Аналитика Telegram-канала
Подписчики
12 154
Охват за 24 ч
977
ER за 24 ч
8,04%
Публикаций
12 705
Динамика подписчиков
7 дней
30 дней
6 месяцев
Больше
15 ноя18 ноя21 ноя
Показаны последние 7 дней
Больше истории →
Охваты публикаций
08.1108.1111.1113.1116.1119.11
507
Средний охват
1,2K
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале
Больше статистики →
Упоминания
244
Упоминаний
124
Из них репостов
72
Каналов
0
Упоминаний за 90 дней
0
Из них репостов
0
Каналов за 90 дней
Последние посты
3 из 12 705 2 из 12 705
ሸክላዉ በእግዛብሔር እጅ የተሰኘ በቄስ ይተፋ ጎበና ህይወት ታሪክ እና አገልግሎት ዙሪያ የተጻፈ መጽሐፍ ሊመረቅ ነዉ
ህዳር 9ቀን2019 ዓ .ም ሸክላዉ በእግዛብሔር እጅ የተሰኘ በቄስ ይተፋ ጎበና ህይወት ታሪክ እና አገልግሎት ዙሪያ በቄስ እሰይ ሞሬሳ የተጻፈ መጽሐፍ ምርቃት አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰቷል።
መጽሐፉን የጻፋት ቄስ እሰይ ሞሬሳ ዋና አላማዉ ሰዎች ለእግዚአብሔር ክብር እንዲሰጡ እና ለዚህ ትዉልድ የግጭት አፈታት ዘዴዎች ለማስተማር እንደሆነ ገልጸዉ
የሸክላዉ ባለቤት እግዚብሔር ስራ ላይ ያተኮረዉ ይህ መጽሐፍ 7ምዕራፎች በ267 ገጾች የተዋቀረ እንደሆነ ገልጸዋል።
በመግለጫዉ ላይም የተገኙት የኢትዮጲያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ፕሬዝዳንት ቄስ ደረጄ ጀምበሩ ይህ መጽሐፍ የቤተክርስቲያን ታሪክም ጭምር መሆኑን ገልጸዉ ለትዉልዱ ብሎም ለሀገር ትልቅ ጥቅም እንዳለዉ አክለዋል።
በኢትዮጲያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነኢየሱስ 22 አብይ ጉባኤ በሚካሔድበት ወቅት ህዳር 17 ቀን2019 ዓ.ም 8:00 ሰዓት ላይ በመካነኢየሱስ ሴሚነሪም እንደሚመረቅም ተነግሯል።
በአማረኛ የተጻፈዉ ይህ መጽሐፍ ወደ ኦሮምኛም የተተረጎመ ሲሆን በቀጣይም በተለያዩ ቋንቋዎች እንደሚተረጎም ተቁሟል።
ለኢቫንጀሊካል ዜና ሩት ዋቅጅራ
ещё
260
0
2 19 ноя, 14:12
የመጋቢ ዮሐንስ ሞገስ “የሕይወት ሚዛን”መጽሐፍ ተመረቀ
ሕዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ም በመጋቢ ዮሐንስ ሞገስ የተጻፈው “የሕይወት ሚዛን”የተሰኘው መጽሐፍ በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን በቦሌ አጥቢያ ጉባኤ ተመረቀ።
በመጽሐፉ ምረቃ ላይ የቀድሞው የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዝዳንት እና የሰርክል ተቋም መሥራች የሆኑት ፓስተር ጽድቁ አብዶ፣ የተለያዩ የቤተክርስቲያን መሪዎች፣ የጸሐፊው ወዳጆችና የመጋቢ ዮሐንስ ሞገስ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
በዝግጅቱ ላይ ፓስተር ጽድቁ አብዶ የእግዚአብሔርን ቃል መሠረት በማድረግ “የሕይወት ሚዛን”የተሰኘውን መጽሐፍ አስመልክተው መልእክት አስተላልፈዋል።
የመጽሐፉ ደራሲ መጋቢ ዮሐንስ ሞገስ በበኩላቸው፣ መጽሐፉ ስለ ግል ሕይወት፣ ስለ ቤተሰብ፣ ስለ ቤተክርስቲያንና ስለ አገር የሚያስፈልገውን የሕይወት ሚዛን በመጠበቅ እንዴት መኖር እንደሚቻል የሚያስተምር መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም ለመጽሐፉ ዝግጅት 20 አመታት የፈጀባቸውን ጊዜና የጽሑፍ ሂደቱን አብራርተዋል።
በሌላ በኩል ፓስተር ቢንያም መጽሐፉን ደሳው የክርስቲያን መሪነት በውስጥ ከሚገኝ የሕይወት መሠረት የሚመነጭ መሆኑን አስመልክተው፣ በሁሉም የሕይወት ዘርፎች ሚዛኑን ጠብቆ መኖር እንደሚገባው አስተምረዋል።
“የሕይወት ሚዛን”መጽሐፍ ምረቃ በእምነት፣ በግል ሕይወት፣ በቤተሰብና በአገልግሎት ዘርፎች ሚዛናዊ ኑሮን ለመገንባት መሆኑ ተገልጾዋል።
ещё
398
0
3 16 ноя, 08:32
ለወንጌላውያን የሚዲያ ባለሙያዎች የተዘጋጀ ስልጠና ተካሄደ
የወንጌላውያን ሚዲያ ባለሙያዎች ማኅበር ከኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ስልጠና በአዲስ አበባ ማዶ ሆቴል ተካሂዷል።
ስልጠናው የሚዲያ ባለሙያዎች በሰላም ግንባታ ላይ ያላቸው ሚና፣ ክርስቲያናዊ የሚዲያ አጠቃቀም፣ ተግባቦት እንዲሁም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው።
በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ምክትል ፕሬዚዳንት በሆኑት ፓስተር ሰንበቶ ባሼ ጸሎት የተከፈተ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ፕሬዚዳንት ፓስተር ደረጀ ታፈሰ በደረጉት ንግግር የሚዲያ ባለሙያዎች ስለ ወንጌል ሲሉ ለሚከፍሉት መስዋዕትነት ዋጋቸውን የማይረሳ ታማኝ ጌታ እንዳለ በመግለጽ የማበረታቻ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ ደራሲ ጋዜጠኛ፣ ተመራማሪ እና የቀድሞ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው በለጠ በሰጡት ስልጠና ባለሙያዎች በሚዲያ አጠቃቀማቸው ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄና ትኩረት ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት የኅብረቱ የሰላምና አድቮኬሲ ዳይሬክተር አቶ ደቻሳ ሂርጳሳ በበኩላቸው የሚዲያ ባለሙያዎች ለሀገር ሰላም መስፈን ትልቅ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል።
በመጨረሻም የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ወንድም ዘሪሁን ግርማ ስልጠናው የወንጌል አገልግሎትን ለማስፋትና ሰላምን ለማስፈን ሰፊ ሚና እንዳለው ገልጸው፣ ለስልጠናው መሳካት አስተዋጽኦ ላደረገው የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ምስጋና አቅርበዋል።
በቤተልሔም ደረጀ
የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል
የወንጌል አማኞች ድምፅ
t.me/evangelicalmedia
📞251 998870672 ላይ ያገኙናል
ещё
381
3
13 ноя, 16:32
Продолжить анализ этого канала
- История роста подписчиков
- Просмотры и охваты публикаций
- Кто упоминает канал и кого упоминает он
- Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней