Аналитика Telegram-канала
Подписчики
702
Охват за 24 ч
73
ER за 24 ч
10,40%
Публикаций
653

Динамика подписчиков

7 дней 30 дней 6 месяцев Больше
16 ноя19 ноя22 ноя
Показаны последние 7 дней Больше истории →

Охваты публикаций

12.1115.1115.1119.1121.1121.11
35
Средний охват
113
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале Больше статистики →

Упоминания

10
Упоминаний
2
Из них репостов
1
Каналов
Все упоминания

Последние посты

3 из 653 2 из 653
+++ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን +++ ✨ ​​​​ሕዳር ሚካኤል ✨ እንኳን ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሲመት በሠላም አደረሰን ! እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡ እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል። ይህን ሁለተኛውን ሹመት ያገኘው በሚያዚያ 2 እንደሆነ አክሲማሮስ በተሰኘው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ አናገኛለን፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ ግን አይደለም ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው ፡፡ ይህም እንደሆነ እንድንረዳ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባለውን እስራኤል ዘሥጋን ሲራዳና ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ በኢያሪኮ ምድረ በዳ እንደተገለጠለት “… ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ የያዘ ሰው በፊቱ ቆመ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? አለው፡፡ እርሱም “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ” (ኢያ.5፡13) ይለናል:: በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ🤗❤️ +++ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ++++ ++++ ወወላዲተ ድንግል ++++ ++++ ወመስቀሉ ክቡር++++ ሀሳብ እና አስተያየቶን ➟➟➟➟@gesem24bot ያስቀምጡልን
ещё
3 1 21 ноя, 07:03
Фото
ещё
3 1 21 ноя, 07:03
† † † በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † † † ◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦             📖 ከመጽሐፍ አንደበት 📖 ◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦ በመስቀል ምልክት ሳታማትብ ከቤትህ አትውጣ፡፡ በትር፣ መሳሪያ፣ የማይበገር ምሽግም ይሆንሀል፡፡ ሰውም ሆነ ጋኔን አንተን ለማጥቃት አይደፍሩም፤ እንደዚህ ያለ ኃይለኛ የጦር ትጥቅ ታጥቀሃልና፡፡ ይህም አንተ ልክ እንደ ወታደር እንደሆንክ፣ ከአጋንንት ጋር ለመዋጋት ዝግጁ እንደሆንክ፣ በድልም አክሊልን እንደምታገኝ ምልክት ነው፡። መስቀሉ ያደረገውን አታውቁምን? ሞትን አሸንፏል፣ ኃጢአትን አጥፍቷል፣ ሲኦልን ባዶ አድርጓል፣ ሰይጣንን ከዙፋን አውርዷል፣ አጽናፈ ዓለሙንም ወደ እግዚአብሔር መልሷል፡፡ ታዲያ ኃይሉን ትጠራጠራለህ? መስቀሉ ይህን ኹሉ ድንቅ ነገር አድርጎልናል፤ መስቀል በአጋንንት ፊት የቆመ የሽንፈታቸው መታሰቢያ ነው፤ ክርስቶስ እባቡን የገደለበት ሰይፍም ነው:: መስቀል የአብ ፈቃድ፣ የአንድያ ልጁ ክብር፣ የመንፈስ ቅዱስ ደስታ፣ የመላእክት ውበት፣ የቤተክርስቲያን ጠባቂ ነው፡፡ ጳውሎስም እንዳለው መስቀል የቅዱሳን መከታ ነው፤ የዓለም ኹሉ ብርሃንም ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የነፍስ ምግብ ገጽ 78 ◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◆◆◆◍◍◍◍◍◍◍◍ ሀሳብ እና አስተያየቶን ➟➟➟➟@gesem24bot ያስቀምጡልን † † †    ወስብሐት ለእግዚአብሔር   † † †
ещё
17 0 19 ноя, 19:28
Больше постов

Продолжить анализ этого канала

  • История роста подписчиков
  • Просмотры и охваты публикаций
  • Кто упоминает канал и кого упоминает он
  • Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней