Детальная рекламная статистика будет доступна после прохождения простой процедуры регистрации
: 44'214 | на пост: 4'181 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-03-28 22:25:09 |
975
0 |
ባህርዳር ከነማ የአለልኝ አዘነን 23 ቁጥር ማሊያ ቁጥር በክብር እንዲቀመጥ ወሰነ
መጋቢት 19/2016 (አዲስ ዋልታ) በድንገት ህይወቱ ያለፈው ወጣቱ አማካይ የእግር ኳስ ተጨዋች አለልኝ አዘነ የሚለብሰው የማሊያ ቁጥር በክብር እንዲቀመጥ መወሰኑን የባህርዳር ከነማ ስፖርት ክለብ አስታወቀ።
የጣና ሞገዶቹ ተጫዋቾች በኮከብ ተጫዋቻቸው ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን በትውልድ ስፍራው በመገኘት ገልፀዋል።
በዚህም አለልኝ አዘነ በባህር ዳር ከነማ ስፖርት ክለብ ይለብሰው የነበረው የማልያ ቁጥር 23 ከዚህ በኋላ ማንም የክለቡ ተጫዋች የማይለብሰው ሆኖ በክብር እንዲቀመጥ የባህርዳር ከነማ ስፖርት ክለብ ወስኗል።
: 44'214 | на пост: 4'181 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-03-28 18:19:46 |
2'651
0 |
: 44'214 | на пост: 4'181 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-03-28 17:39:52 |
2'539
0 |
በመላ ሀገሪቱ ኃይል መቋረጡ ተገለጸ
መጋቢት 19 /2016 (አዲስ ዋልታ) ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት ከ46 ደቂቃ ጀምሮ ከባህርዳርና አካባቢው በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
በሲስተሙ ላይ በገጠመው ችግር ኃይል የተቋረጠ መሆኑን ያስታወቀው ተቋሙ ለጊዜው የችግሩን ምክንያት ለማወቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባወጣው መረጃ አመልክቷል።
የተቋረጠውን ኤሌክትሪክ መልሶ የማገናኘት ሥራ የተጀመረ ሲሆን ችግሩን በመቅረፍ ዳግም ሲስተሙን መልሰን እስከምናገናኝ በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን ብሏል።
: 44'214 | на пост: 4'181 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-03-28 15:06:04 |
3'002
0 |
“በዛሬው ውይይት ከተለያየ የማኅበረሰብ ዳራ የተውጣጡ ከመላው ኢትዮጵያ የመጡ ሴቶችን ሀሳብ አዳምጫለሁ። በኅብረተሰባችን ውስጥ የሴቶች ሚና ብዙ መልክ እና ብዙ ገፅ ያለው ነው።"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
: 44'214 | на пост: 4'181 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-03-28 12:16:57 |
3'407
0 |
: 44'214 | на пост: 4'181 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-03-28 09:11:55 |
3'602
0 |
: 44'214 | на пост: 4'181 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-03-27 19:41:01 |
3'934
0 |
: 44'214 | на пост: 4'181 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-03-27 18:57:55 |
3'787
0 |
"ኢፍጣራችን ለአንድነታችን" ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነ ስርዓት - በምስል
📷 ልዑል ማስረሻ
#አዲስ_ዋልታ
ተጨማሪ ምስሎችን ለመመልከት የፌስቡክ ገፃችንን ይቀላቀሉ 👇
https://shorturl.at/fQVX5
: 44'214 | на пост: 4'181 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-03-27 12:14:51 |
4'307
0 |
: 44'214 | на пост: 4'181 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-03-27 06:37:49 |
4'597
0 |
የባሕር ዳር ከነማ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረው አለልኝ አዘነ በድንገት አረፈ
መጋቢት 18/2016 (አዲስ ዋልታ) የባሕር ዳር ከነማ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረው አለልኝ አዘነ በድንገት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።
ተጫዋቹ በጉዳት ምክንያት ከክለቡ ስብስብ ጋር ያልነበረ ሲሆን በትውልድ ቦታው አርባ ምንጭ ሌሊት በድንገት ማረፉ ተገልጿል።
በቅርቡ የተሞሸረው አለልኝ አዘነ፤ ላለፉት ሁለት አመታት በጣና ሞገዶቹ ቤት ድንቅ ብቃቱን ሲያሳይ ቆይቷል። ከዚህ በተጨማሪም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ተደርጎለት አገልግሎት መስጠቱ ይታወሳል።
ስርዓተ ቀብሩ ዛሬ መጋቢት 18, 2016 በአርባ ምንጭ እንደሚፈፀም ከክለቡ ማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አዲስ ዋልታ ቴሌቪዥን በአለልኝ አዘነ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለመላው የስፖርት ቤተሰብ መፅናናትን ይመኛል።
: 44'214 | на пост: 4'181 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-03-26 17:46:10 |
4'938
0 |
ንግድ ባንክ ያለአግባብ የተወሰደውን ገንዘብ ያልመለሱ ሰዎችን ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ
መጋቢት 17/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት ባጋጠመው ችግር ምክንያት ያለአግባብ የተወሰደውን ገንዘብ ያልመለሱ ሰዎችን ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ።
ባንኩ ይፋ ያደረገውን የስም ዝርዝሩን ለማየት የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👇
https://shorturl.at/ftBG0
: 44'214 | на пост: 4'181 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-03-26 16:36:44 |
4'688
0 |
እንግሊዝ ከቤልጂየም እና ጀርመን ከሆላንድ የወዳጅነት ጨዋታ ያካሂዳሉ
መጋቢት 17/2016 (አዲስ ዋልታ) ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ከ45 ላይ እንግሊዝ ከቤልጂየም እንዲሁም ጀርመን ከሆላንድ የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋሉ።
እንግሊዝ ባለፈው ቅዳሜ በብራዚል 1 ለ 0 የተሸነፈች ሲሆን ቤልጂየም በበኩሏ ከአየርላንድ ጋር 0 ለ 0 መለያዬታቸው ይታወሳል።
ጀርመን በበኩሏ ቅዳሜ ዕለት ከፈረንሳይ ጋር ያደረገችውን ጨዋታ 2 ለ 0 ስታሸንፍ፣ ሆላንድ ስኮትላንድን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፋለች።
ከሁለቱ የወዳጅነት ጨዋታዎች በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን ስሎቬንያ ከፖርቱጋል፣ ኡራጓይ ከአይቮሪ ኮስት፣ ሮማንያ ከኮሎምቢያ፣ አየርላንድ ከሲውዘርላንድ ምሽት 4 ከ 45 ላይ ከሚካሄዱ ግጥሚያዎች ተጠቃሽ ናቸው።
ምሽት 5 ሰዓት ላይ ግብፅ በሜዳዋ ክሮሺያን እንደምታስተናግድ ሲጠበቅ ፈረንሳይ ከቺሊ እንዲሁም ስፔን ጀብራዚል 5 ሰዓት 30 ላይ የሚደርጉት ተጠባቂ ጨዋታዎች ናቸው
: 44'214 | на пост: 4'181 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-03-26 14:41:57 |
3'936
0 |
የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዟችንን ከጀመርንበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ሀገር ወሳኝ ርምጃዎችን ተራምደናል - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ
መጋቢት 17/2016 (አዲስ ዋልታ) የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዟችንን ከጀመርንበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ሀገር ወሳኝ ርምጃዎችን ተራምደናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ለፈጠራ ሰዎች ድጋፍ በማስገኘት እና ለዲጂታል ጉዞ አስቻይ ሁኔታዎችን በመፍጠር በዲጂታል ኢኮኖሚ እንድንበረታ ዐቅም ሆኖናል ሲሉም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
“ዛሬ ያደረግነው የመካከለኛ ዘመን ግምገማ ተግዳሮቶቻችንን ለመፈተሽ ብሎም የጉዟችንን ስኬታማ እጥፋቶች ለማክበር ዕድል ፈጥሮልናል።” ብለዋል።
: 44'214 | на пост: 4'181 | ER: 8.6% Публикации Упоминания Аналитика 2024-03-26 12:46:21 |
4'223
0 |
ሚዛን አማን
#ከተሞቻችን
የሚዛን አማን ከተማ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አንዷ መቀመጫና የቤንች ሸኮ ዞን ዋና መቀመጫ ሆና በማገልገል ላይ ትገኛለች፡፡
ከተማዋ ከርዕሠ መድናችን አዲስ አበባ በ568 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ስትሆን በ1930 ዓ.ም እንደተቆረቆረች ይነገራል።
ሚዛን አማን ከተማ የቀድሞ ሚዛን ተፈሪ የሚለውን ስያሜ ያገኘችው በንጉሱ አፄ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግሥት አካባቢውን እንዲያስተዳድሩ ተሹመው በተላኩት በእንደራሴው ፊታውራሪ አለማየሁ ፍላቴ መሆኑ ይነገራል፡፡
የንጉስ አፄ ኃይለስላሴ ልደት እየተከበረ በነበረበት ወቅት ከተማዋ በመመስረቷ የልደት መታሰቢያ ለማድረግ እንደሆነም ታሪክ ይጠቅሳል።
በ1ሺሕ 451 ሜትር ከባህር ጠለል በላይ ከፍታ ላይ የምትገኘው ሚዛን አማን በአረንጓዴ መልክዓ ምድር የተሸፈነች እና ወይናደጋ የአየር ንብረት ያላት ከተማ ነች።
እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ያላት ሚዛን አማን በዙሪያዋ ከፍተኛ የደን ክምችት ያላት ሲሆን ቡናን ጨምሮ፣ በፍራፍሬ እና በቅመማቅመም ምርቶች ትታወቃለች፡፡ የአረንጓዴ ልማት ፈርጥ ተብላም ትጠራለች።
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid0NMmjbVppnwZjZ9NxBEeKkDnjSQ26t2A9oaG6xmD6MCFc7FEwdAG1pXAJxreKrLnJl