Телеграм канал 'WALTA TV'

WALTA TV


44'201 подписчиков
4'305 просмотров на пост

This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.

For more updates please visit https://www.facebook.com/wmcc

Детальная рекламная статистика будет доступна после прохождения простой процедуры регистрации


Что это дает?
  • Детальная аналитика 5'624'523 каналов
  • Доступ к 1'533'798'153 рекламных постов
  • Поиск по 4'968'260'819 постам
  • Отдача с каждой купленной рекламы
  • Графики динамики изменения показателей канала
  • Где и как размещался канал
  • Детальная статистика по подпискам и отпискам
Telemetr.me

Telemetr.me Подписаться

Аналитика телеграм-каналов - обновления инструмента, новости рынка.

Найдено 13420 постов

“በዛሬው ውይይት ከተለያየ የማኅበረሰብ ዳራ የተውጣጡ ከመላው ኢትዮጵያ የመጡ ሴቶችን ሀሳብ አዳምጫለሁ። በኅብረተሰባችን ውስጥ የሴቶች ሚና ብዙ መልክ እና ብዙ ገፅ ያለው ነው።"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

👍 4
Изображение
ቻይናዊው ወጣት በኪሩቤል ግርማ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን ሰበረ

መጋቢት 19/2016 (አዲስ ዋልታ) ቻይናዊው ወጣት ውሃን ከአፍ ለረጅም ጊዜ በማንቆርቆር/መርጨት ተግባር በኪሩቤል ግርማ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በሰፊ ልዩነት ሰብሮታል።

ኪሩቤል ግርማ ውሃን ለ56 ሰከንድ ከ36 ማክሮ ሰከንድ ያክል ከአፉ በመርጨት ነበር በዓለም የጊነስ ቡክ መዝገብ ላይ ስሙ የሰፈረው።

የ35 ዓመቱ ቻይናዊ ማ ሁዊ ለ5 ደቂቃ ከ51 ሰከንድ ከ88 ማይክሮ ሰከንድ ያህል ያለማቋረጥ ውሃ ከአፉ በመርጨት ተዓምር አስብሏል። የማ ሁዊ ድርጊት በሰው ልጅ ታሪክ ተወዳዳሪ የሌለው አስብሎታል።

ውሃን ለረጅም ጊዜ በአፍ የመርጨት ተግባር ከ17ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበረ ጥበብ ሲሆን በብዛት የተጠጣን ውሃ በአፍ በኩል መልሶ በማውጣት ወደ ውጭ የመርጨት ስልት ነው።

ድርጊቱን በማንኛውም ሰው ሊከወን የማይቻል መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ከፍተኛ የጡንቻ ቁጥጥርና ምጠና ክህሎት እንደሚያስፈልገው ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ቻይናዊው ወጣት ይህን ክብረ ወሰን ለመስበር 4 ሊትር ተኩል ውሃ መጠጣቱን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።
👍 13
👏 3
Изображение
ከተማ አስተዳደሩ በ90 ቀን 108 ቤቶችን ገንብቶ ለአቅመ ደካሞች ለማስረከብ ግንባታ አስጀመረ

መጋቢት 19/2016 (አዲስ ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ90 ቀን 108 ቤቶችን ገንብቶ ለአቅመ ደካሞች ለማስረከብ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ግንባታ አስጀመረ።

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በክፍለ ክተማ የሚገነባውን 108 ቤቶችን የሚይዝ ባለአምስት ወለል ሦስት የመኖሪያ ቤት ህንፃ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ በማስቀመጥ ነው ዛሬ ግንባታውን ያስጀመሩት።

ከተማ አስተዳደሩ በከተማው ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት ህብረተሰቡን በማህበር በማደራጀት የቤት መስሪያ ቦታ ከመስጠት ጎን ለጎን የአቅመ ደካሞችን የቤት ችግር ለማቃለል እየሰራ መሆኑንም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ መኖሪያ ቤት ለሌላቸውና ተከራይተው መኖር ለማይችሉ አቅመ ደካሞች ቤት ገንብቶ ለማስረከብ ግንባታውን አስጀምሯል ብለዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የህዝቡን ተስፋ ለማለምለም፣ በኑሮ ውድነትና በቤት እጦት የሚሰቃየውን ህዝብ በምንችለው ለማገዝ ጥረት እያደረግን እንገኛለን ሲሉም አክለዋል፡፡

የጋራ መኖሪያ ቤት በህብረተሰብ ተሳትፎ እና ባለሃብቶች የሚገነባ መሆኑም ተገልጿል።

በግዛቸው ግርማዬ
👍 11
Изображение

"ኢፍጣራችን ለአንድነታችን" ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነ ስርዓት - በምስል

📷 ልዑል ማስረሻ
#አዲስ_ዋልታ

ተጨማሪ ምስሎችን ለመመልከት የፌስቡክ ገፃችንን ይቀላቀሉ 👇
https://shorturl.at/fQVX5

👍 4
🙏 4
Изображение

የባሕር ዳር ከነማ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረው አለልኝ አዘነ በድንገት አረፈ

መጋቢት 18/2016 (አዲስ ዋልታ) የባሕር ዳር ከነማ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረው አለልኝ አዘነ በድንገት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።

ተጫዋቹ በጉዳት ምክንያት ከክለቡ ስብስብ ጋር ያልነበረ ሲሆን በትውልድ ቦታው አርባ ምንጭ ሌሊት በድንገት ማረፉ ተገልጿል።

በቅርቡ የተሞሸረው አለልኝ አዘነ፤ ላለፉት ሁለት አመታት በጣና ሞገዶቹ ቤት ድንቅ ብቃቱን ሲያሳይ ቆይቷል። ከዚህ በተጨማሪም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ተደርጎለት አገልግሎት መስጠቱ ይታወሳል።

ስርዓተ ቀብሩ ዛሬ መጋቢት 18, 2016 በአርባ ምንጭ እንደሚፈፀም ከክለቡ ማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አዲስ ዋልታ ቴሌቪዥን በአለልኝ አዘነ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለመላው የስፖርት ቤተሰብ መፅናናትን ይመኛል።

😢 15
👍 11
🙏 4
👏 1
Изображение

ንግድ ባንክ ያለአግባብ የተወሰደውን ገንዘብ ያልመለሱ ሰዎችን ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ

መጋቢት 17/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት ባጋጠመው ችግር ምክንያት ያለአግባብ የተወሰደውን ገንዘብ ያልመለሱ ሰዎችን ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ።

ባንኩ ይፋ ያደረገውን የስም ዝርዝሩን ለማየት የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://shorturl.at/ftBG0

👍 25
🙏 4
👎 2
Изображение

እንግሊዝ ከቤልጂየም እና ጀርመን ከሆላንድ የወዳጅነት ጨዋታ ያካሂዳሉ

መጋቢት 17/2016 (አዲስ ዋልታ) ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ከ45 ላይ እንግሊዝ ከቤልጂየም እንዲሁም ጀርመን ከሆላንድ የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋሉ።

እንግሊዝ ባለፈው ቅዳሜ በብራዚል 1 ለ 0 የተሸነፈች ሲሆን ቤልጂየም በበኩሏ ከአየርላንድ ጋር 0 ለ 0 መለያዬታቸው ይታወሳል።

ጀርመን በበኩሏ ቅዳሜ ዕለት ከፈረንሳይ ጋር ያደረገችውን ጨዋታ 2 ለ 0 ስታሸንፍ፣ ሆላንድ ስኮትላንድን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፋለች።

ከሁለቱ የወዳጅነት ጨዋታዎች በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን ስሎቬንያ ከፖርቱጋል፣ ኡራጓይ ከአይቮሪ ኮስት፣ ሮማንያ ከኮሎምቢያ፣ አየርላንድ ከሲውዘርላንድ ምሽት 4 ከ 45 ላይ ከሚካሄዱ ግጥሚያዎች ተጠቃሽ ናቸው።

ምሽት 5 ሰዓት ላይ ግብፅ በሜዳዋ ክሮሺያን እንደምታስተናግድ ሲጠበቅ ፈረንሳይ ከቺሊ እንዲሁም ስፔን ጀብራዚል 5 ሰዓት 30 ላይ የሚደርጉት ተጠባቂ ጨዋታዎች ናቸው

👍 5
👏 1
Изображение

የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዟችንን ከጀመርንበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ሀገር ወሳኝ ርምጃዎችን ተራምደናል - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

መጋቢት 17/2016 (አዲስ ዋልታ) የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዟችንን ከጀመርንበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ሀገር ወሳኝ ርምጃዎችን ተራምደናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ለፈጠራ ሰዎች ድጋፍ በማስገኘት እና ለዲጂታል ጉዞ አስቻይ ሁኔታዎችን በመፍጠር በዲጂታል ኢኮኖሚ እንድንበረታ ዐቅም ሆኖናል ሲሉም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

“ዛሬ ያደረግነው የመካከለኛ ዘመን ግምገማ ተግዳሮቶቻችንን ለመፈተሽ ብሎም የጉዟችንን ስኬታማ እጥፋቶች ለማክበር ዕድል ፈጥሮልናል።” ብለዋል።

👍 14
👎 3
Изображение

ሚዛን አማን

#ከተሞቻችን

የሚዛን አማን ከተማ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አንዷ መቀመጫና የቤንች ሸኮ ዞን ዋና መቀመጫ ሆና በማገልገል ላይ ትገኛለች፡፡

ከተማዋ ከርዕሠ መድናችን አዲስ አበባ በ568 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ስትሆን በ1930 ዓ.ም እንደተቆረቆረች ይነገራል።

ሚዛን አማን ከተማ የቀድሞ ሚዛን ተፈሪ የሚለውን ስያሜ ያገኘችው በንጉሱ አፄ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግሥት አካባቢውን እንዲያስተዳድሩ ተሹመው በተላኩት በእንደራሴው ፊታውራሪ አለማየሁ ፍላቴ መሆኑ ይነገራል፡፡

የንጉስ አፄ ኃይለስላሴ ልደት እየተከበረ በነበረበት ወቅት ከተማዋ በመመስረቷ የልደት መታሰቢያ ለማድረግ እንደሆነም ታሪክ ይጠቅሳል።

በ1ሺሕ 451 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ ከፍታ ላይ የምትገኘው ሚዛን አማን በአረንጓዴ መልክዓ ምድር የተሸፈነች እና ወይናደጋ የአየር ንብረት ያላት ከተማ ነች።

እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ያላት ሚዛን አማን በዙሪያዋ ከፍተኛ የደን ክምችት ያላት ሲሆን ቡናን ጨምሮ፣ በፍራፍሬ እና በቅመማቅመም ምርቶች ትታወቃለች፡፡ የአረንጓዴ ልማት ፈርጥ ተብላም ትጠራለች።
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid0NMmjbVppnwZjZ9NxBEeKkDnjSQ26t2A9oaG6xmD6MCFc7FEwdAG1pXAJxreKrLnJl

👍 14
Изображение

ገንዘቡን ከወሰዱት ግለሰቦች መካከል 560 ሰዎች አልተገኙም

ከዛሬ ጀምሮም ማንነታቸው በባንኩ ማህበራዊ ትስስር ገፅ ይለቀቃል ተብሏል

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በተያያዘ ከ9 ሺሕ በላይ የሚሆኑ ግለሰቦች በፈቃደኝነት ገንዘቡን መመለሳቸው ተገለፀ

መጋቢት 17/2016 (አዲስ ዋልታ) ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በተያያዘ 9 ሺሕ 200 ያህሉ ግለሰቦች በፈቃደኝነት ገንዘቡን መመለሳቸው ተገለፀ፡፡

ባንኩ ካጋጠመው ችግር ጋር ተያይዞ የተከናወኑ ዐበይት ተግባራትን ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዘደንት አቤ ሳኖ በመግለጫቸው ባንኩ ባጋጠመው ችግር ምክንያት 801 ሚሊየን ብር ያለአግባብ ተወስዶ እንደነበር ገልፀዋል።

ነገር ግን በጉዳዩ ላይ ተሳትፎ ከነበራቸው ውስጥ 9 ሺሕ 200 ያህሉ በፈቃደኝነት የወሰዱትን ገንዘብ መልሰዋል ሲሉ ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል፡፡ በዚህም 223 ሚሊየን 475 ሺህ 369 ብር ተመላሽ መደረጉን አንስተዋል።

ከዚህ ባሻገር 5 ሺሕ 160 ያህል ግለሰቦች ደግሞ በፈቃደኝነት የወሰዱትን 148 ሚሊየን 21 ሺሕ 191 ብር በከፊል መመለሳቸውን አክለዋል፡፡

እንደ አጠቃላይ ባንኩ በአጠቃላይ ወጪ ከተደረገው ገንዘብ 78 በመቶ ያህሉን ገንዘብ ተመላሽ ማድረጉም ተገልጿል፡፡

ባንኩ ገንዘብ ወስደው ያልመለሱ ደንበኞች ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የማህበራዊ ድረገፅ ስማቸው እንደሚለጠፍም የባንኩ ፕሬዝዳንት ገልፀዋል።

በዙፋን አምባቸው

👍 15
👏 5
Изображение

በ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ

መጋቢት 16/2016 (አዲስ ዋልታ) በጋና በተካሄደው 13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገባ።

ልዑኩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ አቀባበል አድርገውለታል።

የአፍሪካ ጨዋታዎች ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም በጋና አክራ የተካሄደ ሲሆን በውድድሩ ከ53 ሀገራት የተወጣጡ ከ5 ሺሕ በላይ ስፖርተኞች በ29 የስፖርት አይነቶች ተሳትፈዋል።

ኢትዮጵያም በ165 ስፖርተኞች በአምስት የኦሊምፒክ ውድድሮችና አራቱ ኦሊምፒክ ያልሆኑ ስፖርቶች በድምሩ በዘጠኝ የስፖርት አይነቶች ተሳትፋለች፡፡

በአትሌቲክስ፣ እግር ኳስ፣ ውሃ ዋና፣ የጠረጴዛና ሜዳ ቴኒስ፣ ቦክስ፣ ቅርጫት ኳስ፣ ብስክሌትና ወርልድ ቴኳንዶ ኢትዮጵያ የተሳተፈችባቸው የውድድር አይነቶች ናቸው።

ኢትዮጵያ 9 የወርቅ፣ 8 የብር፣ 5 የነሐስ በአጠቃላይ 22 ሜዳሊያዎችን በማግኘት በሁሉም የስፖርት አይነቶች ስምንተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች።

በ13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች ለተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የእውቅናና የሽልማት መርኃ ግብር እንደሚካሄድም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

👍 19
👎 1
Изображение
26 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የኤሌክትሪክ አውቶብሶች አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

መጋቢት 16/2016 (አዲስ ዋልታ) 26 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የመጀመሪያዎቹ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠሩ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች በአዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት ጀመሩ፡፡

ዛሬ ስራ የጀመሩት 60 አውቶቢሶች በበላይነህ ክንዴ ግሩፕ እህት ድርጅት ቬሎሲቲ ኤክስፕሬስ በገላን እና ደብረ ብርሃን የተገጣጠሙ መሆናቸውን ድርጅቱ ገልጿል፡፡

አውቶብሶቹ ቻርጅ የሚደረጉበት ስፍራ በ30 የተለያዩ የከተማዋ ስፍራዎች መገንባታቸውንና በቤት ውስጥ ቻርጅ መደረግ እንደሚችሉም ተገልጿል፡፡

የአውቶብሶቹ መነሻ ቦሌ ሲሆን መዳረሻቸው በእስጢፋኖስ አራት ኪሎ - ስድስት ኪሎ - ሽሮ ሜዳ መሆኑንም ድርጅቱ አስታውቋል።

በበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የተገጣጠሙ ተሽከርካሪዎች ብዛት እስካሁን ከ216 በላይ መድረሳቸውንም ድርጅቱ ለአዲስ ዋልታ ዲጂታል ሚዲያ አስታውቋል፡፡

በየኔወርቅ መኮንን
👍 17
👏 3
Изображение

Найдено 13420 постов