሚደረግበት ሥርዓት (አንቀጽ 308)፤ መሠየም (የተቀጣ ወይም ይቅርታ የተደረገለት ሰው መልካም ስሙ እንዲመለስ የሚደረግበት ሥርዓት (አንቀጽ 314-315 ) ተዘርግቷል።
👉 የሰበር እና የመጨረሻ ፍርድ እንደገና ማየትበቀድሞው ሕግ ይግባኝ የነበረ ቢሆንም አዲሱ ሕግ ሥርዐቱን አስፋፍቶታል። በ7ኛ መጽሐፍ (አንቀጽ 316-350) የሚከተሉትን ያካትታል፡፡ ተከሳሽ በሌለበት የተሰጠ ፍርድ እንደገና የሚታይበት ሥርዓት (አንቀጽ 316-317)፣ ይግባኝ የሚቀርብበት ጊዜ፣ ሥርዓት እና የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሥልጣን (አንቀጽ 318-326)፣ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት ላይ የሚቀርብ ሰበር ማመልከቻ ሥርዓት (አንቀጽ 336-345)፣ የመጨረሻ ፍርድ እንደገና ማየት (የተፈረደበት ሰው ንጹሕ ሆኖ ሲገኝ ፍርዱ እንደገና የሚታይበትና የካሳ ሥርዓት (አንቀጽ 346-350))።
👉 አዲስ የተካተቱ ሥርዓቶች1. የጥፋተኛነት ድርድር፡- ተከሳሹ ጥፋቱን አምኖ ቀላል ቅጣት እንዲያገኝ የሚያስችል ሲሆንይህም ጊዜ በመቆጠብና ወጪን በመቀነስ ሁለቱም ወገኖች ተጠቃሚ ያደርጋል።
2. ዕርቅ እና ባህላዊ መፍትሄ፡- አነስተኛ ወንጀሎች በማኅበረሰቡ ውስጥ ተፈትተው ሰላም እንዲሰፍን ያግዛል።
3. ለወጣቶች ልዩ ሥርዐት፡- ወጣቶች ከትልቅ ወንጀለኛ ተለይተው፣ በማኅበረሰብ ውስጥ ተሃድሶ እንዲያገኙ ያደርጋል።
4. ልዩ የምርመራ ዘዴዎች፡- ለሙስና፣ ሽብርተኝነት፣ የተደራጁ ወንጀሎች ዘመናዊ የምርመራ ዘዴዎች ተፈቅዷል።
5. የአማራጭ ቅጣት፡- ከእስር ይልቅ የማኅበረሰብ አገልግሎት፣ የግዴታ ሥራ እና ሌሎች አማራጮች ተዘርግተዋል።
6. የፖሊስ እና የዐቃቤ ሕግ ኃላፊነት፡- ፖሊስ ሰብዓዊ መብቶችን በማክበር ምርመራ ማድረግና የተከሳሽን መብት ማስጠበቅ ያለበት ሲሆን ዐቃቤ ሕግ ደግሞ ምርመራን መቆጣጠርና ለተከሳሽ የሚጠቅም ማስረጃ ማድረስ አለበት።
7. ዓለም ዓቀፍ ትብብር፡- ወንጀለኞች ወደ ሌላ አገር ቢሸሹም በዚህ ሕግ መሠረት ሊያዙ እና ሊመለሱ ይችላሉ። እንዲሁም አሳልፎ መስጠት፣ የፍርድ ሒደት ማስተላለፍ፣ የውጭ ፍርዶች እውቅና ማግኘት ተችሏል።8. የመጨረሻ ፍርድ እንደገና እንዲታይ የሚደረግበት ሥርዓት፡- የተፈረደበት ሰው ንጹሕ ሆኖ ሲገኝ ፍርዱ እንደገና እንዲታይ የሚደረግበት ሥርዓት ተዘርግቷል፡፡
…
ещё
176
6
15 ноя, 21:54
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ቀን ሊከበር ነው! ⚖️💎
በሺዎች የሚቆጠሩ የፌዴራል ጠበቆች አምረው፣ ደምቀው እና ተውበው በሚታዩበት ልዩ ቀን‼️
ሁሉንም የፌዴራል ጠበቆች በአንድ ጥላ ስር የሚያሰባስበው ታላቅ "የጠበቆች ቀን" (Lawyers' Day) በቅርብ ቀናት ውስጥ በደማቅ ሁኔታ ሊካሄድ መሆኑን በዝግጅት ኮሚቴው ይፋ ሆነ! ✔️💎
ጠበቆች በሀገር ግንባታ፣ በሕግ የበላይነት እና በፍትህ ማረጋገጥ ሂደት ውስጥ የሚጫወቱት ሚና የማይተካ በመሆኑ፤ የሙያዊ ህብረት እና አወንታዊ ተፎካካሪነትን ማሳደግ፣ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በጋራ መፍትሔ መስጠት እና የሙያ ትስስራቸውን ማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ ይህ በአይነቱ ልዩ የሆነ የጠበቆች ቀን ተዘጋጅቷል‼️
ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ታሪካዊ መርሃ-ግብር የሙያውን ክብር ከፍ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ፣ በፌዴራል ጠበቆች ማህበር አዘጋጅነት ሁሉም ጠበቆች የሚታደሙበት የማይረሳ ምሽት ይሆናል!
🍷ይህ ደማቅ ፕሮግራም ምን ምን ያካተተ ነው?⁉️
🍽 የራት ግብዣ (Gala Dinner)
🎶 የተለያዩ ማራኪ የመዝናኛ ፕሮግራሞች
🤝 የኔትወርኪንግና የእርስ በእርስ ትውውቅ መድረክ
📺 የሀገር ውስጥና የውጭ ትልልቅ ሚዲያዎች ሽፋን
⚖️ የፍትሃዊነትና የጠበቆችን ማህበራዊ ሚና ማጎልበቻ ውይይቶች
ቀን እና ቦታው በጥቂት ቀናት ልዩነት ይፋ ይደረጋል!💡
#የኢትዮጵያፌዴራልጠበቆች #የጠበቆችቀን #FirstLawyersDay #EthiopianLawyers #Networking #GalaDinner #LegalExcellence
ещё
76
0
20 окт, 18:33
Продолжить анализ этого канала
- История роста подписчиков
- Просмотры и охваты публикаций
- Кто упоминает канал и кого упоминает он
- Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней