Аналитика Telegram-канала
Подписчики
12 250
Охват за 24 ч
1,3K
ER за 24 ч
10,96%
Публикаций
3 604
Динамика подписчиков
7 дней
30 дней
6 месяцев
Больше
15 ноя18 ноя21 ноя
Показаны последние 7 дней
Больше истории →
Охваты публикаций
12.1112.1113.1115.1120.1120.11
440
Средний охват
994
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале
Больше статистики →
Упоминания
93
Упоминаний
49
Из них репостов
28
Каналов
5
Упоминаний за 90 дней
2
Из них репостов
2
Каналов за 90 дней
Последние посты
3 из 3 604 2 из 3 604የመፅሐፉ ከቨር ስራ እና የአንዳንድ ቃላት እርማት ስለሚያስፈልገው ትንሽ ብቆይ እንጂ አልዘገይም ለበኩር ቅምሻዬ 🙌🏽
ещё
922
1
2 27 20 ноя, 16:38
COMING SOON 📖
እንኳን ደስ አለኝ «እሳት የወለደችው ሞት» የተሰኘ የመጀመሪያ የበኩር መፅሐፌን በቅርቡ ላንባቢ አደርሳለሁ። ከረጅም ጊዜ የጽሑፍ ጉዞ በኋላ የመጀመሪያ መጽሐፌን ወደ ማጠናቀቅ አድርሻለሁ። ጥቂት የመጨረሻ ማስተካከያዎች ብቻ ይቀሩኛል።
«እሳት የወለደችው ሞት» የህልውናዊ ግጥሞችን (Existential Poetry) አጫጭር ትረካ ድርሰቶችን (Short Prose) እና ዕለታዊ የዕውነት ማስታወሻዎችን (Aphoristic Reflections) የያዘ የሥነ-ጽሑፍ ሥራ ነው። በመጽሐፉ ውስጥ የአንድ ገፀባህርይ ድምፅ በተለያዩ የጽሑፍ ቅርጾች ይመላለሳል።
ይህ የመጀመሪያዬ መጽሐፍ ሲሆን በዲጂታል ቅርጽ (PDF Edition) ለአንባቢዎች የማቀርበው ይሆናል። ያም የሆነበት ምክንያትን አሳታሚ ማጣቴ ነው። በየወሩ ልዩነት በፌስቡክ ፕላትፎርም ብዙ ሰዎች መፅሐፍ አሳተምኩ እያሉ ብቅ ይላሉ። እንደውም በአመት ውስጥ ሦስቴም የሚያሳትሙ አልታጡም። በተለይ ሴቶችሁ የተለየ ቦታ ነው የሚሰጣቸው። በዚህ አንድ ነገር ነው የታዘብኩት፤ እንኳን መፅሐፍ መጻፍ ይቅርና መፅሐፍ አንብበው በጥልቀት የማይረዱ እንደሆነ ከስነጽሁፍ ቃላት አጣጣላቸው ማወቅ የሚቻልበት መራር ሀቅ በየገጹ ቅርንጫፍ ተጽፎ አስተውያለሁ። እኔም ጊዜ እየጠበቅኩ እድሜ ከሚያመልጠኝ በSoft copy መግዛት ለሚፈልጉ ሰዎች የመጀመርያ መፅሐፌን እስከተቻለኝ አቅም ትንሽ ከሸጥኩ በኋላ ሙሉ ለሙሉ በቴሌግራም ቻናሌ ኦፊሻሊ አጋራዋለሁ።
በተያያዘ ወሬ ስለሁለተኛው መጽሐፌ አንድ የምነግራችሁ ነገር ለፍቼበታለሁ። እናም ደግሞ ከመጀመርያው ለቅምሻ ከማወጣው መፅሐፌ በተለየ አቅጣጫ የቀረበ ነው። ስለዚህ በሰፊው ልመጣበት እንደገና ጀምሬያለሁ።
ሁለተኛው መፅሐፌ በማኅበረሰብ ሞራሊዝም (Social Moralism) ላይ የሚያተኩር፣ የፍልስፍናን፣ የሶሺዮሎጂንና የሳይኮሎጂን እይታዎችን በአንድ የሚያቀናጅ ሥራ ነው። እሱ ብቻ ሳይሆን የሃይማኖት ምንነት በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ያለውን ሚና፣ በኢትዮጵያ የተከሰቱ የእርስ በርስ ግጭቶች በሰዎች እምነት፣ በማኅበራዊ እሴቶችና በጋራ መኖር ላይ ያሳደሩትን ተጽዕኖ ይመረምራል። ፖለቲካ እንዴት ከርዕዮተ ዓለም ልዩነት ተሻግሮ ወደ ማኅበራዊ ጥላቻና የማንነት መከፋፈል እንደሚሸጋገርም የጥናቱ አንድ አካል ነው።
በተለይም ራሱን ወግ አጥባቂ (Conservative) እና ሞራላዊ እሴቶችን ጠባቂ አድርጎ የሚገልጽ ማኅበረሰብ፤ በተግባር ግን የተቀመጠውን ማኀበራዊ ባህልን ሲጥስ የሚፈጠረውን የሞራል ተቃርኖ (Moral Contradiction) በጥልቀት ይዳስሳል። በተጨማሪም የማኅበራዊ ግብዝነት (Social Hypocrisy) የግንዛቤ ተቃርኖ (Cognitive Dissonance) የቡድን ማንነት (Social Identity) እና የሞራል መላላት (Moral Disengagement) በማጠቃለል አናላይሲስ የወጣለት መፅሐፌ ነው።
ይህን መፅሐፌን ቀድሞሁኑ ጀምሬው የነበረ ጽሁፍ ቢሆንም፤ ብዙም ሳልሄድበት በጭንቀትና በግል ምክንያቶች ሳቢያ ለጊዜው አቋርጬው ነበር። አሁን ግን ወደመፃፍ ተመልሻለሁ። እስከዚያው ግን «እሳት የወለደችው ሞት»ን እንደ ቅምሻ ወይም በአፍ እንዳለች ከረሜላ እየመጠጣችሁ ጠብቁኝ። ይህ የመጀመሪያዬ የግጥምና የአጫጭር መጣጥፍ ስራዬ ነው፤ ከዚያ በኋላ ግን ሌላ ጠለቅ ያለ መራር ሀሞት በሁለተኛው መፅሐፌ ይጠብቃችኋል።
በመጨረሻም ከመፅሐፉ ጋር በተያያዘ ለመፅሐፉ እና እኔም ለመጻፌ እገዛ ማድረግ የምትፈልጉ ሰዎች በአዋሽ ባንክ የበኩላችሁን አስተዋጾ ማድረግ ትችላላችሁ አመሰግናለሁ፦
013201281880800 Moges beyene
@Armemo_offical
ещё
243
3
1 9 20 ноя, 16:33
በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ጥያቄ እጠየቃለሁ፦«ቻናሌን አስተዋውቅልኝ» እኔም ተመሳሳይ ነገር እመልሳለሁ፦«የማንንም ቻናል እስከዛሬ አስተዋውቄ አላውቅም!» ነገር ግን ኪስ በማይጎዳ መልኩ በቀናት ልዩነት የሚጠፋ የቴሌግራም ማስታወቂያዎችን እሰራለሁ። በዚህ ጉዳይ ተስማምቶ የሚመጣ ሰው ካለ ማስታወቂያ ሊያሰራ ይችላል። እኔን ማግኘት የምትፈልጉ ከስር ባለው username ማውራት ይችላል። አመሰግናለሁ 🙌🏽
https://t.me/I_believes
ещё
994
2
15 15 ноя, 18:23
Продолжить анализ этого канала
- История роста подписчиков
- Просмотры и охваты публикаций
- Кто упоминает канал и кого упоминает он
- Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней