Аналитика Telegram-канала
Подписчики
7 290
Охват за 24 ч
759
ER за 24 ч
10,41%
Публикаций
1 091
Динамика подписчиков
7 дней
30 дней
6 месяцев
Больше
14 ноя17 ноя20 ноя
Показаны последние 7 дней
Больше истории →
Охваты публикаций
17.1117.1118.1118.1119.1119.11
114
Средний охват
267
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале
Больше статистики →
Упоминания
18
Упоминаний
9
Из них репостов
12
Каналов
2
Упоминаний за 90 дней
1
Из них репостов
2
Каналов за 90 дней
Последние посты
3 из 1 091 2 из 1 091ሴቶች ብር ይወዳሉ ይባላል...እኔ ግን አይመስለኝም!
(አሌክስ አብርሃም)
በመረጃ ላስደግፈው....
ሰፈራችን ታዋቂ ፎቶ ቤት ነበር። የጋሽ ሰለሞን ፎቶ ቤት። መስተዋቱ ላይ በጣም የምታምር ልጅ (ትርሲት ነበር ስሟ )ቬሎ ለብሳ በባዶ እግሯ ሳር ላይ ስትሮጥ የተነሳችው ፎቶ በትልቁ ተለጥፏል። መልኳ ብቻ አይደለም፣ አሯሯጧ ራሱ ውበቱና ልብ መስቀሉ ሁልጊዜ አገራችንን ወክላ ኦሎምፒክ የአስር ሺ ፍፃሜ ላይ ያለች ሯጭ እስክትመስለን ትፋሽ ያሳጥራል። ያጓጓናል። ታዲያ የከተማው ሴት በሙሉ ይችን ልጅ እያሰበ ፎቶ የሚነሳው እዛ ቤት ነው። ወንዶችም ፎቶ ቤቱን ትርሲት ፎቶ ቤት እስከማለት ደርሰናል። ቦታ ስንጠየቅ ሁሉ "በትርሲት ፎቶ ቤት አድርገህ..." እያልን ነው የምንናገረው። ትርሲት ማናት ይላል ጠያቂው...ዝርዝሩ ይነገራዋል። ስናልፍ ስናገድም ያንን ፎቶ አየት እናደርገዋለን። ደግሞ ፎቶ ለመነሳት በቀጠሮ ነው ....ጥሩ ገቢ ነበረው ቤቱ።
አንድ ቀን የጋሽ ሰለሞን ሚስት ከመሬት ተነስታ "ያንን ታዋቂ ፎቶ ገንጥልና የኔን የሰርግ ፎቶ ለጥፍ" አለችው። እንደማንኛውም ጥሩ ባል ምክሯን ሰምቶ እንዳለችው አደረገ። ሰፈር ውስጥ ወሬው ሁሉ "ተነሳ" የሚል ሆነ። ተነሳኮ ተነሳ፣ ተነሳ፣ ተነሳ፣ ተነሳ፣ ከዚያ ታች ሰፈር ተነሳ ተነሳ ተነሳ ተነሳ ላይ ሰፈር ተነሳ ተነሳ....የነዳጅ ድጎማ ቢነሳ ራሱ እንደዛ አይወራም! ተነስቶ በሌላ ተተካ ያለ እንኳን አልነበረም። መጀመሪያ ወንዶቹ ተቀየምነው። አቅጣጫ ስንጠየቅ "በወፍጮ ቤቱ ጋ አድርገህ ..." ማለት ጀመርን። ፎቶ ቤቱን ላለመጥቀስ!
ቀስ በቀስ የፎቶ ቤቱ ገበያ ተቀዛቀዘ። ለጡረታ ጉርድ ፎቶ የሚነሱ ሽማግሌወች ቀሩ። የጋሽ ሰሌ ሚስት በሽማግሌ ሁሉ የትርሲት ፎቶ እንዲመለስ ወይም ከጎን እንዲለጠፍ ብትጠየቅ ወይ ፍንክች። ኧረ ያ ሁሉ ገቢ ቀረ ብትባል "ገቢው ጥንቅር ይበል" አለች። በመጨረሻ ፎቶ ቤቱ ከሳስሮ ጥንቅር አለና የመኪና ዕቃ መቀያየሪያ ከፈቱበት። "ጎሹ ስፔር ፓርት" ከነስሙ! በኋላ ቆይቶ ወሬው ከየት እንደመጣ እንጃ የዚህ ሁሉ መዘዝ መነሻ አንድ ቀን ጋሽ ሰለሞን ሚስቱ ጋር ምኝታ ቤታቸው ሆነው "ሲያወሩ" በስህተት "ትርሲትየ" ብሎ ነው አሉ። ጦሱ ለኛም ተረፈ፤ ያችን የመሰለች ልጅ ተነስታ ጎማ፣ ባሌስትራ፣ ፒቺኒ፣ ኪችኒ...ኤዲያ! ብር ቢወዱ ይሻለን ነበር።
ещё
64
0
19 ноя, 11:15
ሁሉም የአሜሪካ ወታደሮች በጦር ሜዳም ይሁን አስጊ የግዳጅ ሁኔታ ባለበት የጥይት መከላከያ ጃኬት መልበስ ግዴታቸው ነው። ወታደራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ውሾቻቸውም እንደዛው! ጃኬቱ ጥይት እና የፈንጅ ፍንጣሪ ይከላከልላቸዋል። ምንም ጋር አይያያዝም!
ኦ የረሳሁት...የውሾቹ ጃኬት ቢጠፉ ፣ቢቆስሉ ወይም ቢሞቱ በፍጥነት እንዲገኙና በክብር እንዲነሱ ጂፒኤስ እንዲሁም ዘለበት ነገር አለው፣ ዘለበቱ ሄሊኮፕተር ሲላክላቸው በገመድ ተያይዞ የሚነሱበት ነው።
ещё
267
0
2 19 ноя, 10:58
"ደህና ነህ?" እና "ደህና ነሽ?"
(አሌክስ አብርሃም)
አንዳንድ አባባሎች ተመሳሳይ ቃል ቢጠቀሙም ስሜታቸው የየቅል ነው። ለምሳሌ የ18 ዓመት ሴት ልጅ እና የ18 ዓመት ወንድ ልጅ ያላቸው ወላጆች ጧት ቁርስ ሲቀርብ ወንዱ ድንገት እየሮጠ ሄዶ አስመለሰው እንበል፤ ወላጆች በጭንቀት "ደህና ነህ?" ይላሉ። በተመሳሳይ ሴት ልጃቸው ቢያስመልሳትስ ያው "ደህና ነሽ?" ነው የሚሉት። ግን በተመሳሳይ ቃል ስሜቱ ሌላና ሌላ ነው። ለወንዱ ታይፎይድ፣ የምግብ መበከል ምናምን የሚል ጭንቀት፣ ለሴቷ ...(ታውቁታላችሁ) ሴት ልጅ በአጠያየቃቸው ብትበሳጭ "ደህና ነሽ ወይ ነው ያልነው ከወንዱ ልጅ የተለየ ምን አልን?" ትባላለች። የተባለው ግን በደንብ ይገባታል። ቃላት ስሜትና እውነትን የመግለፅ ብቻ አይደለም የመሸፈን አቅማቸው ለጉድ ነው። ይታያችሁ...ተፈጥሮ ማስታወክን እንኳን የተለያዮ ሁለት ነገሮች ምልክት አድረገዋለች። ከአንዱ ኋላ ህይወት፣ ከሌላኛው ኋላ ሞት!
የዘንድሮ የአገራችን የሐይማኖት፣ ፖለቲካና ማህበራዊ ጉዳይ ንግግሮች ታዝባችኋል? ተመሳሳይ ባህሪ አላቸው። "ተከባብሮና ተቻችሎ መኖር" የሚለው ቃል ለምሳሌ "ደህና ነህ?" እና "ደህና ነሽ?" አይነት ነው። "ቻሉኝ" ባይና "ቻል" የሚባለው ከኋላ የተሸከሙት የደህንነት ስጋት፣ ፍላጎት፣ ዓላማ የየቅል፣ ውጤቱም እንደዛው ነው። «ተከባብሮና ተቻችሎ መኖር» አይነት ውብ ቃላት በሁሉም ወገን ቢዘወተሩም፣ ተናጋሪዎቹ ከኋላቸው የተሸከሙትን የደህንነት ስጋት ከተናጋሪው ባህሪ፣ አነጋገርና ልምድ እና ከተነገረበት ጊዜና ሁኔታ ወዘተ አንፃር ትርጉሙ ይገባቸዋል። ውጤቱም ለአንዱ ሞት መጨቆን፣ ለሌላው ድሎት ህይወት መሆኑን ያውቁታል። አንዱ ወገን ከደበረው እውነታውን የሚነካ ጥልቅ መፍትሄ አይፈለግም፤ ጨዋታው የቃል ይሆናል "ምን አልን ተቻችሎና ተከባብሮ መኖር ነው ያልነው፣ አሁን ይሄ ያስከፋል?" ትባላለህ። የሆነ ሁኖ ግን "ደህና ናችሁ?"
ещё
57
1
1 18 ноя, 14:59
Продолжить анализ этого канала
- История роста подписчиков
- Просмотры и охваты публикаций
- Кто упоминает канал и кого упоминает он
- Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней