Телеграм канал 'ጥዑም ሚድያ'

ጥዑም ሚድያ


2'249 подписчиков
0 просмотров на пост

📖እንኳን በደህና መጡ📖

➥ እዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ይዘት ያላቸው መዝሙሮች ፣ ግጥሞች ፣ አስተማሪ ሀይማኖታዊ ታሪኮች ይዳሰሳሉ።

ለሀሳብ አስተያየት @ermias_ks ላይ ተቁሙኝ!

2015 ዓ.ም

Детальная рекламная статистика будет доступна после прохождения простой процедуры регистрации


Что это дает?
  • Детальная аналитика 4'226'240 каналов
  • Доступ к 1'487'385'920 рекламных постов
  • Поиск по 3'508'444'763 постам
  • Отдача с каждой купленной рекламы
  • Графики динамики изменения показателей канала
  • Где и как размещался канал
  • Детальная статистика по подпискам и отпискам
Telemetr.me

Telemetr.me Подписаться

Аналитика телеграм-каналов - обновления инструмента, новости рынка.

Найдено 21 пост

ከክፍል 18 (የመጨረሻው ክፍል) የቀጠለ...

ወደለመዱት መልካምነት መመለስ ለኢክራም አይከብድም።
ዛሬም የኢክራምን መልካም ስብዕና እናፍቃለሁ። የጋብቻ የጥሪ
ካርዷን ስትልክልኝ አልማለሁ! እሷ ራሷ ከዘቀጡበት ፈልጋ
ሰብስባ ያፀዳቻቸዉ ነብሶች ዛሬ እሷን እንደመታደግ
ሲጠቋቆሙባት ሳይ እበሳጫለሁ። ኢክራም ከነክህደቷ ብዙ
ንፁሀንን አፍርታለች። በጨዋዋ ኢክራም እጅ ንፅህናን የተቀበሉ
በሙሉ ኢክራምን ወደነበረችበት ከፍታ የመመለስ ግዴታ
አለባቸዉ።
ብሩኬም መልካም ለመሆን ጊዜዉ አልረፈደበትም። ብሩኬ
ለመበላሸቱ ምክንያት የሆኑትን ነገሮች ለማጤን ሞክሬ ነበር።
ዋናዉ ፊልም ነዉ። ፊልሞቹን በከፊል ወስጄ ተመለከትኳቸዉ።
ስሜት ተኮር ናቸዉ። "የሰዉ ልጅ የተመለከተዉን ነገር
ይተገብራል" ይላል ስነ አእምሮ! የሰዉ ልጅ ባህሪዉን
የሚገነባበት አንዱ መንገድ ሲደረግ ያየዉን በመማር
(imitation) ነዉ። ብሩክ ለመበላሸቱ ይመለከታቸዉ የነበሩት
ፊልሞች ግንባር ቀደም ምክንያት ናቸዉ።
ሁለቱም ሰዎች ናቸዉ ተሳሳቱ! እኛ ስህተት ባይኖርብን ፈጣሪ
እኛን አጥፍቶ ሌሎች የሚሳሳቱ ህዝቦችን ይፈጥር ነበር። ግን
ዋናዉ ነገር ጥፋትን ተረድቶ ለመፅዳት መሞከር ነዉ። ጥፋቱ
ክህደት ሆኖ ወንጀላቸዉን አገዘፈዉ እንጂ ብዙ መልካም ነገር
ይኖራቸዋል።
.
ብርጭቆ መሬት ላይ ወድቆ ሲሰበር ከነበርኩበት የሀሳብ
ሰመመን ነቃሁ! አንዱ ጠረዼዛ ላይ ያሉት ጥንዶች ናቸዉ
የሰበሩት። ካፌዉ ዉስጥ አራቱ ቴብሎች ላይ ጥንዶች
ተቀምጠዋል። ረሂማ እየሳቀች ወደኔ መጣች! ከኪሴ ልከፍል
ብር እያወጣሁ ነበር።
ረሂማ እየሳቀች "ወተቱስ?" አለችኝ።
ወይኔ ለካ ቅድም ልታሞቀዉ ወስዳዉ ነበር እርስት
አድርጌዋለሁ።
"እሺ የታለ?" አልኳት እየሳቅኩ!
"አሙቄዉ እዛ ቴብል ላይ ወተት ታዞ ነበር እና ለሱ የታዘዘ
መስሏቸዉ ወሰዱት! አንተም ሙድህ ስለወረደ አዉቄ ነዉ ዝም
ያልኩህ!" አለችኝ እየሳቀች።
.
ካፌዉ ዉስጥ ያሉትን ጥንዶች ተመለከትኳቸዉ! ይስቃሉ
፣ይጎነታተላሉ! እስከሚጣሉ ይጎነታተሉ አልኩ በልቤ! አዎ
ተዋደዱ፣ከነፉ፣ተጣልተዉ አረፉ! ነዉ ከትዳር ዉጪ ያለ ፍቅቅሮሽ
መዳረሻ። ሲከፋም የወንዱም የሴቷም ክብር በዝሙት ይገፈፍና
ለንፁሀን የተከለከሉ ቆሻሻ መሆንን ነዉ የሚያተርፈዉ።
.
ፊርደዉስ ደወለችልኝ። አነሳሁት!
"አንተ እዛ መቆዘሚያ ካፌህ ነህ አይደል?" አለችኝ።
"አዎ ምነዉ ፊርዱ?" አልኳት
"በዚህ ስሜት ዉስጥ ሆነህ መጠየቁ አግባብ ይሁን አይሁን
አላዉቅም! ግን ፈዊ ፈቃደኛ ከሆንክ ካንተ ጋር ኒካህ ማሰር
እፈልጋለሁ! ገንዘብ ምናምን የሚለዉ አያሳስብህ ነብዩ
ሙሀመድ(ሰዐወ) የመጀመሪያ ሚስታቸዉን ኸዲጃን(ረዐ)
ሲያገቡ እሷ በጣም ሀብታም ነበረች! የእዉነት ሀይማኖተኛ
ከሆንክ ይሄ አይጠፋህም" አለችኝ።
የኔ አንበሳ ይሄን ታሪክ ማወቋ በራሱ አስገርሞኛል። እንዴት
እንዴት ነዉ ያገናኘችዉ? ቆንጆ ፖለቲከኛ ይወጣታል። ደሞ ለሷ
ኒካህ ምን አላት? እድሜ ለአባቷ! ገንዘብ እንደልቧ ነዉ። እኔ
የማስተዳድራት እንጂ የምታስተዳድረኝ ሴት ማግባት
አልፈልግም።
"ፊርዱዬ ከኔ ጋር ወንድምነቱ ይሻለናል እሺ! እኔ ለጋብቻ ብቁ
ነኝ ብዬ አላምንም!" አልኳት። ለጋብቻ ብቁ ሆኜ ቢሆንማ
ኢክራምን እስከአሁን አግብቼ ነበር።
"ፈዉዛን እኔ ምን ያንሰኛል? ዉበት ከፈለግክ ማንም አይጠጋኝም
ታዉቃለህ! ገንዘብ አለኝ እንደፈለግክ አድርገዉ! ከማንም እኔ
እሻልሀለሁ።" አለች እየተነጫነጨች። በራስ መተመመኗ እና
ግልፅነቷ በጣም ደስ ይለኛል።
"ፊርዱ እኔ አንቺ ምንም ይጎድልሻል አላልኩም ግን እኔ ብቁ
አይደለሁም! ለሌላ ጊዜ ብቁ ስሆን ግን ከዉበትሽ እና ከገንዘብሽ
በላይ ሀይማኖትሽ ላይ ያለሽን አቋም ስለምፈልገዉ እሱን
አሻሽይ!" አልኳት እየሳቅኩ።
"እሺ በቃ እንደድሮዉ!" አለችኝ እንዳንኮራረፍ ፈርታ።
"እሺ ፊርዱ ፈታ በይ!" አልኳትና ስልኩን ዘጋሁት።
ረሂማ ሚስተናገድ ሰዉ የለም መሰለኝ አጠገቤ መጥታ "አንተ
ግን ዛሬ ምን ሆነህ ነዉ?" አለች። መልሴን ሳትጠብቅ ወዲያዉ
ስልኬን ከጠረጴዛ ላይ አንስታ ሰዓት አየች። እግረ መንገዷን
ሰሞኑን የፃፍኩትን ግጥም ዋልፔፐር አድርጌዉ ስለነበር
አየችዉ። እየሳቀች ጮክ ብላ አነበበችዉ
"ስምሽ ጎዳደፈ አነሱሽ በክፉ፣
ከንፈር ማሳበጤ ይሄ ነዉ ወይ ትርፉ?
ደግሜ ብስምሽ ይፀዳ ይሆን ወይ የህሊና እድፉ!"
አሽኮረመመችኝ! ረሂማ ወዲያዉ ተስተናጋጅ ስለመጣ ትታኝ
ሄደች። ወዲያዉ ስልኬ ጠራ! ረዊና ነበረች። አነሳሁት።
"ፈዉዛኔ የት ነህ? አዲስ አበባ መጥቻለሁ!" አለችኝ።
ረዊና ንፁህ እህቴ ናት! ሁሉንም ነገር ለሷ መተንፈስ ነበር
የሚቀለኝ።
"ስማ ከትምህርት ቤቱ ጀርባ ያለዉ ልብስ ቤት ነኝ!
አትመጣም?" አለች!
"መጣሁ!" ብያት ከካፌዉ ተነስቼ ወጣሁ። ከመሸሸጊያዬ ወጣሁ!
የወዳጅ ጦር ቅርብ ርቀት ላይ ነዉ። ንፁህ እህትነት! ረዊና!

~ተፈፀመ!!~🙏

በሌላ ተከታታይ ታሪክ እስከምንገናኝ ቸር ቆዩልኝ

JOIN @Ye_Hagere_Wegoch_2
JOIN @Ye_Hagere_Wegoch_2
👍 4
⬜️ነጫጭ ጥቁረቶች⬛️

የመጨረሻዉ ክፍል
#ክፍል አስራ ስምንት
.
ፊርደዉስ የተሰማኝን መሰበር ስለተረዳችዉ ያን ሰሞን ከጎኔ
አትጠፋም ነበር። ትምህርት እየቀረች ሁላ እኔ ትምህርት
የሌሉኝን ሰዓቶች አብራኝ ታሳልፋለች። የኢክራም መንፈስ
እየለቀቀኝ ነዉ መሰል ግጥም ፃፍኩ! ለፊርዱ አነበብኩላት
"ፀሀዩ ጠቋቁሮ ፣ ሰማይ ጠል ለበሰ፣
የክህደትሽ ክፋት ብዕሬን ነቅንቆ ጉድሽን አዳረሰ።
ዱላ አልማዘዝም ከድታኛለች ብዬ፣
እችልበታለሁ በብዕር መቅጣቱን በፍቅር አባብዬ"
.
እኔ ከጀርባዬ ሲሰራ የነበረዉን ድራማ እንዳወቅኩ ብሩኬም ሆነ
ኢክራም እንዲያዉቁ አልፈለግኩም። ትንሽ ጊዜ ብሩኬ እና
ኢክራም ላይ መዝናናት ፈለግኩ። ብሩኬን እንደድሮዉ በስርዓቱ
አገኘዋለሁ! ቤቱ ሳይቀር እየሄድኩ አብሬዉ አሳልፋለሁ።
የማዉቃቸዉን ነገሮች እጠይቀዋለሁ፣በዉሸቱ እዝናናለሁ።
ኢክራምን ፌስቡክ ላይ እንደድሮዉ አወራታለሁ። ልክ ምንም
እንዳልተፈጠረ! በነገራችን ላይ ፊርዱ የኢክራምን የፌስቡክ
ፓስወርድ አሳይታኝ ስቄ አላባራሁም። "ብሩክ" ነበር ፓስወርዷ!
ብሩክ የሚል ስም ይዞ አሁን ሰዉ እንደዚህ አይነት ተግባር
ይፈፅማል? ለነገሩ በስም ከተባለ የነብይ ስም ይዘዉ እንዲህ
ርካሽ ተግባር የሚፈፅሙም አይጠፉም። እምነት አንዴ ከተሸረሸረ
መልሶ ማምጣት አይቻልም። ፈረንጆቹ እምነት እንደ ድንግልና
ነዉ አንድ ጊዜ ከጠፋ መልሶ ማምጣት አይቻልም! የሚሉት
ለዚህ ይመስለኛል።
ጊዜዉ እየገፋ ሲመጣ ህመሙን ዉስጤ ማመቁ ስለሰለቸኝ
ብሩኬን ላናግረዉ ወሰንኩ።
.
ብሩኬ ጋር ደወልኩለት! እነ ሄኖክ ሰፈር እንደሆነ እና ሲመለስ
እንደሚደዉልልኝ ነገረኝ። እነ ሄኖክ ሰፈር ማለት እነ ኢክራም
ሰፈር ማለት ነዉ። ከሷ ጋር እንደሆነ እርግጠኛ ሆንኩ። ሲመለስ
ደወለልኝ። አገኘሁት። ሳየዉ ሳቄን መቆጣጠር አቃተኝ።
እየሳቅኩ "የት ነበርክ?" አልኩት።
በጥርጣሬ አይን እያየኝ "እዚሁ ነበርኩ ባክህ ማደያዉ ጋር!"
ምናምን ብሎ ቀባጠረ።
ዛሬ እዉነት እዉነቷን እንድናወራ ስለፈለግኩ በአይኔ የት
እንደነበረ እንደማዉቅ የሚያሳይ ምልክት ሰጠሁት። የስነ አእምሮ
ተማሪ ነኝ! ሰዉን በንግግሩ ዉስጥ ችግሩን ተረድቶ ማከም ነዉ
የምማረዉ።
ያወቅኩ መሆኑን ስለጠረጠረ እየሳቀ! "ባክህ ከሚስትህ ጋር
ነበርኩ!" አለኝ። የሚስትነት ስሟን ለኔ፣ ተግባሩን ደግሞ ለሱ
ከፋፍሎት መሆን አለበት ከሚስትህ ጋር ያለኝ!
"ሚስትህ ስትል አስታወስከኝ ባይዘዌይ ሰሞኑን የሆነ ሰዉ
አካዉንቷን ሀክ አድርጎት ነበርና ከብዙ ሰዉ ጋር ያደረገቻቸዉ
ምልልሶች በሶፍት ኮፒ ተዘጋጅተዉ ሊላኩልኝ ነዉ!" አልኩት።
ብሩኬ ደነገጠ! "ማነዉ ይሄ ባለጌ የሰዉ አካዉንት ሀክ
የሚያደርገዉ?" አለኝ እየተበሳጨ። በዉስጤ እስቃለሁ።
"አላወቅኩም ግን የሚጠቅምህን ነገር አግኝተንበታል ነዉ ያሉኝ!
እነሱ ከኔ የሚፈልጉት ነገር ስላለ ጊቭ ኤንድ ቴክ መሆኑ ነዉ!"
አልኩት ፊቱን እያነበብኩ።
ከብሩኬ ጋር እያወራን የነበረዉ ዎክ እያደረግን ነበር። ዎክ
እያደረግን እነ ረዊና ቤት አካባቢ ደረስን!
ብሩኬ ወሬ ለማስቀየር ይሁን አላዉቅም "አንተ ግን እምነትን
ልብላት ስልህ እምቢ አልክ አይደል?" አለኝ። የረዊናን እህት
እምነትን ነዉ።
ፈገግ ብዬ "ብሩኬ ቆይ ስንቱን ልተዉልህ?" አልኩት!
ብሩኬ እንደድንጋይ ደርቆ "ማንን ተዉክልኝ?" አለኝ።
እየሳቅኩ "ከእምነት ሌላ ምድር ላይ ያሉትን ሴቶች ሁሉ
ትቼልሀለሁ!" ብዬ አስቀየስኩ።
.
ብሩኬ የኢክራም አካዉንት ሀክ መደረጉ በጣም አንገብግቦታል።
"ፈዊዬ ጓደኛህ አይደለሁ! ቢያንስ የኔን እንዳይልኩልህ አድርግ!"
አለኝ።
"ያንተማ ቢላክልኝም ምንም ሚያስጨንቅህ ነገር የለም። እኔ ነኝ
ማነበዉ! አንተ ከኔ ደብቀህ ከኢክራም ጋር የምታወራዉ ነገር
ስለሌለ አትጨነቅ።" አልኩት።
ከጀርባዬ ጭንቅላቱን ይዞ ቆሞ "ፈዉዛኔ ካነበብከዉ ያጣላናል!"
አለኝ። የእዉነት እኔን ከመረጠ መጀመሪያ እሷን እንቢ አይልም
ነበር! አንቺዉ ታመጪዉ አንቺዉ ታሮጪዉ አሉ!
መጫወቱ ሲበቃኝ ወደ ብሩኬ ዞር ብዬ አይን አይኑን እያየሁ
"ግን ምኗን ወደድከዉ?" አልኩት።
ብሩክ ሁሉንም ማወቄን አረጋገጠ። "በቃ ሁሉንም እነግርሀለሁ!"
አለኝ።
ድራማዉ ከጀርባዬ ላለፉት ስምንት ወራት እየተተወነ እንደነበር
ነገረኝ። ኢክራም ስለምታሳዝነኝ ነዉ ምናምን ብሎ ቀባጠረ!
የእዉነት ቢያዝንላት የኔን ዉሳኔ እንድትተገብር ነበር ሊያበረታታት
የሚገባዉ።
"ብሩኬ እኔ ይቅርታ አድርጌልሀለሁ! ኢክራምን የምትወዳት
ከሆነም ግንኙነታችሁን መቀጠል ትችላላችሁ!" አልኩት።
ብሩኬን ላለፉት አስር አመታት አዉቀዋለሁ! በአንድ ሴት
ምክንያት በቃኸኝ ልለዉ አልችልም። ምንም ዛሬ ቢከዳኝም ብዙ
ከባባድ ጊዜዎቼን አብሬዉ አሳልፌያለሁ። ለኔ መልካም ሰዉ
ነበር። ግን አንድ ፈተና ማለፍ አቃተዉ።
.
በቀጣዩ ቀን ከብሩኬ ጋር ተገናኝተን ስናወራ ስለሷ አዉርቶ
መዘባረቅ ሲጀምር "ቆይ ግን እኔን እንደዛ እወድሀለሁ እያለች
የከዳችኝ ኢክራም አንተን ዞራ እወድሀለሁ ስትልህ ነገ ወደ
ሌላዉ እንደማትዞር በምን እርግጠኛ ሆንክ? ቢያንስ በኔ
አትማርም?" አልኩት።
"ባክህ እኔ አልወዳትም!" አለኝ።
"ታዲያ ለምን እሺ አልካት?"
"እሷ እወድሀለሁ አለችኛ!"
በጣም ተበሳጨሁ! ቢያንስ ኢክራምን ወዷት ሴትነቷ አሳስቶት
ቢከዳኝ እሺ! ግን እንዲሁ ለመንዘላዘል ነዉ ክህደት የሰራብኝ?
ከምር አበሳጨኝ! እምቢ ማለት አለመቻል ትልቁ ዝቅጠት ነዉ።
ጠጣ እሺ! ቃም እሺ! ጓደኛህን ክዳ እሺ! በጣም ያሳፍራል።
ከብሩኬ ጋር እንደድሮዉ ለመሆን ብሞክርም በፍፁም ሊሳካልኝ
አልቻለም። እምነት ከተሸረሸረ ትልቅ አደጋ ነዉ።
.
ኢክራም ያደረገችዉ ነገር ምንም አስቀያሚ ቢሆንም ልቤ ዉስጥ
ቅንጣት ጥላቻ ሊፈጠር አልቻለም። አሁንም በጣም
ታሳዝነኛለች። ምናልባት ፈጣሪዬ ከሱ ቀድቼ ለኢክራም
የተናገርኩትን ወዶልኝ ይሆን? "ያለፈዉንም የሚመጣዉንም
ጥፋትሽን ይቅር ብዬሻለሁ!" ያልኳትን። አይ እንደዉም የወደፊቱን
ይቅር ማለት ከሱ ሌላ ማንም እንደማይችል እያሳየኝ ነዉ
የሚሆነዉ! ግን አሁንም ለኢክራም ያለኝ እዝነት አልቀነሰም።
አንድ ቀን ሁሉንም ነገር ማወቄን ፌስቡክ ላይ ነገርኳት። በጣም
ደነገጠች። እኔ አሁንም የድሮዋን ጨዋዋን ኢክራም ለመሆን
ብትሻ ላግዛት ዝግጁ ነኝ። ግን ኢክራም ክህደቷን መቋቋም
አቃታት መሰለኝ ከፌስቡክ ብሎክ አደረገችኝ። የተበደልኩት እኔ!
ዘራፍ ባዩ ሌላ! ይገርማል። ፈጣሪዬ ግን ማገናኘት ካሻዉ ማንም
አያግደዉምና ብሎክ ባደረገችኝ በነጋታዉ መንገድ ላይ
ተገጣጠምን። ዉስጤ ላይ ምንም ጥላቻ የለም። ልክ
እንደድሮዉ ፈገግ አልኩላት! ፈገግታዬን ስታይ ወደኔ መጣች።
ሰላም ከተባባልን በኋላ ስለትምህርቷ አወራን! እሷ ግን
ከመወዛገቧ የተነሳ ስለያዝኩት ቦርሳ ዘባረቀች። ኢክራምን
ከረጅም ጊዜ በኋላ በአካል አገኘኋት! እንደሚሉት የተጋነነ
የአለባበስ ለዉጥ አላስተዋልኩም! በርግጥ ጅልባቡ ወልቆ
ቀሚሱም ጠቧል። የጠበቅኩት የተጋነነ ስለነበር ነዉ መሰለኝ
ብዙም አልደነገጥኩም!
.
አሁን የሚቆጨኝ እኔ ስበላሽ ከጎኔ ሆና ያረመችኝን ኢክራምን
ዛሬ የክህደት እና የስነ ምግባር ዝቅጠት ዉስጥ ስትዘፈቅ
ልታደጋት አለመቻሌ ነዉ።
ለሰዉ ልጅ ክብር ወሳኙ ነገር ከማንነት መስመር የወጣን
አፈንጋጭነት እንቢ ማለት መቻል ነዉ።
የመጀመሪያዉ ስህተት የኔ ነበር! ከፈጣሪ ትዕዛዝ ዉጪ ሴት
ስተዋወቅ! ህይወቴ ዉስጥ ልጨምራት ከፈጣሪ ተጋፍቼ
ያመጣኋት ኢክራም የነበረኝን ብሩክንም አሳጣችኝ። ጌታዬ ልክ
ነበር! ተሳስቶም አያዉቅም! አይሳሳትምም!
ኢክራም ዛሬም መልካም ለመሆን ቅንጣት እንኳ አልረፈደባትም።
👍 3
ነጫጭ ጥቁረቶች ዛሬ ምሽት ይጠብቁን...

ከ20❤️ በዋላ ይለቀቃል
👍 4
""" "እናቴ"" """

ፀጉርሽን አይቼ የኔን ፀጉር ሳየው
እንደ ወንድ ፀጉር ገባ ገባ ያለው
እሳት እንደነካው የተኮማተረው
----ለካ ለፍቅር ነው
የፊትሽ ላይ ቆዳ የተሸበሸበው
እንደ ወየበ ልብስ እንዲህ የገረጣው
እንደ ቼዙ ሜዳ የተዥጎረጎረው
--ለካ ለፍቅር ነው
በጉብዝናሽ ወራት በወጣትነትሽ
እነዚያ ውብ አይንሽ
ጎላ ጎላ ያሉት
ከለሊት ጨረቃ ደምቀው የሚታዩት
አሁን ደም ለብሰዋል
አንቺ ለእኔ ብለሽ በጪስና አቧራ
ሰውተሻቸዋል
---ይሄም ለፍቅር ነው
አንቺ የፍቅር አምድ
ተምሳሌት የመውደድ
አንቺ የፍቅር ማዕድ
ልክ እንደከዘራ ጀርባሽ የጎበጠው
አሁን ነው የገባኝ እኔ ቀና እንድል ነው
------አንቺ እንዲህ የሆንሺው ለካ
ለፍቅር ነው
መዳፍሽን ሳየው
አሻራ እንኳን የለው
ድህነት በልቶታል
ሸክም አጥፍቶታል
-----እናም ውዷ እናቴ
ዝምብየ ሳስበው
ምን አይነት ፍቅር ነው
ይሄን ሁሉ የሆንሺው
አንዴት በትወጂኝ ነው።

JOIN @Ye_Hagere_Wegoch_2
JOIN @Ye_Hagere_Wegoch_2
👍 1
ከ ክፍል 17 የቀጠለ ...

አመታት ጓደኛዉን የእኔን የትዳር ቅዠት ሲያማግጥ ህሊናዉ እንዴት ዝም
አለዉ? ደግሞ እኮ ቃል በቃል "ኢክሩ እንድታገባ እንጂ ከማንም
ወንድ ጋር እንድትንዘላዘል አይደለም የተዉኳት!" ብዬዋለሁ።
አደራ ብዬዉም ነበር! ጌታዬ ሆይ በከለከልከኝ መንገድ ላይ
ተጉዤ የነገድኩት ንግድ ኪሳራን እንጂ አላተረፈልኝም!
.
ፊርደዉስ ቁርሱን ሰርታ አቀራርባ እንድንበላ ልትጠራኝ ስትመጣ
አልጋዉ ላይ ተዘርሬያለሁ። ከአይኔ እንባ ይጎርፋል።
እንሰቀሰቃለሁ።
"ፈዉዛኔ ምን ሆንክብኝ?" አለች እየተንደረደረች መጥታ አንገቴን
ቀና እያደረገች።
በጣቶቼ ላፕቶፑን ጠቆምኳት። ሄዳ አነበበችዉ። ፊቷ ደም
እንደለበሰ ወደኔ ዞራ "ብሩክ አንተን ከዳህ?" አለችኝ ስለ ብሩክ
ታዉቅ ነበር።
ፊርደዉስ ከኔ በላይ መበሳጨት ጀመረች።
"ለኢክራም እኮ መልአክ ነበርክ ፈዊ! ምላሿ ይሄ ነዉ?" አለችኝ
ንዴቷ ይበልጡኑ እየተቀጣጠለ።
አልጋዉ ላይ ከወገቤ ቀና ብዬ ተስተካክዬ እየተቀመጥኩ "ብዙ
ጊዜ ያለመድሽዉ ዉሻ ነዉ የሚነክስሽ!" አልኳት።
"ፈዊ ኢክሩን ቆንጆ ቅጣት ልትቀጣት ይገባል!" አለች ፊርደዉስ
ግድግዳዉን እየደበደበች
እንደ እብድ ጮክ ብዬ እየሳቅኩ "ኢክራም እኮ ቅጣት
አያስፈልጋትም እኔን ከድታ ብሩኬ ላይ የወደቀች ቀን ራሷን
ቀጥታለች። ንፁህ ልቤን ረግጣ ፊልም ላይ ስትመለከተዉ
የኖረችዉን ዝቅጠት ለመተግበር ስትሞክር እና ከቅዱሳን ተራ
ስትወጣ ያኔ ራሷን ቀጥታለች። እኔ መቅጣት አይጠበቅብኝም።
የሚታዘንላት ለንግስትነት የታጨች ዉብ ከመሆን ማንም
እንዳሻዉ የሚጨልፋት ርካሽ መሆንን ስትመርጥ ያኔ ራሷን
ቀጥታለች።" ንግግሬ ሲያልቅ ሰዉነቴ መንዘፍዘፍ ጀመረ።
እየተንሰቀሰቅኩ አለቀስኩ። በህይወቴ እንዲህ ያለቀስኩባቸዉ
ቀናት ዛሬ እና ኢክሩ ልታገባ ስትል ናቸዉ። ሁለቱም በኢክሩ
ምክንያት! ደካማ ጎኔ ሴት ናት! ከሴት ደግሞ ኢክራም!
ፊርደዉስ ለቅሶዬ ሲበረታ አልጋዉ ላይ ከጎኔ ቁጭ ብላ ማባበል
ጀመረች። በእጆቿ እንባዬን ጠረገችልኝ። ደንዝዣለሁ።
ብደበደብም የሚሰማኝ አይመስለኝም። ፊርደዉስ እጆቿን ወደ
አንገቴ ወሰደቻቸዉ። ከንፈሬ ላይ ተለጠፈች። እኔ አያታለሁ
ላስቆማት አልቻልኩም ደንዝዣለሁ! አይኔ እያየ ስልኳን አዉጥታ
ከንፈሬ ላይ እንደተጣበቀች ሰልፊ ፎቶ አነሳች። ፊርደዉስ
ዉርርዷን ፈፀመችብኝ። አደነቅኳት። ምንም የስነ አእምሮ ምሁር
ብትሆን ሴት ልጅን ተንኮል አትበልጣትም። ዛሬ ካፌ ሳይሆን ቤት
እንድንገናኝ ያደረገችዉ አጋጣሚዉን ለመጠቀም ብላ ነበር።
በንፁህ አእምሮ ብሆን ኖሮ ሁሉም ይገባኝ ነበር። ግን
የኢክራምን ጉድ ለማየት መጓጓቴን ፊርዱ ተጠቀመችበት።
ፊርዱ ባደረገችዉ ነገር ምንም አልተቀየምኳትም። እልህ
ተያይዘን ነበር! እሷ አሸነፈች አለቀ!
አእምሮዬ ሲረጋጋ ፊርዱን በአክብሮት እንድታቆም ጠየቅኳት።
ወዲያዉ አቆመች። አየኋት ቆንጆ ናት! ከኢክራምም የበለጠች
ቆንጆ! ግን በሰዓቱ በፍፁም ስለሴት ማሰብ ስላልፈለግኩ ትቻት
ወደ ሳሎን ሄድኩ። ፊርዱ የሰራችዉ ቁርስ ላይ እልሄን
ተወጣሁበት! ፊርዱም መጥታ አብረን በልተን ተያይዘን ከቤቱ
ወጣን!

ይቀጥል...

JOIN @Ye_Hagere_Wegoch_2
JOIN @Ye_Hagere_Wegoch_2
👍 10
⬜️ነጫጭ ጥቁረቶች⬛️
#ክፍል አስራ ሰባት
.
አይነጋም የለ ምሽቱን መንጋቱን በመናፈቅ ስገላበጥ አሳለፍኩት!
የንጋት የስግደት ጥሪ ድምፅ መሰማት ሲጀምር ወደ መስጂድ
አቀናሁ። የሰፈሩ ፀጥታ ደስ ይላል። ከራሴ ጋር ክርክር ዉስጥ
ገባሁ! አዩቤ መልዕክት መላላኬን እንዳያዉቅ ከቫይበር ላይ
እኔና ኢክሩ ያደረግነዉን ምልልስ አጥፍቼዋለሁ። ስልኩን
ያለአግባብ በመጠቀሜ ሌላ ቀን ሰበብ ፈልጌ ይቅርታ ለመጠየቅ
ወሰንኩ።
የንጋት ስግደት እንደተጠናቀቀ ፊርደዉስ ጋር ደወልኩ። ገና አንዴ
እንደጠራ አነሳችዉ።
"ፈዉዛኔ ለሊቱን እንደ አክሱም ቆመህ አደርክ አይደል?" አለችኝ
እየተፍለቀለቀች
"ፊርዱ ተገናኝተን አካዉንቷን እስክንበረብረዉ ልቤ ተሰቅሏል።"
አልኳት ፉገራዋን ችላ ብዬ!
ቁርስ እንደምትጋብዘኝ እና በዛዉም የኢክራምን ጉድ ለማየት
ከአንድ ሰዓት በኋላ መጥታ እንደምትወስደኝ ነገረችኝ። ፊርዱ
ጠዋት ላይ ማንበብ ስለሚያስደስታት በጊዜ ነበር የምትነሳዉ!
.
ባለችኝ ሰዓት መጥታ ወሰደችኝ። ግን የወሰደችኝ ወደ አንድ
የማላዉቀዉ ቤት ነበር።
ከመኪናዉ ሳልወርድ "የማን ቤት ነዉ?" አልኳት።
"ኦፊስ ነዉ ባክህ! ቤት መሆን ሲደብረኝ እዚህ እመጣለሁ። እኔና
ሜሮን ነን የተከራየነዉ!" አለችኝ።
ብቻችንን አንድ ቤት ዉስጥ መግባታችን አግባብ አለመሆኑን
ባዉቅም የኢክሩን ጉድ ለማየት ስለጓጓሁ ከመኪናዉ ወርጄ ወደ
ቤቱ ገባሁ።
ቤቱ ሁሉም ነገር የተሟላለት ነዉ። ሳሎኑ ላይ ሶፋ አለ። መኝታ
ቤቱ ዉስጥ አልጋ እንዲሁም የኢንተርኔት መቀበያ ኬብሎች
የተገጠሙበት ጠረጴዛ ላይ ደግሞ ላፕቶፕ አለ።
"እዚህ ነዉ ብዙዎቹን እቅዶቼን የምነድፈዉ!" አለችኝ ወደ መኝታ
ክፍሉ እየጎተተች እያስገባችኝ።
ወዲያዉ ላፕቶፑን ከፍታ ማታ የሰረቅነዉን ኢሜይል እና
ፓስወርድ አስገባች። ልክ ሲከፈት ወደኔ እየዞረች "ይሄ ነዉ
አይደል ፈዊ? ና እየዉ!" አለችኝ።
አዎ የኢክራም አካዉንት እጃችን ላይ ወድቋል። ወዲያዉ
በፍጥነት ፍቅረኛዋን ለማወቅ ሚሴጅ ዉስጥ ገባሁ። ብፈልግ
ብፈልግ የተለየ ሰዉ የለም! ከማዉቃቸዉ ሴቶች እና ወንዶች ጋር
ነበር የምትፃፃፈዉ።
ወይኔ ብልግናዬ! ኢክሩ ልታናደኝ ነበር ፍቅረኛ ይዣለሁ ያለችኝ
ማለት ነዉ?
.
"ምን አገኘህ ፈዊዬ?" አለችኝ ፊርዱ ቁርስ ልትሰራልኝ ኪችን
ዉስጥ እየተንጎዳጎደች።
"ባክሽ ጥርጣሬዬ ትክክል አልነበረም! ማንም የማላዉቀዉ ወንድ
የለም!" አልኳት ለሷ እንዲሰማት ድምፄን ጮክ አድርጌ።
ፊርዱ ቁርስ መስራቱን ጨርሳ እስክትመጣ ኢክሩ ከማዉቃቸዉ
ሰዎች ጋር የተለዋወጠቻቸዉን መልዕክቶች ለማንበብ አሰብኩ።
መጀመሪያ ላይ የአዩብን አገኘሁት ስከፍተዉ ሰላምታ እና ምክር
ነዉ። እሱ ይመክራታል እሷ ልክ ነህ ትለዋለች። ትንሽ
ተዝናናሁበት።
ቀጣይ ላይ ብሩኬ አለ! የኔዉ ጉድ! ደሞ ብሩኬ ምን እያለ
እየመከራት እንደሆነ ለማየት ምልልሳቸዉን ከፈትኩት።
የመጨረሻዉ መልዕክት "እራት በላሽ?" ይላል! ከብሩኬ የተላከ
ነበር። አይ ብሩኬ እየፎገራት መሆን አለበት። መልዕክቶቹን
ወደኋላ እየመለስኩ አነበብኳቸዉ።ቀስ በቀስ እንደ ድንጋይ ደርቄ
ቀረሁ!
"አፈቅርሀለሁ የኔ አይጥ!"
"እኔም እወድሻለሁ የኔ እብድ!"
"ቆይ በኔና ባንቺ መሀል የፈዉዛንን ያረጀ ታሪክ የሚያዉቅ ማን
አለ?"
"ሪሀና እና ሄኖክ ብቻ!"
"እርሺያቸዉ ባክሽ! ፈዉዛን እንደሆነ ሞኝ ነዉ አይጠረጥረንም!"
"በቃ ረሳኋቸዉ! የኔ ጣፋጭ"
"በርዶኛል አትመጪም?"
"መጥቼስ?"
"እቅፍ አደርግሻለሁ!"
"እቅፍ ብቻ?"
"ኧረ እናግለዋለን አንቺ ብቻ ነይ!"
ከዚህ በላይ ማንበብ ከበደኝ። በምድር ላይ የማምናቸዉ ሁለት
ሰዎች እኩል ከዱኝ። ብሩኬ! እኔ እኮ ለሱ የአስር ዓመት ጓደኛዉ
ነበርኩ። እኔ እኮ ለኢክሩ ማንም ከሚያዝንላት በላይ የማዝንላት
እና የምሳሳላት ሰዉ ነበርኩ። ምናለ ባልጠፋ ወንድ ብሩክን?
የፈጣሪ ያለህ! ብሩኬ ስንት ነገር አብረን እንዳላሳለፍን ለአንዲት
ሴት ብሎ ጓደኝነታችንን ናደዉ? መታመን ካለመቻል በላይ
ዉድቀት የለም። ክህደት የትንሾች ባህሪ ናት። ታላቅ ሰዉ መቼም
አይከዳም! እንቢ ለጓደኝነቴ ይላል! እና ብሩክ ትንሽ ሰዉ ነዉ
ማለት ነዉ? እና ኢክራም ትንሽ ሰዉ ናት ማለት ነዉ? ያሳዝናል!
ቆይ ኢክሩ ይሀ ሁሉ የፍቅር ዉዳሴዋ ተረስቷት ፣ እነዛ ሁሉ ዉብ
ጊዜያት ተዘንግተዋት እኔን ከልቧ ማህደር ፍቃ ጓደኛዬን
አፈቅርሀለሁ ስትል ፈጣሪን እንኳ አልፈራችም? ለነገሩ እኔንም
ከትዳር ዉጪ አፈቅርሀለሁ ስትለኝ ፈጣሪን አልፈራችም ነበር።
ምን እያሉ ቀለዱብኝ ይሆን? ምናልባት ብሩኬ እየዘፈነ እሷ
እያጨበጨበች እንዲህ ብለዉ ይሆናል።
"ባልሽ ግን ሞኝ ነዉ፣ እኔ እወደዋለሁ!
እሱ ባያመጣሽ የት አገኝሻለሁ።"
ደግሞ እሱ እያጨበጨበ እሷ እያዜመች
"ጓደኛህ ሞኝ ነዉ ፣ እኔ እወደዋለሁ!
እሱ ባያመጣህ የት አገኝሀለሁ።" የሚባባሉ ይመስለኛል።
.
የክህደታቸዉ ተራራ ላይ ተኮፍሰዉ እኔን እንደሞኝ አይተዉኝ
ይሆናል። እኔ ለኢክሩ መልካም መሆኔን እና የኢክሩን ክብር
መጠበቄን እንደሞኝነት ቆጥረዉ ተዘባብተዉብኝ ይሆናል። እነሱ
ያልተረዱት ግን በመልካምነት እና በሞኝነት መካከል ልዩነት
መኖሩን ነዉ። እኔ እነሱ መልካም እንደነበርኩ እንዲረዱት ብዬ
መጥፎ አልሆንም! ለፍቅራቸዉ ያልተቀየረዉ አቋሜ
ለጥላቻቸዉም እጅ አይሰጥም። ኢክሩ እኮ ጨዋ ነበረች። እንኳን
እኔ ስለሷ የነገርኩት በሙሉ የሚወዳት ሴት ነበረች። በመቼዉ
ክብሯ ተገፎ እንዲህ ርካሽ ሆነች?
እኔ የሳምኳቸዉን ከንፈሮቿን ብሩክ ነካቸዉ? ቅፍፍ አለኝ። እኔ እኮ
የማግባት አቅም ሲኖረኝ መጀመሪያ ማግባት አለማግባቷን
ላጣራ የወሰንኩት ኢክራምን ነበር። አክብሬያት ከህሊናዬ ቤተ
መንግስት ዉስጥ ንግስት አድርጌያት ነበር። እሷ ግን የንግስትነት
ክብሯን አሽቀንጥራ ከስድ ባሪያዬ ጋር የከብት በረት ዉስጥ
መኖርን የመምረጥ ያህል ረከሰች።
ህልሜን ሁሉ አበላሸችዉ! ረከሰች እና ለከፍታዬ አልመጥን
አለች።
.
ሰዉነቴ ተንዘፈዘፈ። ጣቶቼ የላፕቶፑን ማዉዝ መዳሰስ አቃታቸዉ።
እየተንሰቀሰቅኩ መሬት ላይ በግንባሬ ተደፋሁ። ጌታዬን
አመሰገንኩት። ብሩክን ሩቅ ሳልጓዝ ማንነቱን አሳወቀኝ። ለትዳር
የማስባት ሴት ለክብሬ እንደማትመጥን አሳየኝ። ምንም ነገር
ቢወስድብኝ በተሻለ ነገር ሊተካልኝ ቢሆን እንጂ
የማይወስድብኝን ጌታ አመሰገንኩት። ጌታዬ ከኢክራም የተሻለች
ሴት ቢወስንልኝ ነዉ። አመሰገንኩት። እየተንሰቀሰቅኩ
አመሰገንኩት። ከጌታዬ በቀር እንዲህ ላምነዉ የሚገባ ሰዉ
አለመኖሩን ሊያስተምረኝ እንዳደረገዉ አሰብኩ።
በግንባሬ ከተደፋሁበት ተነስቼ ስለ ኢክራም አሰብኩ። እሷ
እንዲህ ከሆነች ሌላ ሴት ማን ይታመናል? አልኩ በልቤ።
አልጋዉ ላይ በጀርባዬ ተዘረርኩ። ከዚህ በፊት ብሩኬን ኢክራም
ፍቅረኛ እንደያዘች የጠረጠርኩ ቀን ሳማክረዉ "የራሷን ህይወት
ትኑርበት! ተዋት!" ያለኝ ትዝ አለኝ። በርግጥ ከዛ ቀን በኋላ
ብሩኬን ምንም ነገር አላማከርኩትም ነበር። ጥርጣሬ ዉስጥ
ገብቼ ነበር። ግን ጓደኛዬን መጠርጠር ብልግና ነዉ ብዬ
ረሳሁለት። ብሩክ እና ኢክሩን መንገድ ላይ አብረዉ አግኝቻቸዉ
አዉቃለሁ። ግን ድረዊንግ ልስልላት ነዉ ስለሚለኝ እና በፍፁም
ብሩኬ እንዲህ ይከዳኛል ብዬ ስላልገመትኩ
አልጠረጠርኳቸዉም። እህቴ ብሩክን እና ኢክሩን መንገድ ላይ
በተደጋጋሚ አየኋቸዉ ትለኝ ነበር። ግን ብሩኬን እንዴት
ልጠርጥር? ኢክሩ ይሀ ሁላ የፍቅር ሙገሳዋ በክህደት
ይታጠባል ብዬ እንዴት ላስብ? እሺ እኔን ትተወኝ! የጓደኛዋን
የሪሀናን የቀድሞ ፍቅረኛ ማማገጥ ምን የሚሉት የክህደት
ጀብዱ ይሆን?
እሱም የቀድሞ ፍቅረኛዉን የሪሀናን ጓደኛ እና የአስር
👍 8
ነጫጭ ጥቁረቶች ክፍል አስራ ሰባት

ዛሬ ምሽት ይጠብቁን...

JOIN @Ye_Hagere_Wegoch_2
JOIN @Ye_Hagere_Wegoch_2
👍 3
ቅዳሜ!

በጠጉሮቿ መሀል አበባ ሰክታ 
ሲኒማ ኢምፓየር ስሩን ተጠግታ
አስር ጊዜ የጇን ፥ ሰዓት የምትቆጥር
ከመንገዱ ቁልቁል ፍቅሯን የምትማትር
አይመጣም ወይ ብላ ከንፈሯን የጣለች
ይመጣልም ብላ 
ፈገግ ወደማለት ...ዳርዳርታ ላይ ያለች 
እርሷን የምትመስል የቀናት ምስጢር ነች።

ነጠላ ባጣፉ ፣ ቄጠማ በያዙ
ሽቶ ተነስንሰው
ከባንኮኒው ግድም ፣ አልኮልን በሚያዙ
በመዝሙር ውዳሴ ከመላዕክት ጋራ
በማለዳው ጮራ.. .
ደግሞ ወዲህ ምሽት
በሳልሳ በቡጊ.. .. በሬጌ ጭፈራ
በኒህ ሁለት ፅንፎች መሀል ተወስና
"አፍቃሪሽ አይቋረጥ" ብለው የመረቋት
ዘማሪም ደናሹም እኩል የሚወዷት
የቀኖች ንግስት ናት !

JOIN @Ye_Hagere_Wegoch_2
JOIN @Ye_Hagere_Wegoch_2
እወድሻለሁ...

በፍቅሽ መንደዴ እንዲህ መንገብገቤ
ለጊዜያዊ ስሜት አይደለም ማሰቤ
ምኞቴ እሩቅ ነዉ ፍቅር አለ ልቤ
ፀባይሽ
ዉበትሽ
ሣቅና ፈገግታሽ ሁሉ ተደማምሮ
አልወጣ ብሎኛል ልቤ ዉስጥ ተቀብሮ
ፈጣሪን ብዬ አምልልሻለዉ
ከነፍሴ አብላጫ በጣም ወድሻለው

ግጥሙን ከወደዳችሁት ለምትወዱት ጓደኞቻችሁ #share አርጉ

JOIN @Ye_Hagere_Wegoch_2
JOIN @Ye_Hagere_Wegoch_2
👍 3
⬜️ነጫጭ ጥቁረቶች⬛️
#ክፍል አስራ ስድስት

.
ብዙ ሰዎች ኢክሩ በፍፁም ጥፋተኛ እንዳልሆነች ነዉ
የሚያስቡት። "ሳይቸግርህ ጭረሀት" "አንተ ነህ የተዉካት!!"
ምናምን ይሉኛል። መተዉ ምን ማለት ነዉ? እኔ እኮ ኢክሩን
በጊዜዉ ለማግባት ስለማልችል እንድታገባ ብዬ ነበር
የተለየኋት። አደራ ያልኩት እኮ ፈጣሪዬን ነበር። እኔ እሷን
የመናፈቅ እሳቴን አፍኜ ይብቃን ስላት ለሷ የወደፊት ህይወት
ማማር እየተሰዋሁ እንደነበር ለምን አይገባቸዉም? ተዋት ይላሉ
እንዴ? አቅሜን አዉቄ ለፈጣሪ አሳልፌ በሰጠሁ ገፋት ይላሉ
እንዴ? አስመሳይ ሁላ!! ለነገሩ የነሱ ወሬ ለኔ ምንም ነዉ።
ያመንኩበትን ነገር እንጂ አላደርግም! ስሜት ያወረዉ ትዉልድ
የሚታይ ድርጊት እንጂ የታፈነ ስሜት አይገባዉም። ኢክራም
እንደተሰዋሁላት እንዲገባት ከፎቅ ላይ ራሴን መፈጥፈጥ
አይጠበቅብኝም። ማንም ሳያዉቅ በልቤ እንደታፈንኩ እኖራለሁ።
በኔ ዝምታ ዉስጥ ብዙ ትርጉም ነበር። እሷን በመተዌ
ያሳለፍኩትን ስቃይ እኔ ነኝ የማዉቀዉ። እስከዛሬ ጠረኗ
የማይረሳኝ ሰዉ እኮ ነኝ!! ከሷ በኋላ ማንንም ያላየሁ!! አዎ
የሱመያን የድምፅ መስረቅረቅ አድንቄያለሁ ፣ የፊርደዉስን ዉበት
አሞግሻለሁ ግን አንዳቸዉንም ከምላሴ አሳልፌ ልቤ ዉስጥ
አላስገባሁም። በሁሉም ሴቶች ዉስጥ የምትታየኝ ኢኩዬ
ነበረች። ሁሌም ቃሌን አስታዉሳለሁ። ስንለያይ ለራሴ የገባሁትን
ቃል!! የማግባት የስነ ልቦና እና የገንዘብ አቅም ሲኖረኝ
መጀመሪያ ኢኩዬን ፈልጌ ካላገባች ላገባት ለራሴ የገባሁትን
ቃል!! ተዋት ይላሉ እንዴ? ለሷ አልጋዉን አደላድዬ እኔ መሬት
ላይ በተኛሁ ገፋት ይላሉ እንዴ? ወረኛ ሁላ!! ሲጀመር እነሱ
የመዉደድን ልክ የወደዱትን የራስ ከማድረግ አሻግረዉ
መመልከት አልቻሉም። እኔ ዉዴታዬ በዝቶ ለኢክሩ ባል
ተመኘሁላት!! ኢክሩ ንግስት እንድትሆን ከነክብሯ እንድትለየኝ
አደረግኩ። ጌታዬን አስደስቻለሁ እሷ የፈለገችዉን ትበል ግድ
የለም። እንደኔ ያሰበላት፣ ወደፊትም የሚያስብላት ሰዉ ግን
የሚኖር አይመስለኝም።
.
ኢክራም ፍቅረኛ ይዣለሁ ያለችኝ ልታናደኝ ፈልጋ መስሎኝ ነበር።
የኢድ ቀን ስደዉልላት በንግግሯ ዉስጥ የሰማሁት ኩራት እና
ንቀት ግን ኢኩ የእዉነት ፍቅረኛ ይዛለች ወደሚለዉ ድምዳሜ
ስላደረሰኝ ነበር ለአምስት ቀናት ስለሷ መረጃ ያሰባሰብኩት።
ኢክራም በህይወቷ ላይ ብዙ ለዉጦች አስተናግዳለች።
ያቺ የጅልባቧን እጄታ ይዛ ጅልባቧን በጥርሷ ነክሳ እያየችኝ
ስትስቅ ትዝታዋ የማይረሳኝ ኢክራም ጅልባቧን አሽቀንጥራ ጥላ
የቱርክ ፋሽን ማራገፊያ ሆናለች። ያቺ ወንድ የማትጨብጠዋ
ኢኩ ማንም እንዳሻዉ የሚያቅፋት ተራ ሴት ሆናለች። ሌላዉ እነ
ኢክሩ ሰፈር ቀይረዉ እነ ሄኖክ ሰፈር ገብተዋል። እናቷ
አግብታለች።
በጣም ቀፈፈኝ!! ለማንም ያላረከስኩትን እኔነቴን ያረከስኩላት
ሴት ከማንም ጋር እየተንዘላዘለች ነዉ። ከቻፒስቲክ ያለፈ
የማትቀባዋ ኢክራም ሜካፕ ይሉት ዱቄት ማራገፊያ ሆናለች
አሉኝ። በዚህ ሰዓት አጠገቧ ሆኜ ልረዳት ባለመቻሌ በጣም
ተሰማኝ። ሱመያን በቻለችዉ ኢክሩ የተሻለ ሰዉ እንድትሆን
እንድትረዳት ተማፀንኳት። ሱመያ ነገሩ ለጊዜዉ እንደሚከብድ
ነገረችኝ። ከሰፈሩ መራራቅ ባሻገር ለነሱመያ አልተበላሸሁም
ትላቸዉ ስለነበር በግልፅ እስከሚያገኟት መጋፈጡ ከብዷቸዋል።
ኢክሩን ፌስቡክ ላይ አንዳንድ ነገሮችን አወራኋት ፍቅረኛ
የሚባለዉም ነገር ቢቀርባት እንደሚሻል መከርኳት። ሁሉም
ወንድ እንደኔ ነዉ ብዬ አላምንም!! ኢክራም ላይ ማመን
የምችለዉ ወንድ እኔን ራሴን ብቻ ነዉ። ለምክሩ አመስግናኝ
የራሷን መስመር መከተል ጀመረች። እኔ ግን አሁን ላይ ማወቅ
የምፈልገዉ ኢክሩዬን እንደዚህ ያዘቀጣትን ፍቅረኛ ተብዬ ነዉ።
ግን በየት በኩል? እንዴት ልወቀዉ? ለጊዜዉ ጭንቀቴን በስልክ
ለረዊና ሁሉንም ነገር እየተነፈስኩላት አስታግስ ነበር።
.
የሁለተኛ አመት ተማሪ ሆነን አራተኛዉ ወር ተጀምሯል። ረዊናም
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እየተማረች ነዉ።
ብሩኬ የግል ካምፓስ አካዉንቲንግ ተመዝግቦ እየተማረ ነዉ።
ግን ትምህርት ቤቱ የሱሰኞች እና የሴሰኞች መናኸሪያ ስለነበር
ብሩኬ አይኔ እያየ ጫት ሙዱ ሆነ። ስለሴቶች አዉርቶ
አይጠግብም!!
"ፈዉዛኔ የእዉነት ሴቶች ርካሽ ናቸዉ!" አለኝ አንድ ቀን አብረን
ተቀምጠን
"እንዴት ብሩኬ?" አልኩት በጅምላ ሲፈጃቸዉ ደንግጬ
"ፈዉዛኔ እኛ ግቢ ያሉት ሴቶች እንዴት ሱሰኛ እንደሆኑ ብታይ፣
ደሞ ሴክስ በቃ እንደሰላምታ ነዉ!" አለኝ።
ዝም አልኩት!! በንግግሩ ዉስጥ ተግባሩን እየኮነነዉ ቢመስልም
እንደወደደዉ ተረድቻለሁ። ሴት ብቻዋን እንዴት ትረክሳለች?
አብሯት የሚንፈራገጥ ወንድ ግዴታ ያስፈልጋል። ይሄ ማለት
ደግሞ ሁለቱም ረክሰዋል ማለት ነዉ። ወይስ ወንድ
የማይረክሰዉ ሲጀመርም ክብር ስለሌለዉ ነዉ? እኔ የነብሩኬ
ሎጂክ አይገባኝም። ነገር ግን የብሩኬ አካሄድ እያማረኝ
ስላልሆነ አንድ ቀን ከትምህርት ስመለስ ቁጭ አድርጌ እንደ
ከብት እንዳይነዳ እና እንቢ ማለት መቻል እንዳለበት መከርኩት።
ነገር ግን የነብሩኬ ትምህርት ቤት መዓበል ብሩኬን ወደ
ጠጪነት መደብ ወረወረዉ!! እኔ እንዳልሰማ ይጠነቀቃል።
ይቅማል፣ይጠጣል!! በቀን እንደቁምነገር ከጓደኞቹ ጋር መጠጥ
ቤት ይዉላል። ብሩኬን ለማዳን አልቻልኩም!! በሰዓቱ ትኩረቴን
ሙሉ በሙሉ ትምህርቴ ላይ አድርጌ ነበር። ዉጤቴን ለማሻሻል
ታላቅ ትግል ላይ ነበርኩኝ።
.
ጁምዓ(አርብ) ቀን ፊርደዉስ ከትምህርት ስወጣ ልታገኘኝ
እንደምትፈልግ ነገረችኝ። ተገናኝተን ከሷ እቅድ ጋር በተያያዘ
ብዙ አወራን። የተቀመጥንበት ካፌ ዉስጥ ከመቀመጫዋ ተነስታ
ወንበሯን እየጎተተች ከጎኔ ተቀመጠች። ፊርደዉስ ሽቶ
አልተቀባችም። አጠገቤ እንደተቀመጠች
"ፈዊዬ የሆነ ነገር በህይወትህ ዉስጥ አልተፈጠረም? እስኪ
ካንተም ልስማ ንገረኝ!" አለችኝ።
የኔና የኢኩን ታሪክ እስኪሰለቻት ተረኩላት። አሁን ላይ ፍቅረኛ
ተብዬዉ ማን እንደሆነ ማወቅ እንደምፈልግ እና ማወቅ
እንዳልቻልኩ ነገርኳት።
ፊርደዉስ ከአይኖቿ እንባ እየፈሰሰ "ፈዊ በጣም ጥሩ ሰዉ ነህ።
እሷ ብትረዳዉም ባትረዳዉም አንተ ለህሊናህ ታምነሀል!"
አለችኝ።
ወዲያዉ እንባዋን እየጠረገች "ፈዉዛኔ እኔ በቀላሉ ፍቅረኛዋ
ማን እንደሆነ እንድታዉቅ እረዳሀለዉ!" አለችኝ።
አይኗን እያየሁ "እንዴት?" አልኳት።
ፊርደዉስ ወደኔ ጠጋ እያለች
"ፈዉዛኔ ኢክራም የፌስቡክ አካዉንት እንዳላት እርግጠኛ ነኝ።
ፍቅረኛ ተብዬዉም አይ ቲንክ ይኖረዋል። እና በፌስቡክ
መጀናጀናቸዉ ኢቲ ኢዝ ኦቪየስ!! እኔ የሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ
ተማሪ እንደመሆኔ የፌስቡክ አካዉንት ለመጥለፍ የሚያስችል
ማስፈንጠሪያ(Pheshing link) እሰራልሀለሁ። አንተ በቅርብ
እሷ በምታዉቀዉ ስልክ ቫይበር ላይ ሊንኩን ልከህ የሷ ፎቶ
ስላለዉ እንድታየዉ ትነግራታለህ። ታዲያ በራስህ ስልክ ሳይሆን
እሷ በምታዉቀዉ የሌላ ሰዉ ስልክ መሆን አለበት። እሷ ሊንኩን
ስትከፍተዉ ለመግባት ኢሜይል እና ፓስወርዷን እንድታስገባ
ይጠይቃታል። እሷ ፓስወርዷንና ኢሜይሏን ስታስገባ
ከማስፈንጠሪያዉ ጋር በተያያዘዉ የጂሜይል አካዉንት እኛ
ፓስወርዱን እና ኢሜይሉን እናገኛለን። የዛኔ አካዉንቷ ላይ
በነፃነት ገብተህ ጉዷን መበርበርም ሆነ ፍቅረኛዋን ማወቅ
ትችላለህ!! ክሊር?" አለችኝ።
"በጣም ግልፅ ነዉ። የኔ እብድ ምናለ እስከአሁን በነገርኩሽ
ኖሮ!" አልኳት እንደ ህፃን ልጅ እየቦረቅኩኝ።
.
የሰዉን የግል የህይወት መስመር ተላልፎ የግል መረጃዎቹን
መበርበር አግባብ እንዳልሆነ አዉቃለሁ።

ይቀጥላል...
👍 4
የጌታ ስጦታ🥰

በፋኢዛ ✍

እኔ ድሮ........
አምላክ ፈጣሪዬን ሁሌ ምለምነው ፣
የነገዋን ፀሀይ ማየት እንዳልችል ነው፡፡
ግን ጌታን ብለምን ወደ ላይ እያየሁ፣
የመሞትን ፀጋ ለመቸር አልታደልኩ፡፡
ታዲያ ጌታዬ......
ኧረ ስጠኝ ብዬ እኔ ያለመንኩትን፣
የመኖርን ትርጉም ፍቅሬ ሰጠኝ አንተን፡፡
ተመስገን ፈጣሪ ለሰጠኸኝ ፀጋ፣
ስሰግድልህ ልኑር ሲመሽም ሲነጋ፡፡
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏


ዛሬ........
ለጌታ ሰግጄ ሁሌም ቀና እንዳልኩኝ፣
ከአንተ እንዳያርቀኝ እማፀናለሁኝ፡፡
እና ፈራሁ ፍቅሬ፣
ሚስጥረ መኖሬ፡፡
ተዉ ግደለኝ ብዬ 40 ስሰግድለት፣
አሻፈረኝ ብሎ እንዳቆየኝ በህይወት ፡፡
ሁሌ ሰማፀነው ከአንተ እንዳይለየኝ፣
ኧረ እኔ እምቢ ብሎ ፈራሁ እንዳይገለኝ!!

JOIN @Ye_Hagere_Wegoch_2
JOIN @Ye_Hagere_Wegoch_2
👍 3
ከ ክፍል 15 የቀጠለ ...

ላይ የሚሰማኝን መረበሽ ለማስወገድ ያለኝ የመጨረሻ መንገድ ስለሆነ የኢክሩን
የሚስጥር ጓዳ ለመፈተሽ እና የግለኝነት መብቷን ለመግፈፍ
ወሰንኩ።
ፊርደዉስ በሶስት ቀናት ዉስጥ የፌስቡክ ፓስወርድ መስረቂያ
ሊንኩን (Pheshing link) ሰርታ ላከችልኝ። አሁን ለኢክራም
ሊንኩን ልኮ እንድትከፍተዉ ለማድረግ አንድ የምታዉቀዉ ሰዉ
ስልክ ያስፈልጋል። አዎ አዩብ!! አዩብን ስልኩን እንዲያዉሰኝ
ማድረግ እችላለሁ!! የሪም ፍቅረኛ አዩብ!! ለኢክራምም ቅርብ
ስለሆነ በሱ ስልክ አታልዬ ሊንኩን መላክና እንድትከፍተዉ
ማድረግ እችላለሁ።
ቅዳሜ ማታ ላይ አዩብን መስጂድ አገኘሁት። የዛን ቀን ማታ ላይ
ስልኩ እኔ ጋር እንዲያድር ጠየቅኩት። እሱም የዛን ቀን ይፈልገዉ
ስላልነበር ለምን እንኳ ሳይለኝ ጠዋት ለፈጅር ሰላት(ለንጋት
ስግደት) እንዳመጣለት ነግሮኝ ስልኩን ሰጥቶኝ ሄደ።
ገና መንገድ ላይ ሆኜ የአዩብን ቫይበር ከፈትኩት ኢክራም ኦን
ላየን አለች። ሰላም ብያት በቅርቡ ስላገባች አንድ ጓደኛቸዉ
አወራኋት። እሷ ከአዩብ ጋር እንደምታወራ ነዉ እያሰበች
ያለችዉ። አሁን ለሰርጉ የተነሱትን ፎቶ እንዳየሁት ነግሬያት
ማስፈንጠሪያዉን ተጭና እንድታይ ነግሬ የፌስቡክ ፓስዎርድ
መስረቂያ ሊንክ (Pheshing link) ላኩላት። ይመስለኛል አሁን
ፓስወርድና ኢሜይሏን አስገብታለች። አሁን ከመስረቂያ ሊንኩ
ጋር በተያያዘዉ ጂሜይል አካዉንት ሁሉም መረጃ ፊርደዉስ እጅ
ላይ ይገባል።
ወዲያዉ ለፊርደዉስ ያደረግኩትን በቴክስት ሚሴጅ ነገርኳት።
እሷም የጂሜይል አካዉንቱን ቼክ አድርጋ መረጃዉ እጃችን ላይ
መዉደቁን አበሰረችኝ። በነጋታዉ ተገናኝተን ጉዱን ለማየት
ተቀጣጠርን።

ይቀጥላል...

JOIN @Ye_Hagere_Wegoch_2
JOIN @Ye_Hagere_Wegoch_2
👍 8
⬜️ነጫጭ ጥቁረቶች⬛️
#ክፍል አስራ አምስት

.
ሰዓታት ምንም የሰዉ ልጅ ለዉጥ ቢፈጥርም ባይፈጥርም
ከመቁጠር አይወገዱም። ተኝተንም እንዋል በስራ ተጠመድን
ቀን ይነጉዳል። እንደቀልድ አመት አለቀ ይባላል።
ከኢክራም ጋር የፍቅር ግንኙነታችንን ካቋረጥን ከሶስት ወራት
በላይ ተቆጠሩ። በወንድምነት የነበረንንም ትስስር ኢክሩ
ካቆረፈደችዉ ሁለት ወር ሆነ።
የዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ አመት ትምህርቴን አጠናቅቄ ክረምቱን
እየቦዘንኩ ነበር። አንዳንዴ እዚህ ካፌ እየመጣሁ ከረሂማ ጋር
እጫወታለሁ። አንዳንዴ ብሩኬ ጋር እየሄድኩ እደበራለሁ። በዛ
ሰሞን ግን ለተለያዩ ተቋሞች የስነ ፅሁፍ ስራዎችን ድህረ ገፃቸዉ
ላይ በመስራት ተጠምጄ ስለነበር ኢንተርኔት ላይ ተጥጄ እዉል
ነበር።
.
አንድ ቀን እንደተለመደዉ ኢንተርኔት ላይ ተጥጄ ከማላዉቀዉ
ሰዉ መልዕክት ደረሰኝ።
ልጁ ሰላምታ እንደተለዋወጥን
"ፈዉዛኔ እኔ ሰፈር አካባቢ አዉቅሀለሁ። ከኢክሩ ጋርም ግንኙነት
እንደነበራችሁ አዉቃለሁ። አሁን የፍቅር ግንኙነት ዉስጥ ናችሁ
እንዴ?" የሚል መልዕክት ላከልኝ።
ወዲያዉ "እኔና እሷ መገናኘት ካቆምን በጣም ቆይቷል።
በመካከላችን ምንም አይነት ግንኙነት የለም።" አልኩት።
ልጁ አመስግኖ ተሰናበተኝ። ትንሽ ቆይቼ አሰብኩና በመልሴ
ተፀፀትኩ። ፍቅረኛዬ ናት ነበር ማለት የነበረብኝ። ኢክሩን ከዚህ
በኋላ አግብታ እንጂ ከማንም ወንድ ጋር ስትንዘላዘል ማየት
አልፈልግም። የልጁ ጥያቄ ደግሞ ከተዉካት ልዉሰዳት አይነት
ነዉ። ማንም የጣለዉን ሲያነሱበት አይወድም። ሊያዉም
እንድታገባ የምመኝላትን ሴት አብራዉ ስትንዘላዘል ማየት
ያመኛል። ዉስጤ ሰላም አጣ። የኢክሩን የፌስቡክ ገፅ
ለመጎብኘት ገባሁ አንፍሬንድ እንደተደረግኩ ነዉ። ላወራትና
ከልጁ ላስጥላት ፈለግኩ።
.
ከኢክሩ ጋር ከሶስት ወራት በኋላ ድጋሚ ፌስቡክ ላይ አወራን።
ስላለችበት ሁኔታ አንዳንድ ነገሮችን ጠየቅኳት። እንደድሮዉ
በመካከላችን ሰላም አዉርደን በወንድምነት እንድንቀጥል
ጠየቅኳት። መልዕክቱን የላኩላት በእንግሊዘኛ ስለነበር የፍቅር
ግንኙነታችንን ድጋሚ መልሰን እንቀጥል ያልኳት መስሏት
እንዲህ አለችኝ:
"እኔ ስትፈልግ የምትጥለኝ ስትፈልግ የምታነሳኝ እቃ
አይደለሁም። አሁን ከሌላ ሰዉ ጋር የፍቅር ግንኙነት
ጀምሬያለሁ።"
ደነገጥኩ!! እሞትልሀለሁ ስትለኝ የነበረችዉ ኢክሩ ናት በሁለት
ወር ዉስጥ ከህይወቷ ማህደር ፍቃኝ ከሌላ ወንድ ጋር ፍቅቅሮሽ
የጀመረችዉ? ወይስ ሲጀመርም አፈቀርን ሲሉ ሰምታ እንጂ ፍቅር
ምን እንደሆነ እንኳ አታዉቅም? እንዴ እኔ እኮ ኢክሩ ግጥም
ስለማትወድ ብዬ ግጥም መፃፍ ያቆምኩኝ ይኸዉ እስከአሁን
ግጥም አልፃፍኩም። ቆሻሻ ላይ የተወለደ ፍቅር ንፅህና ሊኖረዉ
እንደማይችል ግልፅ ነበር። ትዳር ላይ ያልተመሰረተ ግንኙነት
ፍሬ ሊያፈራ አይችልም። ኢክሩ እንዴት እኔን ረስታ ሌላ ወንድ ጋር
ለመሄድ ደፈረች? እኔ እኮ እንኳን ልረሳት በጣም ስትስቅ
የሚሸበሸበዉ አፍንጫዋ አሁንም አይኔ ላይ አለ። ኢክሩ እኮ
እየተኮላተፈች 'ደ' ስትል አሁንም ጆሮዬ ላይ ይደጋገማል።
.
እራሴን አረጋጋሁ እና ኢክሩ ልታናደኝ ፈልጋ እንጂ እንደዚህ
የምታደርግ ልጅ እንዳልሆነች ብዙ ምክንያቶችን እየሰጠሁ ራሴን
አሳመንኩት።
እንደዉም እኔ እወድሻለሁ ስላት አይኗን ወደ ሰማይ እየሰቀለች
"ፈዉዛኔ የኔ ድመት አንተ ትወደኛለህ። እኔ ላንተ ያለኝ ፍቅር ግን
ካንተ በጣኣኣኣም ይልቃል።" ያለችዉን አስታወስኩ።
ኢክሩ በሁለት ወር ዉስጥ ይሄን ፍቅሯን ከልቧ አስወጥታ
ከነገስኩበት የልቧ ዙፋን ላይ ሌላ ሰዉ እንደማታስቀምጥ ለራሴ
ነገርኩት።
"ምንም ችግር የለዉም። መብትሽ ነዉ!" ብዬ መለስኩላት።
አልተናደድኩልሽም እንደማለት ነበር ያሰብኩት።
እኔ ፍቅረኛ ይዤ ከሆነ ጠየቀችኝ እንዳልያዝኩ ነገርኳት።
.
ወደ ማታ ላይ ብሩኬን አግኝቼ የተፈጠረዉን ነገር ነገርኩት።
ኢክሩ ፍቅረኛ ይዛ ከሆነም ሁለቱን ለመነጣጠል ስል የፍቅር
ግንኙነት ከሷ ጋር ልጀምር እንደምችል ነገርኩት። ማንም እንደኔ
ሊያስብላት አይችልም ብዬ አምናለሁ። ቢያንስ ከኔ ጋር ከሆነች
ዝሙት ላይ አትወድቅም። ሌላ ወንድ ኢኩ ላይ ስሜቱን
ሲያስታግስ መመልከት አልፈልግም። ኢኩ ንግስት ሆና ባል
ስታነግስ ነዉ መመልከት የምሻዉ።
አንገቴን አቀርቅሬ "ብሩኬ ኢኩ የእዉነት የፍቅር ግንኙነት ጀምራ
ከሆነ እኔ ኢኩን እና ልጁን ለማጣላት ከሷ ጋር የፍቅር ግንኙነት
እስከመቀጠል ድረስ ለመጋፈጥ ወስኛለሁ።" አልኩት
ብሩኬ እንደመቆጣት እያለ "በቃ ተዋት የራሷን ህይወት
ትኑርበት!!" አለኝ
ሳግ እየተናነቀኝ "ብሩኬ እኔ እኮ እንድታገባ እንጂ ከማንም ጋር
እንድትንዘላዘል አይደለም የተዉኳት!!" አልኩት።
"በቃ ተዋት አይመለከትህም!!" አለኝ አሁንም ቆጣ እንዳለ ነዉ።
ብሩኬ ይሄን አቋሜን ስላልደገፈልኝ ተበሳጨሁ። ከዚህ በኋላ
የምወስዳቸዉን እርምጃዎች እሱን ሳላማክር ለመዉሰድ
ወሰንኩ።
.
ፊርደዉስ ክረምቱን በተደጋጋሚ እየደወለች እንድንገናኝ
ትጠይቀኛለች። እኔ ግን ዉርርዷን ልትፈፅምብኝ እንደሆነ
ስለማስብ ላገኛት ፈቃደኛ አልሆን አልኳት። እዉነት ለመናገር
በኔና በሷ መካከል ሀይማኖት እና ማህበራዊ ስርዓታችን ልቅ
መሳሳምን ባያወግዝ ኖሮ እኔ ነበርኩ ከንፈሯ እንደ ኢክሩ
እስኪያብጥ የምስማት!! ግን ሰዉ እንደመሆኔ እንደ እንስሳ
ማሰብ የለብኝም። ስጋዬ ይፈልጋል አልዋሽም!! ግን ፈጣሪዬን
ማስቆጣት አልፈልግም። እሱን ካስቆጣሁ አንዷን ፊርደዉስን
አግኝቼ ጌታዬን ላጣ እችላለሁ። እሱን ባስደስት ግን ጌታዬ
የፊርደዉስ አይነት ሴቶች ካዝና በእጁ ነዉ።
አንድ ቀን ሀሙስ እለት ፊርደዉስ ደዉላ የጓደኛቸዉን ልደት
ስለሚያከብሩ እንድገኝ ጠየቀችኝ። ሙስሊም ስለሆንኩ ልደት
እንደማላከብር ነገርኳት።
"ኧረ ፈዉዛኔ ይሄን ያህልማ አታካብደዉ!!" አለችኝ።
በሷ ቤት አክርሬባት ሞታለች።
"ፊርደዉስ እኔ ሙዴ እንደዚህ ነዉ!! እንደየሙዳችን ብንሆን
ይሻላል ከምንከራከር!" አልኳት
"እሺ በጣም ጥሩ!! በርዝደይ ፓርቲዉ ላይ እኔም አልገኝም።
ካንተ ጋር መገናኘት እፈልጋለሁ።" አለችኝ።
ተስማምተን ቀጠሮ ያዝን።
.
ፊርደዉስ ስትስቅ ጉንጮቿ በጣም ይሰረጉዳሉ። በጣም
ታምራለች። ሳር ቤት አካባቢ ተገናኘን። መኪና ይዛ ነበር
የመጣችዉ። ገቢና ገብቼ ከዚህ በፊት ገብቼበት ወደማላዉቀዉ
መናፈሻ ይዛኝ ሄደች። ቦታዉ በጣም ቆንጆ ነዉ። መኪናዋን ቦታ
አስይዛ ካቆመችዉ በኋላ ከመኪናዉ ወርደን ዉቡ የሳር መናፈሻ
ላይ የተቀመጡት ወንበሮች ላይ ተቀመጥን።
"ፈዉዛኔ እኔ ማንንም ወንድ እንዳንተ ተለማምጬ አላዉቅም።
ይህን ሁሉ የማደርገዉ እንድስምህ ስለተወራረድኩ ብቻ
መስሎህ ከሆነ ተሳስተሀል! አንተ የራስህ አቋም አለህ። እንቢ
ማለት መቻልን አስተምረኸኛል። እኔ ደግሞ አላማ አለኝ። ይሄን
አላማዬን ለማሳካት ካንተ የተሻለ አማካሪ የማገኝ
አይመስለኝም።" አለችና በረዥሙ ተነፈሰች
ፊርደዉስ የኮምፒዩተር እዉቀቷ በጣም ከፍተኛ መሆኑን
ከነገረችኝ እቅዶቿ ተረዳሁ። ያለማቋረጥ ለአንድ ሰዓት እቅዷን
ነገረችኝ። አሁን ፊርደዉስን በጣም አከበርኳት። በምችለዉ ሁሉ
ላግዛትም ቃል ገባሁላት።
የኢድ አል አድሀ ማለትም የሀጅ ስነ ስርዓት እንዳለቀ ያለዉ
የኢድ በዓል ደረሰ። ሁልጊዜም እንደማደርገዉ በስም ቅደም
ተከተል ሰዎች ጋር እየደወልኩ እንኳን አደረሳችሁ እያልኩ በኢ
ተርታ ያሉት ጋር ደርሼ ኢክራም ጋር ደወልኩ።
የዛሬን አያድርገዉና ሌላ ጊዜ መጀመሪያ እሷ ጋር ደዉዬ ነበር
ቀሪዎቹ ጋር በስም ቅደም ተከተላቸዉ የምደዉለዉ።
አነሳችዉ "ኢኩዬ እንኳን አደረሰሽ!!" አልኳት።
"እንኳን አብሮ አደረሰን!" አለችኝ
👍 2
የልቤ ሰራቂ

የውበቷ እንቁ ውቧ ፅጌረዳ
ደምቃ እንደወጣች ገና በማለዳ
አብራት ከወጣችው ከፀሀይዋ ልቃ
ልቤን ወሰደችው ካካሌ ፈልቅቃ
የምን ልቤ ብቻ የምን አካላቴ
በፍቅሯ የነደደው መላ እኔነቴ
የፍቅር ጀግናናት አይደፍሩትን ደፋር
ጥልፉ የጣለችኝ በውበቷ አድባር
ከልቤ ካንጀቴ እኔ እዬወደድኳት
በፍርሃት ተውጬ ፍቅሬን ስገልፅላት
በፈጣሪ ፀጋ በውበቷ ኮርታ
አሻፈረኝ ብላ ሄደች ጀራባ ሰታ
የወንድነቴ ጥግ ተሰበረ ወሽመጡ
የማረገው ጠፋኝ አልገባኝም ቅጡ
ኸረ ወቸው ጉዴ አሁን ምን ተሻለኝ?
ከሷ ተነጥዬ መኖር አይቻለኝ
ቀን በቀን ስናፍቅ ልቤ ሲፈልጋት
እንዲው ጥላኝ ስትሄድ ፍቅሬ አልከበዳት
በፍቅሯ ብመንን ካአጀብ ተነጥዬ
መቼም አልጫናት የኔ ሁኚ ብዬ
ውደደኝ ሳትለው ልቤ ከወደዳት
እንዴትስ አድርጌ ሸንጎ ልገትራት
ቀንቶኝም የማያወቀው ደርሶ የኔ ዕጣ
እሷን አገኝ ብዬ እኔው ራሴን ልጣ?

✍ቶፊቅ መሀመድ

JOIN @Ye_Hagere_Wegoch_2
JOIN @Ye_Hagere_Wegoch_2
👍 2
👏 2
⬜️ነጫጭ ጥቁረቶች⬛️
#ክፍል አስራ አራት
.

የኢክራም እግር ትቦዉን ለመሸፈን በተረበረቡ አርማታዎች
መካከል ሾልኮ ሲገባ እኔ ተንደርድሬ ያዝኳት። እግሯ ለመዉጣት
ስላልቻለ ረጋ ብላ እንድታወጣዉ እና ሰዉም እየበዛ ስለነበር
ከሰዉ እይታ ኢክሩን ለመሸፈን ኢክሩን ለቅቄ ከእምነት ጋር ጎን
ለጎን ቆመን ለመከለል ሞከርን። እኔ እግሯን ጎትቼ ላወጣላት
አልችልም። ምክንያቱም አርማታዉ እግሯን ሊቧጭራት ይችላል።
ሁሉም ሰዉ ከመዉደቁ በላይ የሚያመዉ በሰዉ መታየቱ ነዉና
እሷ ተረጋግታ እግሯን እስከምታወጣዉ ድረስ ከእይታ ልጋርዳት
ፈለግኩ። በዚህ መካከል ብሩኬ ኢክራምን ደግፎ ይዟት ነበር።
ሁላችንም የትናንት ጭንቀታችንን አልፎ ስናየዉ ደስ ይለናል።
ኢኩዬም እግሯ ከትቦዉ ዉስጥ ከወጣ በኋላ እንዴት እንደነበረች
እያሰበች እንድትስቅ ብዬ ፎቶ አነሳኋት። ትልቁ ስህተት
የተፈጠረዉ እዚህ ጋር ነዉ። ፎቶ ያነሳኋት በእኔ ሳይሆን በእምነት
ስልክ ነበር።
አንድ አሮጊት "ተሰበረች?" አሉ ወደ ኢክራም እየመጡ።
"የሚሰብር ነገር ይስበሮት!" አለ ብሩኬ በንዴት። አንዳንዴ ሰዎች
የሚጠይቁትን ጥያቄ በአግባቡ አያዉቁም። የታመመ ሰዉ
"ተሻለዉ ወይ" ተብሎ እንጂ "ሞተ ይሆን?" ተብሎ አይጠየቅም።
ሴትየዋም ኢክሩን "እግሯ ከጉድጓዱ ወጣላት?" ብለዉ
እንደመጠየቅ "ተሰበረች?" ብለዉ መጠየቃቸዉ አግባብ
አልነበረም። ግን የዛን ቀን እኔ ስሜታዊ ያልሆንኩትን ያህል
ብሩኬ እንደዛ መቆጣቱ ገርሞኛል። ለነገሩ እኔ ምክንያታዊ
ክርክር እንጂ ቧልታዊ ምልልስ ሲጀመርም አልወድም።
በስንት መከራ የኢክሩ እግር ከትቦዉ ዉስጥ ወጣ። አካባቢዉ
ላይ ከነበረ ቤት ዉሀ ጠይቀን ኢክሩ ተጣጠበች። ዘንቦ ስለነበር
ትንሽ ጭቃ ነክቷት ነበር። የዛን ቀን ብሩኬ ላደረገዉ ነገር
ምስጋና ይገባዋል። በጣም ነበር ሲሯሯጥ የነበረዉ።
.
ከዛ ሁሉ ጭንቅ በኋላ የኢኩዬ እግር በሰላም ወጥቶ መንገድ
እንደጀመርን እኔ ስትወጣ አይታዉ ዘና ትልበትና እናጠፋዋለን
ብዬ አስቤ በእምነት ስልክ ያነሳኋትን ጉድጓዱ ዉስጥ እግሯ
እያለ የሚያሳይ ፎቶ አሳየኋት። አይታዉ ፈገግ አለች!! ልናጠፋዉ
ስንል ግን እምነት በፍፁም አይሆንም አለች። ስልኳ የሚስጥር
ቁጥር ስለሚጠይቅ ያለ እምነት ይሁንታ ማጥፋት አይቻልም።
ነገሩ ከቁጥጥሬ ዉስጥ እንደወጣ ተረዳሁ። ኢክሩ በጣም
እንዳዘነችብኝ ገብቶኛል። እኔ ግን ፎቶዉን ያነሳሁት የኢኩ ፊት
ላይ ፈገግታ ለመፍጠር ነበር። እምነት ሁሉንም ነገር
አበላሸችዉ።
በነጋታዉ ከእምነት ጋር ቤተ መፅሀፍ ስንገናኝ ሰበብ ፈልጌ
የስልኳን የሚስጥር ቁልፍ እንድትከፍትልኝ ጠየቅኳት።
ከፈተችልኝ። ወዲያዉ በፍጥነት ትናንት ያነሳሁትን ፎቶ ከእምነት
ስልክ ላይ አጠፋሁት። እምነት ስልኳን ስመልስላት ወዲያዉ ፎቶ
ዉስጥ ገብታ ምስሉን ማጥፋቴን አይታ ሳቀች።
"ፈዊ እንደምታጠፋዉ አዉቅ ነበር!!" አለችኝ እየሳቀች!
"አሁን እንዴት ቀለል እንዳለኝ ብታዉቂ ከምር ጨንቆኝ ነበር!!"
አልኳት
ሳቋን መቆጣጠር እያቃታት "አይቅለልህ እንደምታጠፋዉ
ስለገመትኩ ኮፒ አድርጌ ሌላ ቦታ ላይ አስቀምጨዋለሁ። ፒሲ
ላይ ሳይቀር አለ።" አለችኝ።
ሌላ ሰዉ ቢሆን እጣላዉ ነበር ግን እምነት ስለሆነች ምንም
ማድረግ አልቻልኩም። ዉስጧ ምንም ክፋት ኖሮ አይደለም
እንዲህ ያደረገችዉ።
.
በቀጣይ ከኢኩ ጋር ቤተ መፅሀፍ መጥታ ስንገናኝ ሁሉም ነገር
ከቁጥጥሬ ዉጪ ሆኖ እንደሆነ ለማስረዳት ሞክሬ ስለፎቶዉ
ይቅርታ ጠየቅኳት። ኢክራም ግን ከላዩ ይቅርታ ብታደርግልኝም
በዉስጧ እንዳዘነችብኝ ያሳብቃል።
ያደረግኩት ነገር በራሱ ትክክል አይደለም። ያደረግኩትን ነገር
ትክክል የሚያደርገዉ ያደረግኩበት ምክንያት ነበር። ኢክሩ ፊት
ላይ ፈገግታ መፍጠር። ግን ሁሉም ነገር ከቁጥጥሬ ዉጪ ሆኖ
ኢክሩ ፊት ላይ ፈገግታ ይፈጥራል ብዬ የሰራሁት ስራ በእምነት
ምክንያት ኢክሩ ፊት ላይ ሀዘን ፈጠረ።
አላማዬ ለመልካም የነበረ ቢሆንም ዉጤቱ መጥፎ ሆኖ
ስላረፈዉ ይቅርታ ከመጠየቅ ዉጪ አማራጭ የለኝም። ይቅርታ
የማያሽረዉ በሽታ የለም!! እምነቴ ነዉ!!
.
ኢክራም ከነዚህ ቀናት በኋላ ከእኔ ጋር ያላት ግንኙነት እየቀዘቀዘ
መጣ። የሚያገናኙንም ምክንያቶች ጠፉ። እኔም እሷ
እየቀዘቀዘች ስትሄድ በጣሙን እየቀዘቀዝኩ መጣሁ።
በዚህ መሀል አንድ የግቢ ጓደኛዬ ሁለት ቆንጅዬ የግቢ
ተማሪዎች ሊተዋወቁኝ እንደሚፈልጉ ነገረኝ። በቁንጅናቸዉ
ከግቢያቸዉ ተነጥለዉ የሚታወቁ ናቸዉ። እነሱ የአምስት ኪሎ
ግቢ ተማሪዎች ሲሆኑ እኔ ደግሞ የስድስት ኪሎ ግቢ ተማሪ
ነኝ። የቆንጆዎች መናኸሪያ የሆነዉ የአምስት ኪሎ ግቢ ዉስጥ
በቁንጅና መታወቃቸዉ ምን ያህል ቆንጆ ቢሆኑ እንደሆነ ግልፅ
ነዉ። ለጊዜዉ ስለማይመቸኝ ከአንድ ሳምንት በኋላ
እንደማገኛቸዉ ነገርኩት።
.
ኢክሩ እኔ ጋር አትደዉልም ግን ብሩኬ ጋር ትደዉላለች። እሱም
ይደዉልላታል።
አንድ ቀን እነ ብሩኬ ቤት ሆነን ብሩኬ ኢኩን ችላ ሳይል
እንዲያማክራት አደራ አልኩት። እሱም አደራዉን ተቀበለ።
ኢክራም ወደ ትዳር ህይወት እንድትገባ ብዬ እንደተዉኳት
ያዉቃል። ስለዚህ ከማንም ጋር እንዳትንዘላዘል መምከር
አያቅተዉም ብዬ አስባለሁ።
.
በቀጣዩ ሳምንት ልጆቹን ለመተዋወቅ ወደ ተቀጣጠርንበት
ከስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ዋናዉ በር ፊት ለፊት ወዳለዉ መናፈሻ
ሄድኩ። ከአንድ ዛፍ ስር ያለ ወንበር ላይ የተቀመጠች ቀይ ሴት
እጇን አዉለበለበችልኝ። እኔ ሁለት ሴቶች እንደሚጠብቁኝ ነበር
የተነገረኝ።
"ፈዉዛን ዌልካም!!" አለችኝ ከመቀመጫዋ ተነስታ እንድቀመጥ
እየጋበዘችኝ።
"ሁለት ሰዉ እንደሚጠብቀኝ ነበር የተነገረኝ!!" አልኳት።
"አዎ ነዉ ግን ዛሬ ለምናወራዉ ነገር የሜሮን መኖር አስፈላጊ
ስላልሆነ ነዉ ብቻዬን የመጣሁት!!" አለችኝ።
"ባይዘዌይ ፊርደዉስ እባላለሁ!!" አለች የአክብሮት ፈገግታ
እያሳየችኝ።
አየኋት በጣም ቆንጆ ናት! በጣም!! ከኢክሩ ሌላ ቆንጆ ነበር
እንዴ? የእዉነት በጣም ዉብ ናት። የለበሰችዉ ቀሚስ ሰፋ ያለ
ነዉ። አይጨንቅም!! በጣም ልብሱን አሳምራዋለች።
"እና እንደዚህ ዉብ ሆነሽ ፊርደዉስ ካላሉ ምን ብለዉ ስም
ሊያወጡልሽ ነበር?" አልኳት እየሳቅኩ!
ፊርደዉስ ሳቋን ለቀቀችዉ!! ጉንጯ ላይ ስርጉድ አለ። ወይኔ በቃ
ይህቺ ልጅ ልቤን ልታሰረጉደዉ ነዉ።
ፊርደዉስ ከጀነት በጣም ያማረዉ ጀነት ነዉ። ጀነት እንደሆቴል
ባለ4 ባለ5 ኮከብ እንደምንለዉ ይለያያል። ሰው እንደስራዉ
ምርጡ ላይ ይገባል። ስሟ እና ዉበቷ በጣም የተስማማ ነዉ።
ፊርደዉስ ስቃ ስትጨርስ "ፈዉዛን መንገድ ላይ ነበር ያየሁህ!
ከዛም ከሰዎች ስላንተ አንዳንድ መረጃዎችን አገኘሁ!!" አለችኝ።
ፈገግ አለችና እጇን እየዘረጋችልኝ ያዘዉ አለችኝ። ይሄ ነገር
ወዴት ወዴት እየሄደ እንደሆነ ግራ ገባኝ።
"ይቅርታ ሴት አልጨብጥም!!" አልኳት
"ለምን?" አለችኝ
የእዉነት የእስልምና እምነት ተከታይ አልመስልህ አለችኝ።
ሙስሊም ሆና ይህን አለማወቋ አሳዘነኝ።
"ቁርዓን ላይ ማን ማንን መንካት እንደተፈቀደልሽ ተፅፏል
አንብቢዉ!!" አልኳት።
"እሺ ለዛሬ ብቻ ጨብጠኝ!!" አለችኝ በአይኖቿ
እየተለማመጠችኝ። አለንጋ ጣቶቿን ፊቴ ድረስ አስጠጋቻቸዉ።
የአይኗን እንቅስቃሴ በሚገባ አጤንኩት ይዞር ይዞርና ወደ ግራ
እየሰረቀ ያያል። የስነ አእምሮ ተማሪ እንደመሆኔ በግራ በኩል
የሚያየን ሰዉ እንዳለ ገመትኩ። ዞር ስል አንዲት ሴት የስልኳን
ካሜራ አነጣጥራ እየቀረፀችን ነዉ።
.
ያላየሁ መስዬ
"ፊርደዉስ ሪያሊቲ ሾዉ ለመስራት አስበሽ ነዉ እንዴ የጠራሽኝ?"
አልኳት
ወዲያዉ እንደባነንኩ ስለገባት ጓደኛዋ መቅረፅ እንድታቆም
በእጇ ምልክት ሰጠቻት።

.....ይቀጥላል...
👍 5
∞∞ግራ ገባኝ🤔

ግራ ገባኝ እኔ ምጠይቀው አጣሁ
ለምን ብዬ አልልም ምላሹን ካገኘሁ
ስጨነቅ ሚ'ጨንቀው ስከፋ ሚ'ከፋው
ደስታዬ ሀሴቱ ጮቤ እሚያስረግጠው
መታመሜን አይቶ ህመም እሚሸከመው
ስለሚያፈቅረኝ ነው ይህንን አውቃለው

ግና ግራ የገባኝ የጠፋኝ ትርጉሙ
ተስፋዬ ሲሟጠጥ ሚሰበር ቅስሙ
እኔ የሆንኩትን በአንድ ለሊት ጀንበር
እሱም ሲፈፅመው በዛች አንድ ቀትር
እውነት ክፋዬ ነው የአጥንቱ ፍላጭ ነኝ?
ወይስ መንታ ወንድሜ ፍፁም ግራ ገባኝ?

✍ፀሀፊ~ ፊያሜታ

@Ye_Hagere_Wegoch_2
@Ye_Hagere_Wegoch_2
👍 2
❤ 1
መጣች።ከኢክሩ ጋር አስተዋዉቄያቸዉ ስለነበር
ምንም አላለችም። እንደዉም ከእምነት ጋር ጥሩ ወዳጅ
ሆነዋል። እንዴት እንደሆነ ባላዉቅም ብሩኬ ቤተ መፅሀፍ መጥቶ
ተቀላቀለን። እያጠናም አልነበረም። ሰዓቱ ሲገፋ ወደ ቤታችን
ለመመለስ መንገድ ጀመርን። እምነትን እና ኢክራምን ሸኝተን
እኛ ወደየቤታችን ለመመለስ ነበር ያሰብነዉ። መንገድ ላይ
እየሄደን ኢክሩ እግሯ ትቦ ለመሸፈን የተደረጉ አርማታዎች
መካከል ሾልኮ ገባ። ለማዉጣት ስትሞክር በፍፁኝ እግሯ
አልወጣም አላት!!
.
.....ይቀጥላል...

@Ye_Hagere_Wegoch_2
@Ye_Hagere_Wegoch_2
⬜ነጫጭ ጥቁረቶች⬛
#ክፍል አስራ ሦስት
.
ወደ ሰፈር ከመመለሴ በፊት አንድ የማላዉቀዉ ስልክ
ተደወለልኝ።
"አቤት!!" አልኩ ስልኩን አንስቼ!! አንዲት ሴት እንደ ሙዚቃ
በሚሰረቀረቅ ዉብ ድምፅ "ፈዉዛን ነህ አይደል?" አለችኝ።
ድምፁ አዲስ ስለሆነብኝ ግራ እየተጋባሁ "አዎ ነኝ ምን
ልታዘዝ?" አልኩ።
ልጅቷ ኢክራም የምትመራዉ ሀይማኖታዊ ማህበር ዉስጥ የስነ
ፅሁፍ ዘርፍ ላይ እንደምትሰራ እና መፅሔት ለማዘጋጀት
እየሞከሩ ስለሆነ እንዳግዛቸዉ ዘፈነችልኝ። (የልጅቷ ድምፅ
ከመስረቅረቁ የተነሳ ተናገረች ማለት ስለሚከብደኝ ነዉ
ዘፈነችልኝ ያልኩት)
እኔም ወደ ሰፈር ስመለስ ላገኛቸዉ ለጁምዓ(አርብ)
ተቀጣጠርን።

ጁምዓ(አርብ) ዕለት ከደወለችልኝ ልጅ ጋር ሰፈር መስጂድ
ዉስጥ በመካከላችን መጋረጃ ተጋርዶ በአካል አወራን።
አልተያየንም!! አብረዋት ሁለት ልጆች ነበሩ። ወንድና ሴት
ዉይይት ሲያስፈልግ ሁሌም እንዲህ ነዉ የሚደረገዉ መጋረጃ
ተጋርዶ እንወያያለን። ይሄ የሚደረገዉ ሀራም(ክልክል) ፆታዊ
መፈላለጎችን ለመታደግ ነዉ።
ልጅቷ ስሟ ሱመያ ነዉ። ድምጿ በጣም ያምራል። በምችለዉ
ሁሉ ላግዛት እና ስለስራዉ በስልክ እየተደዋወልን ለመነጋገር
ተስማምተን ተለያየን።
ሱመያ ገና ከዛዉ ቀን ጀምሮ ፌስቡክ ላይ ስለብዙ ነገሮች
ታማክረኝ ጀመር። ምናለ ታይፕ ተደርገዉ የተላኩ ሚሴጆችን
በፀሀፊዉ ድምፅ የሚያነብ ማሽን በኖረ!! የሱመያን መልዕክቶች
በሷ ድምፅ እሰማበት ነበር። የፈጣሪ ያለህ የሰዉ ድምፅ እንዲህ
ይስረቀረቃል? የሷ በጣም ይለያል።
.
በነጋታዉ ቅዳሜ ኢክሩ ደዉላ የምንገናኝበትን ሰዓት ተነጋገርን።
ሰዓቱ ሲደርስ መንገድ ላይ ተገናኝተን ወደዚህ ካፌ መጣን።
ኢክሩ ጥቁር ሰማያዊ ጅልባብ ለብሳለች። ረሂማ መጥታ
ከታዘዘችን በኋላ ኢክሩ አይኔን ትኩር ብላ እያየችኝ "ፈዉዛኔ ግን
ምንም የአቋም ፅናት የለህም።" አለችኝ። እዉነቷን ነዉ አንድ
ነገር ላይ ለረዥም ጊዜ በፅናት መቆም ይከብደኛል። አሁንም
ከሷ ጋር በፍቅር ግንኙነት ዉስጥ ለመቆየት ከጌታዬ ጋር
የምጋፋበት ፅናት አጥቻለሁ።
እየሳቅኩ "ኢክሩ ልክ ነሽ" አልኳት።
አሁን ከኢክራም እየተረዳሁ ያለሁት ግን ከዚህ ቀደም
በመካከላችን ያለዉን ግንኙነት የጠላት አናስመስለዉ ማለቴን
እንደገና ወደፍቅር ህይወት እንመለስ ለማለት እንዳሰብኩ
አድርጋ ነዉ የተረጎመችዉ። በፍቅር አብረዉት ከነበሩት ልጅ ጋር
ወንድም ሆኖ መቀጠል ይከብዳል። ኢክሩ እኔን ወንድም ብሎ
መቀበል ከብዷታል። እንዴት አይክበዳት? ስንቱን አብረን
አሳልፈናል እኮ!! ትዳር ተወድዶ ጉድ አደረገን። ማህበረሰባችን
የትዳርን ዋጋ አስወድዶ የዝሙትን ዋጋ አርክሶንብን ተቸገርን!!
ወሬ ለመቀየር ያህል "ሱመያ የምትባል ልጅ ከናንተ ጀመዓ
(ህብረት) አናግራኝ ነበር።" አልኳት።
እየሳቀች "እኔ ነኝ እንዲያናግሩህ የጠቆምኳቸዉ!!" አለችኝ።
እኔም ሳቋ ተጋባብኝ!! ከዛ ደግሞ አሳዘነችኝ።
ኢክሩ ነገረ ስራዋ ሁሉ ግራ ያጋባል።
.
ኢኩ ለሷ ጥላቻ እንዳለኝ መጠርጠር ሳትጀምር አትቀርም።
በስልክ ስናወራ እየጮህክብኝ ነዉ ፣ ተቆጣኸኝ ምናምን የሚሉ
ሰበቦችን እየፈለገች ታኮርፋለች። የሚንቃትን ፈዉዛንን እና
ኩርፊያዉን እራሷ በጠርጣሪዉ ጭንቅላቷ ትፈበርካለች። እኔ
እንዴት ኢክሩን እጠላታለሁ? የማይመስል ነዉ።
የዛን ቀን ጉዳያችንን እንደጨረስን ወደ ቤቷ ሸኝቼያት ተመለስኩ።
ከዚህ ቀን በኋላ ከኢክራም ጋር በስልክም በአካልም ያለን
ግንኙነት እየቀዘቀዘ መጣ። እኔ ፍቅረኛ የሚባለዉን ታፔላ
ብታነሳልኝ ከጎኗ ሆኜ እንደወንድም ላማክራት ፈቃደኛ ነበርኩ።
እሷ ግን የፈለገች አይመስለኝም።
.
ከነሱመያ ጋር በቀጣይ ልንገናኝ ስንቀጣጠር ከመስጂድ ዉጪ
ስለነበር ከብሩክ ጋር አብረን ሄድን። አንድ ሙሉ የቆንጆ ቡድን
ከተቀጣጠርንበት ህንፃ ስር ቆሞ ጠበቀን። አራት ነበሩ። ሱመያ
የትኛዋ እንደሆነች አላዉቅም። ወደኔ ቀረብ ሲሉ አንደኛዋ ቀደም
እያለች ስትመራቸዉ እሷ መሆኗን ገመትኩ። ከአራቱ ዉስጥ
አንደኛዋ በጣም ነበር የምታምረዉ!! በጣም!! ሲጀመር ሁሉም
ቆንጆ ነበሩ።
ሱመያ እንደሆነች የገመትኳት ልጅ ፈገግ ብላ አንድ ደብተር
እየሰጠችኝ "ሁሉንም እዚህ ላይ ፅፈነዋል እየዉና አስተያየትህን
ትሰጠናለህ!!" ብላ ሞዘቀች!! ሱመያ ነበረች። ድምጿ ሲስረቀረቅ
ነበር የለየኋት።
ብሩኬ እኔ ከሱመያ ጋር ሳወራ እሱ አብራት ያለችዉን ቆንጅዬ
ልጅ እየተመለከተ ተቁነጠነጠ። ደብተሩን ተቀብያቸዉ ገና ዞር
እንዳሉ ብሩኬ ደብተሩን ቀምቶኝ ሮጠ።
ነገረ ስራዉ ሁሉ ስለገባኝ "ብሩኬ አይሆንም!!" እያልኩ
ተከተልኩት። ደብተሩ ላይ ስልክ ቁጥሮችን ስላየ ነበር ነጥቆኝ
የሮጠዉ።
ብሩኬ ስልክ ቁጥሩን ስልኩ ላይ ለመመዝገብ አስፓልት ተሻግሮ
ሮጠ። ተከተልኩት። ረዥም መንገድ ተሯሯጥን። እኔ በሀይማኖት
ጉዳይ ምክንያት ሴቶች የሰጡኝን የግል መረጃ አሳልፌ መስጠት
አልፈልግም። በሀይማኖት ጉዳይ ተገናኝቶ ፈጣሪን የሚያምፅ
ነገር መፈብረክ ያስጠላል። አንዳንዶች ሀይማኖታዊ ህብረቶችን
ሲቀላቀሉ ቁጥብ እና ቆንጆ የሆኑ ልጆችን ለማጥመድ ነዉ።
ለነገሩ ሁሉም የሀሳቡን ያገኛል። ቆንጆ የፈለገዉ ቆንጆ ፣
የቆንጆዎች ካዝና ባለቤት የሆነዉን ፈጣሪዉን የፈለገ ደግሞ
ፈጣሪዉን!! ለዛ ነዉ ከብሩኬ ጋር እንዲህ የተሯሯጥነዉ።
አለማዊ ሽኩቻዉ ሰልችቷቸዉ መስጂድ የመጡትን ልጆች
ወደማይፈልጉት ጉዳይ ዉስጥ እንዲገቡ መሳሪያ ላለመሆን!! ግን
ብሩኬ ስልክ ቁጥሩ ያለበትን ገፅ ቀድዶ ወሰደዉ።
በኋላ ላይ ሳጣራ ብሩክ የሻፈደባት ልጅ ስም ኢማን ነበር። በኋላ
ላይ ከኔ የወሰደዉ ስልክ ትክክለኛ አለመሆኑን ሲያዉቅ ኢክራምን
እንድትሰጠዉ ለመናት። ኢክራም መጀመሪያ ላይ እኔ ባለሁበት
ሲጠይቃት አልሰጥህም አለችዉ። በኋላ ላይ ግን ሲያኮርፈኝ
ጨነቀኝ ምናምን ብላ ስልኳን ሰጠችዉ። የመጀመሪያ ቀንም
ያልሰጠችዉ እኔ ስለነበርኩና አቋሜን ስለምታዉቅ ላለመጠቆር
ይመስለኛል።
.
አንድ ቀን ከሱመያ ጋር ቻት እያደረግን ሁዳ የምትባል ልጅ አዉቅ
እንደሆነ ጠየቀችኝ። እኔ ማዉቃት ሁዳ ቤተ መፅሀፍ አብረን
የምናነብ የነበረችዉን ቀጮዋን ሁዳ እንደሆነ ነገርኳት። እህቷ
እንደሆነች ነገረችኝ። ገረመኝ በፍፁም አይመሳሰሉም።
መልካቸዉም ድምፃቸዉም ፈፅሞ አይመሳሰልም ነበር። ሱመያ
የሁዳ እህት መሆኗን ካወቅኩ በኋላ በመካከላችን ያለዉ
ግንኙነት እየጠነከረ ሄደ።
.
ብሩክ ሴት ማሯሯጥ ላይ በጣም በርትቷል። ከሪሀና ጋር በአንዴ
ከነፉ ከሷ ጋር ሲደባበሩ ይኸዉ ኢማንን ለመጀንጀን ይሞክራል።
ለነገሩ ኢማን ፊትም አልሰጠችዉም። አልሰማህኝ አለችው። እኔ
የስነ አእምሮ እዉቀቴ ከፍ እያለ ሲመጣ ሰዎችን እንደድሮዉ
በግርድፉ ማዳመጥ አቆምኩ። በንግግራቸዉ ዉስጥ
ስሜታቸዉን እከታተላለሁ፣ በሰዉነት እንቅስቃሴያቸዉ ብቻ
የደበቁትን እረዳለሁ። የተለየ የእይታ ምህዳር ፈጠሩልኝ።
.
ጊዜዉ የፈተና ወቅት የደረሰበት ስለነበር እና ሰፈር ስለነበርኩ
ከሰፈራችን ቤተ መፅሀፍ አልጠፋም ነበር። የረዊና እህት
እምነትም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ስለደረሰ አብራኝ ቤተ
መፅሀፍ መዋል ጀመርን። እምነት በጣም ደስ የምትል ልጅ ናት።
ብሩኬ ሊጀነጅናት ፈልጎ አይሆንም ብዬዋለሁ። የረዊና አደራ
ስላለብኝ እና ብሩኬም በኔ ምክንያት ስለተዋወቃት አርፎ
እንዲቀመጥ ነግሬዉ እሺ አለኝ። ጓደኝነት ለኔ ከአንድ ብቻ
ሳይሆን ከብዙ አቅጣጫ የሚታይ ነገር ነዉ። ረዊናም እንደ ብሩክ
ጓደኛዬ ናትና አደራዋን መጠበቅ ይኖርብኛል። አደራዉ እምነትን
ያልሆነ ነገር ዉስጥ ከመግባት መታደግ ነዉ።
.
አንድ ቀን አስራአንድ ሰዓት አካባቢ እኔናእምነት ቤተ መፅሀፍ
እያነበብን ኢክሩ
👎 1
⬜ነጫጭ ጥቁረቶች⬛
#ክፍል አስራ ሁለት

.
ካምፓስ ገብቼ ሁለተኛዉ የትምህርት ዘመን አጋማሽ ተጀምሯል።
ብሩኬ ጊዜዉን ፊልም በማየት ያሳልፋል። እኔ የላላዉን
ሀይማኖቴ ላይ የነበረኝን አቋም ለማስተካከል እየሞከርኩ ነዉ።
ከኢክሩ ጋር ከሁለቱ ቀናት በኋላ ድጋሚ ተሳስመን አናዉቅም።
አንነካካም!! እናወራለን!! ስለ ጋብቻ እናልምና እንለያያለን!!
አለቀ።
ቀኑ ሀሙስ ነበር። ከ6ኪሎ ካምፓስ ታክሲ ይዤ ወደ ፒያሳ
ሄድኩ። ወደ መስጂደ ኑር!! ይሄ መስጂድ በተለምዶ በኒ
መስጂድ ይባላል። መስጂዱ ዉስጥ ገብቼ ከመድረኩ
የሚሰጠዉን ትምህርት መከታተል ጀመርኩ። የመስጂዱ ግርማ
ሞገስ የሆኑት ሸህ ኡመር ኢድሪስ የቁርዓንን ትርጉም
ይተነትናሉ። ከቁርዓኑ እየተተነተነ የነበረዉ አንቀፅ የዩሱፍ(ዮሴፍ)
ምዕራፍ ነበር። ይህ ምዕራፍ የዩሱፍን ታሪክ በሰፊዉ ይተርካል።
ዩሱፍ በወንድሞቹ የዉሀ ጉድጓድ ዉስጥ ከተጣለ በኋላ
ነጋዴዎች አግኝተዉት ለአንድ የምስር(ግብፅ) ባለስልጣን
ይሸጡታል። ይህ የገዛዉም ሰዉ ዩሱፍን ለሚስቱ በስጦታ መልክ
ያበረክትላታል። ዩሱፍ በጣም ቆንጆ ከመሆኑ የተነሳ የባለስልጣኑ
ሚስት ለነፍሷ ትመኘዋለች። ከዚህ ዉብ ፍጥረት ጋር አለሟን
መቅጨት ያምራታል። ዩሱፍንም በሮቿን ሁሉ ዘጋግታ ለሱ
እንደተዘጋጀችለት እና አብሯት የስጋ ጥሙን እንዲያረካ
ትጋብዘዋለች። ዩሱፍ ግን ጥሪዉን ገፍቶ አልቀበልም ይላል።
የባለስልጣኑ ሚስት እልህ ግን ዩሱፍን ከእርሷ ጋር ከመተኛት
አሊያም ከመታሰር የሚያስመርጥበት ደረጃ ላይ ይደርሳል።

ሸይኹም(መምህሩም) ትኩረት ሰጥተዉ እየተነተኑት ያለዉ ቦታ
ይሄ ነዉ። ዩሱፍ ከመታሰር እና ጌታዉን ከማመፅ ምርጫ
ሲቀርብለት የተናገረዉን ንግግር ሸይኹ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ
"ዩሱፍ ሴቲቱ የዚህ አይነት አጣብቂኝ ዉስጥ ስትከታቸዉ
እንዲህ ብለዉ ጌታቸዉን ለመኑ 'ጌታዬ ሆይ በርሱ ከሚጠሩኝ
ነገር (ከዝሙት) ይልቅ መታሰር ለኔ የተወደደ ነዉ።
ተንኮላቸዉንም ከኔ ላይ ባትመልስልኝ ወደነሱ እዘነበላለሁ ፣
ከስህተተኞችም እሆናለሁ።' አለ። አላህም ፀሎቱን ተቀበለዉና
ታሰረ።"
ከዚህ በላይ ማዳመጡ ከበደኝ ከኢክራም ጋር ያሳለፍኳቸዉ
ሁለቱ ቀናት ትዝ አሉኝ።በጋብቻ ያልተሳሰርኳትን ኢክራምን ከንፈር
የሳምኩባቸዉ ፣ የተከለከልኩትን የአካሏን ክፍሎች የነካሁባቸዉ
ሁለት ቀናት!!
እኔ ጌታዬን ለማመፅ እቅድ አዉጥቼ ተገበርኩ። ዩሱፍ ግን
ማንም ሰዉ በሌለበት ሊያዉም ከባለስልጣን ሚስት የደረሰዉን
የእንተኛ ጥያቄ ገፋዉ ፤ ጌታዉንም ላለማመፅ ሲል ታሰረ።
ዛሬ ሁሉም ነገር ግልፅ ሆኖ ይታየኝ ጀመር። እኔ አሁን ገና
የካምፓስ ተማሪ ነኝ። ኢክራምን ለማግባት የቁስም ሆነ የስነ
ልቦና ዝግጅቱ የለኝም። የኢክራምን ዉድ የወጣትነት እድሜ
እያባከንኩባት ነዉ፤ ጌታዬንም እያስቆጣሁት ነዉ። መጃጃሉ
ይበቃል! ከኢክሩ ጋር እዉነቷን ተነጋግሮ መለያየት ይሻላል!! ግን
የዛን ቀን ለራሴ አንድ ቃል ገባሁ። እኔ የስነ ልቦናም ሆነ የቁስ
ዝግጅቴ ለጋብቻ ብቁ ሲሆን የፈለጉ አመታት ቢነጉዱ እንኳ
ኢክራምን ፈልጌ ካላገባች እሷኑ ላገባ። አዎ በፍቅር
የሰከርኩላትን ፣ ከማንም በላይ የማዝንላትን ኢኩዬን
ለማግባት!!
.
ከስድስት ኪሎ ወደ ፒያሳ ተሳፍሬ ሄጄ የሰማሁት ነገር አቋሜን
ለዉጦት ወደ ስድስት ኪሎ ተመለስኩ።
አሁን ለኢክራም እንዴት ማስረዳት እንደምችል አሰብኩ።
መጀመሪያ እኔ ከሷ ጋር ግንኙነቴን ለማቆም ምክንያት የሆኑኙን
ሁለት ነገሮችን አሰብኩ። ጌታዬን እያስቆጣሁ መሆኑና ኢክሩ
ከእኔ ጋር በመሆኗ ምክንያት አለማግባቷ ናቸዉ። ከኔ ጋር ፍቅር
የሚሉትን እቃቃ ባትጀምር ኖሮ የማግባት እድሏ ሰፊ ነበር። የሷ
ማግባት ደግሞ ለቤተሰቦቿም ጥቅም አለዉ።
ኢክራምን በምክንያት ለማስረዳት ከሞከርኩ እኔዉ ራሴ ከዚህ
በፊት ባስጠናኋት የቃላት ድርደራዎች ልትረታኝ ትችላለች።
ስለዚህ አዲስ ስልት መጠቀም ነበረብኝ። ኢክራምን
እንድትጠላኝ ቢያደርጋትም እንኳ ግንኙነታችንን ለማቋረጥ
እንደሚረዳ አሰብኩ። አዎን ዉጤታማ መንገድ አቀድኩ!!
ለበጎዉም ለመጥፎዉም የማቀድ በሽታ አለብኝ።
.
ኢክሩ ፌስቡክ ላይ ስትፅፍልኝም እንደድሮዉ ትኩረት ሰጥቼ
አላወራት አልኩ። የሳምንቱ የትምህርት የመጨረሻ ቀን ጁምዓ
(አርብ) ሲደርስ ከስድስት ኪሎ ዶርም ወደ ሰፈር ተመለስኩ።
በነገራችን ላይ ከዶርም ወደ ቤት የምመለስበት ዋነኛዉ
ምክንያት ቤተሰቦቼ ናፍቀዉኝ ሳይሆን ኢክራምን ለማግኘት
ነበር። እሷ ሰሞኑን ብዙም በስልክም ስላልተገናኘን ናፍቄያት
ነበር። ደዉላ የምንገናኝበትን ሰዓት ጠየቀችኝ ፤ነገርኳት። አሁን
ልቤ ለአንድ አመት ያክል አብሬያት የነበረችዉን ልጅ ይብቃን
ለማለት ያለዉን ጥንካሬ ሁሉ እየሰበሰበ ነዉ። በቃ ከእዉነታዉ
ጋር መጋፈጥ አለብኝ!!
.
ሰዓቱ ሲደርስ ከኢክሩ ጋር ወደኛ ሰፈር የሚያስገባዉ መንገድ
ጋር ተገናኘን። ኢክሩ ዛሬ ጅልባብ ለብሳ ነዉ የመጣችዉ።
ጅልባብ ማለት ሙስሊም ሴቶች የሚለብሱት ፊትንና እጅን ብቻ
የሚያሳይ ልብስ ነዉ። የሰዉነታቸዉን ቅርፅ በፍፁም አያሳይም።
ሰፊ ነዉ። ኢክሩን በጅልባብ ሳያት ደስ አለኝ። በጅልባብ ደግሞ
በጣም ነዉ የምታምረዉ። ይሄ ፈገግታ ፣ ይሄ ዉበት ላይ ነዉ
ጨክኜ ፣ ከፈገግታዋናዉበቷ ዘላቂ ደስታዋን እና የጌታዬን ክብር
መርጬ በቃን ልላት የወሰንኩት።
ልክ አጠገቤ እንደደረሰች እንደተለመደዉ ከአጠገቤ ቆማ
"አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላህ" አለችኝ። የአላህ ሰላምና
እዝነት ባንተ ላይ ይሁን ማለት ነዉ።
"ወአለይኩሙሰላም ወራህመቱላህ" አልኳት።
ባንቺም ላይ የአላህ ሰላም እና እዝነት ይሁን ማለት ነዉ።
.
ሰላም ተባብለን ከጨረስን በኋላ ወዲያዉ እዛዉ እንደቆምን
ወደገደለዉ ለመግባት ፈለግኩ።
ፊቴን አጨፈገግኩ እና ትንፋሼን ዉጬ "ኢክሩዬ ለረዥም ጊዜ
አብረን ቆይተናል ግን ግንኙነታችን ወዳልሆነ መስመር እየወሰደን
ነዉ። ባለፈዉ ያደረግነዉን ታስታዉሻለሽ አይደል?(መሳሳሙን
ማለቴ ነበር) በዚህ ከቀጠልን ሌሎች ነገሮች ላይም ልንወድቅ
እንችላለን። ስለዚህ ከዚህ በኋላ ለዝሙት ካልሆነ በቀር ወደ እኔ
አትምጪ!!" አልኳት።
ኢክሩ ፊቷ ተቀያየረ ፣ አይኗ በእንባ ተሞላ ፣ ወዲያዉ በዉሸት
ፈገግታዋ እንባዋን ለማጨንገፍ ሞከረች።
"ኢክሩ መናገር የምትፈልጊዉ ነገር አለ?" አልኳት። ልቤ በጣም
ይመታል።
ትንሽ አየችኝና በአሉታ አንገቷን ነቀነቀችልኝ። በቆመችበት ትቻት
ሄድኩ!!
ንግግሬ በራሴ ጆሮ ላይ እየደጋገመ ያስተጋባል። "ለዝሙት
ካልሆነ በቀር ወደ እኔ አትምጪ" የኢክራምን እኔን ለመመለስ
የሚያስችሉ ሙከራዎች ሁሉ ለመክሸፍ የተጠቀምኳት ቃል
ነበረች።
.
እኔ ከኢክራም ጋር ስለያይ ምንም እንኳ ከዚህ በፊት አብረን
የነበርን እንደመሆናችን መልካም የሆነ ወንድማዊ ግንኙነት
እንዲኖረን እናድርግ ማለቴ እንጂ በደረስኩበት አትድረሺ ማለቴ
አልነበረም።
ኢክሩ ዉሳኔዬን ማክበሯን ፌስቡክ ላይ አንፍሬንድ ከማድረግ
ጀመረችዉ።
መንገድ ላይ ስታገኘኝ ባላየ ማለፍ ወይም ለሰላምታ ከብሩክ
ጋር ስሆን ብሩክን ብቻ ጠርታ ሰላም ማለት ጀመረች።
ነገሩ ምንም አልጥምህ ስላለኝ አግኝቼ ላናግራት ወሰንኩ።
ኢክሩ በጣም ልቧ ተሰብሯል ፤ አዝናብኛለች።
ልትረዳዉ ያልቻለችዉ ትልቅ ሀቅ አለ። እኔ ዛሬ ማንንም አይቼ
አይደለም ይብቃን ያልኳት። ግን እዉነቱን መቀበል ነበረብን።
እዉነቱ ደግሞ ድርጊታችን ጌታችንን የሚያስቆጣ ከመሆኑም ጋር
የኢክሩን እምቡጥ እድሜ የሚያባክን ነበር። ግን ከማንም በላይ
የምወዳት ሴት እሷ ነበረች።
.
ኢክራምን አግኝቼ በመካከላችን ያለዉ ግንኙነት የጠላት
እየመሰለ እንደሆነ እና እንድናስተካክለዉ ነገርኳት።
ኢክሩ በሂደት በመካከላችን...
👍 2

Найдено 21 пост