Аналитика Telegram-канала
Подписчики
35 030
Охват за 24 ч
3,5K
ER за 24 ч
10,09%
Публикаций
11 260

Динамика подписчиков

7 дней 30 дней 6 месяцев Больше
14 ноя17 ноя20 ноя
Показаны последние 7 дней Больше истории →

Охваты публикаций

17.1118.1119.1119.1120.1120.11
361
Средний охват
649
Лучший результат
Показаны 6 публикаций — последние в канале Больше статистики →

Упоминания

142
Упоминаний
4
Из них репостов
16
Каналов
Нет примеров за последние 90 дней
Все упоминания

Последние посты

3 из 11 260 2 из 11 260
Фото
የትራምፕ አውሮፕላን ከቻይና ሲመለስ በሳይበር ስለላ ስጋት ምክንያት ስልኮች በልዩ መያዣ እንዲያዙ መደረጋቸው ተገለፀ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይና የመመለሻ ጉዞ ላይ የነበሩ ጋዜጠኞች በቻይና የተጠቀሙባቸውን ስልኮች ምልክት የሚያቋርጡ ልዩ መያዣዎች ውስጥ እንዲያስቀምጡ ተጠይቀዋል። የኋይት ሀውስ እርምጃውን የወሰደው ፕሬዚዳንቱ በቻይና ቆይታቸው ወቅት ሊከሰት የሚችል የሳይበር ስለላ ስጋትን ለመቀነስ መሆኑ ተገልጿል። የሲቢኤስ ኒውስ ዘጋቢ ጄኒፈር ጃኮብስ እንደገለጸችው፣ አውሮፕላኑ ሼንዘንን ለቅቆ ሲመለስ አንድ የኋይት ሀውስ ሰራተኛ የሰራተኞችን ጊዜያዊ የመጠባበቂያ ስልኮች ሰብስቦ መረጃቸው እንዲጠፋ ወይም እንዲሰረዙ አድርጓል። ጋዜጠኞቹም በቻይና የተጠቀሙባቸው ስልኮች ከአሜሪካ እስኪደርሱ ድረስ እንደሚቆዩ እና ከአውሮፕላኑ ካረፈ በኋላ እንደሚመለሱላቸው ተነግሯቸዋል። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስለ እርምጃው ሲጠየቁ፣ “ጥንቃቄ ማድረግ ፈልገን ነበር፤ ሰዎች መጠቀም የሌለባቸውን ስልኮች ይዘው እንዳይኖሩ በጣም ጥንቃቄ አድርገናል” ሲሉ ለኤንቢሲ ኒውስ ተናግረዋል። በተጨማሪም፣ ብዙ ጋዜጠኞች ቻይና ከመድረሳቸው በፊት መደበኛ ስልኮቻቸውን፣ ላፕቶፖቻቸውን እና ስማርት ሰዓቶቻቸውን የመረጃ ምልክትን በሚከላከሉ የፋራዴይ መያዣዎች ውስጥ በኤር ፎርስ ዋን ላይ አስቀምጠው ነበር። በቻይና የግል ስልኮቻቸውን ይዘው የገቡ ጋዜጠኞች ግን እስከ አሜሪካ መመለሻ ሰአታቸው ድረስ የሞባይል አገልግሎት ሳይኖራቸው ቆይተዋል። ትራምፕን የተሸከመው አውሮፕላን ሐሙስ ምሽት በጆይንት ቤዝ አንድሪውስ ካረፈ በኋላ፣ በፋራዴይ መያዣዎች ውስጥ የተቀመጡት ስልኮች ለጋዜጠኞቹ ተመልሰዋል። @Addis_Mereja
ещё
72 0 1 20 ноя, 13:32
Фото
“ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት ብትገጥም ከባድ ዋጋ ትከፍላለች‼️ የዓለም አቀፍ የፖለቲካ ተንታኞች ማስጠንቀቂያ በቀጣናው የጂኦፖለቲካ ሁኔታ ላይ የሚነሱ ትንታኔዎች፣ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ወደ ወታደራዊ ግጭት መግባቷ ከባድ የሆነ የፖለቲካ፣ የደህንነትና የኢኮኖሚ ዋጋ ሊያስከፍላት እንደሚችል ያመለክታሉ። እነ ቲቦር ናጊን ጨምሮ በዓለም አቀፍ ፖለቲካና ዲፕሎማሲ ላይ የሚያተኩሩ ተንታኞች፣ በውስጣዊ ጦርነት ክፉኛ የተጎዳው የሱዳን መንግሥታዊና ወታደራዊ አቅም ተጨማሪ ግጭትን ለመሸከም ያለውን አቅም በጥንቃቄ መመዘን እንዳለበት ያሳስባሉ። ሱዳን አሁን ካለችበት ውስጣዊ ቀውስ ሳትወጣ ከኢትዮጵያ ጋር ወደ ሌላ የጦርነት አዙሪት መግባቷ፣ የቀረውን አቅሟን ከማሟጠጥ ባለፈ የሀገሪቱን ቀውስ ይበልጥ ሊያባብስ ይችላል። ኢትዮጵያ ግን የራሷን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት የመጠበቅ ሙሉ መብት አላት። የሀገር ጥቅምን በጥበብ፣ በዲፕሎማሲና በተዘጋጀ የመከላከያ አቅም ማስጠበቅ የሚጠይቅበት ወቅት ነው። የቀጣናው ሰላም በግጭት ሳይሆን በጋራ መከባበርና በዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ መጠበቅ አለበት። ሆኖም ኢትዮጵያ ለሰላም የምታሳየው ቁርጠኝነት የራሷን ብሔራዊ ጥቅም የመጠበቅ አቅሟን አያሳንስም። @Addis_Mereja
ещё
452 0 3 20 ноя, 11:01
«በባድመ እና አካባቢዋ የድሮን እና ከባድ መሳሪያ ድምጽ በተደጋጋሚ እየተሰማ ነው» ነዋሪዎች ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በሚዋሰኑባት የድንበር ከተማ ባድመ እና አካባቢዋ ከትናንት ረቡዕ ምሽት ጀምሮ ተደጋጋሚ የድሮን እና ከባድ መሳሪያዎች ድምጽ ይሰማ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪ ለዶቼ ቬለ ተናገሩ።በአካባቢው ያየለው ውጥረት ተባብሶ መቀጠሉን ዓለማቀፉ የግጭት ተከታታይ ተቋም (ACLED) እና አንድ የደህንነት ምንጭ አረጋግጠዋል። በኢትዮጵያ የፌደራል ኃይሎች እና አጋሮች እንዲሁም በኤርትራ መንግስት ወታደሮች እና አጋሮቹ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ወደ ሙሉ ጦርነት የመግባት አፋፍ ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።ትናንት ረቡዕ ምሽት ከባድመ ከተማ በ15 ኪሎሜትሮች ርቀት በምትገኘው ዲያራ በተባለች ቀበሌ አካባቢ የድሮን እና የከባድ መሳሪያ ጥቃት ድምጾች መሰማታቸውን ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። በጥቃቶቹ በሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ነው ነዋሪው የገለጹት ባለፈው ወር ከባድመ ተገፍቶ የወጣው የኤርትራ ጦር ባለፈው ሳምንት ከተማዋን መልሶ መቆጣጠሩን የግጭት ተቆጣጣሪው ተቋም (ACLED) ገልጿል።በባድመ አካባቢ ከፍተኛ ውጊያዎች መካሄዳቸውንና የኢትዮጵያ ኃይሎች ወደ ኤርትራ ግዛት ዘልቀው በመግባት መልሰው መውጣታቸውን ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ በኢትዮጵያ የሚገኙ የውጭ የደህንነት ምንጭ ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል። የኤርትራ ኃይሎች በባድመ አቅራቢያ በሚገኙት ጓል ገምሃሎ እና ሰምበል በተባሉ ሁለት የድንበር መንደሮች ከፍተኛ ተጨማሪ ጦር እና ከባድ ወታደራዊ መሳሪያዎች ማሰማራታቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። በተጨማሪም ከትግራይ፣ ከአፋር እና ከአማራ ክልሎች የተውጣጡ የኢትዮጵያ አማጽያን ጥምረት ለኤርትራ ድጋፍ በመስጠት በባድመ አካባቢ እንደሚገኙ በዓለም ዙሪያ የሚደረጉ ግጭቶችን እየተከታተለ የሚሰንደው አክሌድ (ACLED) የተባለ ተቋም አስታውቋል።በኢትዮጵያ በኩል ምሽጎች መቆፈራቸውን አንድ የሰብአዊ እርዳታ ምንጭ ለዜና ወኪሉ (ኤ ኤፍ ፒ) ገልጸዋል።ሁለቱ አገራት ወታደሮች እጅግ ተለዋዋጭ በሆነ ግንባር ላይ በቅርብ ርቀት መስፈራቸው ቀጥተኛና ዘላቂ ጦርነት የመቀስቀስ አደጋ ከፍ ማድረጉን ተቋሙ አክሌድ አስጠንቅቋል።ስለ ወቅታዊው ሁኔታ ከኤ ኤፍ ፒ ለቀረበላቸው ጥያቄ እስካሁን ከሁለቱም መንግስታት በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም። Via DW @Addis_Mereja
ещё
624 0 5 19 ноя, 16:28
Больше постов

Продолжить анализ этого канала

  • История роста подписчиков
  • Просмотры и охваты публикаций
  • Кто упоминает канал и кого упоминает он
  • Похожие каналы и подбор для рекламы
Открыть аналитику
Демо до 14 дней