Аналитика Telegram-канала
Подписчики
2 849
Охват за 24 ч
776
ER за 24 ч
27,24%
Публикаций
1 366
Динамика подписчиков
7 дней
30 дней
6 месяцев
Больше
10 ноя13 ноя16 ноя
Показаны последние 7 дней
Больше истории →
Охваты публикаций
14.1115.1115.1115.1116.1116.11
164
Средний охват
360
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале
Больше статистики →
Упоминания
4
Упоминаний
0
Из них репостов
1
Каналов
3
Упоминаний за 90 дней
1
Из них репостов
2
Каналов за 90 дней
Последние посты
3 из 1 366 2 из 1 366ልክ እንደ ውብአንተ የታመነ ወንድም፣
ማርያምን እያለ ከፊት የሚቀድም፣
እረ ጀግና ውለጅ እረ እናቴ ዳግም።✊
በእውነቱ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ በአማራ ፋኖ የህልውና ትግል ካደረጋቸው ተጋድሎዎች መካከል በወሎ - ቤተአማራ ምድር የከፈላቸው ውድ ዋጋዎች ሁሉ ዘመን አይሽሬና አይተኬ አይረሴ ናቸው።
እነ ውብአንተ አባተ በጋሸና በአንዷ ግንባር የሰሩትን ጀብድ ብቻ ብናነሳ እንኳ እጅግ ተአምራዊ ጀብዶች ነበሩ። እነ ውቤ ሕዳር 21/2014 ዓ.ም የአርቢትን ምሽግ በመሥበር ነበረ በታላቅ ወኔ ወደ ቤተ - አማራ ግንባር ጋሸና የገሰገሱት። እነ ሜ/ጀ ውብአንተ አባተ በሕዳር 23/2014 ዓ.ም በተደረገ እልህ አሥጨራሽ ፍልሚያም ታላቁ የጋሸናን ምሽግ ተቆጣጠሩ። በዚህን ጊዜ ጋሸናን ከተቆጣጠሩ በኋላ የመከላከያ ጀነራሎች እጅጉን ደስተኛ ሁነው ሰንደቅ አላማውን የፋኖ አመራሮች ከፍ አድርገው እንዲያውለበልቡት ፈቀዱላቸው። ሜ/ ጀ ውባንተ አባተና አሠፋ አባ መቅጫ በጋራ በመሆን ሰንደቅ አላማውን ጓደኞቻቸውን በመያዝ ከፍ አድርገው አውለበለቡ። በነጋታው ሕዳር 24/2014 ዓ.ም ወደ ሐሙሢት በትልቅ ደስታ ጦሩን ይዞ ጉዞውን ቀጠለ። በሐሙሲት ግንባርም እልህ አሥጨራሽ ትግል ተደረገ። በዚህ ግዳጅ ነበረ በሕዳር 25/2014ዓ.ም እነ አርበኛ አሰፋ ተሾመ(አባ መቅጫ) ፣ እነ አርበኛ ደሤ ፣ እነ አርበኛ ጌታ ንጉሤ፣ እነ አርበኛ ፍቃዱ ካሣነህ፣ እነ አርበኛ ንጉሴ ቢምራው ....ሌሎች በርካታ አርበኞች በክብር የወደቁት።
ሕዳር 28/2014ዓ.ም ሐሙሢት ላይ እጅግ ከፍተኛ ውጊያ ተካሂዶ ከቀኑ 11:00 ላይ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ከባድ የእጅ በእጅ(ጨበጣ) ውጊያ እያደረገ እያለ አርበኛ ውባንተ አባተ በሥናይፐር ጥይት ለአምስተኛ ጊዜ የቆሰለውና ደሙ እንደ ዥረት የፈሰሰው። ከዛ በኋላ በነበሩ ጠንካራ ጦርነቶች ውስጥ ሜ/ጀ ውብአንተ አባተ ቁስሉ ገና በልኩ ሳያገግም ከሰራዊት ፊት ቀድሞ እየተገኘ ጠላትን በደንብ ገርፎ አበራይቶታል።
እናማ ወዳጄ ሜ/ጀ ውብአንተ አባተ በወሎ - ቤተአማራ መሬት ላይ ወጥቶ ወርዶ ደክሟል ፣ የትግል ጓዶቹ አጥንት የከሰከሱበት ፣ ውድ ሕይወታቸውን የገበሩበት ፣ በጀግንነት የተዋጉበት ምድር ነው። እንኳን አይደለም አንድ ተራ ዲሽቃ ይቅርና የጠላትን ታንክና መድፍ ከጥቅም ውጪ አርጓል ፤ የቀረውንም ማርኮ አሳይቷል።
እኛ ቤተ አማራዎች የወንድሞቻችንን ውድ ዋጋ የምናራክስ ከንቱዎች አልያም ይሄንን የጀግንነት ታሪክ ሸምጥጠን የምንክድ ከሃዲዎች ፈፅሞ አይደለንም። ከጀርባ አይዞህ የሚልህ አካልም ካለ በክብር ተ- ነፋ በለዉ ፤ አንተ በራስህ ተነሳሽነት ብቻ ከሆነም የምትላገገው አርፈህ ተቀመጥ። የወንድሞቻችንን ውድ ዋጋ አታርክስ።
ቋሚ ምሥል፦ ጠላት ላይ ኢላማው በትክክል ሲያርፍለት የአሳምነው ልጅ ፣ የአስቻለው ደሴ ወንድም እያለ ይፎክር የነበረው ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ራሱ ነው።
ነፍስ ሔር ፤ ከደጋጎች ጎን እረፍልን ጀነራል!🙏
ቀኝ አዝማች ይታገሱ አራጋው •
ещё
110
0
16 ноя, 14:01
ደብረወርቅ ከተማ በተደረገ ተጋድሎ 170 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመማረክ አንፀባራቂ ድል ተመዝግቧል።
ህዳር 7/ 2019 ዓ.ም
**********
74ኛ እና 64ኛ ክ/ጦር በመቀናጀት በደብረወርቅ ከተማ በአደረጉት ተጋድሎ 170 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በመማረክ አንፀባራቂ ድል አስመዝግበዋል ። ኢንስፔክተር ሻምበል ጨምሮ የደብረወርቅ ከተማ ሚኒሻ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል አንበል መልካሙ፣ የጥምር ጦር አዛዥ ሸጋው ፣ አጥናፉ ጌታቸው እና ስለሺ የተባሉ የጠላት ቁልፍ ሰዎች በተደመሰሱበት ምሽግ ጀግናው ሰራዊታችን ጀብድ ሰርቷል።
64ኛ ክ/ጦር እና 74ኛ በጋራ በአደረጉት እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ 5 የጠላት ዋና ዋና ሞምሽጎች ተሰብረዋል። በርካታ የጠላት ሰራዊት ተደምስሷል 170 ክላሽ፣ የክላሽ ካዘና፣ ጥይት እና ሽጉጥ ተማርኳል።
በተመሳሳይ የተጋድሎ 64ኛ ክ/ጦር በእነማይ ወረዳ ዲማ ጊዮርጊስ ፣ ወይራ ጠልማ፣ ሁለት አምባ ድቢሳ ከአነጋጉ ጀምሮ ጠንካራ ውጊያ ያደረገ ሲሆን በእንቅስቃሴ ላይ የነበረው የጠላት ሁለት ፓትሮል እና አንድ ዘ- 23 በሹተር ኢላማ ተመተው ከጥቅም ውጭ ሁነዋል።
በሸበል በረንታ እንዲሁ በተፈፀመ ተጨማሪ ጥቃት የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ መሆኑ ተረጋግጧል።
ከአነጋጉ ጀምሮ በአምስት ግምባሮች በተደረገ ወጊያ ጠላት ባልጠበቀው ሁኔታ ከፍተኛ ኪሳራ ያጋጠመው ሲሆን የወገን ኃይል በተቀናጀ መልኩ በአደረገው ተጋድሎ አመርቂ ድል አስመዝግቧል።Yibeltal Getie Mitiku
ещё
146
0
16 ноя, 13:27
በዛሬው እለት ረፋድ 3:00 እና ከደቂቃዎች በፊት 6:00 ላይ'' Ilyushin Il-76 '' የተሰኘው የዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ ወታደራዊ ካርጎ አውሮፕላን በጎንደር አፄ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ አርፏል!
ላለፉት ሁለት ሳምንታት የUAE ግዙፍ ወታደራዊ ካርጎ አውሮፕላኖች ፣ ወታደራዊ ጭነቶችን በተከታታይ በረራዎች ወደጎንደር እያመላለሱ እንደሚገኙ የሚታወስ ነው!
ещё
360
0
15 ноя, 12:48
Продолжить анализ этого канала
- История роста подписчиков
- Просмотры и охваты публикаций
- Кто упоминает канал и кого упоминает он
- Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней