Аналитика Telegram-канала
Подписчики
42 192
Охват за 24 ч
2,6K
ER за 24 ч
6,16%
Публикаций
59 221
Динамика подписчиков
7 дней
30 дней
6 месяцев
Больше
20 ноя23 ноя26 ноя
Показаны последние 7 дней
Больше истории →
Охваты публикаций
18:4418:4419:0919:0920:2520:25
513
Средний охват
739
Лучший результат
Показаны 6 публикаций за 25 ноября
Больше статистики →
Упоминания
1 225
Упоминаний
1 018
Из них репостов
19
Каналов
0
Упоминаний за 90 дней
0
Из них репостов
0
Каналов за 90 дней
Последние посты
3 из 59 221 2 из 59 221ከስውር ትስስር የፀዳ የሎጂስቲክስ ሥርዓት ለሠራዊታችን ሁለንተናዊ ዝግጁነትና ድል ዋስትና ነው
ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም
የመከላከያ ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ24ኛ፣ በሀገራችን ደግሞ ለ23ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም የፀረ-ሙስና ቀን "ስውር ትስስሮችን በማጋለጥ የሙስና ወለድ ወንጀሎችን ሰንሰለት እንበጥስ!" በሚል መሪ ቃል በውይይት፣ በኦንላይን የሀብት ምዝገባ እና በተለያዩ መርሐ-ግብሮች ከፍተኛ የመንግሥትና የሠራዊት አመራሮች በተገኙበት አክብሯል።
በመድረኩ ላይ በተቋም ደረጃ የተዘጋጀውን የመወያያ ሰነድ መነሻ በማድረግ "ሥነ-ምግባር የተላበሰ አገልግሎት አሰጣጥና የፀረ-ሙስና ትግል በሎጂስቲክስ" በሚል ርዕስ ገለጻ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
በቀረበው የመወያያ ጽሑፍና በተነሱ ሐሳቦች ላይ ተመሥርተው መልዕክት ያስተላለፉት የዕለቱ የክብር እንግዳ የመከላከያ ሚኒስቴር የፋይናንስ ሥራ አመራር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊጂ የተጀመረውን የመከላከያ ሪፎርም ለማስቀጠል ከጥቅም ትስስር የፀዳ አሠራርን በታማኝነትና በግልጽነት ማጽናት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የመከላከያ ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል በሰጡት የማጠቃለያ አቅጣጫ፣ ሙስና ባሕሪውን እየቀያየረ እንደሚያጠቃ ቫይረስ የሀገርን ኢኮኖሚ የሚያላሽቅ፣ የሕግ የበላይነትን የሚሸረሽር እና የተቋምን ሞራልና መተማመን የሚያደቅ በመሆኑ በመንግሥት ደረጃ በቀይ መስመር መለየቱን ገልጸዋል።
ሠራዊታችን የተጣለበትን ተልዕኮ በብቃት እንዲወጣ ዋናዎቹ የሎጂስቲክስ አሠራሮች ሥነ-ምግባርን የተላበሱና ከምንም ዓይነት ስውር ትስስር የፀዱ መሆን እንዳለባቸውም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ጠላትን አጥንተን፣ ኃይል መድበንና የስበት ማዕከሉን መትተን እንደምንደመስሰው ሁሉ፤ የሙስናና የብልሹ አሠራር ሥውር ትስስሮችንም ነቅሰን በማውጣት፣ የተጋላጭነት ቀዳዳዎችን አስቀድመን በመዝጋትና በመበጣጠስ ለሀገራችን ሉዓላዊነትና ለሠራዊታችን ክብር ያለንን ታማኝነት በተግባር ማረጋገጥ ይኖርብናል ያሉት ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን፣ ከስውር ትስስር የፀዳ የሎጂስቲክስ ሥርዓት ለሠራዊቱ ሁለንተናዊ ዝግጁነትና ድል ዋስትና መሆኑን አረጋግጠዋል።
የፌዴራል የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ እሸቴ አስፋው በበኩላቸው፣ የዘንድሮው መሪ ቃል ዓለም ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ አንፃር መመረጡን አውስተው፤ ሙስና የጥቅም ግጭትን ከማስከተሉም ባለፈ ግልጽነትና ተጠያቂነትን በማጥፋት የሀገር ዕድገት ማነቆ በመሆኑ በጋራ ልንታገለው ይገባል ብለዋል።
በዕለቱም ግልጽነትና ተጠያቂነትን በተግባር ለማረጋገጥ የሚያስችል የኦንላይን የሀብት ምዝገባ ሥነ-ሥርዓት የተከናወነ ሲሆን፣ የቀረበውን የመወያያ ገለጻ መሠረት ያደረገ የጥያቄና መልስ ውድድርም ተካሂዷል።
ዘጋቢ ዳንኤል ደረጀ
ፎቶግራፍ ወርቅነህ ተስፋው
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
ещё
616
0
10 25 ноя, 20:25
ещё
495
0
3 25 ноя, 20:25
ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ተከበረ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም
በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ 23ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን "ሥውር ትስስሮችን በማጋለጥ የሙስና ወለድ ወንጀሎችን ሰንሰለት እንበጥስ" በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት ተከብሯል።
የኢንተርፕራይዙ አመራሮችና ሠራተኞች በተሳተፉበት በዚህ መድረክ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮርፖሬት ሀብት አስተዳደር ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው በቀለ፣ ዕለቱን ማክበር ያስፈለገው የሙስናና የሙስና ወለድ ወንጀሎችን አስከፊነት በተመለከተ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር መሆኑን ገልጸዋል።
በድርጅቱ ውስጥ ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ አሠራሮችን በጋራ በመለየት ሙስናን የመከላከል ኃላፊነትን ከቃላት ባለፈ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መቀየር እና መላው ሠራተኛ በፀረ-ሙስና ትግሉ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ማነሳሳት የውይይቱ ዋና ዓላማ መሆኑን ተናግረዋል።
በፓናል ውይይቱ ላይ የኢንተርፕራይዙ የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ መንግስቱ ቱፋ፣ ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ሲከበር እንደ ዜጋም ሆነ እንደ ሠራተኛ ሙስናና ብልሹ አሠራሮች በሀገርም ሆነ በተቋም ደረጃ የሚያስከትሉትን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ከባቢያዊ ቀውሶች በውል መረዳት የሚያስችል የውይይት ሰነድ አቅርበዋል።
የኢንተርፕራይዙ የሥነ-ምግባር መከታተያ ቡድን መሪ ሻለቃ ጌትነት አንዷለም በበኩላቸው፣ የፓናል ውይይቱ አመራሩና ሠራተኛው ሙስናንና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል የአሠራር ግልጽነት እንዲፈጥሩ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ የሥራ አካባቢዎችን በጋራ በመለየት ችግሩን ለመቀነስ፣ ሁሉም የኢንተርፕራይዙ አመራርና ሠራተኞች የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት ስኬታማ ሥራ መሥራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
ዘጋቢ ማርታ ተፈሪ
ፎቶግራፍ ጥላሁን ደስታ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
ещё
429
1
4 25 ноя, 19:09
Продолжить анализ этого канала
- История роста подписчиков
- Просмотры и охваты публикаций
- Кто упоминает канал и кого упоминает он
- Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней