Каталог каналов Мои подборки Мои каналы Поиск постов Рекламные посты
Инструменты
Каталог TGAds Мониторинг Детальная статистика Анализ аудитории Бот аналитики
Полезная информация
Инструкция Telemetr Документация к API Чат Telemetr
Полезные сервисы

Не попадитесь на накрученные каналы! Узнайте, не накручивает ли канал просмотры или подписчиков Проверить канал на накрутку
Прикрепить Телеграм-аккаунт Прикрепить Телеграм-аккаунт

Телеграм канал «መንበረ ማርቆስ ወንጌላዊ ጉባኤ ቤት»

መንበረ ማርቆስ ወንጌላዊ ጉባኤ ቤት
47
0
0
0
0
ይሕ ግሩፕ ወደፊት የመ/ብ አድማሱ
ጀምበሬና የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ መታሰቢያ የመጻሕፍት ትርጓሜ ጉባኤቤት ነው። ስለቤተክርስቲያን ሥርዓትና ስለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ዶግማና ቀኖና የምንመማርበት ነው።
…#መንበረ ማርቆስ ወንጌላዊ ጉባኤ ቤት

/joinchat/W9K2FFCCi6I4YWQ0
Подписчики
Всего
491
Сегодня
-1
Просмотров на пост
Всего
382
ER
Общий
66.1%
Суточный
52.5%
Динамика публикаций
Telemetr - сервис глубокой аналитики
телеграм-каналов
Получите подробную информацию о каждом канале
Отберите самые эффективные каналы для
рекламных размещений, по приросту подписчиков,
ER, количеству просмотров на пост и другим метрикам
Анализируйте рекламные посты
и креативы
Узнайте какие посты лучше сработали,
а какие хуже, даже если их давно удалили
Оценивайте эффективность тематики и контента
Узнайте, какую тематику лучше не рекламировать
на канале, а какая зайдет на ура
Попробовать бесплатно
Показано 7 из 47 постов
Смотреть все посты
Пост от 15.05.2026 21:14
299
0
1
ትምህርተ ሃይማኖት

ክፍል ፩

ሃይማኖት የሚለው ቃል እንደ ቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ሦስት ዓይነት ትርጉም አለው።

ይኸውም
👉ዘይቤያዊ
👉ዐውዳዊ
👉ምሥጢራዊ ትርጉም ነው።

✍ዘይቤያዊ ማለት፦
ሃይማኖት የሚለው ቃለ ሀይመነ አመነ አሳመነ ታመነ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን  የማይታየውን የማይመረመረውን የፈጠረ ያለፈውን ወደፊትም የሚሆነውን ረቂቅ ነገር እንደሆነ እንደሚሆን አምኖ መቀበልበዚያውም ሳያወላውሉ ጸንቶ መኖር ሁሉ በእግዚአብሔር መጋቢነት ጸንቶ ይኖራል ማለት እግዚአብሔር እንዴት ሊመለክ እንደሚገባው የሚነገረው ምርምራዊ የሆነው ፈጽሞ ሊረዳ የማይቻለው እንደምሥጢረ ሥላሴ፣ ሥጋዌ የመሳሰለው ክርስቲያናዊ ትምህርት ነክ ቅዱስ አምልኮትንም የሚመላከተው ሁሉሃይማኖት ማለት ዓለም በእግዚአብሔር ቃል በእግዚአብሔር ፈጣሪነት እንደተፈጠረች ማመንየሥራ ሁሉ መጀመሪያ የሥራ ሁሉ መፈፀሚያ ነውበሌላ ነገር ማመን ነው።

✍ዐውዳዊ የሚባለው፦
ሃይማኖት አለው የሚባል ሰው ሃይማኖታዊ በዓላትን፣ ሃይማኖታዊ አጽዋማትን፣ ሃይማኖታዊ ሥርዓትን ጠብቆ ስኬታማ የክርስቶስ አካል፣ ብልት ሆኖ መኖር ነው።
በሃይማኖት ውስጥ ዕሴት፣ ባሕል፣ ትውፊት፣ ቀኖና አለ ይህን ሁሉ አክብሮ፣ ጠብቆ መኖር ነው።

✍ምሥጢራዊ ትርጉሙ፦
ሃይማኖት ማለት በምሥጢራዊ ትርጉም እግዚአብሔር ማለት ነው።
ሃይማኖት ማለት እግዚአብሔር ማለት እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምስክርነት ያለው ሐዋርያዊ ትምህርት ነው።

«ወእመኒ ኢአመናሁ ውእቱሰ ምእመነ ይነብር ወኢይክል ክሒደ ርእሶ ባናምነው፥ርሱ፡የታመነ፡ኾኖ፡ይኖራል፤ራሱን፡ሊክድ፡አይችልምና።»(፪ ጢሞ ፪፥፲፫-

በማለት ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ሃይማኖታዊ ምስክርነቱን ይሰጣል።
ቅዱስ ያሬድም ሃይማኖት ማለት እግዚአብሔር ማለት እንደሆነ በድጓው አንጸባርቆ ይገልፃል፣ ሐዋርያዊ ምስክርነቱንም ለኦርቶዶክሳውያን ይገልፃል።
«ሃይማኖትኒ እንተእምኀበ አብ ተፈጥረት ወኀበ ወልድ ትበጽሕ ወኀበ መንፈስ ቅዱስ ትትፌጸም ሃይማኖት አብን ወላዲ፣ አሥራጺ በማለት ተጀምራ ወልድን ተወላዲ ብላ መንፈስ ቅዱስን ሠራጺ በማለት ትፈጸማለች»
በማለት ይሰብካል፣ ያስተምራል።
ይህ ሁሉ የአንዲት ሃይማኖት የትርጉም ዓይነት ነው።
ይህን አንድ ኦርቶዶክሳዊ የማወቅ ይኖርበታል።
ለቅዱሳን የተሰጠች ይህች ሃይማኖት ናት ይህን በሰፊው ለመረዳት በሳምንት አንዴ ዓርብ ሁለት ሰዓት #ከመንበረ ማርቆስ የሚሰጠውን ትምህርተ ሃይማኖት መከታተል ተገቢ ነው።

ይቀጥላል......


@መምህር ብንያም
👍 7
3
Пост от 15.05.2026 14:36
318
0
1
#ተውግዟል

የወንቅሸቱ የቀበሮ ባሕታዊ በኢቀኖናዊ ድርጊቱ ተወገዘ

👉ብፁዕ አቡነ ተዎፍሎስ የሰሜን ካሊፎርንያ የነቫዳና የአሪዞና ሊቀ ጳጳስ ያለ አገረ ስብከቱ የተደረገውን ኢቀኖናዊ በግለሰብ ደረጃ የተካናወነውን "የገዳም" ምሥረታ በጽኑ አውግዘው በኢቀኖናዊ ድርጊት ማንም እንዳይተባበር ይልቁንም ካህናትና ምእመናን የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥርዓትና አንድነት  ለማስጠበቅ እንዲሰሩ አዘዋል።

👉ይህ ውሳኔ ቢዘገይም እጅግ ወሳኝ ነው። በአንፃሩም አሁንም ምእመናንን የማንቃት ፣የመጠበቅና ከቀሳጥያንና ከምንደኞች ቤተ ክርስቲ ያናችንን መጠበቅ የሁላችን ኃላፊነት ነው።

© ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ
Изображение
Изображение
Изображение
6
Пост от 15.05.2026 08:10
326
0
0
ማስታወቂያ፦

#ከመንበረ ማርቆስ ወንጌላዊ  ጉባኤ ቤት

ተቋርጦ የነበረው ተከታታይ ነገረ ሃይማኖት ትምህርታችን  ግንቦት ፯ (ሰባት )/፳፻፲፰ ዓ/ም
ጀምሮ  በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር ከምሺቱ ሁለት ሰዓት እስከ ሦስት ሰዓት ባለው ቆይታ ሁሌም   ዓርብ ተከታታይ ትምህርት


፩ኛ  ነገረ ሃይማኖት  ተከታታይ ትምህርት
፪ኛ ነገረ ማርያም
፫ኛ  ኦርቶዶክሳዊ ወንድነት በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፉ ማኅበረ ሰብእ

በመምህር ብንያም

፪ኛ መዝሙር

፫ኛ የመሰናበቻና የመግቢያ ጸሎት

ይሁን እንጅ ይህ የዕውቀት ባሕር  መንጭቶ የሚፈስባት ጉባኤ ቤት ናት ።
ከዚህ ጉባኤ ቤት ዕውቀት በየስልቱ እየተሰጠ መልክና ቅርፅ እየያዘ ነውና
ሁሌም ዓርብ ከምሺቱ ሁለት ሰዓት #ከመንበረ ማርቆስ ወንጌላዊ ጉባኤ ቤት ቴሌግራም እየተገኙ  ስለሃይማኖትዎ ግንዛቤ እንዲይዙ በእግዚአብሔር ስም ተጠርተዋል?



በኀጢአት ሰንሰለት ታስራ ለተጨነቀኝ ነፍስ እረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉም ይደርስ ዘንድ

ቻናላችንና ግሩፓችንን join፣ Shar፣ Add አድርጉ።ለሌሎችም አጋሩ

#ቴሌግራም
#ግሩፕ
https://t.me/Menberemarkos
#ቴሌግራም
#ቻናል
https://t.me/Menberemarko
Пост от 15.05.2026 08:10
262
0
0
📝የቤተክህነት ቁማር   ....

👉ዕድሜ የሰጠው ፣ በጆሮው እና በዐይኑ ብዙ ነገር ይሰማል ያያል በተለይ የቤተክህነቱን ሤራ ፣

👉 የቅዱስ ሲኖዶስ  ስብሰባ ከመጀመሩ  እና  ከተጠናቀቀ በኃላ ፣ የሕንፃ ምረቃ ፣ የልማት ሥራ ጉብኝት አብዛኛው ጊዜ ለተርዮ አልያም ፣ የተሰራውን ስህተት  ለመሸፈኛ የሚፈጸሙ ተግባራቶች  ናቸው ፦

👉በዚህ ዘመን ጳጳስ የክህደት ትምህርት  አስተማረ ፣  ጳጳሱ ዘረፉ ፣ ጳጳሱ  ሠረቁ ፣ ጳጳሱ አጭበረበሩ ፦ ይህንን መስማት እንዴት ያማል ፣ ይህንን እውነት ለመዳኘት  የሚቀመጡት እነሱ ናቸው አንዱ አንዱን አሳልፎ አይሰጥም ምክንያቱም አብዛኞቹ ነገ የእኔም እጣ ይህ ነው ብለው ስለሚያስቡ  ትክክለኛ ብይን እና ፍርድ  ከመስጠት ይልቅ አደባብሰው ተሸፋፍነው ያልፋሉ ።

👉 ሰሞኑን የተሰማው እና የታየው እጅግ ይገርማል ጳጳሱ የወርቅ ጽላት ሰረቁ በሚል ጉምጉምታ የፈጠረው የሲኖዶሱ ስብሰባ ጳጳሱን ከቦታ በማንሳት የተዳፈነው ስብሰባ ማለቁን ተከትሉ ለዚህ ማርከሻ  ጳጳሳቱ ተሰብስበው  ሕንፃ መረቁ  በሚል ሚዲያው እና የሁለቱ ጳጳሳት  ምንደኞች  እና ቡቹሎች እንዲህ በማለት ይዝጀምራሉ "በሁለቱ ጳጳሳት ተጀምሮ በሁለቱ ጳጳሳት አለቃ "፣

👉 ገንዘቡን  ከኪሳቸው አውጥተው  ሰርተው እንደጨረሱ ፣ ይህ ህንፃ 10 ዓመት ፈጀ ተባለ ሲጀመር በነሱ የሥልጣን ዘመን ተጀመረ ከተባለ ፣ ዛሬ  ለፓለቲካ ፍጆታ በድጋሚ እንዲመረጡ ከመደረጉ በፊት ለስድት ዓመታት አራት ጳጳስት ተቋሙን መርተውታል ፣  ሁለቱ በጠቅላ ዋና ሥራ አስኪያጅነት አቡነ ያሬድ እና አቡነ አብርሃም  ሁለት ጳጳሳት ደግሞ በቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊነት በድምሩ ለስድት ዓመታት  አገልግለዋል ።

👉ታዲያ በእምነ በርድ ድንጋይ ከተፃፈው ጹሑፍ ጀምሮ ስማቸው እንደ ግል ንብረት ጎልቶ የሚታየው የሁለቱ ጳጳሳት ነው ? ይህ ምን ያሳያል ?  እረ  ሰው ይታዘበናል በሉ ፣ ለቤተክርስቲያን ክብር ሳይሆን ለክብራችሁ የምትጨነቁ እንደሆናችሁ ሁሉም ያውቃል ፣ ፈረጅያ ጎታቾቹ ግን ነገሩን ቀዝቀዝ አድርጉት፣


👉 ይህ በመንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤት በብዙ ቢሊዮን ብር እየተሰራ ያለው የሕንፃ ፕሮጀክት እንዴት ለቅዱስ ሲኖዶስ በሪፖርር መልክ አልቀረበም ፣ ለምንስ አልቀረበም ብሎ የሚጠይቅ ማን ነው?  ፣ ይህ ከፍተኛ ቢሊዮን የወጣበትን ገንዘብ የሚቆጣጠረው ማን ነው ?  ዝርዝሩ ይቀርባል ....
Пост от 15.05.2026 08:10
221
0
0
Изображение
Изображение
Изображение
Изображение
Пост от 14.05.2026 17:54
283
0
0
በመላው ዓለም፣ በደቡብ አፍሪካና በሳውዲ ዐረቢያ የሚኖሩ ዜጎቻችን ሰብዓዊ መብት እንዲከበር፣ የርኅራኄ ምሕረትና ፍትሕ እንዲያገኙ የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ክትትል እንዲያደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ጥሪውን በማቅረብ ለሰባት ቀናት ሲያካሂድ የሰነበተውን ቀኖናዊ ጉባኤ ዛሬ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም. በጸሎት አጠናቋል፡፡

“እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ”

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ/ም

💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሠሮ ለሰይጣን
አግአዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍስሓ ወሰላም

🔵@የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
ስለ አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን
Пост от 14.05.2026 17:54
286
0
0
💠፻፴፬ኛው #የቅዱስ_ሲኖዶስ_መደበኛ_ምልዐተ_ጉባኤ_ተጠናቀቀ::
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ሲኖዶሳዊ በመሆኗ አበው ቅዱሳን በፍትሕ መንፈሳዊና በጉባኤ አድያም ዘአንጾኪያ “ወይኩን ሲኖዶስ ዘጳጳሳት ፪ተ ጊዜያተ በበዓመት - የጳጳሳት ጉባኤም በዓመት ሁለት ጊዜ ይሁን” ብለው በደነገጉት ቀኖና መሠረት፤ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የሚመራው፣ የሐዋርያት መንበር ወራሽ የሆነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤውን በኅብረተ መንፈስ ቅዱስ ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ አካሄዷል፡፡

ምልዓተ ጉባኤው ስለ ሀገር ሰላም፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት፤ ስለ ሰው ልጅ ሁሉ ደኅንነትና ክብር፣ በአጠቃላይ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ሰፊ ውይይቶችን በማድረግ ዘመኑን የዋጁ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ ከውሳኔዎቹም መካከል፡-

የቤተ ክርስቲያናችንን አንድነት መጠበቅና ማስጠበቅ የቅዱስ ሲኖዶስ ተግባር በመሆኑ ጥንታዊትና ሐዋርያዊት የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን በአንድነቷና በሉዓላዊነቷ እንደተረከብናት ለወደፊቱም ሉዓላዊ ክብሯ ተጠብቆ እንድትቀጥል በምልዓተ ጉባኤው የተሠየመው በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራው “የሀገራዊ ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት” ኮሚቴ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ በተረጋጋ መንገድ እንዲካሄድ፣ ለሀገር ሰላምና ለሕዝብ አንድነት በሚጠቅም ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምትጸልይ ሲሆን ምርጫው በሁሉም ወገን ለኢትዮጵውያን ዘላቂ ሰላምንና መረጋጋትን የሚያስገኝ ሆኖ እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንዖት ያሳስባል፡፡

ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የአርሲ ሀገረ ስብከትን በሊቀ ጵጵስና በቋሚነት እንዲመሩ፣ ሕዝቡን እንዲያጽናኑ እየደረሰ ያለውን ችግር ከቋሚ ሲኖዶስና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከሚመራው የሰላም ኮሚቴ ጋር በመሆን የሚመለከተውን የመንግሥት አካል በማነጋገር ዘላቂ መፍትሔ እንዲያፈላልጉ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ወስኗል፡፡

ከጥንት ጀምሮ “ቅዱስ ሲኖዶስ” በሚል ርእስ እየተዘጋጀ ይታተም የነበረው ታሪካዊ መጽሔት የቅዱስ ሲኖዶስ ቀኖናዊ ውሳኔዎችን በማካተት በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አስፈጻሚነት ሕትመቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

የቤተ ክርስቲያናችንን ደንቦች መመሪያዎች መርምሮ ማጽደቅ የቅዱስ ሲኖዶስ ሉዓላዊ ሥልጣን በመሆኑ፡-

  የስብከተ ወንጌል ሐዋርያዊ ተልእኮ ማስፈጸሚያ ደንብ በብፁዕ አቡነ ማርቆስ ሰብሳቢነት

  የአንድነት ገዳማት ኅብረት መተዳደሪያ ደንብ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስና ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ባሉበት በድጋሚ እንዲታይና ሌሎቹም ለውሳኔ የቀረቡ ደንቦች በሊቃውንትና በሕግ ባለሙያዎች ታርመው ለጥቅምት 2019 ዓ/ም ምልዓተ ጉባኤ እንዲቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል

የቀድሞው የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ “የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ”ና “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ” በሚሉ አርእስት አዘጋጅተው ያሳተሟቸው መጻሕፍትን የማሳተምና የማሰራጨት የባለቤትነት መብት ከሚያዝያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

ከተለያዩ አህጉረ ስብከት በቀረቡ ጥናቶችና የማጣራት ውጤቶች መሠረት፡-

የደቡብ ሱዳን ሀገረ ስብከት ከምሥራቅ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ጋር ተደርቦ በብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ሊቀ ጳጳስ እንዲመራ፤
ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ሊቀ ጳጳስ የጋምቤላንና የቤንሻንጉል ጉምዝ አህጉረ ስብከትን ብቻ እንዲመሩ፤
ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጰስ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከትን እንደያዙ እንዲቀጥሉ፤
ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከትን ደርበው በአባትነት እንዲመሩ፣
የኮንታ ዞን ሀገረ ስብከት እንዲሆን የቀረበው ጥያቄ የጸደቀ በመሆኑ ሀገረ ስብከቱ ራሱን ችሎ እንዲደራጅና በብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳስ እንዲመራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የልማት ተግባራትን ምልዓተ ጉባኤው በከፍተኛ ደረጃ በማድነቅ፣ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ/ ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ሲቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ በአባታዊ አመራር የፈጸሙት አስደናቂ የሥራ አፈጻጸም በጉልህ የሚታይ ለውጥ፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የሚጠቅም፣ ሉዓላዊ ክብሯን የሚያስጠበቅ፣ ለሁሉም አበው ምሳሌነት ያለው በመሆኑ ምልዓተ ጉባኤው እጅግ ከፍ ባለ ክብር አመስግኗል፡፡

በዚህም መሠረት በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጁ አባታዊ መሪነት እየተከናወኑ ያሉት ተግባራት ማለትም፡-

የቤተ ክርስቲያንን ቀደምት ሠነዶች በዲጂታል ቴክኖሎጅ እንዲደራጁ የተደረገበት ሥልት ተጠናክሮ እንዲቀጥል፤

ከ1970 ዓ/ም ጀምሮ በመጋዝን ተከማችተው የቆዩ በርካታ ልዩ ልዩ መጻሕፍትን የማሠራጨት ሂደት በተጀመረው መንገድ እንዲጠናቀቅ፤

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የኢንፎርሜሽንና ኮምኒኬሽን ተጠቃሚ እንድትሆን የተጀመረው ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ በሁሉም የቤተ ክርስቲያናችን መዋቅር በየደረጃው ተጠናክሮ ተግባራዊ እንዲሆን፤

በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥር የተጀመሩ የሕንፃ ግንባታዎችና አጠቃላይ የልማት ሥራዎች በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ሁሉም አህጉረ ስብከትና ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽኦና ትብብር እንዲያደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንዖት ያሳስባል፡፡

በሰሜን አሜሪካ የሰሜን ካሊፎርኒያ፣ ኔቫዳና አሪዞና ሀገረ ስብከት ኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስና ቅድስት አርሴማ ገዳም የመንፈሳዊ ኮሌጅ፣ የአብነት ት/ቤት ሥርዓተ ትምህርት የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖና፣ ታሪክና ትውፊት በጠበቀ መልኩ ተጠናክሮ መዋቅራዊ ተጠሪነቱም በአግባቡ ተጠብቆ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ያቀረበውን የ2019 ዓ/ም በጀት በማጽደቅ በተገቢው መንገድ ሥራ ላይ እንዲውል ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡

በመጨረሻም ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በተነጋገረባቸው ጉዳዮች በትኩረት የተወያየው የቤተ ክርስቲያናችንን ሁለንተናዊ ዕድገትና ተቋማዊ ሕልውና ስለማስጠበቅ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ሀገራችንን ጨምሮ በመላው ዓለም እየታየ ያለው ግጭትና የሰላም መታጣት በእጅጉ አሳስቦታል፡፡

በመሆኑም ስለ ዓለምና ስለ ሀገራችን ሰላም፣ ስለ ሰው ልጆች ደኅንነት፣ በየቦታው በሃማኖታቸው ምክንያት መከራ የሚደርስባቸውን በየቦታው የሚገኙና ግጭት ባለባቸው ቦታዎች ያሉ ኦርቶዶክሳውያንን በማሰብ በመጪው የ2018 ዓ/ም ጾመ ሐዋርያት በመላው ዓለም ባሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት፣ አድባራትና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ጸሎተ ምሕላ እንዲደርስ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
👍 1
Смотреть все посты