Аналитика Telegram-канала
Подписчики
3 877
Охват за 24 ч
298
ER за 24 ч
7,69%
Публикаций
614

Динамика подписчиков

7 дней 30 дней 6 месяцев Больше
17 ноя20 ноя23 ноя
Показаны последние 7 дней Больше истории →

Охваты публикаций

27.1001.1105.1111.1121.1121.11
192
Средний охват
454
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале Больше статистики →

Упоминания

4
Упоминаний
0
Из них репостов
4
Каналов
Нет примеров за последние 90 дней
Все упоминания

Последние посты

3 из 614 2 из 614
ጠዋት ስትነሱ! መጀመሪያ የምታስቡት ሃሳብ ምን እንደሆነ በሚገባ ተመልከቱትና ያላችሁበትን የስሜት ሁኔታ ይነግራችኋል፡፡ •  በእለቱ የምታከናውኗቸው ተግባሮቻችሁ ከባድ እንደሆኑ ካሰባችሁ እቅድ የማውጣት ክህሎት ላይ መስራት አለባችሁ፡፡ •  ትናንት ስሜታችሁ ላይ አጉል ተጽእኖ ስለነበረው ሰው ካሰባችሁና ከተረበሻችሁ የሰዎችን ሁኔታ አያያዝ ላይ መስራት አለባችሁ፡፡ •  ምንም የምትሰሩት ስራ እንደሌላችሁ ካሰባችሁ የፈጠራ እና አዳዲስ ነገር የመጀመር አቅማችሁ ላይ መስራት አለባችሁ፡፡ •  ሁኔታችሁ ሊለወጥ እንደማይችል የተስፋ መቁረጥ ሃሳብ ካሰባችሁ የሰዎችን የምክር እገዛ የመጠየቅና የመጠቀም ሁኔታ ላይ መስራት አለባችሁ፡፡ ሃሳቦቻችሁንና እነሱ የወለዷቸው ስሜቶቻችሁን በፍጹም ችላ አትበሏቸው፡፡ ተገቢውን ምላሽ ስጧቸው፡፡ ስላላችሁበት ሁኔታ ሰዎችን መውቀስ አቁሙና አንድ ነገር አድርጉ፡፡ ያላችሁበትን ሁኔታ ለመርሳት ማሕበራዊ ሚዲያ ላይ በመዋል አትደበቁ፡፡ ቀና በሉና ራሳችሁ ላይ ስሩ! join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book
ещё
108 2 21 ноя, 14:37
ሁለት አይነት ስሜታዊነቶች! አንዳንድ ሰዎች ስሜታቸውን በፍጹም መቆጣጠር አይችሉም፡፡ አንድ ስሜት ከተሰማቸው ወይም አንድን ሃሳብ ካሰቡ፣ እንደመጣላቸው ነው የሚለቁት፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች፣ “ግልጽ ሰው ነኝ” በሚል ሰበብም ሆነ በሌሎች ምክንያቶች ሰዎችን እንደጎዱና ተከትሎ ከሚመጣው የማሕበራ ቀውስ የተነሳ እነሱም እንደተጎ ይኖራሉ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ስሜታቸው ካለል ያፍናሉ፡፡ አንድ ስሜት ሲሰማቸው በተገቢው መልክና በልኩ ከመልቀቅ ይልቅ አፍነው በመያዝ ውስጣቸው ያቆዩታል፡፡ ከዚህም የተነሳ ውስጣቸው በጣም ይጎዳል፡፡  ከዚያም አልፎ ስሜቱ ሲጠራቀም አንድ ቀን ይፈነዳና ከፍተኛ የሆነ የግኙነት ቀውስ ይፈጥራል፡፡ በየጊዜው የውስጣቸውን ባለማሳወቅ ቆይተው ሲፈነዱ፣ ካለምንም ምክንያት ስሜታዊ እንደሆኑ በማሰብ ይፈርጇቸዋል፡፡  በስሜት ብልህነት የበሰሉ ሰዎች አንድ ስሜት ሲሰማቸው እንደመጣ ከመልቀቅም፣ ስሜቱን አምቆ ከመያዝና ከማፈንም ራሳቸውን የሚጠብቁ ናቸው፡፡ ይህ ማለት በስሜት ብልህነት በመብሰል ትክክለኛውን ስሜት፣ በትክክለኛው ሰው ላይ፣ ቦታ፣ ጊዜ እና መጠን መግለጥን ይለማመዳሉ፡፡ በዚህ ርእስ ላይ የበለጠ ግንዛቤ በማግኘት ስኬታማ ጉዞ ለመጀመር የሚያስችላችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል፡፡ የስልጠው ርእስ፡- “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence) ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live) የስልጠናው ቀናት፡- መጋቢት 25፣ ሚያዚያ 2፣ ሚያዚያ 9፣ ሚያዚያ16 እና ሚያዚያ 23 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች) የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር) የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል Dr Eyob mamo join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book
ещё
1 0 21 ноя, 14:35
#አልፈልግምን_ፈልገው! ለአንድ ነገር ዋጋ ለመስጠት፣ ያ ነገር ያልሆነውን ነገር አለመቀበል አለብን፡፡ ለ X ዋጋ ለመስጠት X ያልሆነውን ውድቅ ማድረግ አለብን፡፡ ያ ‘አለመቀበል’ እሴቶቻችንንና ማንነታችንን ለመጠበቅ ተፈጥሯዊ እና አስፈላጊ አካል ነው። እኛ የምንገለፀው ላንቀበለው በምንመርጠው ነገር በመሆኑ፣ በራሳችን ውድቅ እንዳንሆን በመፍራት ምንም ነገር ‘አንፈልግም’ የማንል ከሆነ በመሰረቱ ምንም አይነት ማንነት የለንም ማለት ነው። በማንኛውም ዋጋ በመክፈል አለመፈለግን ውድቅ የማድረግ፣ ክርክርና ግጭትን የማስወገድ፣ እንዲሁም እና ሁሉንም ነገር ለማስማማት እና ህብር ለመፍጠር ሁሉንም ነገር በእኩልነት ለመቀበል የመሞከር ፍላጎት ጥልቅ እና ስውር ራስን ከፍ አድርጎ የማየት መንገድ ነው። ራሳቸውን ከፍ አድርገው የሚያዩ ሰዎች፣ ሁልጊዜ ጥሩ ስሜት ሊሰማቸው እንደሚገባ ስለሚሰማቸው፣ እነሱንም ሆነ ሌላ ሰውን ሊያሳዝን ይችላል ብለው ስለሚያስቡ ማንኛውንም ነገር ‘አልፈልግም’ ከማለት ይቆጠባሉ። የትኛውንም ነገር ‘አልፈልግም’ ማለት ባለመቻላቸው ምክንያት ዋጋ የሌለውና ለራስ ብቻ ትኩረት የሚሰጥ በፍላጎት የሚገፋ ኑሮ ይኖራሉ፡፡ ግድ የሚሰጣቸው የማይቀረውን የህይወታቸውን ውድቀት በመሸሽና ስቃይን እንዳባረሩ በማስመሰል ለጥቂት ጊዜ ከፍታ ላይ መቆየት ነው፡፡ አለመፈለግ በጣም አስፈላጊና ወሳኝ የሕይወት ክህሎት ነው፡፡ join us...      @Ab_book    @Ab_book    @Ab_book
ещё
416 1 11 ноя, 20:31
Больше постов

Продолжить анализ этого канала

  • История роста подписчиков
  • Просмотры и охваты публикаций
  • Кто упоминает канал и кого упоминает он
  • Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней