Аналитика Telegram-канала
Подписчики
27 462
Охват за 24 ч
2,4K
ER за 24 ч
8,85%
Публикаций
2 057
Динамика подписчиков
7 дней
30 дней
6 месяцев
Больше
4 ноя7 ноя10 ноя
Показаны последние 7 дней
Больше истории →
Охваты публикаций
03.1104.1105.1106.1106.1109.11
653
Средний охват
1,8K
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале
Больше статистики →
Упоминания
7
Упоминаний
2
Из них репостов
5
Каналов
0
Упоминаний за 90 дней
0
Из них репостов
0
Каналов за 90 дней
Последние посты
3 из 2 057 2 из 2 057
የወተት ላም እርባታዎ ወደ ሰፊ የንግድ ደረጃ ተሸጋግሯል?
የስራ መጓተቶችን ለማስወገድ፣ የጉልበት ወጪን ለመቀነስ እና የእለት ተእለት ምርታማነትዎን ለማሳደግ ዝግጁ ከሆኑ፤ ከቱርክ አገር በቀጥታ ያስመጣነውን እጅግ ዘመናዊ "Vepmir" ብራንድ አውቶማቲክ የላም ማለቢያ ማሽን በመጠቀም ፍጹም አዲስ የውጤታማነት ምዕራፍን እንዲለማመዱ እንጋብዝዎታለን።
እየተስፋፉ ላሉ ሰፋፊ እርሻዎችና የግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ተብሎ ልዩ ዲዛይን የተደረገው ይህ ጠንካራ እና ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሰራው ማሽን፤ በአንድ ጊዜ 10 ላሞችን ፍጹም በሆነ ጥንቃቄ እና ቅልጥፍና ለማለብ ያስችላል።
ጠንካራና ለረጅም ጊዜ በሚያገለግል የብረት መዋቅር የተገነባ ሲሆን፣ 10 ኮንቲነሮች የያዘ ሲሆን እያንዳንዳቸው ባለ 30 ሊትር ወተት የመያዝ አቅም ያላቸው እና በፈለጉት ቦታ በቀላሉ ለማንቀሳቀስ የሚያስችሉ የተገጠሙ ጎማዎች አሉት።
ይህንን ዘመናዊ ማለቢያ በ 1.8 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር (ተጨማሪ እሴት ታክስ - VAT ን ጨምሮ) ከኛ ዘንድ ያገኙታል።
@AgriLancer
ещё
293
0
9 ноя, 08:13
በወተት ከብት እርባታ ቢዝነስ ውስጥ መጀመሪያው ሁልጊዜም አስቸጋሪው ምዕራፍ ነው።
ይህንን የመጀመሪያዎቹን ከ3 እስከ 5 ዓመታት ፈታኝ ጊዜ ማለፍ ትልቅ ስኬት ቢሆንም፣ ሁልጊዜ ባለበት መርገጥ ግን እውነተኛ አቅምዎን ይገድበዋል። ሊደርሱበት የሚችሉትን ከፍተኛ ስኬት ለማስመዝገብ፣ እርሻዎን ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግና ማስፋፋት (scale up) የግድ ይላል።
ዛሬ በታላቅ ስኬት ላይ ከደረሱ የወተት እርባታዎች በስተጀርባ ብዙዎች በግልጽ የማይናገሩት አንድ እውነት አለ፦ እያንዳንዳቸው ለትልቅ እመርታ ከመብቃታቸው በፊት፣ በዚያ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ስልታዊ የፋይናንስ ብድር አግኝተዋል።
የካፒታል ኢንቨስትመንት እርሻን ለማስፋፋት፣ የተሻሻሉ የወተት ጊደሮችን ለማሟላት፣ የቴክኖሎጂ ማለቢያ ማሽኖችን ለመግጠም እና የመኖ ማቀነባበሪያዎችን ለማደራጀት ዋናው ሞተር ነው።
በከብት እርባታ ስራ ላይ የስራ ማስፋፊያ ብድር ከባንክ ለመጠየቅ የተደራጀ የንግድ እቅድ (Business Plan) ማቅረብ፣ የፋይናንስ ሰነዶችን ማዘጋጀት እና የብድር ማስያዣ (Collateral) ማቅረብ ዋናዎቹ እርምጃዎች ናቸው።
ባንኮች ብድር ከመፍቀዳቸው በፊት የእርባታው ስራ አትራፊ መሆኑን እና የተበደሩትን ገንዘብ መመለስ እንደሚችሉ ማረጋገጥ ይፈልጋሉ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ባንኮች (ለምሳሌ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወይም የግል ባንኮች) የስራ ማስፋፊያ ብድር ለመጠየቅ የሚከተሉትን ዋና ዋና ቅድመ-ሁኔታዎች ማሟላት ያስፈልግዎታል፦
1. የንግድ እቅድ እና የስራ ማስፋፊያ ፕሮፖዛል (Business Proposal)
ባንኩ ብድሩን ለምን እንደፈለጉት እና ስራውን እንዴት እንደሚያሰፉት የሚያሳይ ዝርዝር ሰነድ ይፈልጋል።
የአሁኑ አቅም: በአሁኑ ሰዓት ያሎትን የከብት ብዛት እና የወተት/የስጋ ምርት መጠን ማሳየት።
የማስፋፊያ እቅድ: ብድሩ ሲፈቀድ የሚገዙትን የከብት ዝርያ፣ የሚገነቡትን በረት ወይም የሚገዙትን መኖ ማብራራት።
የገበያ ትንተና: ምርትዎን ለማን እና የት እንደሚሸጡ (ለምሳሌ ለወተት ማቀነባበሪያዎች፣ ለሆቴሎች) ማሳየት።
2. ህጋዊ እና የፋይናንስ ሰነዶች
የእርባታ ስራዎ ህጋዊ እውቅና ያለው እና ታክስ የሚከፍል መሆኑን ማረጋገጥ አለብዎት።
የታደሰ የንግድ ፈቃድ: በከብት እርባታ ስራ የተሰማሩበት ህጋዊ ፈቃድ።
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN ቁጥር): ከገቢዎች የተሰጠ ሰነድ።
የአመቱ የሂሳብ መግለጫ (Financial Statement): የድርጅትዎን ገቢ፣ ወጪ እና ትርፍ የሚያሳይ የኦዲት ሪፖርት።
የባንክ ደብተር እንቅስቃሴ (Bank Statement): ባለፉት 6 ወራት ወይም 1 አመት በባንክ ሂሳብዎ የነበረውን የገንዘብ ዝውውር ማሳያ።
3. የብድር ማስያዣ (Collateral)
አብዛኛዎቹ ባንኮች ለግብርና ማስፋፊያ የሚሆን የንብረት ማስያዣ ይፈልጋሉ።
የመኖሪያ ወይም የንግድ ቤት ካርታ: በከተማ ውስጥ ያለ ህንፃ ወይም ቤት።
የእርባታው ቦታ የሊዝ/የይዞታ ማረጋገጫ: ለረጅም ጊዜ የተከራዩት ወይም የእርታ ቦታው ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ።
ተሽከርካሪ ወይም ማሽነሪ: ለስራው የሚጠቀሙባቸው የጭነት መኪናዎች ወይም የወተት ማለቢያ ማሽኖች (በባንክ ሊያዙ የሚችሉ)።
4. የብድር ማመልከቻ ሂደት (ደረጃ በደረጃ)
መረጃ መሰብሰብ: ወደሚፈልጉት ባንክ በመሄድ ለግብርና/ከብት እርባታ የሚሰጡ የብድር አይነቶችን እና የወለድ መጠናቸውን ይጠይቁ።
ማመልከቻ ማስገባት: የተዘጋጀውን የንግድ ፕሮፖዛል፣ የሂሳብ ሪፖርት እና የማስያዣ ሰነዶችን አያይዘው ማመልከቻ ያስገቡ።
የመስክ ምልከታ: የባንኩ ባለሙያዎች የእርባታ ቦታዎን በአካል መጥተው ይጎበኛሉ፤ የስራውን እንቅስቃሴ ይገመግማሉ።
ግምት እና ውሳኔ: የባንኩ የብድር ኮሚቴ የቀረበውን ማስያዣ ንብረት ገምግሞ የብድሩን መጠን ይወስናል፤ ከዚያም ውል ይፈረማል።
ማስታወሻ:- ስራውን ሲጀምሩ ባሎት ካፒታል እንዲጀምረ እንመክራለን። ብድር ስራውን ለመጀመር ከመጠየቅ ይልቅ ስራውን ለማስፋፋት መጠየቁ የተሻለ አማራጭ ነው።
@AgriLancer
ещё
1 798
0
18 6 ноя, 09:34
⚡️የወተት ከብት እርባታ ስራ ማስፋፊያ ስለመጠየቅ
ещё
394
0
6 ноя, 09:33
Продолжить анализ этого канала
- История роста подписчиков
- Просмотры и охваты публикаций
- Кто упоминает канал и кого упоминает он
- Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней