Аналитика Telegram-канала
Подписчики
772
Охват за 24 ч
97
ER за 24 ч
12,56%
Публикаций
5 555

Динамика подписчиков

7 дней 30 дней 6 месяцев Больше
22 окт25 окт28 окт
Показаны последние 7 дней Больше истории →

Охваты публикаций

27.1027.1027.1027.1028.1028.10
11
Средний охват
16
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале Больше статистики →

Упоминания

148
Упоминаний
137
Из них репостов
7
Каналов
Все упоминания

Последние посты

3 из 5 555 2 из 5 555
ከኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለሕልውና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ! የብልፅግና አገዛዝ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያወጀውን ያልተቋረጠ ጦርነት አጠናክሮ በመቀጠል፣ በንፁኃን ዜጎች ላይ ጭፍጨፋ፣ ስልታዊ ማፈናቀልና ውድመት እያካሄደ ይገኛል። ተመሳሳይ ተግባራትን መፈፀም ተልዕኮው የሆነው ዘረ ፈጁ የብልፅግና አገዛዝ ሰሞኑንም የተጠናከሩ የጅምላ ጭፍጨፋ ወንጀሎችን በተለያዩ አካባቢዎች ፈፅሟል። በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በአማራና በሌሎች ኢትዮጵያዊያን ሕዝቦች ላይ ከከፈታቸው ይፋዊ መንግስታዊ ጦርነቶች በተጨማሪ በጉልህ የሚጠቀሱት የአገዛዙ ሰሞናዊ የወንጀል ድርጊቶችም፦ 1ኛ) ወለጋ፦ በምስራቅ፣ በምዕራብና በቄለም ወለጋ ዞኖች አገዛዙ በቀጥተኛና በተዘዋዋሪ መዋቅሮቹ በንፁሃን የኦሮሞ እና የአማራ ህዝብ ላይ ግድያ፣ ስልታዊ ማፈናቀልና የኢኮኖሚ ውድመት እየፈጸመ ይገኛል። በተለይም ካለፈው ነሀሴ ወር ጀምሮ በተከታታይ በተፈፀሙ ወንጀሎች በምስራቅ ወለጋ በርካታ ትናንሽ ከተሞችን በማውደም ከ80 ሺህ በላይ አማሮችን ያለ መጠለያ እና ሰብአዊ እርዳታ በጫካ በትኗል። በሺህ የሚቆጠሩትን ገድሏል። ድርጊቱ ዛሬም እንደቀጠለ ይገኛል። 2ኛ) አርሲ ዞን፦ በሽርካ ወረዳ እና በአጎራባች ወረዳዎች የሚኖሩ ሰላማዊ የአማራ ተወላጅ ኦርቶዶክሳዊያን በእርሻ ማሰማሪያቸው ላይ እያሉ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል። ላለፈው አንድ ዓመት በአካባቢው በማንነታቸው እና በእምነታቸው ምክንያት የተጨፈጨፉት አማራዎች ቁጥር ከአንድ ሺህ የሚልቅ ሲሆን በሺህ የሚቆጠሩት ደግሞ ተፈናቅለዋል። ህዝብን በብሔርና በሃይማኖት ከፋፍሎ ዘላቂ ግጭት ውስጥ በማስገባት ስልጣንን ለማራዘም የሚደረገው ይህ አረመኔያዊ ተግባር በአገዛዙ ቀጥተኛ ድጋፍ እና ባለቤትነት የሚፈጸም ነው። 3ኛ) ሞያሌ፦ የኦሮሞ እና የሶማሌ ህዝብ በመስተጋብር የሚኖሩበትን የሞያሌ ከተማ የቀውስ ማዕከል በማድረግ በተለይም በአገዛዙ የሚመሩ የየክልል የፀጥታ አካላት እንዲዋጉ በማድረግ እንዲሁም የጸጥታ ክፍተት በመፍጠርና የህዝብ አገልግሎቶችን በማቋረጥ ንጹሃን የኦሮሞ እና የሶማሌ ተወላጆችን ለሞትና ለስደት ዳርጓል። 4ኛ) ጋምቤላ፦ አገዛዙ በጋምቤላ ክልል ከጥቅምት 3-5/2019 ዓ.ም የክልልና የፌደራል ኃይሎችን በማሰማራት ሰላማዊ ዜጎችን በብሔር ማንነታቸው በመነሳት የዘር ፍጅት ፈፅሞባቸዋል፤ ይህ አረመኔያዊ ተግባር በአገዛዙ ቀጥተኛ ድጋፍ እና ባለቤትነት የተፈፀመ ነው። በመሆኑም አገዛዙ በዜጎች ላይ እየፈፀማቸው ያሉት የዘር ፍጅት፣ ማፈናቀልና ሌሎች ኢ-ሰብዓዊ ተግባራትን ትብብር ለህልውና የሽብር ድርጊቱ ባለቤት የሆነውን የቀውስ አገዛዝ በመታገል ህዝባችንን ከዚህ ጥቃት የመከላከል ኃላፊነታችንን በመወጣት በሀገሪቱ ላይ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የምናደርገዉን ሁለንተናዊ ተጋድሎ አጠናክረን የምንቀጥል መሆናችንን እናረጋግጣለን። ለዚህ ሁሉ ወንጀል ተጠያቂ የሆኑት ሁሉ ከፍትህ ፊት አያመልጡም። ትብብር ለህልውና ህዝባችንን ከጥቃት ለመታደግና አምባገነናዊውን አገዛዝ ለማስወገድ የጀመረውን ትግል በቁርጠኝነት ይቀጥላል። ጥሪያችን፦ ለትብብር ለህልውና አባል ድርጅቶች ሰራዊትና አመራር፦ በሁሉም ግንባሮችና ቀጠናዎች ወታደራዊና ፖለቲካዊ ፀረ-ማጥቃታችንን በማፋጠን፣ የአገዛዙን የጭቆና መዋቅሮች በመሰባበርና ሕዝባችንን ከጥቃት በመከላከል የሕዝብ ደጀንነታችንን እንድናሳይና ታሪካዊ አደራችንን እንድንወጣ እናሳስባለን። ሰራዊታችን በወታደራዊ ዲሲፕሊንና በዓለም አቀፍ የሰብአዊ ህጎች ተገዥነት፣ ንፁሃን ዜጎችን ከጥቃት በመጠበቅ ይንቀሳቀሳል። ለመላው ኢትዮጵያዊያን፦ ይህንን አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ከህዝባዊ ኃይሎች ጎን እንድትሰለፉ፣ የተቀናጀውን ትግል በአንድነትና በቁርጠኝነት እንድታጠናክሩ ጥሪ እናቀርባለን። ለጎረቤት ሀገራትና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ፦ ይህ አገዛዝ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ቀንድ ቀውስንና ጦርነትን ከማምረት ውጪ ሰላምን የማስፈን ፍላጎትም ሆነ አቅም እንደሌለው ተገንዝባችሁ፣ ዝምታችሁን እንድታቆሙና ከኢትዮጵያ ህዝብ የፍትህ፣ የዲሞክራሲና የህልውና ትግል ጎን እንድትቆሙ እንጠይቃለን። ድል ለሕዝባዊ ኃይሎች! ጥቅምት 17/2019 ዓ.ም
ещё
11 0 28 окт, 16:49
አሳዛኝ ዜና አሁን ከወለጋ ጥቅምት 18/2019 ዓ/ም በምስራቅ ወለጋ ሲቡ ስሬ ወረዳ 80 ህጻናት እና ሴቶች መንገደኞችን የኦሮሞ ገዳ ኮማንዶ ኃይል ከአውቶብስ አስውርዶ ወደ ጫካ ከወሰደ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ ዛሬ ሌሊቱን መጨፍጨፉ ተሰማ ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ ዐያና ወረዳ ተፈናቅለው ነፍሳቸውን ለማትረፍ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ በነበሩ ንጹሃን ዜጎች ላይ አሰቃቂ ጭፍጨፋ መፈጸሙን ከስፍራው የወጡ መረጃዎች አመላከቱ። እንደ መረጃ ምንጮች ገለጻ፣ ተፈናቃዮቹ የአንገር ወንዝን በነፍስ ወከፍ 3,000 ብር እየከፈሉ ከተሻገሩ በኋላ፣ በሲቡ ስሬ ወረዳ አካባቢ ወደ አዲስ አበባ የሚያጓጉዛቸውን አውቶብስ ይዘው ሲጓዙ መንገድ ላይ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል። አውቶብሱ ከተያዘ በኋላ ተሳፋሪዎቹ በሙሉ በኃይል ተገደው እንዲወርዱ እና ወደ ጫካ ከተወሰዱ በኋላ በቆንጨራ እና በገጀራ አሰቃቂ ጭፍጨፋ እንደተፈጸመባቸው ተገልጿል። ከተገደሉት ንጹሃን መካከል 80 በመቶ ያህሉ ሴቶች እና ህጻናት ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ 20 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ አዛውንቶች እና ሽማግሌዎች እንደሆኑ ተጠቅሷል። በተመሳሳይ መልኩ ወንዙን ተሻግረው በሌላ ካምፕ ውስጥ መጠለያ ይዘው በነበሩ ተፈናቃዮች ላይ በደረሰ ጥቃት፣ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ የሟቾች ቁጥር ከ60 በላይ መድረሱ ተገልጿል። በአሁኑ ወቅት ወደ አዲስ አበባም ሆነ ወደ ጎጃም የሚያመሩ የየብስ መንገድ መስመሮች በመዘጋታቸው እና በአየር መንገድ በኩልም ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በመደረጉ፣ ከአካባቢው ለመውጣት የሚሞክሩ ተፈናቃዮችና መንገደኞች መውጫ አጥተው ለከፍተኛ ከበባ መጋለጣቸው ተጠቅሷል። እስከ አሁን ድረስ የሟቾች አስክሬን ከአካባቢው አለመነሳቱ የተገለጠ ሲሆን የስድስት ህፃናት አስክሬን በጅብ መበላቱ ታውቋል፡፡ ከወለጋ አሁን የተላከ መረጃ
ещё
1 0 28 окт, 10:06
Фото
የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ነ- ቀርሳ ፣ በወንድማማቾች መሐል እየገባ ሲከፋፍል የነበረ ሸይጣን የሚቀናበት አሪዮስ በስተመጨረሻም "ትግል በቃኝ" ብሎ ራሱን ከአፋብን ድርጅት አግልሏል። በራሱ አንደበት ለአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ራሱን ለማግለል ደብዳቤ ማስገባቱን በድምፁ አንብቦ ባጋራው ማመልከቻ ላይ ገልጿል። አሁን የአፋብንን የመጨረሻ መጨረሻ ውሳኔ እንጠብቃለን። ይሄ አርዮስ ከዚህ ቀደም ለአመታት ወንድማማቾችን ዶላር እየበተነ ሲያገዳድል ከርሟል - አፋብንም ፀጥ ብሎ ጭራሽ ሹመት ሰጥቶት መጣ። ከዛ በመቀጠል እንሽላሊቱ ተራ አባል ሁኜ እታገላለው አልፈልጋቹህም አለ። አፋብንም አሁንም ምንም አይነት እርምጃ አልወሰደም ነበረ። ይኼው ዛሬ በስተመጨረሻ ከድርጅቱ በይፋ ራሴን አግልያለው በማለት ደብዳቤ ማስገባቱን ተናግሯል። አሁን በዚህ ወቅት አፋብን በዚህ ወንጀለኛ ሰውዬ ላይ የመጨረሻ መጨረሻ የሚለዉን ውሳኔ ወስኖ ካላሳዬ ድርጅቱ የመጨረሻ የሞተ ልፍስፍ ድርጅት መሆኑን በይፋ ያሳያል። የድርጅቱ ልፍስፍስነት እንጂ ይሄ አርዮስ ከአብይ አህመድ እኩል ለፍርድ የሚቀርብ ነ- ቀርሳ ነበረ.....
ещё
13 0 27 окт, 22:32
Больше постов

Продолжить анализ этого канала

  • История роста подписчиков
  • Просмотры и охваты публикаций
  • Кто упоминает канал и кого упоминает он
  • Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней