Аналитика Telegram-канала
Подписчики
2 431
Охват за 24 ч
601
ER за 24 ч
24,72%
Публикаций
601

Динамика подписчиков

7 дней 30 дней 6 месяцев Больше
27 окт30 окт2 ноя
Показаны последние 7 дней Больше истории →

Охваты публикаций

29.1029.1029.1029.1030.1031.10
219
Средний охват
450
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале Больше статистики →

Упоминания

10
Упоминаний
8
Из них репостов
3
Каналов
Все упоминания

Последние посты

3 из 601 2 из 601
በዛሬው ዕለት ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤው የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ገዳምን አስመልክቶ በቀረበው አጀንዳ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ (#EOTCTV ጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ.ም) የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዕለታዊ ውሳኔዎችን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት (#EOTCTV )ማብራሪያ የሰጡት  የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል (ረ/ፕ )  በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥንታውያን ገዳማት ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል በግንቦት የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ በተሰጠው ውሳኔ መሠረት በጥቅምት 2019 ዓ/ም በሚያደርገው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከሁሉም ወገን ያሉ ተወካዮች ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በአካል ቀርበው እንዲያስረዱ መመሪያ መተላለፉን  አስታውቀዋል ፡፡  ይህንኑ ተከትሎ ምልዓተ ጉባኤው በአካል የተገኙትንና በጽሐፍ የቀረቡትን መግለጫዎች በቅደም ተከተል በመስማት እና የሁሉንም ሰነዶች በመቀበል ሰፊ ውይይት ማድረጉ የተገለጸ ሲሆን ፤  በዚሁ መሠረት ችግሩን በዘላቂነትና በሰላም ለመፍታት እንዲያስችል የሕግ ባለሙያዎች በጥንቃቄ በሚያዘጋጁት ሰነድ መካተት የሚገባቸው ሐሳቦች በዝርዝር በማስቀመጥ፤ ሁለት ብፁዓን አባቶች ማለትም አንደኛ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ሀገረ ሰብከትና ሐዋሳ ታቦር መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ሰብከትና የወልቂጤ አቡነ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በላይ ሊቀ ጳጳስ በጋራ በመሆን ችግሩን እንዲፈቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ወስኗል ሲሉ መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል (ረ/ፕ) ዕለታዊ ማብራሪያቸውን አጠቃለዋል። @ የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/
ещё
450 1 31 окт, 16:46
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  ለጋምቤላ ፣ ቄለም ወለጋ ሀገረ  እና ለሰቲት ሁመራና ወልቃይት ጠገዴ ሀገረ ስብከት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን መደበ። በብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ላይ ቀኖናዊ ውሳኔ አስተላልፏል ። (#EOTCTV ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ.ም) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ/ም ባደረገው ስብሰባ በአጀንዳ ቅደም ተከተሉ መሠረት ጉባዔውን ቀጥሎ የተለያዩ ውሳኔዎች ማሳለፉን ለመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት (#EOTCTV )የገለጹት የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል (ረ/ፕ ) ገለጹ። መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል (ረ/ፕ ) በዕለታዊ መግለጫቸው በዛሬው ዕለት ጉባዔው በመጀመሪያ የተመለከተው ቀደም ሲል በአጀንዳ ተይዞ ለምልአተ ጉባኤ ቀርቦ የነበረውን የጋምቤላ ሀገረ ስብከትንና የቤንሻንጉል ጉምዝ አሶሳ ሀገር ሰብከትን የተመለከቱ አጀንዳዎች ሲሆን ፤ በወቅቱ የአጣሪዎች ሪፖርት በንባብና በቪድዮ መቅረቡን አስታውሰው ፤ በአጣሪ ልዑካን ከማስረጃዎች ጋር የቀረቡ የሰነድ ማስረጃዎች፣ የሂሳብና ንብረት ቁጥጥር ሪፖርት ፣ ከሊቀውንት ጉባኤ ፣ ከሕግ አገልግሎትና ከሕግ አማካሪ የቀረቡ የውሳኔ ሐሳቦች በቅደም ተከተል ከቀረቡ በኋላ የአህጉር ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ለተፈጠሩት ጥፋቶች በጉባኤው ፊት በአካል ቀርበው ይቅርታ በመጠየቃቸውና ፣ የይቅርታ ጥያቄያቸውንም በቀረቡት የቀኖና  ጥሰቶች፣ የአስተዳደርና ፣ የአሠራር  ክፍተቶች በመጥቀስ በዛሬው እለት የይቅታ ጥያቄምታቸውን  ለምልአተ ጉባኤው በጽሐፍ አቅርበዋል ። ምልአት ጉባኤውም ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ያቀረበትን የይቅርታ ደብዳቤ በንባብ ከሰማ በኋላ በየርዕስ ጉዳዩ ተገቢውን የቀኖና እና አስተዳደራዊ ውሳኔ ለመስጠት በስፋት በመወያየት የሚከተሉትን ወስኗል። በዚህም መሠረት የብፁዕነታቸውን የይቅርታ ደብዳቤ በመቀበልና የቀኖና ውሳኔ በመስጠት ፤ አንደኛ ፡ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ለቀርቡባቸው የቀኖና ጉዳዮች እስከ ግንቦት 2019 ዓ/ም የርክበ ካህናት ምልእተ ጉባኤ ድረስ በየትኛውም ሀገረ ስብከት ሳይመደቡ በደብረ ሊባኖስ ቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም በጸሎትና በሱባኤ ተወስነው እንዲቆዩ ፣ ሁለተኛ ፡ ብፁዕነታቸው ለአህጉር ስብከት ማስረከብ ይገባቸው የነበሩ መኪኖችን ወደ ገዳም ከመሄዳቸው በፊት ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅለይ ቤተ ክህነት እንዲያስረክቡ ፣ ሦስተኛ ፡ ከሂሰብ ጋር የተያያዘው እስከ ግንቦት 2019 ዓ/ም የርክበ ካህናት ምልእተ ጉባኤ በሚገባ ተጠርቶ እንዲቀርብ እና ዉሳኔ እንዲያገኝ ምልእተ ጉባኤው ወስኗል ብለዋል። መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል (ረ/ፕ ) ለመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት (#EOTCTV ) በሰጡት መግለጫ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በመቀጠል የተመለከተው ክፍት በሆኑ አህጉር ስብከት ብፁዓን አባቶችን መመደብ ሲሆን ፤  በዚሁ መሠረት ፡  አንደኛ ፡ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ለወደፊቱ አባት እስኪመደብ ድረስ የቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከትን ደር,በው እንዲመሩ ሁለተኛ ፡  ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ (ዶ/ር)  የጋምቤላ ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ ሦስተኛ ፡ ብፁዕ አቡነ ሰላማ የሰቲት ሆመራና ወልቃይት ጠገዴ ሀገረ ስብከትን ደር,በው እንዲመሩ ፣ በማለት ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል ብለዋል፡፡ አክለውም በዛሬው ዕለት ምልአተ ጉባኤው የአዲስ አባባ ሀገረ ስብከትን የተመለከተ የአጣሪዎች ሪፖርት በንባብ በመሰማት ፣ የብፁዕ አቡነ ሕርያቆስንና አብረው ይሠሩ የነበሩ የተወሰኑ የአስተዳደር ጉባኤ አባላትን ምላሽ በማዳመጥ  ወይይቱን ቀጥሏል ሲሉ ዕለታዊ መግለጫቸውን አጠቃለዋል። @ የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/
ещё
430 3 7 30 окт, 21:02
Фото
ещё
128 0 29 окт, 19:43
Больше постов

Продолжить анализ этого канала

  • История роста подписчиков
  • Просмотры и охваты публикаций
  • Кто упоминает канал и кого упоминает он
  • Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней