Телеграм канал 'WALTA TV'

WALTA TV


44'964 подписчиков
4'398 просмотров на пост

This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.

For more updates please visit https://www.facebook.com/wmcc

Детальная рекламная статистика будет доступна после прохождения простой процедуры регистрации


Что это дает?
  • Детальная аналитика 5'851'767 каналов
  • Доступ к 1'533'798'153 рекламных постов
  • Поиск по 5'773'112'708 постам
  • Отдача с каждой купленной рекламы
  • Графики динамики изменения показателей канала
  • Где и как размещался канал
  • Детальная статистика по подпискам и отпискам
Telemetr.me

Telemetr.me Подписаться

Аналитика телеграм-каналов - обновления инструмента, новости рынка.

Найдено 13598 постов

#አጀንዳ+
👉አሸባሪ መረጃዎች፣ ከፋፋይ ዜናዎች፣ አፍራሽ ፕሮፓጋንዳ በኢትዮጵያ እና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን ይዳስሳል

ዛሬ ምሽት 3:00 ሰዓት ይጠብቁን!
https://www.youtube.com/watch?v=Brdybxke900
👍 16
😢 2
Изображение
አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ ለአምስት ዓመታት ከአትሌቲክስ ውድድር ታገደች

ሚያዝያ 14/2016 (አዲስ ዋልታ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ የተከለከለ አበረታች መድኃኒት በመጠቀሟ ለአምስት ዓመታት ከአትሌቲክስ ውድድር ታገደች፡፡

አትሌቲክስ ኢንቴግሪቲ ዩኒት ይፋ ባደረገው መረጃ የ21 ዓመቷ የመካከለኛ ርቀት አትሌት ሁለት የተከለከሉ ንጥረ-ነገሮች መውሰዷን አምናለች ብሏል።

አትሌቷ ሦስት ጊዜ ምርመራ የተደረገላት ሲሆን በሁለቱ የተከለከለ አበረታች መድኃኒት መጠቀሟ ተረጋግጧል፡፡

የዓለም አትሌቲክስ አካል የሆነው አትሌቲክስ ኢንቴግሪቲ ዩኒት ባወጣው መግለጫ አትሌቷ ቴስቶስቴሮን የተባለውን እና ኢፒኦ የተሰኘውን አትሌቶች በደማቸው ውስጥ የበለጠ ኃይል እንዲያገኙ የሚያደርገውን ንጥረ ነገር መውሰዷን አምናለች ብሏል፡፡

ዋዳ የተሰኘው ዓለም አቀፉ የፀረ-አበረታች መድኃኒት ተቋም በ2023 ባወጣው ዝርዝር መሠረት አትሌቷ የወሰደችው ንጥረ-ነገር ሕግን የሚጥስ መሆኑ ተዘግቧል።

ከባለፈው ዓመት ኅዳር ወር ጀምሮ እገዳ ተጥሎባት ምርመራ ላይ የቆየች ሲሆን ዛሬ በይፋ መቀጣቷን አትሌቲክስ ኢንቴግሪቲ ዩኒት አስታውቋል፡፡

አትሌቷ ውሳኔውን በመቃወም ይግባኝ መጠየቅ እንደምትችልም በመግለጫው ላይ ተጠቁሟል፡፡

በሐብታሙ ገደቤ
👍 11
👏 3
😢 2
Изображение
ስለፕላስቲክ ብክለት መረጃዎች ምን ይላሉ?

#አዲስ_ዋልታ
👍 3
Изображение

60 ሺሕ ቻይናዊያንን ያፈናቀለው ከባድ ጎርፍ

ከሰሞኑ በተለያዩ ሀገራት የሚከሰቱ ኃይለኛ የጎርፍ አደጋዎች ሕይወት የሚቀጥፉ፣ ሃብትና ንብረት የሚያወድሙ በአጠቃላይ ከባድ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ሆነዋል። አውራ ጎዳናዎችና መኖሪያ ቤቶች በጎርፍ ተጥለቀለቁ የሚሉ ዜናዎች በተደጋጋሚ እየተሰሙ ነው። ይህን መሰል የጎርፍ አደጋ ዛሬ በቻይና ተከስቶ ዜጎችን ከቀያቸው አፈናቅሏል።

በቻይና ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት በሚስተዋልበት የጓንግዶንግ የባህር ዳርቻ ግዛት ለቀናት የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በተከሰተው ጎርፍ ወደ 60 ሺሕ የሚጠጉ ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸው መፈናቀላቸው ተሰምቷል። 11 ሰዎች የጠፉ ሲሆን እስካሁን በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት አለመድረሱ ተገልጿል።

በመንግስት ሚዲያዎች እና በበይነ መረብ ላይ የተሰራጩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በጎርፍ የተጥለቀለቀ ሰፊ መሬት ላይ የነፍስ አድን ሰራተኞች በጀልባዎች በጥልቅ እና ሰፊ ውሃ ላይ ሲንሳፈፉ ያሳያሉ።

ትላልቅ ወንዞች ሞልተው በዳርቻቸው ጎረፍ ይፈሳል። የሀገሪቱ የሚቲዎሮሎጂ ባለስልጣናት አደገኛውን ሁኔታ እና ከፍተኛውን የውሃ መጠን በቅርበት እየተከታተሉ መፍትሄ የሚሉትን ሁሉንም እየሞከሩ ናቸው ተብሏል።
ሙሉውን ለማንበብ ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ👇👇
https://shorturl.at/bsDNX

👍 9
ከአበባ የተሰራው የመጀመሪያው አልማዝ

ቻይና በዓለም የመጀመሪያ የሆነውን ከአበባ የተሰራ አልማዝ አበረከተች።

አልማዝ በተፈጥሮ ከሚገኙ እጅግ ውድ ማዕድናት መካከል አንዱ ነው፡፡ በተፈጥሮ ከሚገኙ ነገሮችም እጅግ ጠንካራው ነው፡፡ ይሁን እንጂ የቻይና ሳይንቲስቶች ፔኦኒ ከተሰኘ ቀይ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ በላብራቶሪ ውሰጥ ይህን በተፈጥሮ የሚገኝ ውድ ማዕድን መስራት መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡

ይህ አልማዝ ሎያንግ ታይም ፕሮሚስ የተሰኘ በቻይና ሎያንግ ከተማ ውሰጥ የሚገኝ ድርጅት የሰራው ሲሆን አልማዙን ከአበባው በሚገኝ የካርቦን ንጥረነገሮች በመጠቀም እንደተሰራ ገልጸዋል፡፡

አልማዙ ከከተማው የፔኦኒ አባባ ማእከል በተገኙ አበቦች የተሰራ ሲሆን ድርጅቱ የተሰራውን 3 ካራት አልማዝ መልሶ ለአበባ ማእከሉ አበርክቷል፡፡

የአምራች ድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አልማዙ 41 ሺሕ ዶላር የሚጠጋ ዋጋ እንዳለው ጠቅሰው አልማዙን ለማምረት ባዮ ጄኒክ ካርቦን ኤክስትራክሽን የተሰኘ ከፍተኛ ሙቀትና ግፊት የሚጠቀም ቴክኖሎጂ እንደሚጠቀሙ ገልጸዋል፡፡

ይህ በቴክኖሎጂ በመታገዝ የሚሰራ አልማዝ በተፈጥሮ ከሚገኘው አልማዝ ጋር በአካልና በኬሚካል ስሪታቸው አንድ አይነት ሲሆኑ የሚለዩትም በዋጋቸውና ለመሰራት በሚፈጁበት ጊዜ ነው ተብሏል፡፡

ሰው ሰራሽ አልማዞቹ በወራት የሚፈጠሩ ሲሆን በተፈጥሮ የሚገኝ አልማዝ ግን ለመፈጠር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዓመታትን ይፈጃሉ፡፡ በተጨማሪም በላብራቶሪ ውስጥ የሚሰሩት አልማዞች ዋጋቸው በተፈጥሮ ከሚገኙት አነስ ያለ ነው መባሉን ከብሪዚ ስክሮል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
👍 16
Изображение
ጀጎል የምስራቅ አፍሪካው አውራ ግንብ
#ሀገሬ

ሀገራችን ድንቅና ውብ የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ መስህቦች እንዲሁም ታሪካዊ ቅርሶችና ባህላዊ እሴቶች ባለቤት ናት። እነዚህ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች የውስጥና የውጭ ጎብኚዎችን ቀልብ በመግዛት ይታወቃሉ። ምርጥ የቱሪዝም መዳረሻ ከመሆን ባሻገርም የዓለም ቅርስ ሆነው የተመዘገቡ ብዙ ናቸው፡፡

ከእነዚህ የሀገራችን ውብ ቅርሶች በምሥራቁ የሀገራችን ክፍል የሚገኘው የጀጎል ግንብ አንዱ ሲሆን የግንባታው መሀንዲሶች በወቅቱ የነበሩ አባቶች ናቸው። የጀጎል ግንብ የሀረሪ ህዝብ የኪነ ህንፃ ችሎታውን የሚያስመሰክር የታሪክ እና የጥበብ ውጤትም ነው፡፡

የሀረር ከተማ መለያና የዓለም ቅርስ የሆነው የጀጎል ግንብ የተገነባው በ16ኛው ክፍለ ዘመን በአሚር ኑር ቢን ሙጃሂድ መሆኑን ታሪክ ያስረዳል።

ጀጎል በሀገር በቀል ዕውቅ የፈጠራ ባለቤቶች የተገነባ የሀገረሰብ ጥበብ ውጤት መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በዘመኑ አባቶች ያለምንም ቴክኖሎጂ እገዛ ነበር ግንቡን ያበጃጁት። ከፋብሪካ ውጤቶች ነፃ የሆነና በአካባቢያቸው የሚገኘውን ጥሬ ዕቃ በመጠቀም የገነቡት የዚህ ግንብ ቆይታው ደግሞ የአባቶችን የጥበብ ከፍታን ያሳየ ነው። በዘመኑ በምስራቅ አፍሪካ በግንብ የታጠረች የመጀመሪያዋ ድንቅ ከተማ ሀረር እንደሆነች መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የግንባታው ዓላማም ከተማዋን ከጠላት ለመከላከል እንደሆነ ይነገራል፡፡
👇👇
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid02VCyxBNeQPPKMBqs55dzGPXpj5j7YSUapF4h1uHe9Hjcdh2yQMPZx7PMT4KiFvtH8l
👍 8
👏 6
🙏 1
Изображение

በኬንያ በተካሄደው የ5 ሺሕ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች አሸነፉ

ሚያዝያ 13/2016 (አዲስ ዋልታ) ትላንት ማምሻውን በኬኒያ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ኮንቲኔንታል ቱር ጎልድ ውድድር  በ5 ሺሕ ሜትር በሁለቱም ፆታዎች  ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል።

በሴቶች የ5 ሺሕ ሜትር ውድድር አትሌት ማርታ አለማየው ርቀቱን 15 ደቂቃ ከ14 ሰከንድ ከ54 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በአንደኝነት ስትጨርስ፣ ለምለም ንብረት  15 ደቂቃ ከ20 ሰከንድ ከ99 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት ውድድሩን በመጨረስ 3ኛ ሆና አጠናቃለች። ሌላዋ አትሌት ሽቶ ጉሚ ውድድሩን በአራተኝነት አጠናቃለች።
 
በሌላ በኩል በወንዶች የ5 ሺሕ ሜትር ውድድር አብዲሳ ፈፍሳ ርቀቱን 13 ደቂቃ ከ34 ሰከንድ ከ77 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ አሸናፊ መሆኑን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

👍 33
👏 2
😢 1
Изображение

አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ በዲያመንድ ሊግ 1 ሺሕ 500 ሜትር ውድድር አሸነፈች

ሚያዚያ 12/2016 (አዲስ ዋልታ) በቻይና ዝያሜን እየተካሄደ ባለው ዲያመንድ ሊግ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ 3:50:30 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን ማሸነፍ ችላለች።

በተያያዘ የ2024 የዲያመንድ ሊግ ውድድር አትሌት ለሜቻ ግርማ በ5 ሺሕ ሜትር የሩጫ ውድድር አሸንፏል።

አትሌት ለሜቻ ግርማ በውድድሩ ርቀቱን በቀዳሚነት ለማጠናቀቅ 12:58.96 ስዓት ፈጅቶበታል።

ውድድሩ ለ6 ወራት የሚቆይ ሲሆን አራት አህጉራት በ15 ከተሞች የሚካሄድ ይሆናል።

👍 33
🙏 7
Изображение

የጉራጌ ሕዝብ በአንድነት ውስጥ የሚገኘውን ጸጋ ከሕይወት ልምዱ የተገነዘበ ነው - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ሚያዝያ 12/2016 (አዲስ ዋልታ) የጉራጌ ሕዝብ በአንድነት ውስጥ የሚገኘውን ጸጋ ከሕይወት ልምዱ የተገነዘበ ሕዝብ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

የለውጡን መንግስት የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር የጉራጌ ሕዝብ ስለአንድነት እና አብሮነት አበክሮ ያስተማረና በተግባር ያሳየ አንድነት ኃይል ነው ብሎ የሚያምን መሆኑን አንስተዋል።

ስለሰላም ሳናስብ፤ ስለሰላም ሳንናገር ሰላምን ልንጎናጸፍ አንችልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጉራጌ ስለሰላም የሚያስተምር፤ በሰላም የሚኖር ሰላምን የሚያስተጋባ ሕዝብ መሆኑንም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን ለመከፋፈል በየዕለቱ ገንዘባቸውን፣ ዕውቀታቸውንና ጉልበታቸውን ለሚያጠፉ ለአትዮጵያ ጠላቶች ጉራጌ አንድነት ኃይል ነው ብሎ ስለሚያምን ኢትዮጵያዊያን ከዚህ ልንማር ይገባል ብለዋል።

አክለውም የኢትዮጵያ አንድነትን ጠብቀን ለትውልድ ማሻገር እንድንችል ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

👍 35
👏 3
Изображение

በወልቂጤ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት እየተካሄደ ነው

ሚያዝያ 12/2016 (አዲስ ዋልታ) በርካታ የከተማው ነዋሪዎች የተሳተፉበት የለውጡን መንግስት የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

በድጋፍ ሰልፉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የፌደራል ፣የክልልና የዞን አመራሮች እንዲሁም የከተማው ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡

👍 22
👎 9
Изображение
ባለፉት 9 ወራት ከ2 ቢሊየን ብር በላይ በአስቸኳይ የሙስና መከላከል ስራ ማዳን መቻሉ ተገለጸ

ሚያዝያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) ባለፉት 9 ወራት 2 ቢሊየን 176 ሚሊየን 455 ሺሕ ብር በአስቸኳይ የሙስና መከላከል ስራ ማዳን መቻሉን የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።

ሀገር አቀፍ የፀረ ሙስና ኮሚሽኖች የትስስር ጉባኤ ላይ የ2016 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት የሥነምግባር ግንባታና የሙስና መከላለከል አገር አቀፍ አፈፃፀም ግምገማ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ለክልሎች ከ354 ሺሕ በላይ ስልጠናዎች መሰጠቱ የተገለጸ ሲሆን ይህም ሙስናን በመከላከሉ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተመላክቷል።

በ9 ወራት ውስጥ እንደ ሀገር 1 ሺሕ 451 የጥቆማ መረጃዎችን የመቀበል ስራ መስራቱን የገለጸው ኮሚሽኑ እንደ ሀገር 373 የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ጥናት አጥንቶ ከ2 ቢሊዮን 176 ሚሊዮን 455 ሺሕ 388.7 ብር በላይ ማዳን መቻሉን አስታውቋል።

ከገንዘቡ በተጨማሪ መጠኑ 25 ሚሊየን በላይ የሆነ ካሬ ሜትር የሆነ የከተማና የገጠር ቦታ ከሙስና ምዝበራ ለማዳን ተችሏል ተብሏል።

ተቋሙ ከኢንሳ እና መሰል ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋት ሙስናን የመከላከል ስራዎችን አጠናክሮ እየሰራ እንደሚገኝም ተመላክቷል።

በመድረኩ ላይ የፌደራልና የክልል የፀረ ሙስና ኮሚሸን ኮሚሽነሮችና ምክትል ኮሚሽነሮች ተገኝተዋል።

ማሕሌት መህዲ (ከአዳማ)
👍 13
👎 3
Изображение
1600 ዓመታትን ያስቆጠሩ ቅርሶች የሚገኙበት የግል ሙዚየም

በሐረር ከተማ የሚገኘው የቀድሞው የተፈሪ መኮንን ታሪካዊ ጫጉላ ቤት አሁን ታሪካዊ ቅርሶች ተሰባስበው የተቀመጡበት የኢትዮጵያውያን፣ የውጭ አገር ዜጎችንና ቱሪስቶችን ቀልብም የሚስብ ልዩ ሙዚየም ሆኗል።

ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊ እና የተለያዩ እምነቶች እንዲሁም ብሔረሰቦች መገለጫ የሆኑ በ10ሺዎች የሚገመቱ ቅርሶችን አሰባስቦ የያዘ ነው፤ በበጎ ሰው ሽልማት ተሸላሚው በሀረሚያ ዩኒቨርሲቲ የክቡር ዶክትሬት በተበረከተላቸው ውልደት፣ እድገት፣ ትዳር እና ኑሯቸውም በሀረር ከተማ የሆነው አብደላ አሊ ሸሪፍ የመሰረቱት “ሸሪፍ ሙዚየም”።

ከ1600 ዓመታት በላይ ያስቆጠሩ ቅርሶች፣ ከአክሱም ዘመን ጀምሮ መገልገያ የነበሩ ሳንቲሞች፣ የትየለሌ ዓመታትን ህልው መሆን የቻሉ የሃይማኖት መጻሕፍት፣ የነገስታት ሰይፍ እና መሰል የጦር መሳሪያዎች፣ ንጉሳዊያን የተጻጻፏቸው ደብዳቤዎች፣ የተፈረሙ ውሎች እና ሌሎችም እጅን በአፍ የሚያስጭኑ ታሪካዊ ቅርሶችና ሰነዶች በሸሪፍ ሙዚየም ውስጥ በከፍተኛ ጥንቃቄ እና እንክብካቤ ተቀምጠዋል።

በቀደምት ሀረሬዎች የተዘጋጁ በአረብኛ ፊደል በኦሮሚኛ ቋንቋ የተጻፉ ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸው መጻሕፍት፣ በሀረር እናቶች በጥበብ እና በጥንቃቄ የተሳሉ የሃይማኖት መጻሕፍት ሽፋን እንዲሁም ሌሎች ረጅም ዓመታትን ያስቆጠሩ መጻሕፍት በሙዚየሙ ውስጥ እንደልብ ማግኘት ይቻላል፡፡

ሀረሬዎች ይገለገሉባቸው የነበሩ ሳንቲሞች እኛ በዚህ ዘመን ከምናውቃት አምስት ሳንቲም በመጠን 3 እጥፍ የሚያንሱ ሲሆን በአስገራሚ መልኩ በዚች እጅግ ጠባብ ዲያሜትር ባላት ሳንቲም ውስጥ “ነብዩ መሀመድ የአላህ መልዕክተኛ” የሚል ጽሑፍ ታትሞ ይታያል።

ከ1600 ዓመታት በፊት መገበያያ የነበሩትን የአክሱም ሳንቲሞችን ጨምሮ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ያሉ ገንዘቦች እና በምስራቅ አፍሪካ የተለያዩ አካባቢዎችም ግብይት ይፈጸምባቸው የነበሩ ጥንታዊ ገንዘቦች በሙዚየሙ ውስጥ ከአስፈላጊው ገለጻ ጋር በክብር ተቀምጠው ትውልድ ይጎበኛቸዋል፣ ይደነቅባቸዋል፣ ታሪክ ይማርባቸዋል።

ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ👇
https://shorturl.at/pqtwx
👍 13
👏 4
🙏 1
አጓጊው ደሞ አዲስ በመጪው እሁድ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ #በቀጥታ ስርጭት ለእናንተ ለተመልካቾቻችን ተወዳዳሪዎቹን ይዞላችሁ ይቀርባል።

በቀጥታ ስርጭትም ዳኞችና ተወዳዳሪዎች በተመልካቾች ድምፅ ይዳኛሉ። በዕለቱም በተሰጣቸው ኮድ በ8970 SMS ድምጽ ይስጡ!

ዮሐንስ ወርቁ በA1

አብርሐም ሸዋንቅጣው በA2

አብርሐም ኸይሩ በA4

ማትያስ ደርብ በA5

#ደሞ_አዲስ #አዲስ_ዋልታ #music #Idol

እሁድ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን 🎼🎹🥁🎤🎺🎷🎸🎻
👍 13
Изображение

Найдено 13598 постов