Поиск по каналам Каналы в закладках Мои каналы Поиск постов
Инструменты
Мониторинг упоминаний Детальная статистика Анализ аудитории Telegraph-статьи Бот аналитики
Полезная информация
Инструкция Telemetr Документация к API Чат Telemetr
Полезные сервисы
Защита от накрутки Создать своего бота Продать/Купить канал Монетизация

Телеграм канал «ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ»

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ
5.0K
117
586
9
1.6K
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

. #ዝክረ_ቅዱሳን
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ
፩.ግጻዌ
፪.የዘወትር፡ስንክሳር 📖
፫.መዝሙር
፬.ዜና ቤተክርስቲያን ፡ ምክር፡ለወዳጅ እና
የተለያዩ ፡መርሃ-ግብሮች፡ይቀርቡበታል

ማንኛውንም ሀሣብ፡ አስተያየት እንዲሁም ጥቆማ በ @zikrekdusannbot ላይ
ቢያስቀምጡልን ይደርሰና
Подписчики
Всего
4 271
Сегодня
+2
Просмотров на пост
Всего
201
ER
Общий
3.58%
Суточный
5.5%
Динамика публикаций
Telemetr - сервис глубокой аналитики
телеграм-каналов
Получите подробную информацию о каждом канале
Отберите самые эффективные каналы для
рекламных размещений, по приросту подписчиков,
ER, количеству просмотров на пост и другим метрикам
Анализируйте рекламные посты
и креативы
Узнайте какие посты лучше сработали,
а какие хуже, даже если их давно удалили
Оценивайте эффективность тематики и контента
Узнайте, какую тематику лучше не рекламировать
на канале, а какая зайдет на ура
Попробовать бесплатно
Показано 7 из 5002 постов
Смотреть все посты
Пост от 08.06.2025 21:23
147
0
0
​​👼 ቅዳሴ ማለት ምንም ማለት ነው? 🤔 በቅዳሴ ጊዜ 5ቱ ምሥዋዕቶች ምን ምን ናቸው? 🥰 14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት እነማን ይሆኑ? 😇 ካህናት በቅዳሴ ወቅት 2: 3: 4: 5: 7: 12: ወይም 24: ሆነው ከቀደሱ ምሳሌነቱ ምን ምን ይሆን? 🧎‍♂ እኛ ክርስቲያኖች ቅዳሴን ባስቀደስን ቁጥር 4 ነገሮች እናገኛለን ምን ይሆኑ? 👼 አምስቱ የስሜት ሕዋሳት በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ያስቀድሳሉ እንዴት?             ይ🀄️ላ🀄️ሉ ይማሩ                   👇🏾👇🏾👇🏾
Пост от 08.06.2025 17:07
225
1
0
Изображение
Изображение
Изображение
Изображение
Пост от 08.06.2025 17:05
184
0
0
††† እንኳን ለቅዱሳን ነቢያት ዮሐንስና ኤልሳዕ ዓመታዊ የፍልሠት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ††† †††የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ ቅዱስ ዮሐንስ:- ¤በብሥራተ መልዐክ የተጸነሰ ¤በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት ¤በበርሃ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ ¤እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ ¤የጌታችንን መንገድ የጠረገ ¤ጌታውን ያጠመቀና ¤ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው:: ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን:- ነቢይ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ጻድቅ: ገዳማዊ: መጥምቀ መለኮት: ጸያሔ ፍኖት: ቃለ ዐዋዲ . . . ብላ ታከብረዋለች:: ††† ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ ††† ††† ከነቢያተ እሥራኤል አንዱ ኤልሳዕ:- ¤ከእርሻ ሥራ ቅዱስ ኤልያስን የተከተለ ¤መናኔ ጥሪት የተባለ ¤በድንግልና ሕይወት የኖረ ¤የታላቁ ነቢይ ኤልያስ መንፈስ እጥፍ የሆነለት ¤እጅግ ብዙ ተአምራትን ያደረገ ¤አንዴ በሕይወቱ : አንዴ በአጽሙ ሙታንን ያስነሳ ታላቅ ነቢይና አባት ነው:: ቅዱሳት መጻሕፍት ሁለቱን ቅዱሳን በመልካቸውም ይገልጿቸዋል:: ቅዱስ ዮሐንስ ¤ቁመቱ ልከኛ ¤አካሉ በጸጉር የተሸፈነ ¤የራሱ ጸጉር በወገቡ ¤ጽሕሙ እስከ መታጠቃያው የወረደ ¤ግርማው የሚያስፈራ የ31 ዓመት ጎልማሳ ነበር:: ቅዱስ ኤልሳዕ ¤በጣም ረዥም ¤ራሱ ገባ ያለ (ራሰ በራ) ¤ቀጠን ያለ ¤ፊቱ ቅጭም ያለ (የማይስቅ) ሽማግሌ ነበር:: በዚሕች ቀን በ350 ዓ/ም አካባቢ የሁለቱም ቅዱሳን አጽም ከኢየሩሳሌም ወደ ግብፅ ፈልሷል:: በወቅቱ ክፋተኛ የነበረው ንጉሥ ዑልያኖስ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት ሞክሮ ነበር:: ለዚሕ እንዲረዳው በ70 ዓ/ም የፈረሰውን የአይሁድ ቤተ መቅደስ አንጻለሁ ቢልም 3 ጊዜ ፈረሰበት:: ምክንያቱን ቢጠይቅ "የክርስትያኖች አጽም በሥሩ ስላለ እሱን አውጥተህ አቃጥል" አሉት:: ሲቆፈር በመጀመሪያ የሁለቱ ቅዱሳን አጽም በምልክት በመታወቁ በኢየሩሳሌም የነበሩ ክርስቲያኖች በብዙ ብር ገዝተው : ወደ ግብፅ አውርደው ለቅዱስ አትናቴዎስ ሰጥተውታል:: እርሱም በስደት ላይ ነበርና በክብር ደብቋቸዋል:: በኋላም በቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘመን ቤተ ክርስቲያናቸው ታንጾ በዚህ ቀን ተቀድሷል:: በቅዳሴው ሰዓትም ቅዱስ ቴዎፍሎስ ዮሐንስ መጥምቁና ቅዱስ ኤልሳዕ ወርደው ሕዝቡን ሲባርኩ በይፋ ተመልክቷል:: ††† አምላከ ቅዱሳን የወዳጆቹን ፍቅር ያድለን:: †††ሰኔ 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት (ፍልሠቱ) 2.ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ (ፍልሠቱ) 3.አባ ቀውስጦስ ኢትዮዽያዊ †††ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ 2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ 3.ቅዱስ አቤል ጻድቅ 4.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ) 5.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ 6.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ †††"ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ . . . ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችሁአለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን . . . እውነት እላቹሃለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም . . . ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ:: ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ ነው:: የሚሰማ ጀሮ ያለው ይስማ::" ††† (ማቴ. 11:7-15) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† © ዝክረ ቅዱሳን ማኀበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር 🌿 @zkretewahdo 🌿 @zkretewahdo 🌿 @zikrekdusannbot
Пост от 08.06.2025 17:02
119
0
0
✝✝✝ ወንጌል ዘቅዳሴ 🌺📖የማቴዎስ ወንጌል ፲፩ ፥ ፩ - ፲፮ ፩ ኢየሱስም አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ማዘዝ በፈጸመ ጊዜ በከተሞቻቸው ሊያስተምርና ሊሰብክ ከዚያ አለፈ። ፪ ዮሐንስም በወህኒ ሳለ የክርስቶስን ሥራ ሰምቶ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከና፦ ፫ የሚመጣው አንተ ነህን? ወይስ ሌላ እንጠብቅ? አለው። ፬ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ሄዳችሁ ያያችሁትን የሰማችሁትንም ለዮሐንስ አውሩለት፤ ፭ ዕውሮች ያያሉ አንካሶችም ይሄዳሉ፥ ለምጻሞችም ይነጻሉ ደንቆሮችም ይሰማሉ፥ ሙታንም ይነሣሉ ፮ ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤ በእኔም የማይሰናከለው ሁሉ ብፁዕ ነው። ፯ እነዚያም ሲሄዱ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ እንዲህም አለ፦ ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጣችሁ? ፰ ነፋስ የሚወዘውዘውን ሸምበቆን? ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ቀጭን ልብስ የለበሰ ሰውን? እነሆ፥ ቀጭን ልብስ የለበሱ በነገሥታት ቤት አሉ። ፱ ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ፥ ከነቢይም የሚበልጠውን። ፲ እነሆ፥ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነውና። ፲፩ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤ በመንግሥተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል። ፲፪ ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፥ ግፈኞችም ይናጠቋታል። ፲፫ ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ፤ ፲፬ ልትቀበሉትስ ብትወዱ፥ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይህ ነው። ፲፭ የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ። ፲፮ ነገር ግን ይህን ትውልድ በምን እመስለዋለሁ? በገበያ የሚቀመጡትን ልጆች ይመስላሉ፥ እነርሱም ባልንጀሮቻቸውን እየጠሩ። ✥✥✥ቅዳሴ፦ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ) 🌿  @zkretewahdo 🌿  @zkretewahdo 🌿  @zkretewahdo
Пост от 08.06.2025 17:02
163
0
0
❀✞ አስተርእዮተ ሥጋሆሙ ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ወለኤልሳዕ ነቢይ ወበዓለ ሰዊት አው ዘአዊት ወቄርሎስ ወእኬልጥስ ወቀውስጦስ። ✞❀ የሰኔ ፪ #ግጻዌ 🌺❤🌺❤🌺❤🌺❤🌺❤🌺 ✝ ዘነግህ ምስባክ ‹‹ወለነዳያኒሃኒ አጸግቦሙ እክለ። ወለካህናቲሃኒ አለብሶሙ ሕይወተ። ወጻድቃኒሃኒ ትፍሥሕተ ይትፌሥሑ።›› ‹‹አሮጊቶችዋን እጅግ እባርካለሁ፥ ድሆችዋንም እንጀራ አጠግባለሁ። ካህናቶችዋንም ደኅንነትን አለብሳቸዋለሁ፥ ቅዱሳኖችዋም እጅግ ደስ ይላቸዋል።›› 🌺📖መዝሙር ፻፴፩ ፥ ፲፭ ✝✝✝ ወንጌል ዘነግህ 🌺📖የዮሐንስ ወንጌል ፰ ፥ ፲፩ - ፲፱ ፲፩ እርስዋም፦ ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ አለች። ኢየሱስም፦ እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ አላት። ፲፪ ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው። ፲፫ ፈሪሳውያንም፦ አንተ ስለ ራስህ ትመሰክራለህ፤ ምስክርነትህ እውነት አይደለም አሉት። ፲፬ ኢየሱስ መለሰ አላቸውም፦ እኔ ስለ ራሴ ምንም እንኳ ብመሰክር ከወዴት እንደመጣሁ ወዴትም እንድሄድ አውቃለሁና ምስክርነቴ እውነት ነው፤ እናንተ ግን ከወዴት እንደ መጣሁ ወዴትም እንድሄድ አታውቁም። ፲፭ እናንተ ሥጋዊ ፍርድን ትፈርዳላችሁ፤ እኔ በአንድ ሰው ስንኳ አልፈርድም። ፲፮ የላከኝ አብ ከእኔ ጋር ነው እንጂ ብቻዬን አይደለሁምና እኔ ብፈርድ ፍርዴ እውነት ነው። ፲፯ የሁለት ሰዎችም ምስክርነት እውነት እንደ ሆነ በሕጋችሁ ተጽፎአል። ፲፰ ስለ ራሴ የምመሰክር እኔ ነኝ፥ የላከኝም አብ ስለ እኔ ይመሰክራል። ፲፱ እንግዲህ፦ አባትህ ወዴት ነው? አሉት። ኢየሱስ መልሶ፦ እኔንም ወይም አባቴንም አታውቁም፤ እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር አላቸው። ✝✝✝ የእለቱ ቅዳሴ ምንባባት 🌺📖፩ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ፲፬ ፥ ፳፱ - ፍጻሜው ፳፱ ነቢያትም ሁለት ወይም ሦስት ሆነው ይናገሩ ሌሎችም ይለዩአቸው፤ ፴ በዚያ ለሚቀመጥ ለሌላ ግን አንድ ነገር ቢገለጥለት ፊተኛው ዝም ይበል። ፴፩ ሁሉም እንዲማሩ ሁሉም እንዲመከሩ ሁላችሁ በእያንዳንዳችሁ ትንቢት ልትናገሩ ትችላላችሁ። ፴፪ የነቢያትም መናፍስት ለነቢያት ይገዛሉ፤ ፴፫ እግዚአብሔርስ የሰላም አምላክ ነው እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና፤ በቅዱሳንም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዲህ ነው። ፴፬ ሴቶች በማኅበር ዝም ይበሉ፤ ሕግ ደግሞ እንደሚል እንዲገዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውምና። ፴፭ ለሴት በማኅበር መካከል መናገር ነውር ነውና፥ ምንም ሊማሩ ቢወዱ በቤታቸው ባሎቻቸውን ይጠይቁ። ፴፮ ምን ነው? የእግዚአብሔር ቃል የወጣ ከእናንተ ነውን? ወይስ ወደ እናንተ ብቻ ደርሶአልን? ፴፯ ማንም ነቢይ ወይም መንፈሳዊ የሆነ ቢመስለው ይህች የጻፍሁላችሁ የጌታ ትእዛዝ እንደ ሆነች ይወቅ፤ ፴፰ ማንም የማያውቅ ቢኖር ግን አይወቅ። ፴፱ ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ትንቢት ለመናገር በብርቱ ፈልጉ፥ በልሳኖች ከመናገርም አትከልክሉ፤ ፵ ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን። 🌺📖የያዕቆብ መልእክት ፭ ፥ ፲፪ - ፲፯ ፲፪ ከሁሉም በፊት፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ በሰማይ ቢሆን በምድርም ቢሆን በሌላ መሐላም ቢሆን በምንም አትማሉ፤ ነገር ግን ከፍርድ በታች እንዳትወድቁ ነገራችሁ አዎን ቢሆን አዎን ይሁን፥ አይደለምም ቢሆን አይደለም ይሁን። ፲፫ ከእናንተ መከራን የሚቀበል ማንም ቢኖር እርሱ ይጸልይ፤ ደስ የሚለውም ማንም ቢኖር እርሱ ይዘምር። ፲፬ ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት። ፲፭ የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታም ያስነሣዋል፤ ኃጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል። ፲፮ እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። ፲፯ ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤ ሁለተኛም ጸለየ፥ 🌺📖የሐዋርያት ስራ ፲፫ ፥ ፳፬ ፥ ፴፪ ፳፬ ከመምጣቱ በፊት ዮሐንስ አስቀድሞ ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የንስሐን ጥምቀት ሰብኮ ነበር። ፳፭ ዮሐንስም ሩጫውን ሲፈጽም ሳለ፦ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ታስባላችሁ? እኔስ እርሱን አይደለሁም፤ ነገር ግን እነሆ፥ የእግሩን ጫማ እፈታ ዘንድ ከማይገባኝ ከእኔ በኋላ ይመጣል ይል ነበር። ፳፮ እናንተ ወንድሞቻችን፥ የአብርሃም ዘር ልጆች ከእናንተ መካከልም እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሆይ፥ ለእናንተ የዚህ የመዳን ቃል ተላከ። ፳፯ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎችና አለቆቻቸው እርሱንና በየሰንበቱ የሚነበቡትን የነቢያትን ድምፆች ስላላወቁ በፍርዳቸው ፈጽመዋልና፤ ፳፰ ለሞትም የሚያደርስ ምክንያት አንድ ስንኳ ባያገኙበት፥ ይገድለው ዘንድ ጲላጦስን ለመኑት፤ ፳፱ ስለ እርሱም የተጻፈውን ሁሉ በፈጸሙ ጊዜ ከእንጨት አውርደው በመቃብር አኖሩት። ፴ እግዚአብሔር ግን ከሙታን አስነሣው፤ ፴፩ በሕዝብም ዘንድ ምስክሮቹ ለሆኑት ከእርሱ ጋር ከገሊላ ወደ ኢየሩሳሌም ለወጡት ብዙ ቀን ታያቸው። ፴፪ እኛም ለአባቶች የተሰጠውን ተስፋ የምስራቹን ለእናንተ እንሰብካለን፤ ✝ ምስባክ ዘቅዳሴ ‹‹ናሁ ሠናይ ወናሁ አዳም። ሶበ ይሄልዉ አኀው ኀቡረ። ከመ ዕፍረት ዘይውኀዝ እምርእሱ እስከ ጽሕሙ።›› ‹‹ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው። ከራስ እስከ ጢም እንደሚፈስስ፥ እስከ አሮን ጢም፥ በልብሱ መደረቢያ እንደሚወርድ ሽቱ ነው።›› 🌺📖መዝሙር ፻፴፪ ፥ ፩  
Пост от 08.06.2025 08:07
222
0
0
Видео/гифка
Пост от 08.06.2025 08:07
204
0
0
Видео/гифка
Смотреть все посты