Не попадитесь на накрученные каналы! Узнайте, не накручивает ли канал просмотры или подписчиков Проверить канал на накрутку
Прикрепить Телеграм-аккаунт Прикрепить Телеграм-аккаунт

Телеграм канал «👑ደሩ (ሙእሚነት )የሰለፊያ ሴቶች መድራክ👑»

👑ደሩ (ሙእሚነት )የሰለፊያ ሴቶች መድራክ👑
1.2K
0
70
33
0
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة الم

🌷የሱነ ኡስተዞች ደአወ አጫጭር ቲለወ ጠቃሚ ምክሮች እንዲውም ያታላያዩ የምክር ፁሁፎች ይለቃቅበታል ኢንሸ አለህ ተውሂድ ያበለይ ይሆነል ኢንሻ አለህ ቢድአ ይራክሰል ሰዎች አወገዙ አወዳሱ ፅነ በሀቅ ለይብቻሀሀንም ብቶን እንከን ሀቅ በዞራበት እዞራለ‼️
Подписчики
Всего
5 717
Сегодня
0
Просмотров на пост
Всего
225
ER
Общий
3.93%
Суточный
2.69%
Динамика публикаций
Telemetr - сервис глубокой аналитики
телеграм-каналов
Получите подробную информацию о каждом канале
Отберите самые эффективные каналы для
рекламных размещений, по приросту подписчиков,
ER, количеству просмотров на пост и другим метрикам
Анализируйте рекламные посты
и креативы
Узнайте какие посты лучше сработали,
а какие хуже, даже если их давно удалили
Оценивайте эффективность тематики и контента
Узнайте, какую тематику лучше не рекламировать
на канале, а какая зайдет на ура
Попробовать бесплатно
Показано 7 из 1 177 постов
Смотреть все посты
Пост от 27.10.2026 23:12
43
0
1
🌸🌸
Пост от 27.10.2026 23:08
1
0
0
🌸🌷
Пост от 27.10.2026 19:23
28
0
0
በሰለፍያ መንሀጅ፣ በትክክለኛው ተውሂድ እና በነቢዩ (ﷺ) ሱና ላይ ፀንቶ መሞት ምንኛ መታደል ነው!
ወላሂ! ህይወትን ለዲን አሳልፎ፣ ሰዎችን ወደ ቀጥተኛው የሰለፎች መንገድ እየመሩ፣ ከቢድዓና ከአንጃዎች ጥምመት እየጠበቁ መሞት ትልቅ የሁስኑል ኻቲማ (የመልካም መጨረሻ) ምልክት ነው።

ዛሬ ታላቅ የሰለፍያ ሼኻችንን፣ የሱና አንበሳ እና የኡማው መካሪ በሞት ተለይተውናል።
ልባችን በሀዘን ተሰብሯል፣ አይናችንም ያለቅሳል፤ ነገር ግን አላህ የወሰነውን በጸጋ እንቀበላለን።

ይህቺ ዱንያ ለአንድም ሰው አትቀርም፤ ዋናው ትርፍ በትክክለኛው መንሀጅ ላይ ፀንቶ ለጌታ መገኘት ነው።

ያ አላህ! ይህንን የሱና እና የሰለፍያ ዳዕዋ ባለውለታ የነበሩትን ሼኻችንን ማራቸው፣ እዘንላቸው። ያስተማሩትንና ያገለገሉትን የዲን ስራ ሰደቃ ጃሪያ አድርግላቸው።

የላቀችውን ጀነተል ፊርደውስን ወፍቃቸው።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለተማሪዎቻቸው እና ለመላው የሰለፊያ መስመር ተከታዮች ፅናቱንና ሰብሩን ይስጠን።

ውድ የቻናላችን ተከታዮች፣ ለሼኻችን በዱዓ አንርሳቸው

telemetr.me/https_Nissa_aselefyea
telemetr.me/https_Nissa_aselefyea
Пост от 27.10.2026 17:47
19
0
1
💦<<<<ኢላሂ>>>>💦

ልቤ ሲደርቅብኝ ሳምፅህ በወንጀል

እርቂ ከደጅህ አንተን ከመከጀል

ድክመት ተሰምቶኝ አንተን ለመከጀል

ስብራት ተሰማኝ አንተን በመወጀል ፣

ከትዛዝህ ራቅኩ አመፅኩህ ያጀባር

ግን አንተ አዛኝ ነህ ጠንገንከኝ በስቲግፍር

እዝነትን ለገስከኝ ዳግም  ለመወልወል

ፍራት እንዳይዘኝ እንዳልሰባበር

ከዴጅህ እንድቆም አገዝከኝ የገፍር

እዝነተ ሰፊ ነህ  ያረቢ ያጀባር

ቀና አድርገህኛል ውድቄ እንዳልቀር

ካንተ የተጠጋ ማንም አይሰበር

ሲርቅህ ነው እንጅ የሚለው ስብርብር
telemetr.me/Yselefeyoch_channel
telemetr.me/Yselefeyoch_channel
Пост от 27.10.2026 08:46
16
0
0
👉 ከሸይኻችን ሞት ምን ተማርን ?

ሸይኽ ሙሐመድ ዐረብ የሚገርሙ ሰው ነበሩ ። በስነምግባራቸው ፣ በመተናነሳቸው ፣ በፈገግታቸው ፣ ሁሉንም በውዴታ አይን በማየታቸው ፣ ለሁሉም በመታዘዛቸው የተለዩ ነበሩ ።
በጣም የሚገርመው ሸይኽ ሙሐመድ በሐሳብ ብቻ ሳይሆነ በተግባርም ጭምር ለሞት የተዘጋጁ ሰው ነበሩ ። ባለፈው አመት ዱና ላይ ከመሻኢኾች ጋር ለመገናነኘት አስፈሪውን የአካባቢው ሁኔታ አቋርጠው ሲመጡ ከፈናቸውን ይዘው ነበር የወጡት ! ቀናቸው አልደረሰም ነበርና ከፈኑን ይዘውት ዱና መጥተው ከመሻኢኾች ጋር ተገናኝተው ይዘውት ተመልሰው ለዛሬ ሆናቸው ! ይህ ማለት ሸይኽ ሙሐመድ ሁሌም ከፈን አብሯቸው ይኖር ነበር ማለት ነው ።
የአላህ ውሳኔ ቅሮት የለውምና ቀኑና ሰአቱ ሲደርስ እሱ በፈለገው ሰበብ ይህችን ምድር ተሰናበቱ ።
ውድ ሰለፍዮች የሱና ዑለሞች ሞት የኡማው ሞት ነው ። ወደ ሱና የሚጣራ ከቢዳኣ የሚያስጠነቀቅ ፣ ወደ ተውሒድ የሚጣራ ከሽርክ የሚያስጠነቅቅ ዓሊም ሲሞት ሲንቀሳቀስባቸውና ዒባዳ ሲያደርግባቸው የነበሩ ቦታዎች ያለቅሳሉ ! ኸይር ስራው ከምድር ወደ ሰማይ ይሄድ ስለነበር ሲቋረጥ ሰማይና ምድር ያለቅሳሉ ! እንደነዚህ አይነት ዑለሞች ለኡማው ብርሃን ናቸውና የሚተካቸው ከሌለ በእነርሱ ብርሃን ሲጓዝ የነበረው ማህበረሰብ ጨለማ ይውጠዋል ። ለዚህ ነው የዑለሞች ሞት የኡማው ሞት ነው የሚባለው ።
ውድ ሰለፍዮች ኒዕማ በመወገዱ እንጂ አይታወቅም እንደሚባለው የዑለሞቻችንን ጥቅም አውቀን በህይወት እያሉ እንጠቀምባቸው ፣ እናክብራቸው ፣ እናግዛቸው ፣ ደረጃቸውን እንወቅላቸው ፣ ከስር ስራቸው እየሄድ ከብርሃናቸው ፍንጣቂ እናጠራቅም እንጂ የቆሻሻ ገንዳ ተሸክመን እየዞርን ድክመታቸውን እየለቀምን አናጠራቅም ። ይህ እነርሱን ባይጎዳም የኛን ዱንያና አኼራ ያበላሻል ። ደካማ ጎን የሌለበት ዓሊም የፈለገ ሰው ከመላኢካ ጋር ሄዶ ይኑር ! ምክንያቱም የሰው ልጅ ሆኖ ደካማ ጎን የሌለበትና የማይሳሳት የለምና ! እንዲህ አይነቱ ተግባር ድንገት ለሚመጣው ሞት መዘጋጀት ካለበት ሰው አይጠበቅም ። ምክንያቱም የሰዎችን ደካማ ጎን የሰበሰቡበት የቆሻሻ ገንዳ ለቀብር ስንቅ የሚሆን የለበትምና ቆሻሻ ገንዳውን ጥለን ራሳችንን በተውበት አፅድተን ለቀብር የሚሆነንን ስንቅ እያጠራቀምን ለቀብራችን መዘጋጀት ይኖርብናል ።
አው ሞት ቀጠሮ የለውም ፣ ሞት እኛ የያዝነውን ፕሮግራም እስክንጨርስ አይጠብቅም ! እኛ ወደርሱ እየሄድን ነው እርሱም ወደኛ እየመጣ ነው የት እንደምንገናኝ አናውቅምና ጉዟችን የታሰበበትና የተዘጋጀንበት መሆን ይኖርበታል ።
ከሸይኻችን ሞት ሁሌም ለሞት መዘጋጀትን ነው የተማርነው ። እሳቸውን አላህ በእዝነቱ ይቀበላቸው ። ከወደዳቸው ባሮቹ ጋር ያኑራቸው ። የሳቸው መጨረሻ ያማረ ለመሆኑ አላህ ምልክቶች አሳይቶናል ። በዱንያ ፣ በጥቅም ሳይሸነገሉ ለሱና እየታገሉ እያሉ ወደ አኼራ ሄደዋል ። አሟሟታቸው ደግሞ ሸሃዳ የሚያስከጅልላቸው ነው ።
ማናችንም መጨረሻችንን አናውቅም ። ነገ ካለንበት ሐቅ እናፈንግጥ ወይም እንፅና የሚያውቀው አላህ ብቻ ነው ። አንድ ሰው መጨረሻው አማረ የሚባለው በሐቅ ላይ ሆኖ ሳይቀየርና ሳይቀይር እቺን ምድር ሲሰናበት ነው ። ታዲያ የኛ ሁኔታ ምን ይሆን የሚለው የሁላችንም ፍርሃት ሊሆን ይገባል ።
በሀገራችን ዙሪያ ያሉ ሰለፍዮች ሸይኻችንን ለመቅበር አካባቢው ያለበት ሁኔታ ስለማይፈቅድ ውስጣችን እየታመመ የምንችለው ዱዓእ ማድረግ ብቻ ሆነ ። በአቅራቢያና አካባቢ ያላችሁ ሸይኻችንን መቅበር የምትችሉ ሰለፍዮች በሙሉ ሶላተል ጀናዛ ሰግዳችሁ እንድትቀብሯቸው አደራ እንላለን ። ክስተቱ ከባድ ቢሆንም ዘመድ አዝማድ ሶብር አድርጎ ከአላህ ምህረትን እየለመነላቸው ጀናዛቸው አላህን በሚያስደስት መልኩ መሸኘት አለበት ። በህይወት እያሉ የኖሩትን ሱና ዛሬ በሰው እጅ የገባው ጀናዛቸው ሊያጣው አይገባም ።
ውድ የቱሉ ጋና ሰለፍዮች ሆይ አላህ ፅናቱን ይስጣችሁ አደራ ሸይኻችንን በሱና ሸኟቸው ። የትኛውንም እንቅስቃሴ በሱና እንዲሆን የበኩላችሁን አድርጉ ። ቤተሰባቸውን በማፅናናት ከመቀበራቸው በፊት እዳ ካለባቸው ማጣራት ምናልባት ያስቀየሙት ካለ አውፍ እንዲላቸው በማድረግ መልካም አሻራ አኑሩ ።
በማንኛውም የሚያስፈልግ ነገር መላው ሰለፍይ ከጎናችሁ ነውና አብሽሩ ። በተለይ እዳ ካለባቸው አጣርታችሁ ቶሎ ከመቀበራቸው በፊት ንገሩን በአላህ ፈቃድ ለመክፈል ዝግጁ ነን ።
አላህ የሁላችንንም መጨረሻ ያሳምርልን ።

telemetr.me/bahruteka
Пост от 26.10.2026 22:32
50
0
2
▫️ ሸይኽ መሀመድ አረብ ረሂመሁሏሁ

♦️በአል_ወሰጢያ መድረሳ አለም ባንክ በንግድነት ተገኝተዉ ከመግሪብ በኋላ ያደረጉት ሙሀዷራ

ርዕስ:- የአላህ መልክተኛ ያመጣላቹሁን ነገር ያዙ የከለከላቹሁን ነገር ተከልከሉ ከሚለዉን በመነሳት ተዉሂድን እና ሽርክን የዳሰሱበት አጠር ያለ መሳጭና ጣፋጭ ምክር

ሼር ሼር አርጉት ሁሉም ሰለፍይ ጋር እንዲዳረስ አላህ አጅራቸዉን ከፍያድርግላቸዉ የጥሩ ስራቸዉን ቀጣይነቱን ያብዛዉ ማረፍያቸዉን በጀነት ያድርግላቸዉ

telemetr.me/Abuabdellah_As_Selefiy
Видео/гифка
Пост от 26.10.2026 21:19
59
0
1
በሸይኽ ሙሀመድ ዐረብ #ከወለጋ
الاستقامة في الدين
✅በድን ላይ መፅናት
በሚል ርዕስ የተደረገ ጣፋጭ ሙሀደራ ነው።

"ወይፈን ከደበሰቀው አባት በሬ ያማጠጠው" እንደሚባለው ሀቅ በትልቅ ሰው ሲወራ እንደት ደስ ይላል!

صفر ١٤٤٨ه‍ حواسا (ነሀሴ-3-2018)
telemetr.me/hutemariwochchannel
telemetr.me/hutemariwochchannel
-------------------------------------------
إنا لله وإنا إليه راجعون، إن العين لتدمع وإن القلب ليحزن، وإنا على فراقك لمحزونون، ولا نقول إلا ما يرضي ربنا

اللَّهُمَّ اغْفِرْ شيخنا وَارْحَمْهُ وَعَافِهِ وَاعْفُ عنْه، وَأَكْرِمْ نُزُلَهُ، وَوَسِّعْ مُدْخَلَهُ، وَاغْسِلْهُ بالمَاءِ وَالثَّلْجِ وَالْبَرَدِ، وَنَقِّهِ مِنَ الخَطَايَا كما نَقَّيْتَ الثَّوْبَ الأبْيَضَ مِنَ الدَّنَسِ.
Звукозапись
Смотреть все посты