Аналитика Telegram-канала
Подписчики
16 480
Охват за 24 ч
2K
ER за 24 ч
12,21%
Публикаций
8 145

Динамика подписчиков

7 дней 30 дней 6 месяцев Больше
9 ноя12 ноя15 ноя
Показаны последние 7 дней Больше истории →

Охваты публикаций

11.1112.1112.1113.1114.1114.11
505
Средний охват
1,6K
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале Больше статистики →

Упоминания

763
Упоминаний
582
Из них репостов
75
Каналов
Все упоминания

Последние посты

3 из 8 145 2 из 8 145
Фото
" የተሰረቀ ዕቃ በቅናሽ ዋጋ መግዛት ወይም ይዞ መገኘት እንደ ወንጀሉ ክብደት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት ያስቀጣል " - የሕግ ባለሙያ አንዳንድ ሰዎች የተሰረቁ ስልኮች፣ ላፕቶፖችና ሌሎች ዕቃዎች በርካሽ ዋጋ የሚሸጡባቸውን ቦታዎች በማፈላለግ ሲገዙ ይስተዋላል። አንዳንዶች ምንጫቸውን ሳያውቁ ያገለገሉ ዕቃዎችን በርካሽ ስላገኟቸው ብቻ ከሰዎች ላይ ይገዛሉ ፤ ሌሎች ደግሞ እቃውን በትንሽ ብር ገዝተው አትርፈው ይሸጣሉ። ታዲያ አንድ ሰው " ዕቃው በቅናሽ ዋጋ ስለቀረበልኝ በቅን ልቦና ነው የገዛሁት ፤ የተሰረቀ መሆኑን አላውቅም ነበር " ቢል ከሕግ ተጠያቂነት ያመልጥ ይሆን ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ላይ ዓለም አቀፍ የሕግ ባለሙያና ጠበቃ የሆኑትን አቶ ጥጋቡ ደሳለኝን አነጋግሯል። የሚያስከትለው የሕግ ተጠያቂነት ምንድነው ? በአነስተኛ ዋጋ ስለተገኘ ብቻ የተሰረቀ ዕቃ የሚገዙና አትርፈው የሚሸጡ አካላት፣ በቅን ልቦናም ይሁን ሳያውቁ ቢገዙ ከሕግ ተጠያቂነት ነጻ እንደማይሆኑ አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ገልጸዋል። በሕግ ፊት " የተሰረቀ መሆኑን አላውቅም ነበር " የሚል ምክንያት ተቀባይነት እንደሌለውም አስረድተዋል። " የተሰረቀ ዕቃ የዋጋ ቅናሽ ስላለውና ደረሰኝ ስለሌለው መግዛት፣ በሕጉ መሠረት የተሰረቀ ዕቃ በመግዛት እና ደረሰኝ የሌለው ዕቃ ይዞ በመገኘት እንደ ነገሩ ክብደት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት ያስቀጣል። ከተጠያቂነት ነጻ መሆን የሚቻለው ከሕጋዊ ነጋዴ በስሙ የተቆረጠ ሕጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ ሲቻል ብቻ ነው " - አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ የአንድ ግብይት ሕጋዊነት የሚረጋገጠው በደረሰኝ ብቻ መሆኑን ያነሱት ባለሙያው፤ ሻጩ ለሰጠው ዕቃ ወይም አገልግሎት ደረሰኝ የመስጠት፣ ገዢውም የከፈለበትን ደረሰኝ የመቀበል ግዴታ እንዳለበት ተናግረዋል። ግብይቱ በደረሰኝ እስካልተረጋገጠ ድረስ የትኛውም ግብይት የወንጀል ተጠያቂነትን እንደሚያስከትል አሳስበዋል። የኦንላይን (ማኅበራዊ ሚዲያ) ግብይቶች ተጠያቂነት አለባቸው ? ከሰው ላይ የተሰረቁ ወይም በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኙ (የወንጀል ፍሬ የሆኑ) ዕቃዎችን ሰዎች ትክክለኛ መስሏቸው በቴሌግራም ቻናሎች፣ በፌስቡክ ገጾች እና በሌሎች የበይነመረብ አማራጮች ተታልለው ቢገዙና በኋላ የተሰረቀ ዕቃ መሆኑ ቢታወቅ፣ የወንጀል ተጠያቂነቱ በቀጥታ የሚያርፈው ዕቃውን ባሻሻጡት የኦንላይን ገጽ ባለቤቶች ወይም አንቀሳቃሾች (ኦፕሬተሮች) ላይ መሆኑን ጠበቃው ገልጸዋል። አክለውም በማኅበራዊ ሚዲያ " ዕቃ እናሻሽጣለን፣ ሻጭና ገዢ እናገናኛለን፣ የዴሊቨሪ አገልግሎት እንሰጣለን " የሚሉ አካላት በቀጥታ በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ጠቅሰዋል። እነዚህ አካላት ዕቃውን ከማስተዋወቃቸው በፊት ዕቃው በሕጋዊ መንገድ የተገኘና የወንጀል ፍሬ አለመሆኑን፣ እንዲሁም ከትክክለኛ አቅራቢ ተገዝቶ ለትርፍ የቀረበ መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው። ዕቃው በፖሊስ ቢወሰድ ገዢው ምን መብት አለው ? አንድ ገዢ በቅን ልቦና ያገለገለ ዕቃ ገዝቶ የተሰረቀ መሆኑ ተደርሶበት በፖሊስ ከተወሰደበት፣ ዕቃውን ለመግዛት ያወጣውን ገንዘብ ከካሳ ጋር በፍርድ ቤት የመጠየቅ ሕጋዊ መብት እንዳለው አቶ ጥጋቡ ጠቁመዋል። ሆኖም የፍትሕ ሂደቱ እስከ 6 ወር ወይም ከዚያ በላይ ሊወስድ ስለሚችል፣ ዜጎች ገና ከጅምሩ በደረሰኝ በመገበያየት ራሳቸውን ከእንግልትና ከኪሳራ መጠበቅ እንደሚገባቸው መክረዋል። የተሰረቀ ዕቃ በስጦታ መልክ መቀበል የሚያመጣው ችግርስ ? " የተሰረቀ ዕቃ መሆኑን ሳያውቁ በስጦታ መቀበል ከሕግ ተጠያቂነት ያድናል ወይ ? " ለሚለው ጥያቄም የሕግ ባለሙያው የሚከተለውን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡ የተሰረቀ ዕቃን በስጦታ የተቀበለ ሰው በሕግ ሲጠየቅ፤ " ዕቃው የተሰጠኝ በማኅበረሰቡ የመሰጣጣት ባህልና ልማድ መሠረት በስጦታ ነው፤ ቀደም ሲል በእኔ እጅ አልነበረም፤ እከሌ የሚባል ሰው ነው የሰጠኝ " ብሎ በሰው ምስክር ማረጋገጥ ከቻለ ከወንጀል ተጠያቂነት ነጻ ይሆናል። በሰነድ እንኳ ባይሆን በሰው ምስክር ማረጋገጥ ካልቻለ ግን፣ የተሰረቀ ዕቃን ለማሸሽ፣ ለመሸሸግ፣ ለመደበቅ፣ ለመሰወር ወይም አትርፎ ለመሸጥ የተደረገ ሙከራ ነው ተብሎ በወንጀል ይጠየቃል። በሕግ አግባብ ስጦታ መቀበል የሚቻለው ስጦታ ሰጪው ንብረቱ የራሱ ስለመሆኑ በውልና ማስረጃ መሥሪያ ቤት ሲያረጋግጥ ብቻ መሆኑን የገለጹት ባለሙያው፤ በማኅበረሰቡ ዘንድ በተለመደው መንገድ ብቻ ዝም ብሎ ስጦታ መቀበል ከሕግ ተጠያቂነት እንደማያድን አስገንዝበዋል። በመጨረሻም ማኅበረሰቡ ለሚፈጽማቸው ማናቸውም ግብይቶች ሕጋዊ ደረሰኝ መስጠትና መቀበልን ባህሉ ሊያደርግ እንደሚገባ አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ አሳስበዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia
ещё
147 2 14 ноя, 21:21
Фото
የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዳኞች በአፍጋኒስታን ተፈጽመዋል በተባሉ ወንጀሎች ላይ ቀደም ሲል ተከፍቶ የነበረውን የመጀመሪያውን የምርመራ መዝገብ በይፋ እንዲዘጋ ወሰኑ የአናዶሉ የዜና ወኪል የፍርድ ቤቱን ሰነድ ጠቅሶ እንደዘገበው፥እንዲዘጋ የታዘዘው ይህ መዝገብ የአሜሪካ ወታደሮች ፈጽመዋቸዋል የተባሉ ወንጀሎችን ጨምሮ፣ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2016 ወዲህ በእስላማዊ መንግሥት የኾራሳን ክንፍ ወይም በአይ.ኤስ.አይ.ኤስ-ኬ ላይ ተከፍቶ የነበረውን ምርመራም የሚያካትት ነበር። የፍርድ ቤቱ ዳኞች ለውሳኔያቸው በምክንያትነት ያቀረቡትየዓቃቤ ሕግ ቢሮ በዚህ የመጀመሪያ መዝገብ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ወይም የክስ ሂደቶችን በውጤታማነት ማከናወን እንደሚችል ማሳየት አለመቻሉን ነው። በመሆኑም የሕግ ግልጽነትን እና የተገቢውን የዳኝነት ሥርዓት አስተዳደር ለማስጠበቅ ሲባል የፍርድ ቤቱ መዝገብ ቤት የመጀመሪያውን መዝገብ እንዲዘጋ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። በሌላ በኩል የውጭ ኃይሎች ከአፍጋኒስታን መውጣታቸውን ተከትሎ ታሊባን ወደ ሥልጣን ከተመለሰበት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከኦገስት 2021 ወዲህ ተፈጽመዋል በተባሉ ወንጀሎች ላይ የተከፈተው የተናጠል ምርመራ አሁንም እንደቀጠለ ነው። ይህ የቀጠለው ምርመራ በዋናነት ታሊባን በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ ፈጽሟቸዋል በተባሉ ወንጀሎች፣ እንዲሁም በፖለቲካዊ፣ በብሔርና በሃይማኖታዊ ምክንያቶች በሚፈጸሙ ስደቶች ላይ ያተኮረ ሲሆን፥በአራት የታሊባን አመራሮች ላይ የወጡት የእስር ማዘዣዎችም እንደጸኑ ናቸው። ይህ በእንዲህ እንዳለ፤የፍርድ ቤቱ ዓቃቤ ሕግ ቢሮ ዳኞቹ የመጀመሪያውን ምርመራ ለመዝጋት በሰጡት ውሳኔ ላይ ይግባኝ ማለቱን ዓለም አቀፍ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ልዑል ወልዴ ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ም
ещё
419 1 14 ноя, 15:55
Фото
በሙያዊ ጉዟችን ውስጥ የምናየው እውነታ አንድ ነው🙏✍️ ጠንካራ ሥርዓት የሚገነባው ሕግ ሲከበር እና ዜጎች መብታቸውን ብቻ ሳይሆን ግዴታዎቻቸውንም በንቃት ሲገነዘቡ ነው። ​እንደ ባለሙያ፣ እንደ ዜጋ፣ እና ለነገ የምንተወውን ትውልድ ስንገነባ ትልቁ መሳሪያችን "እውቀት" እና "መተማመን" ነው። ዛሬ በሥራችን የምንዘራው ትክክለኛ ነገር ነገ ለሚፈጠረው ፍትሃዊ አየር ንብረት እና የፍትሕ ምህዳር መሰረት ይሆናል። ​ለዛሬን ዓላማችን ጽኑ፣ ለሕግ ያለን ክብር የጸና ይሁን! መልካም ቀን ይሁንልን። ስለ ፍትህ እና ሙያው የጋራ ኃላፊነት አለብን 🙏✍️ ⚖️ ፍትህ የጥቂቶች ብቻ ሳይሆን የሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል የዕለት ተዕለት ትግል ውጤት ነች። በታማኝነት የሚመራ የላቀ የሕግ አገልግሎት 🙏 የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ Mikias Melak AleHig #ሚኪያስመላክ #AleHig #Law #Legal #LegalConsultancy #AddisAbaba #ProfessionalLife #BusinessCompliance #Ethiopia #LegalEducation
ещё
1 613 2 22 13 ноя, 09:58
Больше постов

Продолжить анализ этого канала

  • История роста подписчиков
  • Просмотры и охваты публикаций
  • Кто упоминает канал и кого упоминает он
  • Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней