Каталог каналов Каналы в закладках Мои каналы Поиск постов Рекламные посты
Инструменты
Каталог TGAds beta Мониторинг Детальная статистика Анализ аудитории Telegraph-статьи Бот аналитики
Полезная информация
Инструкция Telemetr Документация к API Чат Telemetr
Полезные сервисы
Защита от накрутки Создать своего бота Продать/Купить канал Монетизация

Не попадитесь на накрученные каналы! Узнайте, не накручивает ли канал просмотры или подписчиков Проверить канал на накрутку
Прикрепить Телеграм-аккаунт Прикрепить Телеграм-аккаунт

Телеграм канал «የፀጋ ወንጌል»

የፀጋ ወንጌል
121
12
1
1
169
📌በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች ይለቀቃሉ
📌ጥያቄዎች ከመፅሐፍ ቅዱስ አንፃር ይመለሳሉ
📌የእናንተ ድርሻ Share በማድረግ ሰው የእውነትን ወንጌል እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ ነው

Group
https://t.me/Graceofjesushighpriestgroup

ሀሳብ እና አስተያየት +251985406785(@yabsen)
+251953843618(@josi1423)
✍የጌታን ፀጋ ይብዛላቹህ
Подписчики
Всего
414
Сегодня
0
Просмотров на пост
Всего
45
ER
Общий
10.87%
Суточный
9.4%
Динамика публикаций
Telemetr - сервис глубокой аналитики
телеграм-каналов
Получите подробную информацию о каждом канале
Отберите самые эффективные каналы для
рекламных размещений, по приросту подписчиков,
ER, количеству просмотров на пост и другим метрикам
Анализируйте рекламные посты
и креативы
Узнайте какие посты лучше сработали,
а какие хуже, даже если их давно удалили
Оценивайте эффективность тематики и контента
Узнайте, какую тематику лучше не рекламировать
на канале, а какая зайдет на ура
Попробовать бесплатно
Показано 1 из 121 постов
Смотреть все посты
Пост от 27.12.2025 00:05
39
0
1
♦️#የገና_በዓል_መጽሐፍ_ቅዱሳዊ_ነውን?♦️ ================================== 📌ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በታህሳሥ ወር አለመወለዱን ያውቃሉ??? "መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል" 1ቆሮ 2፡15 ✍️ዮሐንስ 8:31-32 ኢየሱስም ያመኑትን አይሁድ፡— እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል፡ አላቸው። 1) በእውነት ኢየሱስ ክርስቶስ በታህሳስ ወር ተወልዷልን??? 2) የሚደረገው ስርዓትስ ከክርስትና ጋር ግንኙነት አለው?? 3) የገና ዛፉስ ከየት መጣ??? 4) መብራቱ እና አፉፋውስ(ፊኛ) ከየት መጣ??? 5) ቅዱስ ኒቆላዎስስ ( የገና አባት ) የተባሉት ከየት መጡ??? ✍️መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል 1ቆሮ 2:15 📌 መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል ፦ ========================= መሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደው በታህሳስ እንዳልሆነ ይናገራል። ✍️1ዜና 24፡7-19 ንጉሥ ዳዊት ካህናትን በተራቸው ወደ እግዚአብሔር መቅደስ ገብተው ያጥኑ ዘንድ መደባቸው 24 ካህናት ነበሩና በወር 2 ካህን ማለትም( ከ 1-15 እና ከ 16-30) በ 12 ወር 24 ካህናትን አደረገ ። ✍️በእስራኤላዊያን ቀን አቆጣጠር መሰረት ደግሞ የመጀመሪያ ወራቸው ኒሳን (Nisan) ይባላል። አስቴር 3፡7 , 8፡9 የእስራኤል የመጀመሪያ ወር ኒሳን በኢትዮጵያውያን ቀን አቆጣጠር ሚያዚያ መሆኑ ነው። ✍️ በምድቡም መሰረት ===================== 📌በአንደኛው ወር (ኒሳን) ከ 1-15 ቀን== ዮአሪም ከ 16-30 ቀን== ዮዳኤ 📌በሁለተኛው ወር (እያር) ከ 1-15 ቀን==ካሪም ከ 16-30 ቀን==ሥዖሪም 📌በሶስተኛው ወር (ሲቫን) ከ 1-15 ቀን==መልክያ ከ 16-30 ቀን==ሚያሚን ♥️በአራተኛው ወር ( ታሙዝ) ከ 1-15 ቀን== አቆስ ከ 16-30 ቀን== ♦️አብያ♦️ በሉቃስ ወንጌል 1፡5- 13 #ከአብያ ቤተሰብ የሆነ ስሙ ዘካርያስ የሚባል ሰው እናገኛለን በ 4ኛው ወር (ታሙዝ) የወሩ ሁለተኛ አጋማሽ ማለት ከ 16-30 ቀን በክፍሉ ተራ ለማጠን ወደ እግዚአብሔር መቅደስ ይገባል። በመቅደስ ውስጥ እያጠነ መልአኩ ገብርኤል ተገልጦ ልጅ እንደሚወልድ ይነግረዋል ተራውንም ጨርሶ ወደ ቤቱ ይመለሳል ከዚያም ዩሐንስ መጥምቁ ይፀነሳል። ✍️መጥምቁ ዩሐንስ በተጸነሰ በ6ኛው ወር መልአኩ ገብራኤል በናዝሬት አውራጃ ገሊላ በሚባል አካባቢ ወደምትኖር ስሟ ማርያም ወደምትባል ድንግል ሴት ያቀናል ከመንፈስ ቅዱስ እንደምትጸንስና ኢየሱስ ክርስቶስን እንደምትወልድ ይነግራታል። ሉቃ 1:26 ኢየሱስም በ 10ኛው ወር (#ቴቬት) ይፀነሳል ቴቬት 10ኛ ወራቸው በኢትዮጵያ አቆጣጠር በጥር ወር ኢየሱስ ይፀነሳል ከጥር ጀምሮ 9 ወር ስንቆጥር መስከረም (ቴስር) መጨረሻ ጥቅምት መጀመሪያ ላይ ኢየሱስ ይወለዳል ። 📌መጽሐፍ ቅዱስ እንደዚህ የሚናገር ከሆነ የገና በዓል እየተባለ በታህሳስ ወር የሚከበረው ከየት መጣ ?? --------------------- ✍️እንግዲህ በአጭሩ የገናን በዓል ታሪክ ወደ ኃላ መለስ ብለን ስንቃኘው ክርስትና ከመስፋፋቱ በፊት በሮም እና በአውሮፓ የተለያዩ አረማዊ (Pagan) በዓላት በታኅሣሥ ወር ይከበሩ ነበር። ክርስትና ከተጀመረ ከ 313 በኃላ ቤተክርስቲያን ነፃነቷን ስታገኝ ከአህዛብን አለም የመጡትን አዳዲስ አማኞች ተከትሎ የገባ የአህዛብ በዓል ነው። ታሪክ እንደሚነግረን አህዛቦች የብርሃን አምላካችን የተወለደበት ብለው ጨለማው አለፈ የበጋው ብርሃን መጣ በማለት እሳትን እያነደዱ የለመለመ ዛፍን እየቆረጡ ያከብሩ ነበር። ይህ አህዛባዊ በዓል በቤተክርስቲያን ውስጥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ተብሎ ተቀየረ ። ቆይቶም የካቶሊክ ቅዱስ የተባሉት ኒቆላዎስ የገና አባት ተብለው በየቤተክርስቲያኑ ውስጥ ተቀባይነት ካገኙ ዘመናትን አስቆጥረዋል ። ✍️በኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የተቀየሩት የአህዛብ ጣኦታት እነዚህ ናቸው ፣ 👉• ሳተርናሊያ (Saturnalia)፦ ሮማውያን ለግብርና አምላካቸው ሲሉ ከታኅሣሥ አጋማሽ ጀምሮ የሚያከብሩት፣ በድግስና በስጦታ ልውውጥ የታወቀ በዓል ነበር። 👉• የማትበገረው ፀሐይ ልደት (Sol Invictus)፦ በታኅሣሥ 25 ይከበር የነበረ የፀሐይ አምላክ በዓል ነው። ክርስቲያኖች "እውነተኛው የጽድቅ ፀሐይ ክርስቶስ ነው" በሚል ትርጉም በዚያው ቀን ማክበር ጀመሩ። 👉• ዩል (Yule)፦ በሰሜን አውሮፓ የክረምት ወቅት አጋማሽን ለማክበር የሚደረግ በዓል ሲሆን፣ የገና ዛፍን የማስጌጥ እና ግንዶችን የማቃጠል ልማድ ከዚያ የመጣ ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ ቤተክርስቲያንም እነዚህን በዓላት በክርስትና ትርጉም ለመተካት የልደት በዓልን በዚያው ሰሞን እንዲሆን አድርጋለች፦ ✍️ገላትያ 4 (Galatians) 8፤ ነገር ግን በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን ሳታውቁ በባሕርያቸው አማልክት ለማይሆኑ ባሪያዎች ሆናችሁ ተገዛችሁ፤ 9፤ አሁን ግን እግዚአብሔርን ስታውቁ ይልቅስ በእግዚአብሔር ስትታወቁ እንደ ገና ወደ ደካማ ወደሚናቅም ወደ መጀመሪያ ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ? እንደ ገና ባሪያዎች ሆናችሁ ዳግመኛ ለዚያ ልትገዙ ትወዳላችሁን? 10፤ ቀንንና ወርን ዘመንንም ዓመትንም በጥንቃቄ ትጠብቃላችሁ። 11፤ ምናልባት በከንቱ ለእናንተ ደክሜአለሁ ብዬ እፈራችኋለሁ። ✍️ የገና በዓል እንዲህ ስር የሰደደ እና በብዙኀን ዘንድ ተቀባይነት ቢያገኝም እውነት ሊሆን አይችልም እውነቱ የእግዚአብሔር ቃል የሚናገረው ብቻ ነው። ♦️ከተወለደበት ቀን ይልቅ ወደ ተወለደው ማንነት መዞር ይሁንልን ቀኑ ሳይሆን ኢየሱስ ነው መፍትሄው 📌"ኢየሱስም ሞቱን እንድናስብ ነው ያዘዘን" ✍️ ይሁዳ 1፡17 እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤ ✍️ 2 ቆሮንቶስ 13 (2 Corinthians) 14፤ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን። https://t.me/Graceofjesushighpriest
1
💯 1
Смотреть все посты