Аналитика Telegram-канала
Подписчики
1 392
Охват за 24 ч
260
ER за 24 ч
18,68%
Публикаций
1 808

Динамика подписчиков

7 дней 30 дней 6 месяцев Больше
23 окт26 окт29 окт
Показаны последние 7 дней Больше истории →

Охваты публикаций

25.1025.1025.1025.1025.1026.10
114
Средний охват
205
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале Больше статистики →

Упоминания

68
Упоминаний
63
Из них репостов
3
Каналов
Все упоминания

Последние посты

3 из 1 808 2 из 1 808
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተሰጠ የኀዘን መግለጫ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በአርሲ ዞን ጥቅምት 10 እና 14 ቀን 2019 ዓ/ም በመርቲ ወረዳ አንጋዳ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጎራ ሲሊንጎ 14 ምእመናን፣ በሸርካ ወረዳ ጠሬታ ጮሌ ቢርቦ 46 ምእመናን ግፍን በተሞላ ጭካኔ ተገድለው ሕይወታቸው ማለፉን፣ የ20 ምእመናን መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ መቃጠላቸውን፣ ከ20 በላይ የሆኑ ወገኖቻችን ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታል እንደሚገኙ ከሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት የቀረበውን ሪፖርት የሰማነው በከፍተኛ ኀዘን ነው፡፡  በአርሲ ሀገረ ስብከትና በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች በሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ንፁሐን ልጆቻችን ላይ የሚፈጸመው እጅግ አሰቃቂና ዘግናኝ ጭፍጨፋ፣ መፈናቀል፣ የአካልና የንብረት ጉዳት ተከታታይነት ባለው ሁኔታ፣ ያለማቋረጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱና ከአሁን በፊትም በዞኑ ሥር በሚገኙ ወረዳዎች በርካታ ምእመናን መገደላቸው የሚታወስ ነው፡፡ በመሆኑም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን እጅግ አሳዛኝ ግፍና መከራ ጥልቅ በሆነ የኃዘን ስሜት ተመልክቶ እንዲህ ዓይነቱ አስነዋሪ ድርጊት በየትኛውም እምነት አስተምህሮም ሆነ በሰው ልጅ ሰብዓዊ መብት ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ የሃይማኖት ነፃነትና በሕይወት የመኖር ሕገ መንግሥታዊ መብትን የጣሰ፣ ከሃይማኖትም ሆነ ከተፈጥሮ ሕገ ሰብእና የወጣ፣ ተከባብሮ የመኖር ሀገራዊ ዕሴቶቻችንን የሚያጠፋ፣ ሊወገዝ የሚገባው ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በጽኑ አውግዞታል፡፡ የንፁሐኑ ግድያ እንዲቆም ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላትም ይህን ኢ-ሰብዓዊ የሆነ ተግባር በይፋ በማውገዝና በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠውን በሕይወት የመኖርና በነጻነት የማምለክ መብትን እንዲያስከብሩልን፣ ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈጸሙትን ወንጀለኞችም ለሕግ በማቅረብ የሕግ የበላይነትን ከማረጋገጥ በተጨማሪ እንዲህ ዓይነቱ አረመኔያዊ ተግባር ከእንግዲህ በኋላ እንዳይደገም አስፈላጊውን የሕግ ከለላ በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጥብቅ ያሳስባል፡፡ በደረሰው የልጆቻችን ሕልፈተ ሕይወት የተሰማንን ከፍተኛ ኃዘን በድጋሚ እየገለጽን፣ - ምእመናን ልጆቻችን በያሉበት ተመሳሳይ ጥቃት እንዲይደርስባቸው መንግሥት አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግላቸው ፣ - የሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሰጥተው ችግሩ እስከሚፈታ ድረስ እንደመንግሥት አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርጉና አደጋዎችን ማስቀረት የሚያስችል ሥራ እንዲሠሩ እያሳሰብን ለሟች ቤተሰቦችና ለመላው ኢትዮጵያውያን መጽናናትን በመመኘት በግፍ ሕይወታቸውን ላጡት ወገኖቻችን እግዚአብሔር አምላክ ዕረፍተ ነፍስንና ክብረ ሰማዕታትን እንዲያድልልን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትጸልያለች፡፡ በመጨረሻም በዛሬው ዕለት ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ/ም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አባላት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ጸሎተ ፍትሐት እንዲፈጸም፣ ነገ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም. ከሥርዓተ ቅዳሴ በኋላ በመላው ዓለም በምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማትና አድባራት በሙሉ ጸሎተ ፍትሐት እንዲደረግ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ከሚመለከተው የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን ጋር ቀጠሮ ተይዞለት ውይይት እንዲያደርግና በቀጣይም ችግሩን በዛላቂነት ለመፍታት ጥናት የሚያደርጉ አባቶችን፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንንና የሕግ ባለሙያዎችን ያካተተ ኮሚቴ እንዲሰየም መመሪያ በመስጠት  ተገቢው ጥረት እንዲደረግ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ወስኗል፡፡   የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
ещё
82 0 1 26 окт, 19:04
የምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና ወረዳ ቤተ ክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት 13ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በድምቀት አጠናቀቀ ​አዳማ — የምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና ወረዳ ቤተ ክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት 13ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በተሳካ ሁኔታ አካሄዶ አጠናቀቀ። ​በዕለቱ ከተለያዩ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የተወከሉ የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች፣ የትምህርትና ሥልጠና ተጠሪዎች፣ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች እና የጽ/ቤቱ ኃላፊዎች በጉባኤው ተገኝተዋል። ጉባኤው የባለፈውን ዓመት አፈጻጸም በመገምገም እና አዳዲስ አቅጣጫዎችን በመንደፍ ረገድ ትልቅ ምዕራፍ የሆነ ዝግጅት ሆኖ ተጠናቋል። ​ጉባኤው ያከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት እና ውሳኔዎች 👉​በዕለቱ በጉባኤው ቀርቦ በተደረገው ሰፊ ውይይት፤ የ2018 ዓ.ም የሥልታዊ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ተገምግሞ የቀረበ ሲሆን፣ እንዲሁም ለቀጣዩ ዓመት የተዘጋጀው የ2019 ዓ.ም የትኩረት እቅድ ቀርቦ ከውይይት በኋላ በሙሉ ድምፅ ጸድቋል። 👉​በነባሩ አመራር አቅራቢነት ተሠይመው በጠቅላላ ጉባኤው በጸደቁት አስመራጭ ኮሚቴ አማካኝነት እጩ የሥራ አመራርና የአፈጻጸም ክትትል ጉባኤ አባላት ቀርበዋል። ጉባኤውም አዲሱን የሥራ አመራርና የአፈጻጸምና ክትትል አባላት መንፈሳዊ ሥርዓት በሆነ መንገድ አስመርጦ አጽድቋል። በተጨማሪም ቀሪዎቹ መዋቅራዊ ክፍሎች በነባሩና በአዲሱ አመራር በጋራ በመሆን በውይይት እንዲደለደሉ ግልጽ አቅጣጫ ተቀምጧል። 👉በጉባኤው ላይ የተገኙት የምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ምክትል ሥራ አስኪያጅ መጋቢ ጥበባት ቀሲስ ጌቱ ሞቲ "ዕብ 10-:-24 ለፍቅር እና ለመልካምም ሥራ እንድነቃቃ እርስ በእርሳችን እንተያይ" በሚል ጥልቅ የመጽሐፍ ቅዱስ መሪ ቃል ላይ ተንተርሰው አጭር ትምህርታዊ መመሪያና ወቅታዊ መልዕክት አስተላልፈዋል። መልዕክታቸውም ለአገልግሎት ጥራትና ለአንድነት መጠናከር ያላቸውን ከፍተኛ ፋይዳ አጽንኦት ሰጥቷል። 👉​በመጨረሻም የአንድነቱ  መልዕክቶች እና መመሪያዎች ለጉባኤው ከቀረቡ  በኋላ የምሳ መርሐግብር ተከናውኖ የጉባኤው አጠቃላይ መርሐግብር በሰላም እና በድምቀት ተጠናቀዋል። ✍የመንበረ ጵጵስና ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጽ/ቤት
ещё
205 0 5 25 окт, 21:12
ещё
117 1 25 окт, 21:09
Больше постов

Продолжить анализ этого канала

  • История роста подписчиков
  • Просмотры и охваты публикаций
  • Кто упоминает канал и кого упоминает он
  • Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней