Аналитика Telegram-канала
Подписчики
7 848
Охват за 24 ч
741
ER за 24 ч
9,44%
Публикаций
5 329

Динамика подписчиков

7 дней 30 дней 6 месяцев Больше
16 ноя19 ноя22 ноя
Показаны последние 7 дней Больше истории →

Охваты публикаций

21.1121.1121.1121.1121.1122.11
97
Средний охват
219
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале Больше статистики →

Упоминания

1 606
Упоминаний
878
Из них репостов
153
Каналов
Все упоминания

Последние посты

3 из 5 329 2 из 5 329
1️⃣ ሥነ-ጽሑፍ በእስልምና ያለውን ደረጃ ከሚያሳዩ የቁርአን አንቀጾች ውስጥ ሁለት አንቀጾች በፕሮግራማችን ላይ ተጠቅሰዋል። እነሱም፦ ሀ.ሱረቱል ቀለም የመጀመሪያው አንቀጽ ነው። ن ۚ وَالْقَلَمِ وَمَا يَسْطُرُونَ አላህ ታላቅ ነው፤ እሱ ታላቅ በሆኑ ነገሮች እንጂ አይምልም። በዚህ አንቀጽ አላህ በቀለምና በሚጽፉት ነገር መማሉ የሥነ-ጽሑፍን ታላቅነት ያሳያል። ለ.ሱረቱል ኢቅራዕ የመጀመሪያው አንቀጽ ነው። اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ በፕሮግራማችን ላይ እንደተነሳው ምንም እንኳን እንደ አማርኛ «አንብብ» የሚለውን መተክያ ብንቀስድም ቃሉ ግን ማንበብን ብቻ ሳይሆን ሐሳብን ማስተላለፍን ያካትታል። 2️⃣ ሐ. ቢላል መጽሔት በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ታሪክ የመጀመሪያው መጽሔት ቢላል መጽሔት ሲሆን የተጀመረውም በ1984 የወጣውን አዋጅ ተከትሎ ነው። ሥራውን ያስጀመሩት ሼኽ መሐመድ ወሌ ሲሆኑ ለ28 ወራት 20 ተከታታይ ቅጾችን አሳትመዋል። መጽሔት በሙስሊሞች ጉዳይ የሚነሱ አጀንዳዎችን ከማቅረብና ከማብራራት አልፎ በሚያቀርባቸው ሁሉን አቀፍ ይዘቶች አዲስ አጀንዳን መፍጠር ይችላል ነበር። 3️⃣ በሱረቱል ረሕማን አንቀጽ 4 ላይ አላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል፦ عَلَّمَهُ الْبَيَانَ «አል-በያን መጽሔት»ም ይህንን መልእክትና አደራ መሠረት በማድረግ የተማሪዎችን ድምጽ በግልጽነት፣ በክብር፣ በጥበብና በኃላፊነት ለማቅረብ የሚዘጋጅ መጽሔት ነው። 4️⃣ «አንዲት ሐሙስ» በሚል በመጽሔታችን የቀረበችው ቀን የዋለችው መጋቢት 03 ቀን 2018(ረመዳን 24:1447) ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ለተማሪዎች ጥያቄ ምላሽን ሳይሰጥ ምላሽ የነፈጋቸውን ተማሪዎች ኢፍጣር በጠራበት ወቅት የተገኙ እህቶች የቀረበላቸውን ምግብ በመተውና ድምጻቸውን በማሰማት የቀረበላቸውን ምግብ ብቻ ሳይሆን በደልንም እምቢ ያሉባት ታሪካዊ ምሽት ናት። 5️⃣ መ. ዶ/ር ሰሚር — ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በፕሮግራማችን ላይ እንደተነሳው ከ2002–2004 መንግሥት ሙስሊሙን ለመበታተን በያዘው አቅጣጫ የአሕባሽን አስተምህሮ ወደ ሀገር አስገብቷል። ይህንን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግም ኡስታዞችንና ሌሎች የሃይማኖት መምህራንን በዚህ አስተምህሮ ለማጥመቅ ዶ/ር ሰሚር የሚባል ለዚሁ ዓላማ የተላከ ግለሰብ ወደ ሀገር ገብቷል። ይህንን ዕቅድ ተግባራዊ ማድረግ የተጀመረው ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን ሕዝቡን ከዚህ አደጋ ለመታደግ ይዘጋጁ የነበሩ ጽሑፎችና መረጃዎችን ከማሰራጨት እና ህዝቡን ከማንቃየት በተጨማሪ በኋላ ላይ በ2004 ለተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል። የጥያቄና መልስ ውድድሩ አሸናፊ እህታችን ሂክማ ሆናለች። እህታች እንኳን ደስ ያለሽ! ሽልማቱ በ ዶ/ር መሐመድ አዛህራኒ የተዘጋጀ " Healing of the heart" የሚል መፅሀፍ ሲሆን ለአሸናፊያችን የሚደርሳት ይሆናል ኢንሻላህ! "የወረቀት ላይ እውነት: ከትላንት ጭቆና እስከ ዛሬ ትግል" በሚል የተዘጋጀው ፕሮግራም በዚሁ ተጠናቋል። ከዝግጅቱ ብዙ እንደተጠቀማቹበት ተስፋ እያረገን በቀጣይ በአሏህ ፈቃድ በሌሎች ርዕሶች የምንገናኝ ይሆናል። @aaumsu
ещё
82 1 2 22 ноя, 10:34
🌟የብርሃን ዱካዎች ክፍል 13 ዑመር ኢብኑ ዐብዱልዐዚዝ ሕዝቡ ቃል-ኪዳን (በይዓ) ከገባለት በኋላ ከደማስቆ መስጂድ ሚንበር እንደወረደ፣ በመስጂዱ በር ላይ የበኑ ኡመያ ነገሥታት የለመዱትን ትዕይንት ተመለከተ፤ አዲሱን ኸሊፋ በታላቅ ግርማና ሥልጣን ወደ ቤተ-መንግሥቱ ለማድረስ የተሰለፉ ረጃጅም የሽልም ፈረሶች፣ የቅንጦት በቅሎዎችና የንግሥና አጃቢዎች ይጠባበቁት ነበር! ዑመር ቆም አለና፣ ከዚህ ብልጭልጭ ጀርባ ያለውን የጀሀነም እሳት በሚያይ የዛሂድ ዓይን በመገረም ፦ “እነዚህ ምንድን ናቸው?” አለ። እነርሱም፦ “አሚረል ሙእሚኒን ሆይ! እነዚህ የኸሊፋው መጓጓዣዎች ናቸው!” አሉት። እርሱም በእጁ እየገፈተረ ፦ “እኔ ከእነዚህ ጋር ምን ጉዳይ አለኝ? ለእኔ ይበልጥ የምትመቸኝን የራሴን በቅሎ አቅርቡልኝ! እነዚህን ፈረሶች ግን ሽጧቸውና ገንዘቡን በሙስሊሞች ግምጃ ቤት (በይቱል ማል) ውስጥ አስገቡት!” አለ። ዑመር በዚህ አላበቃም ፤ወደ ኸሊፋው ቤተ-መንግሥት ገባና፣ ራሱን ከሰው ሀቅ ማጽዳቱን ከቅርብ ሰዎቹ ጀመረ፤ እርሷም በታሪክ የኸሊፋ ልጅ፣ የኸሊፋዎች እህትና የኸሊፋ ሚስት ተብላ የተወደሰችው ተወዳጅ ባለቤቱ ፋጢማ ቢንት ዐብዱልመሊክ ነበረች። በፊቷ ቆሞ፣ አባቷ ከመንግሥት ግምጃ ቤት የሰጣትን ውድ ወርቆችና ጌጣጌጦች እየተመለከተ፣ ፍቅርና የአላህ ፍራቻ በተሞላበት ጽኑ ድምፅ እንዲህ አላት፦ “ፋጢማ ሆይ! አባትሽ እነዚህን ጌጣጌጦች የሰጠሽ ከሙስሊሞች ግምጃ ቤት (በይቱል ማል) ነው... ስለዚህ ከሁለት አንዱን ምረጪ፤ ወይ ወደ ግምጃ ቤቱ መልሰሻቸው ከእኔ ጋር በድህነትና ባለን ነገር ተብቃቅተን እንኑር፣ አለበለዚያ እነርሱን ይዘሽ ወደ ቤተሰቦችሽ ቤት ሂጂ፤ እኔና እነዚህ ጌጣጌጦች በአንድ ቤት ውስጥ ፈጽሞ አንሰበሰብምና!” ፋጢማ ለአንዲት ቅጽበት እንኳ አላመነታችም! ታሪክን ባስደመመ ታማኝነት፦ “በአላህ እምላለሁ ዑመር ሆይ! ካንተ አስበልጬ የምመርጠው አንዳችም ነገር የለም፤ ገንዘብም ሆነ ወርቅ አልፈልግም፤ ሕይወቴ ያንተ ሕይወት ናት!” አለችና ጌጣጌጦቿን በሙሉ ሰብስባ ወደ በይቱል ማል አስገባቻቸው!። በዚያው ዕለት ሌላ ክስተት ሌላ የፍትህ ከፍታ ...... ነገሩ ለድሆች እንዲታደል ከሙስሊሞች ምርኮ የተገኘ “ፖም” መጥቶ ነበር። ዑመር በቤቱ ውስጥ ሳለ፣ ትንሹ ልጁ ከዚያ የሕዝብ ሀብት የተገኘ አንድ ፖም ይዞ  እየበላ ወደ እርሱ ገባ! ዑመር ልክ እባብ እንደነደፈው ሰው በድንጋጤ ተስፈንጥሮ ተነሳ! ወደ ልጁ ሮጦ ፖሙን ከአፉ ላይ በኃይል ነጥቆ ወደ ሩቅ ወረወረው! ሕፃኑም በምሬት እያለቀሰ ወደ እናቱ ፋጢማ ሮጠና፦ “እማዬ፣ አባቴ ፖሙን ከአፌ ነጠቀኝ!” ሲል አቤት አለ። የእናት አንጀት ራራለትና አንድ አገልጋይ ልካ ከራሷ የግል ገንዘብ ለልጇ ፖም አስገዛችለት። ዑመር ወደ ቤቱ ሲመለስ የፖሙን ሽታ አሸተተ፤ ፊቱም ተለዋወጠና ፍርሃት በተቀላቀለበት ቁጣ፦ “ፋጢማ ሆይ! ፖሙን ከቤቴ አላስወጣሁትም ነበር እንዴ? ሽታውን እያሸተትኩ ነው!” አላት። እርሷም፦ “በአላህ እምላለሁ ከሙስሊሞች ገንዘብ አይደለም፤ እያለቀሰ ወደ አንተ በመጣ ጊዜ ከራሴ የግል ገንዘብ በአንድ ዲርሃም የገዛሁለት ነው” አለችው። በዚህ ጊዜ... የዑመር ትንፋሽ ተረጋጋ፣ እንባዎቹም በጢሙ ላይ እየወረዱ  ታሪካዊ ንግግርን ተናገረ፦ “ፋጢማ ሆይ! በአላህ እምላለሁ ፖሙን ከልጄ አፍ ስነጥቀው ልክ ከልቤ ውስጥ የነጠቅኩት ያህል ነበር የተሰማኝ... ነገር ግን ከሙስሊሞች ገንዘብ በተወሰደች አንዲት ፖም ምክንያት በአላህ ፊት ራሴን ማዋረድን ፈራሁ!” ዑመር.... የሰው ሀቅን መጠበቅ ከገዛ ቤተሰቡ የጀመረ የፍትህ አምባር!። የመንግሥት አስተዳደሩን እንዴት ለወጠው? የበኑ ኡመያ መኳንንትስ ምን ገጠማቸው? #ሚሽካት የብርሃን ዱካዎች ይቀጥላል..... ⚖️✨ @aaumsu
ещё
96 0 2 21 ноя, 21:07
Фото
ещё
96 0 21 ноя, 21:07
Больше постов

Продолжить анализ этого канала

  • История роста подписчиков
  • Просмотры и охваты публикаций
  • Кто упоминает канал и кого упоминает он
  • Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней