Детальная рекламная статистика будет доступна после прохождения простой процедуры регистрации
: 44'979 | на пост: 4'851 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-04-24 18:00:51 |
809
0 |
: 44'979 | на пост: 4'851 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-04-24 14:41:05 |
2'153
0 |
: 44'979 | на пост: 4'851 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-04-24 12:21:37 |
2'632
0 |
: 44'979 | на пост: 4'851 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-04-24 09:32:07 |
2'992
0 |
የመኖሪያ ቤት ተደርምሶ ባደረሰው አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ
ሚያዝያ 16/2016 (አዲስ ዋልታ) በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በግንባታ ላይ የሚገኝ የመኖሪያ ቤት ተደርምሶ በጀርባ በሚገኝ ሌላ መኖሪያ ቤት ላይ በማረፉ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
አደጋው የተከሰተው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ስሙ ጠሮ መስጊድ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ መሆኑን የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አይዳ አወል ለአዲስ ዋልታ ዲጂታል ሚዲያ ገልጸዋል።
በግንባታ ላይ የነበረው የግለሰብ መኖሪያ ቤት ተደርምሶ በጀርባ በሚገኝ ሌላ መኖሪያ ቤት ላይ በማረፉ በቤቱ ውስጥ ለነበሩ ሰባት ነዋሪዎች ሕይወት ማለፍ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል።
አደጋው ሌሊት ከ10፡30 በኋላ የተከሰተ መሆኑን የገለጹት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ እስካሁን የሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ጠቁመዋል።
አደጋ ለደረሰባቸው የቤተሰብ አባላት መጽናናትን ተመኝተው ኅብረተሰቡ ላይ መሰል አደጋዎች እንዳይደርሱ በህንፃ ግንባታዎች ላይ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡
በአድማሱ አራጋው
: 44'979 | на пост: 4'851 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-04-23 16:42:28 |
4'105
0 |
የጨረታ ማስታወቂያ
የጉምሩክ ኮሚሽን ተሽከርካሪዎች፣ ጥሬ ዕቃዎች፣ ተንቀሳቃሽ እና የሚገጠሙ ፎርክ ሊፍቶች፣ የዳይፐር ማምረቻ ማሽኖች እና መለዋወጫዎች፣ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶች እንዲሁም በሼድ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ዕቃዎችን በሙሉ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ መነሻ ዋጋው 315 ሚልዮን 671 ሺሕ 341 ብር ከ14 ሣንቲም ነው።
ተጨማሪ መረጃ ሐዋሳ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በስልክ ቁጥር 0462125396 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
: 44'979 | на пост: 4'851 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-04-23 13:30:16 |
4'233
0 |
በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ አርሰናል ከቼልሲ ዛሬ ምሽት ይጫወታሉ
ሚያዚያ 15/2016 (አዲስ ዋልታ) በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ላይ አርሰናል በኤምሬትስ ስታዲዬም ከቼልሲ ጋር ወሳን ጨዋታ ያካሂዳሉ።
አርሰናል በ33 ጨዋታዎች በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በ74 ነጥብ አንደኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን በተመሳሳይ 74 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘነው ሊቨርፑል በጎል ክፍያ ነው የሚለያዩት።
ለአርሰናል የዛሬ ምሽቱ ጨዋታ የዋንጫ ፉክክሩን ለማጠናከር በጥንቃቄ እንደሚጫወት ሲጠበቅ በጥሩ መነቃቃት ላይ የሚገኘው ቸልሲ ዘንድሮ ከታላላቆቹ የሊጉ ቡድኖች ጋር ጠንክሮ በመታየቱ የምሽቱን ጨዋታ አጓጊ ያደርገዋል።
ቼልሲ 31 ጨዋታዎችን አድርጎ በ47 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን የዛሬ ምሽቱን ጨዋታ ካሸነፈ ደረጃውን ወደ 7ኛ ከፍ ሊያደርግ የሚችልበት እድል ያገኛል።
: 44'979 | на пост: 4'851 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-04-23 12:21:43 |
4'106
0 |
#ከተሞቻችን
ዓዲግራት
በ14ኛው ክፍለ ዘመን እንደተቆረቆረች የሚነገርላት ታሪካዊቷ የዓዲግራት ከተማ ከመዲናችን አዲስ አበባ በስተሰሜን አቅጣጫ 1ሺሕ 38 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡
የአመለሸጋ ሕዝብ መገኛ፣ የአብሮነት ማሳያና በእንግዳ አክባሪነቷ ተምሳሌት የሆነች ከተማ ናት፡፡
ከተማዋ ከባሕር ጠለል በላይ 2 ሺሕ 457 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኝ ሲሆን ደጋማ የአየር ፀባይ አላት፡፡
ለከተማዋ ስያሜ የሆነውና "ዓዲግራት" የሚለው ቃል ትግርኛ ሲሆን ትርጓሜውም "የእርሻ መሬት ሀገር" እንደ ማለት ነው።
በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደተገነባ የሚነገርለት "ደብረ ዳሞ" እና የ"ጉንዳ ጉንዶ" ገዳማት በዓዲግራት አካባቢ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎች ናቸው፡፡
የከተማዋ ተወላጆች ከየአሉበት ተሰባስበው ከወላጆቻቸው ጋር የመስቀል እና የአረፋ በዓላትን በድምቀት የሚያከበሩባት ከተማ ነች።
ሙሉውን ለማንበብ ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ👇👇
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid0AJQXDKAqaHh6RecyrUZ85bL8CvqapPPVVEJrhjcTUR4XzYDDCKNa1SBB5HEkEGQgl
: 44'979 | на пост: 4'851 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-04-22 18:04:56 |
4'939
0 |
: 44'979 | на пост: 4'851 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-04-22 17:14:25 |
4'804
0 |
: 44'979 | на пост: 4'851 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-04-22 15:13:34 |
4'351
0 |
: 44'979 | на пост: 4'851 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-04-22 13:28:20 |
4'644
0 |
60 ሺሕ ቻይናዊያንን ያፈናቀለው ከባድ ጎርፍ
ከሰሞኑ በተለያዩ ሀገራት የሚከሰቱ ኃይለኛ የጎርፍ አደጋዎች ሕይወት የሚቀጥፉ፣ ሃብትና ንብረት የሚያወድሙ በአጠቃላይ ከባድ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ሆነዋል። አውራ ጎዳናዎችና መኖሪያ ቤቶች በጎርፍ ተጥለቀለቁ የሚሉ ዜናዎች በተደጋጋሚ እየተሰሙ ነው። ይህን መሰል የጎርፍ አደጋ ዛሬ በቻይና ተከስቶ ዜጎችን ከቀያቸው አፈናቅሏል።
በቻይና ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት በሚስተዋልበት የጓንግዶንግ የባህር ዳርቻ ግዛት ለቀናት የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በተከሰተው ጎርፍ ወደ 60 ሺሕ የሚጠጉ ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸው መፈናቀላቸው ተሰምቷል። 11 ሰዎች የጠፉ ሲሆን እስካሁን በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት አለመድረሱ ተገልጿል።
በመንግስት ሚዲያዎች እና በበይነ መረብ ላይ የተሰራጩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በጎርፍ የተጥለቀለቀ ሰፊ መሬት ላይ የነፍስ አድን ሰራተኞች በጀልባዎች በጥልቅ እና ሰፊ ውሃ ላይ ሲንሳፈፉ ያሳያሉ።
ትላልቅ ወንዞች ሞልተው በዳርቻቸው ጎረፍ ይፈሳል። የሀገሪቱ የሚቲዎሮሎጂ ባለስልጣናት አደገኛውን ሁኔታ እና ከፍተኛውን የውሃ መጠን በቅርበት እየተከታተሉ መፍትሄ የሚሉትን ሁሉንም እየሞከሩ ናቸው ተብሏል።
ሙሉውን ለማንበብ ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ👇👇
https://shorturl.at/bsDNX
: 44'979 | на пост: 4'851 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-04-22 12:16:37 |
4'339
0 |
: 44'979 | на пост: 4'851 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-04-22 10:16:12 |
4'612
0 |
: 44'979 | на пост: 4'851 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-04-21 10:16:00 |
5'668
0 |
በኬንያ በተካሄደው የ5 ሺሕ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች አሸነፉ
ሚያዝያ 13/2016 (አዲስ ዋልታ) ትላንት ማምሻውን በኬኒያ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ኮንቲኔንታል ቱር ጎልድ ውድድር በ5 ሺሕ ሜትር በሁለቱም ፆታዎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል።
በሴቶች የ5 ሺሕ ሜትር ውድድር አትሌት ማርታ አለማየው ርቀቱን 15 ደቂቃ ከ14 ሰከንድ ከ54 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በአንደኝነት ስትጨርስ፣ ለምለም ንብረት 15 ደቂቃ ከ20 ሰከንድ ከ99 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት ውድድሩን በመጨረስ 3ኛ ሆና አጠናቃለች። ሌላዋ አትሌት ሽቶ ጉሚ ውድድሩን በአራተኝነት አጠናቃለች።
በሌላ በኩል በወንዶች የ5 ሺሕ ሜትር ውድድር አብዲሳ ፈፍሳ ርቀቱን 13 ደቂቃ ከ34 ሰከንድ ከ77 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ አሸናፊ መሆኑን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
: 44'979 | на пост: 4'851 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-04-20 16:48:50 |
6'224
0 |
አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ በዲያመንድ ሊግ 1 ሺሕ 500 ሜትር ውድድር አሸነፈች
ሚያዚያ 12/2016 (አዲስ ዋልታ) በቻይና ዝያሜን እየተካሄደ ባለው ዲያመንድ ሊግ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ 3:50:30 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን ማሸነፍ ችላለች።
በተያያዘ የ2024 የዲያመንድ ሊግ ውድድር አትሌት ለሜቻ ግርማ በ5 ሺሕ ሜትር የሩጫ ውድድር አሸንፏል።
አትሌት ለሜቻ ግርማ በውድድሩ ርቀቱን በቀዳሚነት ለማጠናቀቅ 12:58.96 ስዓት ፈጅቶበታል።
ውድድሩ ለ6 ወራት የሚቆይ ሲሆን አራት አህጉራት በ15 ከተሞች የሚካሄድ ይሆናል።
: 44'979 | на пост: 4'851 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-04-20 10:53:33 |
5'857
0 |
የጉራጌ ሕዝብ በአንድነት ውስጥ የሚገኘውን ጸጋ ከሕይወት ልምዱ የተገነዘበ ነው - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ
ሚያዝያ 12/2016 (አዲስ ዋልታ) የጉራጌ ሕዝብ በአንድነት ውስጥ የሚገኘውን ጸጋ ከሕይወት ልምዱ የተገነዘበ ሕዝብ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
የለውጡን መንግስት የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር የጉራጌ ሕዝብ ስለአንድነት እና አብሮነት አበክሮ ያስተማረና በተግባር ያሳየ አንድነት ኃይል ነው ብሎ የሚያምን መሆኑን አንስተዋል።
ስለሰላም ሳናስብ፤ ስለሰላም ሳንናገር ሰላምን ልንጎናጸፍ አንችልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጉራጌ ስለሰላም የሚያስተምር፤ በሰላም የሚኖር ሰላምን የሚያስተጋባ ሕዝብ መሆኑንም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያን ለመከፋፈል በየዕለቱ ገንዘባቸውን፣ ዕውቀታቸውንና ጉልበታቸውን ለሚያጠፉ ለአትዮጵያ ጠላቶች ጉራጌ አንድነት ኃይል ነው ብሎ ስለሚያምን ኢትዮጵያዊያን ከዚህ ልንማር ይገባል ብለዋል።
አክለውም የኢትዮጵያ አንድነትን ጠብቀን ለትውልድ ማሻገር እንድንችል ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
: 44'979 | на пост: 4'851 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-04-20 09:55:42 |
5'226
0 |