Аналитика Telegram-канала
Подписчики
680
Охват за 24 ч
68
ER за 24 ч
10,00%
Публикаций
213

Динамика подписчиков

7 дней 30 дней 6 месяцев Больше
13 ноя16 ноя19 ноя
Показаны последние 7 дней Больше истории →

Охваты публикаций

11.1114.1115.1115.1116.1117.11
22
Средний охват
28
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале Больше статистики →

Упоминания

1
Упоминаний
0
Из них репостов
1
Каналов
Нет примеров за последние 90 дней
Все упоминания

Последние посты

3 из 213 2 из 213
Фото
ሠለስቱ ምዕት (318ቱ ሊቃውንት) በሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከሊብያ የተወለደ ሰባልዮስ የሚባል ሰው በትምህርት ምክንያት ሮም ሄዶ የክህደት ትምህርት ተምሮ መጥቷል። በቤተ ክርስቲያን የመጀመርያው ከሃዲ በመኾን ወልድ ፍጡር ነው (ሎቱ ስብሐት) ብሎ ያስተማረው አርዮስ የሊብያ ተወላጅ ነበር። በሮም ያሉ መናፍቃን አንድ አካል አንድ ገጽ እያሉ ያስተማሩት ትምህርት ሦስትነት የለም የሚል የተሳሳተ ፍልስፍና ነበር። አርዮስም የሰባልዮስ ተማሪ ነበር። የነሰባልዮስ አባባል፦ "አንዱ አካል ብሉይ ኪዳንን ስለሰራ አብ፤ በዘመነ ሥጋዌ የማርያምን ሥጋ ስለተዋሀደ ወልድ በበዓለ ኀምሳ በእሳት አምሳል ስለወረደ መንፈስ ቅዱስ ተባለ እንጂ ፈጣሪ አንድ አካል አንድ ገጽ ነው" በማለት ይኽን ክህደት አስተምሯል። በሊብያ የተወለደው አርዮስም ወልድ ፍጡር ነው በማለቱ በ፫መቶ ፳፭ ዓ.ም. ፫፻፲፰ ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት አባቶች በኒቅያ ተሰብስበው የለዩት ኅዳር ፱ ነው። ይኽን ጉባዔ የጀመሩት መስከረም ፳፩ ቀን ነበር፤ ውሳኔው ወይም ውግዘቱ የተሰጠው ኅዳር ፱ ቀን ነው፤ በዚኽ ጉባዔም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከ፫፻፲፰ቱ አባቶች አንዱ ነበር።
ещё
24 0 17 ноя, 20:27
ኪሩቤል- አርባዕቱ እንስሳ ኪሩቤል የብዛት ስም ሲኾን በነጠላ ሲጠራ ኪሩብ ነው። ቅዱሳን መላእክት ኾነው እንስሳ መባላቸው በእንስሳት አምሳል የሚታዩ ስለ ኾኑ ነው። ስራቸው የእግዚአብሔርን ዙፋን ተሸክመው እግዚአብሔር ለፈቀደው መገለጽ ነው። ከአራቱ አንዱ ባራ ማራ ይባላል፤ ፊቱም በአንበሳ ይመሰላል። ስለ አራዊት የሚለምነው መልአክም ይኽ ነው። ቅዱስ ማርቆስም በዚኽ አንበሳ ይመሰላል። ኹለተኛው መሊጦን ይባላል፤ ፊቱም በላም ይመሰላል። ስለ እንስሳት ይለምናል። ቅዱስ ሉቃስም በላም ይመሰላል። ሦስተኛው እግረ ማጣ ይባላል፤ ፊቱም የሰውን ልጅ ፊት ይመስላል። ለሰው ልጅ ሥርየት ይለምናል። ቅዱስ ማቴዎስም በሰው ፊት ይመሰላል። አራተኛው ሱርትዮን ይባላል፤ ፊቱም በንሥር ይመሰላል። ለአዕዋፍ ይለምናል። ቅዱስ ዮሐንስም በዚኽ ይመሰላል። ለኪሩቤል ለእየአንዳንዳቸው አራት ፊት አላቸው። ወደ ኋላ ወደ ፊት ግራ ቀኝ መዞር አያስፈልጋቸውም ማለት ነው። ለእያንዳቸው ስድስት ክንፍ አላቸው። በኹለት ክንፋቸው ፊታቸውን፤ በኹለት ክንፋቸው እግራቸውን ይሸፍናሉ። አንድ ክንፋቸውን ወደ ላይ አንድ ክንፋቸውን ወደ ታች ይዘረጋሉ። ፊታቸውን መሸፈናቸው አቤቱ ባሕርይህን መመርመር አንችልም ሲሉ፤ እግራቸውን መሸፈናቸው ከአንተ ፊት ጸንተን መቆም አንችልም አጽናን ሲሉ፤ ወደላይ ከፍ እና ወደታች ዝቅ ያለው ክንፍ ብንወጣ ብንወርድ አትመረመርም ማለታቸው ነው። አርባዕቱ እንስሳ ኪሩቤል በዓላቸው ኅዳር ስምንት ቀን ይከበራል።
ещё
28 0 1 16 ноя, 20:19
ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኅዳር ፯ ቅዳሴ ቤቱ የሚከበርበትና ቃልኪዳን የተቀበለበት ነው። ይኽም ቀን በቤተ ክርስቲያን በትልቅ ክብር ይከበራል። በዚኹም ዕለት በየቤተ ክርስቲያኑ የሚደረግ ስርዓት ወይም ጸሎት ይኽ ነው። በዐውደ ምሕረት ምእመናን ተሰብስቦ፤ መስቀል፣ ሥዕለ አድኅኖ፣ ተአምረ ማርያም ወጥቶ አራት መቶ ጸሎተ ምሕላ ይደርሳል። እኩሌቶቹ ካህናት ደግሞ መዝሙረ ዳዊት ተከፋፍለው መቶ ሃምሳውን ያደርሳሉ። ከአራቱም ወንጌል የሚነበቡ ወይም የሚደገሙ ክፍሎች አሉ። ምእመናንም የወይራና የግራር ፍልጥ ይዘው ይመጣሉና፤ ካህናቱ እስከ ስብከታቸው ወይም ወጥተው አካባቢውን እግዚኦታ እያደረሱ ያጥናሉ። ከሌላም ቤተ ክርስቲያን ከሚመጣ ጋር ሲገናኙ አብረው ጸሎት አድርሰው ወደየ ዐውደ ምሕረታቸው ይመለሳሉ። ይኽ ስርዓት ከኅዳር ፲፪ ጋር ይመሳሰላል። ይኽ ጸሎት የሚጠቅመው፤ የአየር አጋንንትን (ኃጢአት የሚያሰሩ፣ ርኩስ ትንፋሻቸውን በመተንፈስ ደዌ የሚያሲዙ፣ መሬትን በድርቅ የሚጎዱ፣…)  በምሕላው እና በማዕጠንቱ እነዚኽን አጋንንት አቃጥሎ ያጠፋቸዋል። በሀገራችንም ወርኃ ክረምት አልፎ ኅዳር ሚካኤል እስከሚታጠን ድረስ ሩቅ መንገድ አትኺዱ የሚባለው ለዚኽ ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስ የተሰጠው ቃልኪዳንም ስምኽን የጠራ በዓልኽን ያከበረ ዝክርኽን የዘከረ በጥምቀተ ክርስትና ልጁን በስምኽ የሰየሙትን ከምድራዊ አደጋ በሰማይም ከኵነኔ አድናቸዋለኹ ብሎታል። በተጨማሪም የምድራቸውን አዝመራ እባርክላቸዋለኹ፤ ቤታቸውን ቤተሰቦቻቸውን ዕድሜ፣ ጤና፣ ፍቅር እሰጣቸዋለኹ ብሎታል።
ещё
19 1 1 15 ноя, 20:28
Больше постов

Продолжить анализ этого канала

  • История роста подписчиков
  • Просмотры и охваты публикаций
  • Кто упоминает канал и кого упоминает он
  • Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней