Аналитика Telegram-канала
Подписчики
340
Публикаций
328
Динамика подписчиков
7 дней
30 дней
6 месяцев
Больше
27 окт30 окт2 ноя
Показаны последние 7 дней
Больше истории →
Охваты публикаций
08.1013.1014.10
98
Средний охват
129
Лучший результат
Показаны 3 публикации — последние в канале
Больше статистики →
Упоминания
2
Упоминаний
1
Из них репостов
1
Каналов
2
Упоминаний
0
Из них репостов
2
Каналов
Последние посты
3 из 328 2 из 328"የምርትና የአቅርቦት ዋጋ ከቁጥጥር ውጭ ለመውጣት እያቆበቆበ ይገኛል..."
(ሙሼ ሰሙ)
በኢትዮጵያ ለጥቂት ጊዜ ያህል የዘለቀው ባለ አንድ አሃዝ የዋጋ ግሽበት (9.5%) ከዓመት በኋላ በተለይ ካለፉት ሶስት ወራት ወዲህ እንደገና በማገርሸት እንደ "Silent killer" የዜጎችን የመግዛት አቅም በእጅጉ መፈታተኑን አጠናክሮ ቀጥሎበታል።
የመንግስት ኦፊሴላዊ መረጃዎች የዋጋ ግሽበት መቀነሱን በተደጋጋሚ እየዘገቡ ቢሆንም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃና በቋሚ ገቢ የሚተዳደሩ ዜጎች የኑሮ ሁኔታ አሳሳቢነት ትኩረት የሚሻ መሆኑን መሸሽ በማይቻልበት ደረጃ እንደገና እያገረሸ ነው።
ምንም እንኳን አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ከ2022ቱ በከፍተኛ ደረጃ ከናረበት (ከ34% በላይ) ወደ ነጠላ አሃዝ (9.4%) በ2026 መጀመሪያ ላይ ቢወርድም፣ በቅርቡ የተከሰቱ መዋቅራዊ ጫናዎች (Structiral Shocks) ግሽበቱ እንደገና በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያገረሽ እያደረጉት ነው።
በዚህም ምክንያት እስከ ኦገስት 2026 (የ September Report ገና አልወጣም) ድረስ ዓመታዊው የዋጋ ግሽበት መጠን ከአምና ተመሳሳይ ጊዜ 13.6% ወደ 15.1% ከፍ ብሏል።
መንስኤዎቹም:-
1. ሪፖርትና መሬት ላይ ያለው የዋጋ "ተቃርኖ" (Paradox) “The Anatomy of Inflation in Ethiopia: Structural Shocks, Policy Credibility, and the Path to Price Stability” (Research Report 004/2026 ያጤኗል)
በኦፊሴላዊ ስታቲስቲክስ የሚነገረው የግሽበት መረጋጋት ዜናና እና በተጨባጭ መሬት ላይ የሚታየው የዋጋ ንረት መካከል ያለው ልዩነት ከፍተኛ መሆኑ እየታወቀ እውነታውን ተቀብሎ ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ ፈቃደኝነት መጥፋት።
የዋጋ ግሽበት መጠኑ ቀነሰ ቢባልም የዋጋ ጭማሪው ፍጥነቱን መቀነሱን እንጂ የአቅርቦቶች መረጋጋትን ወይም " ዋጋ መቀነስን" አያሳይም። የምግብ እና አልኮል-ያልሆኑ መጠጦች የሸማቾች የዋጋ ቅርጫት (consumer price basket) 54% ድርሻ እንደመያዛቸው መጠን በቅርቡ የታየው የምግብ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ (እንደ ስኳር፣ ስ፣ ዶቦና ዘይት ባሉ ምርቶች ላይ) የዜጎችን አጠቃላይ አቅም በከፍተኝ ሁኔታ እየተፈታተነ ይገኛል።
2. ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ዋጋ ቅነሳ (Devaluation) በአለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) በሚደገፈው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እቅድ ማዕቀፍ መሰረት ዶለርን በብር ለመለወጥ ዛሬ የሚያስፈልገው ኢትዮጵያ የብርን መጠን exchang Beaurau 177 ምንዛር ተመን መሰረት (Birr price of one US dollar increased) በ210.53% መጨመሩና Nominally the birr's dollar value 63% ግሽበት ማሳየቱ የምንዛሬ ተመን ማሻሻያውን ተከትሎ የመጣው የብር ዋጋ መውረድ ቀጣይነት ባለው መልክ የመግዛት አቅም በመሸርሸር የዋጋ ንረቱን ለመባባሱ ተጠቃሽ ምክንያት መሆኑ ቀጥሏል። (በኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር (EEA) የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው 83.5% የሚሆኑ ባለሙያዎች ይህንን አመክንዮ ይደግፉታል።)
በተለይ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ በምርት ማስመጣት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ የገንዘብ የመግዛት አቅም መሸርሸር ከውጭ በሚገቡ አስፈላጊ ሸቀጦች ላይ የማይታይ ግብር ሆኖ የዜጎችን አቅም እያዳከመ ይገኛል።
3. የአቅርቦት መስተጓጎል፣ የሰላም እጦት፣ የነዳጅ እጥረትና ከአገር ውጭ የሚከሰቱ የጂኦ-ፖለቲካዊ ክስተቶች፣ በተለይም ከመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ጋር የተያያዘው የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል የትራንስፖርት ወጪን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር ማድረጉ በአገር ውስጥ የሚመረቱ የግብርና ምርቶችን ወደ ከተማ ማዕከላት ለማጓጓዝ የሚወጣውን ወጪ በከፍተኛ ደረጃ እንዲንር ማድረጉ፣ በችርቻሮ ዋጋም ላይ ቀጥተኛ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ እንዲኖር ክፍተት መፍጠሩ።
4. ከፍተኛ የሆነ ክልላዊ ልዩነት:- የዋጋ ግሽበት በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ላይ እኩል ተጽዕኖ እያሳደረ አለመሆኑ ሌላው ተጠቃሽ ነው። የሀገሪቱ አማካይ የግሽበት መጠን 15% አካባቢ ቢሆንም፣ እንደ ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ (25.57%)፣ አዲስ አበባ (24.25%) እና ድሬዳዋ (24.05%) ያሉ አካባቢዎች ላይ የዋጋ ንረቱ እጅግ ከፍተኛ እና ያልተመጣጠነ ጫና እያሳደረ ይገኛል። በእነዚህ ክልሎች የሚኖሩ በቋሚኘገቢና በደመወዝ የሚተዳደሩ የከተማ ነዋሪዎች፣ በከተሞቹ ውስጥ ባለው እጅግ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ሳቢያ ቋሚ ደመወዛቸው በከፍተኛ ፍጥነት ዋጋ እያጣ ይገኛል።
ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ለገጽታ ግንባታ ሲባል የችግሩን ጥልቀትና ስፋት አምኖ በመቀበልና ተመጣጣኝ የመፍትሔ አቅጣጫ ቀይሶ የዜጎችን ሕይወት ከኑሮ ውድነት፣ ከስቃይና ከፈተና ለመታደግ ቁርጠኝነት መታጣት ችግሩን በማወሳሰብ መፍታት ማቅረብ ወደማይቻልበት ፈታኝ ሁኔታ ኢኮኖሚውን እንዳይወስደው ስጋት አለ።
በየቀኑ ገበያው እያበደ፣ የምርትና የአቅርቦት ዋጋ ከቁጥጥር ውጭ ለመውጣት እያቆበቆበ ይገኛል። በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘውና ቋሚ ገቢ ያለው ዜጋ በየእለቱ ፈተናው እየበረታበትና አቅሙን እየተፈታተነው ነው። ዛሬም ኢኮኖሚው ትኩረት ይሻል።
ещё
95
0
14 окт, 01:16
LLDPE 218WJ
Urgent Sale
Product name :LLDPE
Brand :Sabic
Code:218 WJ
Quantity :Available
Status : warehouse
Price:Attractive
join us 👇👇👇
https://t.me/grmche
ещё
69
0
13 окт, 22:06
Available row material
We have HDPE crate DOW,
Brand: DOW
Code: KT10000
Status: In store
📞 Call for Price:
0944252513
0945257051
ещё
129
0
8 окт, 22:25
Продолжить анализ этого канала
- История роста подписчиков
- Просмотры и охваты публикаций
- Кто упоминает канал и кого упоминает он
- Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней