Не попадитесь на накрученные каналы! Узнайте, не накручивает ли канал просмотры или подписчиков Проверить канал на накрутку
Прикрепить Телеграм-аккаунт Прикрепить Телеграм-аккаунт

Телеграм канал «💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀»

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
1.6K
50
1.2K
592
1.1K
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Подписчики
Всего
8 798
Сегодня
-2
Просмотров на пост
Всего
478
ER
Общий
5.43%
Суточный
3.55%
Динамика публикаций
Telemetr - сервис глубокой аналитики
телеграм-каналов
Получите подробную информацию о каждом канале
Отберите самые эффективные каналы для
рекламных размещений, по приросту подписчиков,
ER, количеству просмотров на пост и другим метрикам
Анализируйте рекламные посты
и креативы
Узнайте какие посты лучше сработали,
а какие хуже, даже если их давно удалили
Оценивайте эффективность тематики и контента
Узнайте, какую тематику лучше не рекламировать
на канале, а какая зайдет на ура
Попробовать бесплатно
Показано 7 из 1 612 постов
Смотреть все посты
Пост от 26.10.2026 15:39
8
0
0
Видео/гифка
Пост от 26.10.2026 13:13
28
0
2
Видео/гифка
Пост от 26.10.2026 07:58
38
0
0
👉ከሰዎች እይታ በራቅሽ ቁጥር ወደ አላህ እየቀረብሽ ነው የምትሄጅው!!

~
Пост от 25.10.2026 22:36
95
0
2
🔖የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

   “ከሰዎች ሁሉ እጅግ ከባድ ቅጣት ያለባቸው ሁለት አይነት ሰዎች ናቸው። ባሏን ያመፀች ሴት እና ሰዎች እርሱን(በሐቅ) እየጠሉት ኢማም ሆኖ ያሰገደ።”
📚[ሰሒሁ አትቲርሚዚ (359)]

telemetr.me/https_Asselfya
Пост от 25.10.2026 13:55
46
0
0
ዑመር ብኑል ኸጣብ የደካሞች ጋሻ!
~
አገሩ ወዲያ ነው - ከመካ በረሃ
ክንዱ የሚፋጀው - የሚያሰኘው ውሃ!
.
ዑመር ብኑል ኸጣብ ከመስለማቸውም በፊት በሃይለኝነታቸው በአይበገሬነታቸው የሚታወቁ ነበሩ። አቡ ጀህልም እንዲሁ ነበር። አቡ ጀህል ስሙ ዐምር ብኑ ሂሻም ብኒል ሙጊራ አልመኽዙሚይ ይባላል። ነብዩ ﷺ የነዚህን ሁለት ሰዎች መስለም በእጅጉ ይፈልጉ ነበር። ይህም የሆነው በጊዜው እንግዳ ለሆነው ኢስላም ክብርና አይደፈሬነትን ይሰጣል በሚል መነሻ ነበር። ለዚህም ነበር የአላህ መልእክተኛ ﷺ “አምላኬ ሆይ! ኢስላምን ከነዚህ ሁለት ሰዎች አንተ ዘንድ በተወደደው አስከብረው'' ማለታቸው። በአቡ ጀህል ወይም በዑመር ብኑል ኸጣብ! ከሁለቱ እሱ ዘንድ የተወደደው ዑመር ሆነ፡፡ [ቲርሚዚይ፡ 3681]

ኢብኑ መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- “ዑመር እስከሚሰልም ድረስ ከዕባ አካባቢ መስገድ አንችልም ነበር፡፡ ዑመር ሲሰልም ግን ቁረይሾችን ተፋለማቸው፡፡ ከዚያም ከዕባ ዘንድ ሰገደ፡፡ ከሱም ጋር ሰገድን።” “ዑመር ብኑል ኸጣብ ከሰለመ ጀምሮ የተከበርን ሆነናል፡፡” [ቡኻሪይ፡ 3684]

ኡሙ ዐብዲላህ ቢንት አቢ ሐስማህ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ትላለች:- “ወላሂ ወደ ሐበሻ ምድር ልንሰደድ እየተዘጋጀን ነበር፡፡ ባለቤቴ ዓሚር የሆነ ጉዳያችንን ሊፈፅም ወጥቶ ሳለ ዑመር መጣና ቆመ፡፡ በሺርኩ ላይ እንዳለ ነው፡፡ ከሱ ፈተናና ስቃይ ይደርስብን ነበር፡፡ ከዚያም፡

* “የምርም መጓዛችሁ ነው ኡሙ ዐብዲላህ?” አለኝ፡፡
- “አዎ ወላሂ! አላህ መውጫ እስከሚያደርግልን ድረስ ከአላህ ሀገሮች ወደ አንዱ እንወጣለን፡፡ አስቸገራችሁን አሰቃያችሁን!” አልኩት፡፡
* “አላህ አብሯችሁ ይሁን” አለ፡፡
ቀድሜ አይቸው የማላውቀው መቆርቆር አየሁበት፡፡ ከዚያም ተመልሶ ሄደ፡፡ ሳስበው መውጣታችን በርግጥም አሳዝኖታል፡፡ ባለቤቴ ዓሚር የሄደበትን ጉዳያችንን ፈፅሞ ሲመጣ፡

- “የአብደላህ አባት ሆይ! እንዲያው ዑመርን ቅድም ብታየው፣ ለኛ መቆርቆሩንና ማዘኑን” አልኩት፡፡
* “ይሰልማል ብለሽ ከጀልሽ እንዴ?” አለኝ፡፡
- “አዎ” አልኩት፡፡
* “የኸጣብ አህያ ሳይሰልም ያ ያየሽው ሰውዬ አይሰልምም!” አለኝ፡፡ “በኢስላም ላይ የሚያደርሰውን ጭካኔና ድርቅና በማየት ተስፋ ቆርጦ ነው።”

ዐብዱላህ ብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡-

“ዑመር ሲሰልም ቀድሞ በክህደት የተቀመጠባቸውን ስብሰባዎች አንድም ሳያስቀር መስለሙን ሊያውጅባቸው ለነብዩ ﷺ ቃል ገብቶ ነበር፡፡ እናም በሰለመ ጊዜ፡
- 'ከቁረይሽ እጅግ ወሬ አራጋቢ የሆነው ማነው?' ሲል ጠየቀ፡፡
* 'ጀሚል ብኑ መዕመር ነው' አሉት፡፡
ቀጥታ ወደሱ ሄደ፡፡ ምን እንደሚሰራ ለማየት ከስር ከስሩ ተከትየው ሄድኩኝ፡፡ በጊዜው የማየውን ሁሉ በደንብ የማስተውል ልጅ ነበርኩ፡፡ ጀሚል ጋ መጣና፡
- 'ጀሚል ሆይ! መስለሜን አወቅክ ወይ? ወደ ሙሐመድ ሃይማኖት ገባሁ'ኮ!' አለው፡፡

ወላሂ ከዚያ በኋላ ጀሚል ለዑመር አልመለሰም፡፡ ቀጥታ ኩታውን እየጎተተ ወጣ፡፡ ዑመር ተከተለው፡፡ እኔም ዑመርን ተከተልኩት፡፡ ጀሚል ከመስጂዱ በር ቆመና ድምፁን በጣም ከፍ አድርጎ ጮኸ፡-

* 'የቁረይሽ ህዝብ ሆይ! አዋጅ! የኸጣብ ልጅ አፈንግጧል' አለ፡፡ በከዕባ ዙሪያ ተሰብስበው ነበር፡፡ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ከኋላው እየተከተለ፡
- “ዋሸ! ባይሆን እኔ በርግጥም ሰልሜያለሁ፡፡ ከአላህ ውጭ በሐቅ የሚመለክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ እንደሆነ መስክሬያለሁ” አለ።

ዑመርን ሮጠው ከበቡት። ሲታገላቸው ሲታገሉት እኩለ ቀን ሆነ፡፡ ዑመር አቃተውና ቁጭ አለ፡፡ በራሱ ላይ ወጡበት፡፡ እሱ ይህኔ
* “የታያችሁን ሁሉ አድርጉ፡፡ በአላህ እምላለሁ! በርግጠኝነት ሶስት መቶ ወንዶች ብንሆን መካን ወይ እንተውላችኋለን፣ ወይ ትተውልናላችሁ!” አላቸው። ከሁለት አንዳችን ይወጣል እያላቸው ነው።

በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ አንድ የቁረይሽ ሽማግሌ መጣ፡፡ የተቀለመ ሙሉ ልብስ ለብሷል፣ ቀሚስ ጋር፡፡ ቀጥታ ካጠገባቸው ቆመና፡
- “ምን እየሆናችሁ ነው?” አላቸው፡፡
* “ዑመር አፈንግጦ ነው” አሉት፡፡
- “ቢሆንስ?! እረፉ! አንድ ሰው ለራሱ የሆነ ነገር መረጠ፡፡ ታዲያ ምንድን ነው የምትፈልጉት? ይህን ሰውዬ እንዲህ ስታደርጉት የዐዲይ ጎሳዎች ዝም የሚሉ መሰላችሁ? ከሰውየው ዞር በሉ!” አላቸው፡፡
ከዚያም በአላህ ይሁንብኝ ልክ ከላዩ ላይ እንደተገፈፈ ልብስ ሆኑ! (ባንዴ ለቀቁት)፡፡ አባቴ ወደ መዲና ከተሰደደ በኋላ:
* “አባዬ ሆይ! ያኔ መካ የሰለምክ እለት እነዚያን ሲታገሉህ የነበሩትን ሰዎች የተቆጣቸው ሰውዬ ማነው?” አልኩት፡፡
- “ያማ አልዓስ ብኑ ዋኢል አሰህሚ ነው የኔ ልጅ” አለኝ፡፡ (አልዓስ ብኑ ዋኢል አሰህሚ ማለት የብልሁ ፖለቲከኛ የዐምር ብኑል ዓስ አባት ነው።)
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 1/2006)
የቴሌግራም ቻናል፦
telemetr.me/IbnuMunewor
telemetr.me/IbnuMunewor
Пост от 25.10.2026 13:55
1
0
0
ወረፋን አለመጠበቅ
~
ወረፋ በሚጠበቅበት የትኛውም ቦታ ላይ የቀደሙ ሰዎች እያሉ በጉልበትም ይሁን በመሸወድ ቀድሞ መግባት ነውረኛ ተግባር ነው። የታክሲ፣ የውሃ፣ የክፍያ ቦታዎች፣ ሃኪም ቤቶች፣ የተለያዩ መስሪያ ቤቶች፣ ... ከኛ የቀደሙ ተገልጋዮች እያሉ በየትኛውም ጤነኛ ባልሆነ መንገድ ቀድሞ ተጠቃሚ መሆን አላህን ለሚፈራ ሰው ሞኝነት እንጂ ብልጠት አይደለም።

ይልቁንም ነፍሰ ጡር እና ልጅ የያዙ እናቶችን፣ ህመምተኞችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ አዛውንቶችን ማስቀደም አጅር ያለው ተግባር ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
telemetr.me/IbnuMunewor
telemetr.me/IbnuMunewor
Пост от 25.10.2026 12:13
14
0
0
telemetr.me/AbumuslimAlarsi/14608
Видео/гифка
Смотреть все посты