Телеграм канал 'WALTA TV'

WALTA TV


45'218 подписчиков
4'242 просмотров на пост

This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.

For more updates please visit https://www.facebook.com/wmcc

Детальная рекламная статистика будет доступна после прохождения простой процедуры регистрации


Что это дает?
  • Детальная аналитика 5'685'568 каналов
  • Доступ к 1'533'798'153 рекламных постов
  • Поиск по 6'011'181'299 постам
  • Отдача с каждой купленной рекламы
  • Графики динамики изменения показателей канала
  • Где и как размещался канал
  • Детальная статистика по подпискам и отпискам
Telemetr.me

Telemetr.me Подписаться

Аналитика телеграм-каналов - обновления инструмента, новости рынка.

Найдено 13706 постов

በግብርና ዘርፍ ያገኘነውን ስኬት በኢንዱስትሪው ዘርፍ ለመድገም ትልቅ ትልም አለን - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ግንቦት 2/2016 (አዲስ ዋልታ) በግብርና ዘርፍ ያገኘነውን ስኬት በኢንዱስትሪው ዘርፍ ለመድገም ትልቅ ትልም አለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታን በኦሮሚያ ክልል እና በሲሲኢሲሲ መካከል በተደረገ በገዳ የኢኮኖሚ ዞን የሉሜ ነፃ የንግድ ቀጠና ማልማት ስራ የመግባቢያ ስምምነት መርኃግብር ማስጀመራቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።

ይህን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የገዳ ኢንዱስትሪ ዞን የሀገራችን እና የቀጠናችን አቅም በመግለጥ ርዕያችንን ለማሳካት የሚረዳ ቁልፍ ተቋም ሆኖ ያገለግላል ብለዋል።

የሉሜ ነፃ የንግድ ቀጣና በኢንዱስትሪ ዞን ውስጥ ሆኖ በምስረታው ብሎም ተግባራዊ ስራ በሚጀምርበት ወቅት ከድሬዳዋ በመቀጠል ሁለተኛው ነፃ የንግድ ቀጣና ይሆናል ሲሉም አክለዋል፡፡

በዚህም ነጻ የንግድ ቀጣናው ለኢኮኖሚ እድገት እና ልማት እድሎችን ያሰፋል ሲሉ ገልጸዋል።

በግብርና የተገኘው ስኬት በኢንዱስትሪው ዘርፍ የመድገምን አስፈላጊነት አፅንዖት ሰጥተው ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህም የፖሊሲ ድጋፍ ብሎም ለኢኮኖሚ ዞኑ ቀጣይ እንቅስቃሴ ጠንካራ የመሰረተ ልማት ስራ ሊከናወን እንደሚገባ አስምረውበታል።

ከአዲስ አበባ ከተማ በስተምሥራቅ በ65 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ ተቋም ኤክስፖርትን ለማሳደግ፣ የንግድ እና ሎጂስቲክስ ማዕከል የመመስረት፣ የውጭ ኢንቨስትመንትን የመሳብ፣ የኢንዱስትሪ የንግድ ኢንቨስትመንት እና የከተማ ልማት ስራዎችን የማበልፀግ አላማ ያነገበ መሆኑ ተገልጿል።

👍 6
👎 1
Изображение
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታን አስጀመሩ

ግንቦት 2/2016 (አዲስ ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታን በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረዋል።

የኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳደር ሽመልስ አብዲሳ ፕሮጀክቱ የአገራችንን አዲስ የፈጠራና ከፍተኛ የኢኮኖሚ ልማት ጅማሮን የሚያበስር መሆኑን ገልጸው የኢኮኖሚ ፈጠራን በማራመድ፣ የአከባቢውን ማህበረሰብ በማብቃትና ዘላቂነትን በማረጋገጥ ረገድም ከፍተኛ ሚና የሚጫወት መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

የኢኮኖሚ ፈጠራን በማራመድ ረገድ ገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ስትራቴጂ የማዕዘን ድንጋይ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንት በመሳብ፣ የወጪ ንግድ በማስፋፋትና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ በመተካት እንዲሁም የላቁ የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪዎችን በማጎልበት ረገድ ግንባር ቀደም ሚና እንዲኖረው ታስቦ የተነደፈ እንደሆነም አንስተዋል።

ስትራቴጅካዊ ትኩረቱን በላቁ የማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂና በዘላቂ አሠራሮች ላይ በማድረግ፣ ዞኑ ለመላው አፍሪካ የኢኮኖሚ ዞኖች አዲስ ደረጃ ያስቀምጣልም ነው ያሉት።
👇👇
https://shorturl.at/iJKX3
👍 9
👎 2
Изображение

የፊታችን እሁድ ግንቦት 4/2016 ዓ.ም ለ#ጽዱ_ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 50 ሚሊዮን ብር የማሰባሰብ ዲጂታል ቴሌቶን ይቀላቀሉ

#ጽዱ_ኢትዮጵያ
#CleanEthiopia

🙏 4
👎 1
Изображение
በኮርደር ልማት መልሶ የተገነቡ የኤሌክትሪክ መስመሮች አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

ግንቦት 2/2016 (አዲስ ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮርደር ልማት የኤሌትሪክ መስመር ማዛወር እና መልሶ ግንባታ ስራ አጠናቆ ለደንበኞች አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገለጸ፡፡

በመስመር ማዛወር ስራው ወቅት የልማት ተነሺ ለነበሩ 2 ሺሕ 700 ደንበኞች በአዲስ መልክ በሰፈሩበት አካባቢ አዲስ ኃይል የማገናኘት ስራ መከናወኑም ተገልጿል፡፡

የኃይል መስመር ማዛወር ስራው በአጠቃላይ 68 ኪ.ሜ የሚሸፍን ሲሆን በቀጣይ የኃይል መቆራረጡን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ ታሳቢ በማድረግ 50 ኪ.ሜ የመካከለኛ እና 18 ኪ.ሜ የዝቅተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመር ላይ ማሻሻያ መደረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ ያመላክታል፡፡
👍 5
Изображение

የሀገር ውስጥ ምርትን በመጠቀም በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የተገኙ ውጤቶችን ይበልጥ ማስቀጠል ይገባል - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ግንቦት 1/2016 (አዲስ ዋልታ) የሀገር ውስጥ አምራቾችን በመደገፍ እና የሀገር ውስጥ ምርትን በመጠቀም በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የተገኙ ውጤቶችን ይበልጥ ማስቀጠል አለብን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖን አስጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች በግብዓት፣ በኢነርጂ፣ በገበያ እና በሰው ሀይል ኢትዮጵያ ያላትን አቅም በተሻለ ወደ ውጤት ለመለወጥ መትጋት ይኖርባቸዋል ሲሉም በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።

👍 20
Изображение

በሕገወጥ መንገድ በአውሮፓ የሚኖሩ ዜጎችን ለመመለስ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ ነው

ግንቦት 1/2016 (አዲስ ዋልታ) በሕገወጥ መንገድ በአውሮፓ የሚኖሩ ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ከአውሮፓ ሕብርት ጋር እየሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

እስካሁን ሕጋዊ የመኖርያ ፈቃድ ያላገኙ 15 ኢትዮጵያዊያን ከአውሮፓ ወደ ሀገራችው መመለሳቸው ተገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ነብዩ ተድላ የአውሮፓ ሕብረት ሕጋዊ የመኖርያ ፈቃደ ሳያገኙ በሕብረቱ አባል ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መጠየቁን ገልጸው የተወሰኑ ዜጎችንም እንዲመለሱ መደረጉን ተናግረዋል።

የአውሮፓ ሕብረት 86 ሰዎችን ኢትዮጵያዊያን ናቸው ብሎ የለየ ቢሆንም በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ኢትዮጵያዊያኑ 26 መሆናቸው ተረጋግጧል ብለዋል።

ከእነዚህም ውስጥ 5 ከኖርዌ፣ 5 ከስዊድን፣ 8 ከሲዊዘርላንድ፣ 6 ከፊላንድ እና 2 ከኔዘርላንድ መሆናቸው ተጠቅሷል።

መንግስት ሕገወጥ ሰዎችን ለመመለስ እየሰራ ቢሆንም የአውሮፓ ሕብረት የኢትዮጵያ መንግስት ፈጣን ምላሽ አልሰጠም በሚል የሕብረቱ ምክር ቤት ለኢትዮጵያውያን የቪዛ አሰጣጥ ላይ ያወጣው ማዕቀብ ጊዜውን ያልጠበቀ እና ፍትሐዊ ያልሆነ መሆኑን ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።

የአውሮፓ ሕብረት ምክር ቤት ከሰሞኑ ለኢትዮጵያውያን ቪዛ አሰጣጥ ላይ ገደብ ማውጣቱ ይታውሳል።

ምክር ቤቱ ቪዛ ለማግኘት ይወስድ የነበረውን የ15 ቀን ጊዜ ወደ 45 ቀን ከፍ እንዲል ውሳኔ አሳልፏል።
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid0U5aRnqoysa1JbSURjajeGVbqxDujugDR9eKLtVQJbLiWdsgwAxmRpShniiXkLR65l

👍 10
🙏 1
Изображение

የአዲስ ዋልታ የትንሳኤ በዓል የወርቅ ደረጃ አጋር!
የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ

👍 2
🙏 1
Изображение
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2016ን በይፋ ከፈቱ

ግንቦት 1/2016 (አዲስ ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2016ን በይፋ ከፍተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አዘጋጅነት ከግንቦት 1 እስከ 5/2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ የሚካሄደውን የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2016ን ነው በይፋ የከፈቱት፡፡

ለአምስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው ኤክስፖ ከ200 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ ከ50 ሺሕ በላይ የአገር ውስጥና የውጪ ሀገር ጎብኚዎች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተገልጿል። በኤክፖው ወደ 3 ቢሊዮን ብር የገበያ ትስስር ይፈጠራል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

በኤክስፖው መክፈቻ ላይ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የኢንዱስትሪ አንቀሳቃሾች፣ የውጭ ባለሃብቶችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በሳሙኤል ሓጎስ
👍 9
👎 1
Изображение

ዛሬ ምሽት በዩሮፓ ሊግ ሁለት የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ

ግንቦት 1/2016 (አዲስ ዋልታ) ዛሬ ምሽት በዩሮፓ ሊግ ሁለት የሁለተኛ ዙር የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

ምሽት አራት ሰዓት የቡንደስ ሊጋው ሻምፒዮን ባየር ሊቨርኩሰን ከሮማ እንዲሁም አታላንታ ከኦሎምፒክ ማርሴይ ይጫወታሉ።

በመጀመሪያ ዙር በተደረጉ ጨዋታዎች ባየር ሊቨርኩሰን ሮማን 2 ለ 0 ያሸነፈ ሲሆን አታላንታ ከኦሎምፒክ ማርሴይ 1 ለ 1 መለያዬታቸው ይታወሳል።

በሌላ በኩል ኦሎምፒያኮስ ከአስቶን ቪላ በዩሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ውድድር በተመሳሳይ 4 ሰዓት የሚጫወቱ ሲሆን በመጀመሪው ዙር ኦሎምፒያኮስ አስቶንቪላን 4 ለ 2 ማሸነፉ ይታወሳል።

ትናንት ምሽት በተደረገ ሌላ የዩሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ጨዋታ የጣሊያኑ ፊዮረንቲና ክለብ ቡርዥን 4 ለ 3 በሆነ ድምር ውጤት አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን አረጋግጧል።

👍 1
Изображение

#ሐሳብ_ላይ
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወለጋ ጎዞ ትርጉሙ እና አንድምታው 👇
https://youtu.be/5uy2vZUZlK4?si=ywOc4F7RPKE6VSVL
ዛሬ ምሽት 3፡00 ይጠብቁን!

👍 9
👏 6
🙏 4
👎 1
Изображение
ሕዝቡ በሰላም፣ በአንድነትና በልማት ላይ በማተኮር እጅ ለእጅ ተያይዞ መስራት አለበት - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ሚያዝያ 30/2016 (አዲስ ዋልታ) ሕዝቡ በሰላም፣ በአንድነትና በልማት ላይ በማተኮር እጅ ለእጅ ተያይዞ መስራት አለበት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

በነቀምቴ ከተማ ወለጋ ስታዲየም የለውጡን መንግስት የሚደግፍ ሰልፍ ''ወለጋ የሰላምና የብልጽግና ምድር'' በሚል መሪ ሃሳብ የአራቱ ወለጋ ዞኖች ነዋሪዎች የተሳተፉበት ሰልፍ ተካሂዷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ህዝቡ በሰላም፣ በአንድነትና በልማት ላይ እንዲያተኩር ጥሪ አቅርበዋል።

ሰላም የሁሉ ነገር መሰረት መሆኑን ጠቅሰው ''ሰው ውስጡ ሰላም የሆነ፣ ሀገሩ ሰላም ከሆነ ልክ እንደ ዛሬ በፍቅርና በወንድማማችነት መንፈስ ተገናኝቶ መለያየት ይችላል'' ነው ያሉት።

ከሁሉም በላይ ለልማት፣ የተለያየ ሀሳብ ለማመንጨት አንድነት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ትውልዱን የሚጎዳ ነገር ከማድረግ በመቆጠብ በመመካከር አንድነትን ማጽናት ይገባል" ብለዋል።

ከኢኮኖሚ አኳያ ከለውጡ በፊት ብዙ ችግር ተደቅኖ እንደነበር አንስተው ከለውጡ በኋላ ግን በብዙ ችግሮች ውስጥ ትልቅ የኦኮኖሚያዊ ለውጥ እየተመዘገበ መሆኑን አብራርተዋል።

በለውጡ ዓመታት በተሰራ ሥራ ግብርናንና ከተማን የሚለውጥ፣ ሀገር የሚያሸግር ኢኮኖሚ እየተመዘገበ መሆኑን አስረድተዋል።

''የጀመርነውን ስራ ከግብ ለማድረስ የሚያስቆመን ሃይል አይኖረም፣ በንጹህ ልባችን ሀገር ለመለወጥ ነው እየሰራን ያለነው'' ብለዋል፡፡
👇👇
https://shorturl.at/bQZ24
👍 18
👏 4
👎 1
Изображение

የአዲስ ዋልታ የትንሳኤ በዓል የወርቅ ደረጃ አጋር!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ

🙏 7
👍 1
Изображение
Изображение

Найдено 13706 постов