Аналитика Telegram-канала
Подписчики
78 956
Охват за 24 ч
4,1K
ER за 24 ч
5,14%
Публикаций
6 747
Динамика подписчиков
7 дней
30 дней
6 месяцев
Больше
8 ноя11 ноя14 ноя
Показаны последние 7 дней
Больше истории →
Охваты публикаций
04:5804:5907:3107:3114:5814:59
191
Средний охват
362
Лучший результат
Показаны 6 публикаций за 13 ноября
Больше статистики →
Упоминания
247
Упоминаний
85
Из них репостов
86
Каналов
0
Упоминаний за 90 дней
0
Из них репостов
0
Каналов за 90 дней
Последние посты
3 из 6 747 2 из 6 747
ጥያቄ፡-
ሰላም ዶክተር:
ዶክተር፣ ሰዎችን በሙሉ ልቤ መቀበል አቁሜያለሁ። ማለትም፣ የትኛውንም ሰው ሳውቅ ግንኙነታችን ለጥቂት ጊዜ እንጂ ዘላቂ እንደማይሆን ውስጤ ይነግረኛል። ያመንኳቸው ከድተውኛል። የተደገፍኳቸው ሰዎች በሚያስፈልጉኝ ሰዓት ጥለውኝ ጠፍተዋል። ይህ ለሰዎች እምነት እንዳይኖረኝ አደረገኝ።
የሚገርመው፣ አሁንም ለሰዎች ደስታ ስል ራሴን እሠዋለሁ፤ ለእኔ ደስታ ግን ማንንም አልጠብቅም። ሲከፋኝ ከአምላኬ ውጭ ለማንም አልነግርም፤ ምክንያቱም በሰዎች ተስፋ አጥቻለሁ። በውስጤ እያለቀስኩ በሰዎች ፊት መሳቅ ልማዴ ሆኗል።
ዶክተር፣ ግን ይህ ነገር ወደ ለየለት ብቸኝነት እየወሰደኝ ነው። ራሴን ከሰዎች እያገለልኩ ነው። ምን ላድርግ?
መልስ፡-
ይህንን ሁኔታህን ወደ ስነ-ልቦነባዊው ትርም ስንወስደው ሰዎችን ከማመን ጋር ስለሚያያዝ የስሜታዊ መገለል (Emotional Withdrawal) ይባላል።
ሊኖሩ የሚችሉ የሥነ-ልቦና መንስኤዎች፦
1. ከክህደት የመጣ የስሜት ጉዳት: በተደጋጋሚ በታመኑ ሰዎች መከዳትና መተው።
2. የመተው ፍርሃት: አዲስ ግንኙነት ሲጀምርም በመጨረሻ እንደሚተውን መጠበቅ።
3. ስሜትን ማፈን፡ ስንጎዳ ወይም ስዝን ለሌሎች አለመግለጽ።
4. ሌሎችን ለማስደሰት መጣር: የራስን ፍላጎት በመሰዋት የሌሎችን ደስታ ማስቀደም።
5. በመራቅ ችግርን መቋቋም (Avoidant Coping): እንደገና እንዳይጎዱ ከሰዎች መራቅና መገለል።
ይህ ከ ስጋት-ተኮር ትስስር (Insecure Attachment) ጋር ይያያዛል፡፡ በተለይም፣ ሰዎችን የመቅረብ ፍላጎት እያለ በተመሳሳይ ጊዜ መጎዳትን በመፍራት ከሰዎች የመራቅ ትስስር ዘይቤ (Fearful-Avoidant Attachment Pattern) ጋር ሊያያዝ ይችላል።
በአጭሩ፣ የሰዎችን ቅርበት ትፈልጋለህ፣ በተመሳሳይ ጊዜ ግን እንደገና መጎዳትን ስለምትፈራ ትርቃለህ።
ማድረግ ያለብህ . . .
· ሁሉንም ሰው እኩል ከመጠራጠር ይልቅ እምነትን በቀስታ መገንባት።
· ስሜትህን ለምታምነው ለአንድ ሰው በማጋራት መላመድ።
· የራስህን ፍላጎትና ድንበር ማክበርንና ሰዎችን መቅረብን አጣምሮ መያዝ ላይ መስራት።
· ከቀድሞ የክህደት ልምዶች የተነሳውን ቁስል ለመፈወስ ከሙያተኛ አማካሪ ጋር መሥራት።
https://t.me/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ещё
362
1
2 13 ноя, 14:59
የትኛውንም ሰው ሳውቅ ግንኙነታችን ለጥቂት ጊዜ እንጂ ዘላቂ እንደማይሆን ውስጤ ይነግረኛል . . .
ещё
349
0
1 13 ноя, 14:58
የመጽሐፍ አጻጻፍ ጥበብና ዘዴ (The Art and Techniques of Book Writing)
የቡድን ኮቺንግ (Group Coaching)
መጽሐፍ በመጻፍ ማስተላለፍ የምትፈልጉት መልእክት ካለና ሃሳባችሁን አዋቅራችሁ እንዴት ለህትመት ማብቃት እንዳለባችሁ ተጨማሪ ስልጠና እና መመሪያ ከፈለጋችሁ ይህ የቡድን ኮቺንግ ሊጠቅማችሁ ይችላል፡፡
ይህ ፕሮግራም የቡድን ሥልጠናንና የግል ኮቺንግን ያቀናጀ (Hybrid) የመጽሐፍ አጻጻፍ የኮቺንግ ፕሮግራም ነው፡፡ ማለትም የግሩፕ ስልጠናን እና በግል የሚደረግ ኮቺንግን የቀላቀለ አቀራረብ ነው፡፡
የ online የቡድን ሥልጠና፦ ስለ መጽሐፍ አጻጻፍ መርሆዎች፣ ዘዴዎችና ሂደቶች በ online በቡድን መሰልጠን።
የግል (individual) ኮቺንግ፦ የ online ስልጠናው ሲጠናቀቅ ተሳታፊዎች በየራሳቸው የመጽሐፍ ፕሮጀክት ላይ ተመስርተው የግል እገዛና መመሪያ ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ በአካል ወይም በ online ማግኘት።
ይህ የቡድን ኮቺንጉ የሚሰጠው ከ10 እስከ 15 ለሚሆኑ ሰዎች ብቻ ነው፡፡ ይህም የሚሆነው ሰልጣኞች ከዶ/ር ኢዮብ ጋር በግል የማሳለፍ እድል እንዲያገኙ ነው፡፡
የቡድን ሥልጠና (Telegram Live Training) ቀን
📖 የሚቆይበት ጊዜ፦ ሁለት ሳምንታት
📖 የሥልጠና ቀናት፦ ሰኞ እና ሮብ (ሰኞ ሕዳር 21 እና ሮብ ሕዳር 23 እንዲሁም ሰኞ ሕዳር 28 እና ሮብ ሕዳር 30 - 2019)
📖 ሰዓት፦ ከምሽቱ 2:00 እስከ 3:30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)
📖 የሥልጠና መንገድ፦ Telegram Live
📖 የሥልጠና ብዛት፦ በጠቅላላ አራት ክፍለ ጊዜዎች
የግል ኮቺንግ (Individual Coaching Sessions)
📖 ይህ ክፍል እያንዳንዱ ተሳታፊ በራሱ የመጽሐፍ ፕሮጀክት ላይ ተመስርቶ የግል መመሪያና እገዛ የሚያገኝበት ነው።
📖 ተሳታፊዎች እንደ ምርጫቸው ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር በአካል ወይም በTelegram/ስልክ በመገናኘት ኮቺንጉን ያገኛሉ። የቀጠሮ ቀንና ሰዓትም በግል ስምምነት ይወሰናል።
📖 እያንዳንዱ ተሳታፊ በሦስት ሳምንታት ውስጥ ሦስት የአንድ ሰዓት የግል ኮቺንግ ክፍለ ጊዜዎችን ያገኛል።
በዚህ coaching ለመሳተፍ፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡
Thank You!
ещё
108
0
1 13 ноя, 07:31
Продолжить анализ этого канала
- История роста подписчиков
- Просмотры и охваты публикаций
- Кто упоминает канал и кого упоминает он
- Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней