Телеграм канал 'WALTA TV'

WALTA TV


44'820 подписчиков
4'451 просмотров на пост

This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.

For more updates please visit https://www.facebook.com/wmcc

Детальная рекламная статистика будет доступна после прохождения простой процедуры регистрации


Что это дает?
  • Детальная аналитика 5'798'858 каналов
  • Доступ к 1'533'798'153 рекламных постов
  • Поиск по 4'863'852'277 постам
  • Отдача с каждой купленной рекламы
  • Графики динамики изменения показателей канала
  • Где и как размещался канал
  • Детальная статистика по подпискам и отпискам
Telemetr.me

Telemetr.me Подписаться

Аналитика телеграм-каналов - обновления инструмента, новости рынка.

Найдено 13571 пост

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ

ሚያዝያ 9/2016 (አዲስ ዋልታ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 30ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በዚህም መሰረት፡-
1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅ ላይ ሲሆን ረቂቁ በ29ኛው የሚኒስትሮች ም/ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ቀርቦ የፀደቀውን የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ፖሊሲ መሰረት በማድረግ ፖሊሲውን ለማስፈፀም እንዲቻል ተደርጎ የተዘጋጀ ነው።

በተጨማሪም ረቂቅ አዋጁ በ2010 ዓ.ም ጸድቆ ስራ ላይ የዋለው አዋጅ በትግበራ ሂደት የታዩ ክፍተቶችን በተለይም የመንግስት ሠራተኞች አስተዳደርን ነጻ፣ ገለልተኛ፣ ቀልጣፋ፣ ተደራሽነት እና ተጠያቂነት ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት፤ እንዲሁም ከጊዜው ጋር የሚራመድ የአስራር ስርአት ለመዘርጋት የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምከር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ተወያይቶ ግብዓቶችን በማከል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የሽግግር ፍትሕ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ነው፡፡ በሀገሪቱ በተለያዩ ዘመናት የተከሰቱ እና የቀጠሉ ተደራራቢ እና ሰፊ የተጎጂና የአጥፊ ወሰን ያላቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ የእርስ በእርስ ግጭቶች፣ ያልጠሩ ትርከቶች እና በደሎችን ለመፍታት የተለያዩ ሙከራዎች ተደርገዋል፡፡ ሆኖም እነዚህ አሰራሮች በእውነት፣ በዕርቅ፣ በምህረት እና በፍትሕ ላይ የተዋቀረ እና በግልፅ ፖሊሲ የሚመራ ሁለንተናዊ የሽግግር ፍትሕ ስልትን አካታች፣ ሰብአዊ መብት-ተኮር በሆነ እና በተሰናሰለ መንገድ ባለመተግበራቸው የሚፈለገውን ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት አልቻሉም።👇
https://shorturl.at/BGZ04
👍 21
🙏 3
Изображение
ዛሬ ምሽት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሁለት የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ

ሚያዝያ 9/2016 (አዲስ ዋልታ) ዛሬ ምሽት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ሁለተኛ ዙር የሩብ ፍጻሜ መርኃ ግብር ሁለት ወሳኝ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

ምሽት 4 ሰዓት ማንችስተር ሲቲ ከሪያል ማድሪድ የሚያደርጉት የሁለተኛ ዙር የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በእግር ኳሱ አፍቃሪያን ዘንድ በከፍተኛ ጉጉት ይጠበቃል።

ሁለቱ ቡድኖች በጠንካራ አጨዋወት ሊጎቻቸውን በአንደኝነት ከመምራታቸው ባሻገር በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት የሻምፒዮንስ ሊግ ግጥሚያ 3 ለ 3 በሆነ አቻ ውጤት መጠናቀቁ የዛሬ ምሽቱን ጨዋታ ተጠባቂ ያደርገዋል።

በሌላ በኩል ምሽት አራት ሰዓት ላይ ባየር ሙኒክ በሜዳው ከአርሰናል ጋር የሚጋጠም ሲሆን ሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያ ዙር የሩብ ፍጻሜ ጨዋታቸውን በሁለት አቻ ውጤት ማጠናቀቃቸው ይታወሳል።

በቡንደስ ሊጋው የውድድሩን ዋንጫ በዣቪ አሎንሶ የሚመራው ባየር ሊቨርኩሰን ማሸነፉን ተከትሎ ባየር ሙኒክ የአውሮፓ ትልቁን ክብር በማንሳት ለማካካስ ጠንክሮ እንደሚጫወት ይጠበቃል።

አርሰናል በበኩሉ በፕሪሚዬር ሊጉ በአስቶን ቪላ ከደረሰበት ሽንፈት ለመውጣት ጠንካራ ፉክክር እንደሚያደርግ ይገመታል።

ትናንት ምሽት በተካሄዱ ሁለት የሩብ ፍጻሜ ግጥሚያዎች አስገራሚ ውጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን ፒ.ኤስ. ጂ ባርሴሎናን በሜዳው 4 ለ 1 አሸንፎ 6 ለ 4 በሆነ ድምር ውጤት ወደ ግማሽ ፍጻሜ ማለፉን አረጋግጧል። በሌላ በኩል የጀርመኑ ቦሩሲያ ዶርትመንድ አትሌቲኮ ማድሪድን 4 ለ 2 አሸንፎ 5 ለ 4 በሆነ ድምር ውጤት ወደ ቀጣይ ዙር አልፏል።

ፒ.ኤስ.ጂ እና ዶርትመንድ የመጀመሪያውን ዙር የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ተሸንፈው እንደነበር አይዘነጋም።
👍 15
Изображение
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከተወሰደው ገንዘብ 95 በመቶ ማስመለሱን ገለጸ

ሚያዝያ 9/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከተከሰተው የሲስተም ችግር ጋር በተገናኘ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ገንዘብ 95 በመቶ የሚሆነውን ማስመለሱን አስታወቀ።

ባንኩ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ በተጠቀሰው ዕለት በተፈጠረ ችግር ምክንያት ብር 801 ሚሊዮን 417 ሺሕ 747.81 ያለአግባብ ተወስዶ እንደ ነበር መገለጹ ይታወሳል።

ከተወሰደው ገንዘብ 762 ሚሊዮን 941 ሺሕ 341 ብር ማስመለስ መቻሉን ባንኩ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባወጣው መረጃ አመልክቷል።

ይህም መሰብሰብ ከነበረበት ገንዘብ ውስጥ 95 በመቶ የሚሸፍን ሲሆን ቀሪውን 38 ሚሊዮን 474 ሺሕ 938 ብር የማስመለስ ስራ እንደሚቀጥልም ገልጿል።
👍 14
Изображение
ፌዴሬሽኑ በአወዛጋቢው የማራቶን ውጤት ላይ ምርመራ እንደሚያከናውን አስታወቀ

ሚያዝያ 8/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአወዛጋቢው የቤጂንግ ግማሽ ማራቶን ውጤት ላይ ምርመራ እንደሚያከናውን አስታወቀ።

ባለፈው እሁድ በተደረገው የቤጂንግ ግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ ሦስት አፍሪካዊያን አትሌቶች ሆን ብለው ሄ ጂ የተባለው ቻይናዊ አትሌት እንዲያሸንፍ ማድረጋቸውን የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን መዘገባቸው ይታወሳል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዮሐንስ እንግዳ ከአዲስ ዋልታ ጋር በነበራቸው ቆይታ በዕለቱ ውድድር ላይ የተሳተፈው ኢትዮጵያዊ አትሌት ጀደኔ ኃይሉ ከፌዴሬሽኑ እውቅና ውጭ ወደ ውድድሩ ስፍራ ማቅናቱን ገልጸው ያደረገውን ተግባር እንደሚያጣራ አስታውቀዋል።

የውድድሩ አዘጋጆች በምን መስፈርት ተወዳዳሪውን እንዳሳተፉት ፌዴሬሽኑ እንደማያውቅ አመልክተዋል። አትሌቱ ወደ ሀገር ሲመለስ ፌዴሬሽኑ ስለሁኔታው እንደሚያነጋግርም አንስተዋል።

በቤይጂንግ ግማሽ ማራቶን ላይ የተሳተፉት ኬኒያዊያኑ ሮበርት ኬተር፣ ዊሊ ምናንጋት እና ኢትዮጵያዊው ደጀኔ ኃይሉ ከስፖርታዊ ስነ ምግባር ባፈነገጠ መልኩ ሆን ብለው ሌላ ተወዳዳሪ እንዲያሸንፍ ፍጥነታቸውን በመቀነስ እንዲሁም በማበረታታት እንዲያሸንፍ ማድረጋቸው በተንቀሳቃሽ ምስል ይፋ መሆኑ ይታወሳል።

በሐብታሙ ገደቤ
👍 6
😢 1
Изображение
ሮቦት እና ሰዎች የተሳተፉበት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ፊልም ተመረቀ

ሚያዝያ 8/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከሰዎኛ ፊልም ፕሮዳክሽንና ኢንተርቴይመንት ጋር በመተባበር ያቀረበው "አስተውሎት" የተሰኘ ፊልም በዛሬው ዕለት ተመረቀ።

በመርኃግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በኢትዮጵያ ምድር የተሰሩ ሮቦቶችን በማሳተፍ ቀዳሚ የሆነ ፊልም እንደሆነም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና ኢትዮጵያን ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ፊልሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ አንድ ዓመት ተኩል ጊዜ መፍጀቱን አመልክተዋል።

"አስተውሎት" ፊልም በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ሳይንሳዊ ፊልም ሲሆን በሚካኤል ሚሊዮን ተዘጋጅቶ ተፈሪ ዓለሙ እና ሀረገወይን አሰፋን ጨምሮ አንጋፋና ወጣት ተዋንያን የተሳተፉበት መሆኑም በመርኃግብሩ ተገልጿል።

በአማረ ደገፋው
👍 12
Изображение
በኮሪደር ልማት ዝግ ሆነው የቆዩ መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት ሆኑ

ሚያዝያ 8/2016 (አዲስ ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ በተወሰኑ አካባቢዎች እየተከናወኑ በሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ምክንያት ዝግ ሆነው የቆዩ መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት መደረጋቸውን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በዚህም መሰረት፡-

• ከደጃች ውቤ በአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

• ከባሻወልዴ ችሎት በቱሪስት ሆቴል ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር

• ከዳኑ ሆስፒታል እስከ ቱሪስት ሆቴል በመውጣት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር

• ከአራዳ መስተዳደር ወደ ዳኑ ሆስፒታል መውረጃ በአንድ አቅጣጫ ብቻ አሽከርካሪዎች መጠቀም እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እየተከናወኑ ባሉ የልማት ሥራዎች ምክንያት ለአጭር ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ በጥብቅ መከልከሉንም ነው ፖሊስ ያሳሰበው፡፡
👍 8
👏 3
Изображение
ሻሸመኔ
#ከተሞቻችን

የምዕራብ አርሲ ዞን ዋና መቀመጫ የሆነችው የሻሸመኔ ከተማ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ አቅጣጫ 255 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ሲሆን በ1913 እንደተቆረቆረች ይነገርላታል።

ከከተማዋ ስያሜ ጋር በተያያዘ እንደ አፈታሪክ የምትነሳ አንዲት "ሻሼ" የምትባል እንግዳ ተቀባይ ሴት በአካባቢው ትኖር እንደነበር እና የሻሼ ቤት ወይም በኦሮምኛ "መነ-ሻሼ" የሚለው የስፍራው ስያሜ በጊዜ ሂደት ተቀይሮ ሻሸመኔ እንደተባለ በታሪክ ይወሳል።

ወይና ደጋ የአየር ንብረት ያላት የሻሸመኔ ከተማ ከባህር ጠለል በላይ 1937 ሜትር ከፍታ ላይ ትገኛለች።

ጀምበር የማይጠልቅባት የሻሸመኔ ከተማ የዞኑ ዋና የንግድ እና የትራንስፖርት ማዕከል ስትሆን ሐዋሳን ጨምሮ ወላይታ እና ዲላን የምታገናኝ ባለ5 በር ኮሪደር ከተማ ነች።

የተለያዩ ብሄረሰቦችን በጉያዋ ያቀፈችው ሻሸመኔ በ12 ወረዳ እና 4 ክፍለ ከተማዎች የተዋቀረች ስትሆን አቦስቶ፣ ጎፋ፣ አዋሾ፣ ኩዬራ እና አራዳ ከሰፈር ስያሜዎቹ መካከል ተጠቃሾች ናቸው።

ከበሀማስ፣ ከኮቤኮ፣ ከካሪቢያን እና ከጃማይካ የመጡ ዜጎች ለበርካታ ዓመታት ከትመው የሚኖሩባት ከተማ እንደሆነችም ይነገርላታል።

በከተማዋ ሻሸመኔ ሙዚየምና የተለያዩ የትምህርት ተቋማት የሚገኙ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ሊድ ስታር ኢንተርናሽናል አካዳሚ፣ ሉሲ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ሚሊኒየም ሻሸመኔ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ እናት ኮሌጅ እና የሻሸመኔ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ይገኙበታል።
👇👇
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid0tqnYZqVyqH8k4ni2NZqrG57kTBLcjgagtMR986bCEyGm6CVVHv7gsMjX8ct6TbNpl
👍 19
👏 2
Изображение

የአዲስ ዋልታ የኢድ አልፈጥር በዓል የወርቅ ደረጃ አጋር!
የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ

👍 3
Изображение

ኢትዮ ቴሌኮም "ቴሌ ብር-ኢንጌጅ" የተባለ አዲስ አገልግሎት አስጀመረ

ሚያዚያ 7/2016(አዲታ ዋልታ) ኢትዮ ቴሌኮም "ቴሌ ብር-ኢንጌጅ" የተሰኘ አዲስ አግለግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አደረገ።

አገልግሎቱ ይፋ በተደረገበት ወቅት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንደገለጹት፣ኩባንያው በሁሉም ዘርፍ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው ብለዋል።

አገልግሎቱ ያለ ኢንተርኔት ክፍያ በደንበኞች መካከል መረጃዎችን መለዋወጥ ፣ ገንዘብ ማስተላለፍ፣ ክፍያዎችን መፈጸም እና መሰል አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚያስችል ነው የተናገሩት።

አገልግሎቱ በዲጂታል ፋይናንስ ሽግግር ውስጥ የንግድ፣ የመንግስትና የግል ተቋማትን ትኩረት በማድረግ የዲጂታል ኢኮኖሚ ምህዳሩን ለማስፋት የሚረዳ ነው ብለዋል።

የግለሰብም ሆነ የንግድ ደንበኞች የተናጠል ወይም የቡድን ቀጥታ ውይይቶችን ለማድረግ፣ የግብይት መረጃዎችን ለመለዋወጥ፣ በውይይቶች ወቅት ገንዘብ ለመላክና ለመቀበል እንደሚያስችል ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በአዲሱ አገልግሎት ደንበኞች የንግድ ወይም ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮቻቸውን በፅሁፍ፣ በፎቶ፣ በድምጽ፣ በቪዲዮና በሰነድ መልክ መለዋወጥ እንደሚያስችላቸው ኢትዮ ቴሌኮም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

👍 21
Изображение

ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሀደ ነው

ሚያዚያ 7/2016 (አዲስ ዋልታ) ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በጉባዔው የሃይማኖት መሪዎች፣ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ ሚንስትሮች ፣ አምባሳደሮች፣የአፍሪካና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።

ኮንፈረንሱ በአፍሪካ ውስጥ የሃይማኖቶች የጋራ ተግባርን ለማስከበር እና ለማበረታታት፣ ሰላምን፣ ሰብአዊ ክብርን፣ ልማትን እና አካባቢን መጠበቅ እና የጥላቻ ንግግርን ፣ ጥቃትን እና የውጭ ዜጋ ጥላቻን መከላከል በሚል መሪቃል እየተካሄደ ነው ።

በአህጉርና ዓለም አቀፍ ደረጃ ሠላምና ልማትን ማረጋገጥ፣ ሰብዓዊ ክብርን መጠበቅ፣አካባቢን መጠበቅ፣ የጥላቻ ንግግርንና መጤ ጠልነትን በጋራ መከላከል የሚያስችል ምክክር ማድረግ የጉባኤው ዋና ዓላማ መሆኑም ተገልጿል።

ጉባዔው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የበላይ ጠባቂነት የተዘጋጀ ሲሆን ዛሬ እና ነገ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል።

በሰማኸኝ ንጋቱ

👍 17
Изображение

የአዲስ ዋልታ የኢድ አልፈጥር በዓል የወርቅ ደረጃ አጋር!
የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ

👏 7
👍 1
Изображение
Изображение

Найдено 13571 пост